አንድ አሰሪ ሰራተኛው ህጋዊ የመብት ጥያቄ በማቅረቡ ምክንያት የስራ ውለን ማቋረጥ ህገወጥ ተግባር ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀፅ 26(2)(ሐ)
No summary available.
ቀን 14/07/2007 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመስል አመልካች፡- ፒተርድስ ፕሮዲክስት ማንፊክቸሪንግ (አ.ማ) አልቀረቡም ተጠሪች፡- 1. ወ/ሮ ይፍቱስራ ነጋሽ ጠበቃ ኤሉያስ አበበ ቀረቡ 2. ወ/ሮ ገነት ወንድሙ ጉዲዩን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ነው። በስር ፍርድ ቤት አንደኛ ተጠሪ አንደኛ ከሳሽ ፤ በዚህ ክርክር ተሳታፉ ያልሆነችው ወ/ሪት መድሀኒት ሙቃ ሁለተኛ ከሳሽ ሁለተኛ ተጠሪ ሶስተኛ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
የክርክሩ መነሻ ተጠሪዎች ያቀረቡት ክስ ነው። ከሳሾች ተከሳሽን ለምንድን ነው ለእኛ የቦነስ ክፍያ የማይከፈለን በማለት በእረፍት ሰዓት በመጠየቃችን ከስራ አግድ አቆይቶ ሚያዝያ 2 ቀን 2005 ዓ/ም በተፃፈ ደብዲቤ ከህግ ውጭ ያሰናበተን ስለሆነ የካሳ ክፍያ ፣ የማሰጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ ፣ ክፍያ የዘገየበት ክፍያና ወጭና ኪሳራ እንዱከፍል ይወስንልን በማለት ክስ አቅርበዋል። አመልካች በስር ፍርድ ቤት ተከሳሽ ሆኖ ቀርቦ ከሳሾች ህገ ወጥ የስራ አድማ እንዱያደርጉ ላልች ሰራተኞችን በማስተባበርና በመቀሰቀስ ፤ የአድማ ስራ በመሆንና ረብሻና ሁከት የመፍጠር ሙከራ ማድረጋቸው ተረጋግጦ ከስራ የተሰናበቱ በመሆኑ ስንብቱ ህግን መሰረት ያደረገ ነው በማለት ተከራክሯል።
የስር ፍርድ ቤት በግራ ቀኙ በኩል ያቀረቡትን ምስክሮች ከሰማ በኃላ ተከሳሽ ከሳሾችን ከስራ ያስናበታቸው በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27 ንዐስ አንቀጽ 1(ሸ) መሰረት በመሆኑ ስንብቱ ህግን መሰረት ያደረገ ነው በማለት የከሳሾችን ክስ ውድቅ አድርጎታል። የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ተጠሪዎች ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል። የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ ግራ ቀኙ በስር ፍርድ ቤት አቅርበው የሰማቸውን ምስክሮች ቃል በሰፉው ፤ ከዘረዘርና ከመርመር በኃላ አመልካች የቦነስ ክፍያ የማይከፈል መሆኑን በማስታወቂያ በመግለጽ ፤ ሰራተኞች ለምን አይከፈለንም የሚል ጥያቄ ያቀረቡ መሆኑን ፣ አመልካች ሰራተኞችን በሁለት ከፍል ማነጋገር እንደጀመርና ይግባኝ ባዮች (ተጠሪዎች) መብታችን ይከበር በማለት መግለፃቸውን ፣ አመልካች ይህንን በመናገራቸው ምክንያት አድማ ቀስቅሰዋል በማለት ይግባኝ ባዮችን (ተጠሪዎችን) ከስራ ያገደና ያስናበታቸው መሆኑ በማስረጃ የተረጋገጠው ፍሬ ጉዲይ እንደሆነ ገልፆና አንደኛ ይግባኝ ባይ (አንደኛ ተጠሪ) ዘግይተው ወደስራ የገባች መሆኑና እሷ ስራ ከመግባቷ በፉት ላልች ሰራተኞች ቦነስ ለምን አይከፈለንም የሚል ጥያቄ ማንሳታቸውን በአመልካች (መልስ ሰጭ) ምስክር የተረጋገጠ መሆኑን በውሳኔው አስፍሮ ፣ በዕለቱ ይግባኝ ባዮች ፣ የተናገሩት ንግግር የመብት ጥያቄ እንጅ ህገ ወጥ የስራ ማቆም አድማ ቅስቅሳ አይደለም። ይግባኝ ባዮች ረብሻና ሁከት የመፍጠር ተግባር አልፈፀሙም በማለት ስንብቱ ህገ ወጥ ስለሆነ መልስ ሰጭ (አመልካች) ለይግባኝ ባዮች (ለተጠሪዎች) የስራ ስንብት ክፍያ ፣ የካሳ ክፍያና የማስጠንቀቂያ ክፍያ ይክፈል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች ጥቅምት 3 ቀን 2007 ዓ/ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ፣ በዕለቱ አመልካች ምርት ባለማምርቱ ፣ ኪሳራ እንደደረሰበት ተረጋግጧል። ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የአመልካች ምስክሮች ቃል ተዓማኒነትና ክብደት በአግባቡ ሳይመዝን ስንብቱ ህገ ወጥ ነው በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪዎች ጥር 12 ቀን 2007 ዓ/ም በተፃፈ መልስ ተጠሪዎች ህገወጥ አድማ ሰራተኛ ያነሳሳን ስለመሆኑ በማስረጃ እንዲላስርዲ በማረጋገጥ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ የህግ ስህተት የላለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት መልስ ሰጥተዋል። አመልካች የካቲት 5 ቀን 2007 ዓ/ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው የፅሁፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አመልካች ተጠሪዎችን ከስራ ያስናበተው ከህግ አግባብ ውጭ ነው በማለት የሰጠው ውሳኔ የህግ መሰረት አለው? ወይስ የለውም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው ከላይ የተያዘውን ጭብጥ ለመወሰን በመጀመሪያ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ፍሬ ጉዲይ የማጣራት ፣ ማስርጃ የመመርመርና የመመዘን ስልጣኑን በመጠቀም የደርሰበትን የፍሬ ጉዲይና የማስረጃ ምዘና መደምደሚያ መመልከት አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል። አመልካች ህገ ወጥ አድማ ተደርጓል በሚልበት ቀን ፣ የቦነስ ክፍያ እንደማይከፍል ማስታወቂያ በመለጠፍ ፣ የድርጅቱ ሰራተኞች ለምን ቦነስ አይከፈለንም?
የሚል ጥያቄ ማንሳታቸውን ፣ አመልካችም በሰራተኞች ጥያቄ ምላሽ በመስጠትና ሰራተኞችን በሁለት ከፍል ያነጋገረ መሆኑን ፣ አመልካች ሰራተኞችን በሚያነጋግርበት ጊዜ ተጠሪዎች ፣ መብታችን ይከበር በማለት መናገራቸውን ፣ ከዚህ ውጭ ተጠሪዎች የፈጸሙት ፣ ተግባር የላለ መሆኑንና አንደኛ ተጠሪ ወደ ስራ የገባችው ዘግይታ እንደሆነ አመልካች በማስረጃ የተረጋገጠ ፍሬ ጉዲይ መሆኑን የስር ፍርድ ቤት የፍሬ ጉዲይና የማስረጃ ምዘና ስህተት በይግባኝ የመመርመርና የማረም ስልጣኑን በመጠቀም የደረሰበት የፍሬ ጉዲይና የማስርጃ ምዘና መደምደሚያ ያሳያል።
ይህንን ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የደረሰበትን የፍሬ ጉዲይና የማስረጃ ምዘና መደምደሚያን አመልካች ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የምስክሮችን ቃል ተአማኒነትና ክብደት ሲመዝን ፈጽሞታል የሚለውን ስህተት ፣ በሰበር ፣ የማየትና የማረም ስልጣን ለዚህ ሰበር ችልት በህገመንግስቱ አንቀጽ 80 ንዐስ አንቀጽ 3(ሀ) እና በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 አልተሰጠውም። በመሆኑም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የደርሰበትን የፍሬ ጉዲይና የማስረጃ ምዘና መደምደሚያ ዕውነት ነው ብለን በመቀበል ፤ ተጠሪዎች አመልካች ሰራተኞች በሁለት ቡድን ከፍል ሲያወያይ ፣ መብታችን ይከበር በማለት ሀሳባቸውን መግለፃቸው ወይም መናገራቸው የህገወጥ የስራ ማቆም አድማ መሪና የረብሻና የሁከት መፍጠር ሙከራ ነው ተብል ተጠሪዎችን ያለማሰጠንቀቂያ ከስራ ለማሰናበት የሚያበቃ ምክንያት መሆኑን አግባብነት ካላው የህግ ድንጋጌ ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
ሰራተኞችን አመልካች ቦነስ ክፍያ ስለማይከፈልበት ምክንያት በሁለት ከፍል በሚያነጋግርበት ወቅት ተጠሪዎች መብታችን ይከበር የሚል ንግግር መናገራቸው ፤ ህጋዊ መብታችን ነው የሚለት የቦነስ ክፍያ እንዱከፈላቸው ሀሳባቸውን የገለጹ መሆኑን እንጅ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27 ንዐስ አንቀጽ 1(ሸ) መሰረት በአሰሪው ንብረት ወይም ከድርጅቱ ስራ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ባለው በማናቸውም ንብረት ላይ ሆነ ብል ወይም በከባድ ቸልተኝነት ጉዲት የማድረስ ጥፊት የፈፀመ መሆኑን የሚያሳይ አይደለም። አንድ አሰሪ ሰራተኛው ህጋዊ የመብት ጥያቄ በማቅረቡ ምክንያት የስራ ውለን የሚያቋርጥ ከሆነ ህገወጥ ተግባር እንደሆነ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 26(2) ሐ) ተደንግጓል። ከዚህ አንፃር ሲታይ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት አመልካች ተጠሪዎችን ከስራ ያስናበተው ከህግ አግባብ ውጭ ነው በማለት አመልካች ለተጠሪዎች የካሳ ክፍያ ፣ የስንብት ክፍያና የማስጠንቀቂያ ክፍያ እንዱከፍል የሰጠው ውሳኔ ከላይ የጠቀሳቸውን የህግ ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገና መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለው ነው በማለት ወስነናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሀምላ 30 ቀን 2006 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት ህዲር 15 ቀን 2007 ዓ/ም የሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል ይፃፍ።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጣውን ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገበ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ የማይነበብ የአመስት ዳኞች ፊርማ አለበት።