የአንድ ድርጅት ሰራተኛ በሰራው ጥፊት ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውለ ቢቋረጥም ያልወሰደው የዓመት እረፍት ካለ ወደ ገንዘብ ተቀይሮ ሉከፈል የሚገባው ስለመሆኑና የፕሮቪደንት ፈንድም በከፈለው ልክ የማግኘት መብት ያለው ዲሽን ባንክ እና እነ ተፈሪ አሳልፈው /ሦስት ሰዎች/ II
No summary available.
ሚያዝያ 30 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች-፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- ዲሽን ባንክ አክሲዮን ማህበር - ነ/ፈጅ ሰለሞን አያኖ - ቀረቡ።
ተጠሪዎች፡-
አቶ ተፈሪ አሳልፈው
አቶ አየለ ገብረሃና ከጠበቃ ሳህለ ሀብቴ ጋር - ቀረቡ።
አቶ በኃይለ ዓለማየሁ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሳሾች የነበሩት የአሁኖቹ ተጠሪዎች በአሁኑ አመልካች ላይ በ07/08/2005 ዓ.ም አዘጋጅተው ባቀረቡት ክስ ነው።የክሳቸውም ይዘት ባጭሩ፡-ከሳሾች በተከሳሽ ድርጅት ተቀጥረው ቄራ አካባቢ በሚገኘው መጋዘን በመስራት ላይ እያለ ከመጋዘኑ ግቢ ያልወጣን ንብረት “ለግል ጥቅማችሁ አውላችኃል” በማለት ከ13/07/2005 ዓ.ም ጀምሮ የስራ ውላቸውን ያቋረጠ መሆኑን፣ከሳሾቹ ንብረት ከመመዝገብ በስተቀር ንብረት የመያዝም ሆነ የመጠበቅ ኃላፉነት እና የስራ ድርሻ የላላቸው መሆኑን፣ንብረት የመጠበቅ ኃላፉነት የተሰጠው ሰራተኛ በስሩ የሚገኘውን ንብረት ለአጠባበቅ ያመቸኛል በማለት ከመደበኛ ቦታ ውጭ በማስቀመጡ ድርጅቱ እርምጃ መውሰድ የሚገባው ጥፊተኛ ሆኖ በተገኘው ሰራተኛ ላይ ብቻ ሆኖ እያለ ከሳሾቹን ጭምር በማሰናበት የወሰደው እርምጃ የአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 27 (1) (መ) እና የድርጅቱን የሕብረት ስምምነት አንቀጽ 36 (1.3) የሚቃረን መሆኑን የሚገልጽ ሆኖ የስራ ስንብት እርምጃው ሕገወጥ ነው ተብል ድርጅቱ ውዝፍ ደመወዝ ከፍል ወደስራ እንዱመልሳቸው፣ይህ የሚታለፍ ከሆነም ሕገ ወጥ የስራ ስንብት የሚያስከትላቸውን እና ተዛማጅ ክፍያዎችን እንዱከፍላቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት የተጠየቀበት ነው።
ተከሳሽ ድርጅት በበኩለ በ17/10/2005 ዓ.ም በሰጠው መልስ ከሳሾቹ ከብር 180,000 በላይ ዋጋ ያላቸውን የተለያዩ ዕቃዎች እርስ በርስ በመመሳጠር በስቶር ክለርክነት ከሚሰሩበት የዕቃ ግምጃ ቤት ሰርቀው በመውሰድ በመጸዲጃ ቤት ውስጥ በመደበቅ እና የመጸዲጃ ቤቱን በመቆለፍ የቆጠራ ሰራተኞች እንዲያገኟቸው ያደረጉ መሆኑን፣ንብረቶቹ ለተለያዩ የአካባቢ ባንኮች እና የስራ ክፍልች የተሰራጩ ተደርገው የሚታወቁ መሆኑን፣ከሳሾቹ ንብረቶቹን ከሚሰራጩት ዕቃዎች ቀንሰው ያጠራቀሟቸው እንደሆነ መረጋገጡን፣ስለጉዲዩ ሲጠየቁም እርስ በርስ የሚጋጭ መልስ መስጠታቸውን፣እንዱሰናበቱ የተደረገውም በፈጸሙት የስርቆት እና የማጭበርበር ድርጊት በአዋጁ አንቀጽ 27 (1) (ሐ) እና (ተ) እና በሕብረት ስምምነቱ አንቀጽ 36 /1.1 እና 36 /1.2/ መሰረት በአግባቡ መሆኑን፣የሚፈለግባቸውን ዕዲ በማቻቻል ተራፉ ገንዘብ ካለ ከሁለት ዓመት በላይ ያልተላለፍ የዓመት ዕረፍታቸውን ድርጅቱ ለመክፈል ፈቃደኛ መሆኑን፣የፕሮቪደንት ፈንድ የለም እንጂ አለ ከተባለ ድርጅቱ ክፍያውን ለመክፈል የሚገደደው ከሳሾቹ የሚጠበቅባቸውን ግዳታ በመወጣት ክፍያ እንዱፈጸምላቸው ጥያቄ ሲያቀርቡ ብቻ በመሆኑ ከሳሾቹ ይህንን ግዳታ ተወጥተው ክፍያ እንዱፈጸምላቸው ጥያቄ ባላቀረቡበት ሁኔታ ድርጅቱ የሶስት ወር ደመወዝ ለመክፈል የሚገደድበት ምክንያት አለመኖሩን በመግለጽ ክሱ ውድቅ እንዱደረግ ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱም ክሱን እና የተከሳሽ ድርጅትን ሶስት ምስክሮች ከሰማ በኃላ አጠቃላይ ክርክሩን መርምሮ በስቶር ውስጥ በነበረው ዕቃ ጉድለት ያልተገኘ ቢሆንም ከሳሾች በመመካከር ዕቃዎቹ ከመጸዲጃ ቤት ውስጥ እንዱቀመጡ ማድረጋቸውን ተከሳሽ ድርጅት ያስረዲ መሆኑን፣ ይሁን እንጂ ይህ መሆኑ ከሳሾቹ ዕቃዎቹ ትርፍ መሆን አለመሆናቸው ወይም በመጠየቂያ መሰረት ያልተሰጡ ዕቃዎች መሆን አለመሆናቸው እስኪለይ ድረስ አስቀምጠናቸዋል በማለት ለተከሳሽ ድርጅት ምስክሮች በቃል እና በጽሁፍ ከሰጡት መግለጫ አንጻር ከሳሾቹ ዕቃዎቹን ከመደበኛ ቦታቸው ውጪ መጸዲጃ ቤት ውስጥ ማስቀመጣቸው አግባብ አይደለም ከሚባል በቀር ከሳሾቹ በመመካከር ዕቃዎቹን ለግል ጥቅማቸው ለማዋል በማሰብ ከሚላኩ ዕቃዎች ቀንሰው አውጥተው ወስደዋል ለማለት የሚያስችል አለመሆኑን ገልጾ ከሳሾቹ የስርቆት እና የማጭበርበር ድርጊት ፈጽመዋል በማለት ተከሳሽ ድርጅት የወሰደው የስንብት እርምጃ ሕገወጥ ነው በማለት ለእያንዲንዲቸው የስድስት ወር ውዝፍ ደመወዝ ከፍል ወደ ስራ እንዱመልሳቸው ውሳኔ ሰጥቷል።
ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በበኩል የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ ስንብቱ ሕገወጥ ነው በማለት የተሰጠውን ውሳኔ ሲያጸናው ተጠሪዎቹ ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደስራ እንዱመለሱ የተሰጠውን የውሳኔ ክፍል ግን በመሻር ሕገወጥ የስራ ስንብት የሚያስከትላቸው ክፍያዎች፣የፕሮቪደንት ፈንድ እንዱሁም ያልተጠቀሙበት የዓመት ዕረፍት ክፍያ ለ1ኛ ተጠሪ የ27 ቀናት፣ለ2ኛ እና ለ3ኛ ተጠሪዎች ለእያንዲንዲቸው የ15 ቀናት ክፍያ ተፈጽሞላቸው እንዱሰናበቱ ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች አቤቱታውን ለዚህ ችልት ያቀረበው ይዘቱ ከላይ የተመለከተው የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ሲሆን የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ጉዲይ ተጠሪዎች በነበራቸው የስራ ግንኙነትና አጋጣሚ የአመልካች የሆኑ ለልዩ ልዩ ቅርንጫፍች የሚታደለ በመጋዘን ውስጥ የነበሩ ንብረቶችን ከመጋዘን አውጥተው በግቢው ውስጥ ባለ መጸዲጃ ቤት ውስጥ አስቀምጠውት የነበረው ንብረት በጠቋሚዎች አማካኝነት በፍተሻ መያዙን የስር የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በማስረጃ ካረጋገጠ በኃላ ንብረቶቹን መጋዘኑ ካለበት ግቢ አውጥተው ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸው እስካልተረጋገጠ ድረስ አድራጎታቸው እንደስርቆት እንደማይቆጠር ገልጾ ስንብቱ ሕገ ወጥ ነው በማለት የመወሰኑን እና ውሳኔውም በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የመጽናቱን አግባብነት ተጠሪዎቹ ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል። ከዚህም በተጨማሪ ወደ ገንዘብ ተቀይሮ ሉከፈለኝ የሚገባው የዓመት ዕረፍት የ71 ቀናት ሆኖ ሳለ የ27 ቀናት ብቻ ታስቦ የ44 ቀናት የታለፈብኝ አላግባብ ነው በማለት 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡት መስቀልኛ የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች መልስ እንዱሰጥበት በ13/06/2007 ዓ.ም. በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በመስቀልኛ አቤቱታው ጉዲይም አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም በጉዲዩ እልባት ማግኘት የሚገባቸው ነጥቦች፡-
አመልካች አቤቱታ ያቀረበበት የውሳኔ ክፍል መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ወይስ አይደለም?
1ኛ ተጠሪ ያቀረቡት መስቀልኛ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡበት የውሳኔ ክፍል መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ወይስ አይደለም?
የሚለ መሆናቸውን በመገንዘብ ጉዲዩን ከእነዚሁ ነጥቦች አንጻር መርምረናል።
በዚህም መሰረት የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ ተጠሪዎቹ በአመልካች ድርጅት ውስጥ ይሰሩ የነበሩት በስቶር ክለርክነት መሆኑ፣በዚሁ የስራ መደብ ከሚሰሩበት የዕቃ ግምጃ ቤት ወጪ ተደርገው ለባንኩ የተለያዩ አካባቢዎች እና የስራ ክፍልች እንደተሰራጩ ተደርገው የተመዘገቡትን የተለያዩ ዕቃዎች ከንብረት ጠባቂው ጋር በመተባበር ከሚሰራጩት ዕቃዎች ቀንሰው በመጸዲጃ ቤት ውስጥ በመደበቅ እና የመጸዲጃ ቤቱን በመቆለፍ የቆጠራ ሰራተኞች እንዲያገኟቸው ያደረጉ መሆኑ፣ንብረቶቹን ለተለያዩ የአካባቢ ባንኮች እና የስራ ክፍልች የተሰራጩ እንደሆኑ አድርገው የመዘገቡትም እነዚሁ ተጠሪዎች መሆናቸው በስር ፍርድ ቤቶች በማስረጃ የተረጋገጡ ፍሬ ጉዲዮች መሆናቸውን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።ተጠሪዎቹም እኛ ንብረት ከመመዝገብ ባለፈ ንብረቱን የመያዝ እና የመቆጣጠር የስራ ድርሻ እና ኃላፉነት የላለን ስለሆነ ለዕቃዎቹ በመጸዲጃ ቤት ውስጥ ተደብቀው መገኘት በኃላፉነት የምንጠየቅበት ምክንያት የለም፣ዕቃዎቹም የተገኙት ከግቢው ሳይወጡ ነው፣በግቢው መውጫ ላይ የሚደረገው ፍተሻ ዕቀዎቹን ከመጋዘኑ ግቢ ለማውጣት የሚያስችል አይደለም በሚል ከመከራከር በቀር በስር ፍርድ ቤቶች ስለተረጋገጡት ከላይ ስለተጠቀሱት ፍሬ ነገሮች ያቀረቡት የማስተባበያ ክርክር የለም።ከንብረት ጠባቂው ጋር በመሆን ዕቃዎቹን ከመደበኛ ቦታቸው ውጭ በመጸዲጃ ቤት ውስጥ ቆልፍ ለማስቀመጥ ያስቻላቸው ሕጋዊ ተቀባይነት ያለው ምክንያት ስለመኖሩም ገልጸው አልተከራከሩም።
የስር ፍርድ ቤቶች ይዘቱ ከላይ የተመለከተው ፍሬ ነገር መረጋገጡን ከተቀበለ በኃላ ስንበቱ ሕገወጥ ነው ለማለት የቻለት በዋነኛነት ዕቃዎቹ የተገኙት በግቢው ውስጥ እንዲለ በመሆኑ ተጠሪዎቹ ዕቃዎቹን ወስደዋል ማለት አይቻልም በማለት መሆኑን ከውሳኔዎቹ ይዘት ተገንዝበናል።በእርግጥ ዕቃዎቹ በመጸዲጃ ክፍል ውስጥ ተቆልፈው እንዲለ በጥቆማ ተይዘዋል ከመባለ በስተቀር ከግቢ ውጪ አልተወሰደም።አመልካችም ቢሆን ዕቃዎቹ ከግቢ ውጪ ተወስደዋል በማለት አልተከራከረም።ይሁን እንጂ ተጠሪዎቹ ዕቃዎቹን ወጪ ተደርገው ለተለያዩ የባንኩ ቅርንጫፍች እና የስራ ክፍልች እንደተሰራጩ አድርገው በመመዝገብ እና ከተሰራጩት ዕቃዎች በመቀነስ ከመደበኛ የዕቃ ማከማቻ ቦታ ውጭ በመጸዲጅ ክፍል ውስጥ ቆልፈው ያስቀመጡበት ሕጋዊ ምክንያት መኖሩን አስካላስረደ ድረስ የፈጸሙት አድራጎት በድርጅቱ ላይ የተፈጸመ የማጭበርበር ድርጊት ነው ልባል የማይችልበት ምክንያት የለም።ዕቃዎቹ ከግቢው ሳይወጡ ድርጊቱ በሙከራ ደረጃ ላይ እንዲለ የተደረሰበት መሆኑ እና በግቢው መውጫ ላይ ፍተሻ የሚደረግ መሆኑም ተጠሪዎቹ ዕቃዎቹን ከግቢው አውጥተው ለግል ጥቅማቸው የማዋል ሀሳብ አልነበራቸውም ወደሚል ድምዲሜ ሉያደርስ የሚችል አይደለም።በመሆኑም ተጠሪዎቹ ዕቃዎቹን ከመደበኛ ቦታቸው ውጪ መጸዲጃ ቤት ውስጥ ማስቀመጣቸው አግባብ አይደለም ከሚባል በቀር በመመካከር ዕቃዎቹን ለግል ጥቅማቸው ለማዋል በማሰብ ከሚላኩ ዕቃዎች ቀንሰው አውጥተው ወስደዋል ለማለት እና በስራቸው ላይ የስርቆት እና የማጭበርበር ድርጊት ፈጽመዋል ለማለት የሚያስችል ባለመሆኑ ስንብቱ ሕገወጥ ነው በማለት የስር ፍርድ ቤቶች የደረሱበት ድምዲሜ በክርክሩ ከተረጋገጠው ፍሬ ነገር ውጭ በመሆኑ ሕጋዊ ተቀባይነት ሉሰጠው የሚገባ ሆኖ አልተገኘም። እንደጥፊቱ ክብደት ሰራተኛው በስራው ላይ የሚፈጽመው የማታለል ወይም የማጭበርበር ተግባር ደግሞ ካለማስጠንቀቂያ የስራ ውል ለማቋረጥ የሚያበቃ ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 በአንቀጽ 27 (1) (ሐ) ስር ተመልክቷል።በመሆኑም የመጀመሪያው ጭብጥ ሲጠቃለል ስንብቱ ሕገወጥ ነው በሚል በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው የውሳኔ ክፍል መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት እና ሉታረም የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
ሁለተኛውን ነጥብ በተመለከተ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለ1ኛ ተጠሪ የ27 ቀናት የዓመት ፈቃድ ወደ ገንዘብ ተቀይሮ እንዱከፈል በሚል ውሳኔ የሰጠው ተጠሪው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ ላይ ያላቸው የዓመት ፈቃድ ወደ ገንዘብ ተለውጦ እንዱከፈላቸው በደፈናው ከመጠየቅ ውጭ ያላቸውን የዓመት ፈቃድ መጠን ጠቅሰው እና ለይተው አለማቅረባቸውን በመግለጽ እና በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 77 (1)፣(5) እና 79 (5) ላይ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች መሰረት አድርጎ ተገቢ ነው ያለውን ግምት በመውሰድ ነው።በሰበር ክርክራቸውም ቢሆን ያላቸውን የዓመት ፈቃድ መጠን በክሳቸው ለይተው አቅርበው የነበረ ስለመሆኑ ተጠሪው ያቀረቡት ክርክር የለም።እንዱህ ከሆነ ደግሞ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመዝገቡን ግልባጭ እና የግራ ቀኙን ክርክር መሰረት አድርጎ ለተጠሪው ሉከፈል የሚገባው የዓመት ዕረፍት መጠን የ27 ቀናት ነው በማለት የሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍበት ሕጋዊ ምክንያት የለም።በመሆኑም በዚህ ረገድ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም።
ሲጠቃለል የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በከፉል መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት እና ሉሻሻል የሚገባው ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ09/10/2006 ዓ.ም.
ተሻሽል የጸናው ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
በአመልካች የተወሰደው የስንብት እርምጃ ሕገወጥ ነው በሚል የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ተሽሯል።
በተጠሪዎቹ መፈጸሙ የተረጋገጠው ጥፊት በአዋጅ ቁጥር 377/1996 በአንቀጽ 27 (1) (ሐ) ድንጋጌ መሰረት የስራ ውላቸውን ካለማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ የሚያስችል በመሆኑ ስንብቱ ሕጋዊ ነው በማለት ወስነናል።
ስንበቱ ሕጋዊ በመሆኑ አመልካች ለተጠሪዎቹ የካሳ ክፍያ እና የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ ሉከፍል አይገባም በማለት ወስነናል።
አመልካች ለተጠሪዎቹ የዓመት ዕረፍት ወደገንዘብ ቀይሮ እንዱከፍላቸው የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ፀንቷል።
አመልካች ለተጠሪዎቹ የፕሮቪደንት ፈንድ ሉከፍል የሚገባው ተጠሪዎቹ ባዋጡት መጠን ብቻ ነው በማለት ወስነናል።
በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ የተያዘው አፈጻጸም ታግድ እንዱቆይ በዚህ መዝገብ በ17/11/2006 ዓ.ም. ተሰጥቶ የነበረው ትዕዛዝ ተነስቷል።ይጻፍ።
እንዱያውቁት የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይላክ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቶአል።
No topics extracted.