አንድ ሰራተኛ በመደዲው ለአምስት የስራ ቀናት ካለበቂ ምክንያት ከስራ መቅረቱ የተረጋገጠ እስከሆነ ድረስ አሰሪው በዚሁ ምክንያት ሰራተኛውን ካለማስጠንቀቂያ ከስራ ያሰናበተው ስለመሆኑ በደብዲቤ ሳይገልፅ መቅረቱ የሥራ ውለ በሕግ አግባብ አልተቋረጠም ወደሚል መደምደሚያ የሚያደርስ ስላለመሆኑ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀፅ 27(1) (ለ)
No summary available.
መጋቢት 3 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- መድሕን ኪሮስ አልማው ወላ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመስል አመልካች፡- አቶ መልካሙ አረጋ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ተስፊዬ ለገሰ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ - ጠበቃ ይትባረክ መኮንን ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቶአል።
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ አመልካች በአሁኑ ተጠሪ ላይ በ09/12/2005 ዓ.ም አዘጋጅተው ባቀረቡት ክስ ነው። የክሳቸውም ይዘት ባጭሩ፡-ከሳሽ ከጥር 30 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ በወር ብር 8,076 ደመወዝ እና ብር 100 አበል እየተከፈላቸው በተከሳሽ ድርጅት ውስጥ በድዘር ኦፕሬተርነት የስራ መደብ ተቀጥረው በመስራት ላይ እያለ ተከሳሽ ከ01/11/2005 ዓ.ም ጀምሮ በእርሳቸው ምትክ ላላ ሰራተኛ በመቅጠር የስራ ውላቸው በቃል ያቋረጠባቸው መሆኑን የሚገልጽ ሆኖ የስንብት እርምጃው ሕገወጥ ነው ተብል ሕገ ወጥ የስራ ስንብት የሚያስከትላቸውን ክፍያዎች እና ያልተጠቀሙበትን የዓመት ዕረፍት ክፍያ በድምሩ ብር 106,381.00 ተከሳሽ እንዱከፍላቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት የተጠየቀበት ነው።
ተከሳሽ ድርጅት በበኩለ በ11/02/2006 ዓ.ም በሰጠው መልስ ከሳሽ በራሳቸው ከስራ ከመቅረታቸው ውጪ ተከሳሽ ያላሰናበታቸው መሆኑን፣ሁለም ሰራተኞች ለተረከቡት የድርጅቱ ንብረት ዋስትና እንዱያቀርቡ ተከሳሽ ያስተላለፈውን ትዕዛዝ ከሳሽ ለመቀበል ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸውን፣ዋስትና ለማቅረብ ያላቸውን ፈቃደኝነት ከ21/10/2005 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 30/10/2005 ዓ.ም ድረስ እንዱያስታውቁ በቃልም ሆነ በጽሁፍ ቢገለጽላቸውም ከሳሽ ይህንን ከማድረግ ፊንታ ከ21/10/2005 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 30/10/2005 ዓ.ም ድረስ በተከታታይ ከስራ መቅረታቸውን፣በ03/11/2005 ዓ.ም ቢሮ ተገኝተው ተመሳሳይ መልዕክት ቢነገራቸውም ያልፈጸሙ እና እንደገና ከ03/11/2005 ዓ.ም እስከ 08/12/2005 ዓ.ም ድረስ ስራ ላይ አለመገኘታቸውን፣ከዚህ በኃላ ከሳሽ በ08/12/2005 ዓ.ም ቢሮ ቀርበው ስራቸውን በፈቃዲቸው መልቀቃቸውን በመግለጻቸው የተዘጋጀላቸውን ክፍያ እና የስራ ልምድ እንዱወስደ ተጠይቀው ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸውን፣በከሳሽ ምትክ ላላ ሰራተኛ የተቀጠረው ከዚህ ሁለ በኃላ በ05/01/2006 ዓ.ም. መሆኑን በዝርዝር በመግለጽ ክሱ ውድቅ እንዱደረግ ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱም ክሱን እና የግራ ቀኙን ምስክሮች ከሰማ በኃላ አጠቃላይ ክርክሩን መርምሮ የከሳሽ ምስክሮች ቃል ተከሳሽ ከሳሽን በቃል ከስራ እንዲሰናበተ የሚያስረዲ አለመሆኑን፣ከሳሽ ዋስ የሚጠሩ መሆን አለመሆኑን እስከ 30/10/2005 ዓ.ም ድረስ እንዱያስታውቁ፣ይህ ካልሆነ ግን ስራቸውን በራሳቸው ፈቃድ እንደለቀቁ ተቆጥሮ የስራ ግንኙነቱን እንደሚያቋርጥ ተከሳሽ በ21/10/2005 ዓ.ም የሰጠው ማስታወቂያ በይዘቱ ከሳሽ እስከተባለው ቀን ድረስ ሀሳባቸውን ካልገለጹ ተከሳሽ ከ30/10/2005 ዓ.ም ጀምሮ የስራ ውለን እንደሚያቋረጥ የሚያመለክት መሆኑን፣የስራ ውላቸው ከ30/10/2005 ዓ.ም ጀምሮ እንደተቋረጠ የሚቆጠር ከሆነ ደግሞ ከዚህ ቀን በኃላ ከሳሽ በስራ ቦታው የሚገኙበት ምክንያት ስለማይኖር ከሳሽ በተጨማሪ ከ03/11/2005 ዓ.ም እስከ 08/11/2005 ዓ.ም ድረስ ስራ ላይ አልተገኙም በማለት ተከሳሽ ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት የላለው መሆኑን፣ከሳሽ ከ21/10/2005 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 30/10/2005 ዓ.ም ድረስ በመደዲው ከስራ መቅረታቸው የተረጋገጠ ቢሆንም ተከሳሽ ይህንን ድርጊት የማሰናበቻ ምክንያት አድርጎ በደብዲቤ እስካልገለጸ ድረስ ከሳሽ የተሰናበቱት በመደዲው ከአምስት የስራ ቀናት በላይ ከስራ በመቅረት በራሳቸው አነሳሽነት ነው ልባል የሚችል አለመሆኑን፣በአጠቃላይ ከሳሽም በራሳቸው አነሳሽነት ሰራቸውን ስላልለቀቁ እና ተከሳሽም ስላላሰናበታቸው ስንብቱ ሕገወጥ መሆኑን ገልጾ በክሱ ከተጠየቀው ክፍያ ውስጥ ተከሳሽ ብር 79,189.66 ግብር ከተቀነሰ በኃላ ለከሳሽ እንዱከፍል ውሳኔ ሰጥቷል።
በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ተከሳሹ ባቀረበው ይግባኝ ሳቢያ የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ ተከሳሽ በ21/10/2005ዓ.ም የሰጠው ማስታወቂያ በማስረጃነት የቀረበው በከሳሽ ሳይሆን በተከሳሽ በኩል ሆኖ እያለ እና የማስታወቂያው ይዘትም የስራ ውለ በተከሳሽ አነሳሽነት መቋረጡን የማያረጋግጥ ሆኖ እያለ እንዱሁም ከሳሽ በመደዲው ከአምስት የስራ ቀናት በላይ ከስራ መቅረታቸው ተረጋግጦ እያለ የስር ፍርድ ቤት የስራ ውለ የተቋረጠው በተከሳሽ አነሳሽነት ነው፣ስንብቱም ሕገወጥ ነው በማለት የሰጠው ውሳኔ ተገቢነት የላለው መሆኑን ገልጾ ውሳኔውን በማሻሻል ተከሳሽ ከሕግ ውጪ የስራ ውለን አቋርጧል በሚል የተሰጠውን እና ሕገወጥ የስራ የስንብት እርምጃ የሚያስከትላቸውን ክፍያዎች ተከሳሽ ለከሳሽ እንዱከፍል የተሰጠውን የውሳኔ ክፍል ሽሮ የዓመት ዕረፍት በገንዘብ ተቀይሮ እንዱከፈል የተሰጠውን የውሳኔ ክፍል ብቻ በማጽናት ውሳኔ ሰጥቷል።አመልካች አቤቱታቸውን ለዚህ ችልት ያቀረቡት ይዘቱ ከላይ የተመለከተው የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ሲሆን የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ አመልካች ዋስ ካልጠሩ ተጠሪው የስራ ውላቸውን እንደሚያቋርጥ ገልጾ የጻፈላቸው መሆኑ በተረጋገጠበት እና አመልካች ዋስ አለማቅረባቸው ባልተካደበት ሁኔታ ስንብቱ ሕጋዊ ነው ተብል በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የመወሰኑን አግባብነት ተጠሪው ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል። የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር መርምረናል።
በዚህም መሰረት አመልካች ክስ ያቀረቡት ተጠሪው ከ01/11/2005 ዓ.ም ጀምሮ በእርሳቸው ምትክ ላላ ሰራተኛ በመቅጠር የስራ ውላቸውን በቃል ያቋረጠባቸው መሆኑን በመግለጽ ሲሆን ተጠሪው በበኩለ አመልካችን እንዲላሰናበተ እና በራሳቸው ከስራ እንደቀሩ በመግለጽ ተከራክሯል።በመሰረቱ ማንኛውም ተከራካሪ ወገን ለክርክሩ ምክንያት የሚያደርጋቸውን ፍሬ ነገሮች የማስረዲት ሸክም እንዲለበት የሚታወቅ ነው።በተያዘው ጉዲይ የአመልካች የምስክሮች ቃል ተጠሪው አመልካችን በቃል ከስራ እንዲሰናበተ የሚያስረዲ አለመሆኑን የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ተቀብል በውሳኔው ላይ አስፍሯል።እንዱህ ከሆነ ደግሞ አመልካች በክሳቸው መሰረት አስረድተዋል ልባል የሚችልበት ሕጋዊ ምክንያት አይኖርም።በአሰሪው በቃል ከስራ ተሰናብቻለሁ በሚል ክስ የሚያቀርብ ሰራተኛ ይህንኑ የማስረዲት ግዳታ ያለበት ስለመሆኑ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመዝገብ የተሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ለተያዘው ጉዲይ ተፈጸሚነት ሉኖረው የሚገባው መሆኑን ተገንዝበናል።
በልላ በኩል ተጠሪው ከ 01/11/2005 ዓ.ም ጀምሮ ከስራ እንደሚያሰናብተኝ በ 21/10/2005 ዓ.ም በጻፈው ማስታወቂያ አረጋግጦ እያለ ስንብቱ ሕገወጥ አይደለም ተብል የተወሰነው በአግባቡ አይደለም በማለት አመልካች ተከራክረዋል። ይሁን እንጂ አመልካች ከ21/10/2005 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 30/10/2005 ዓ.ም ድረስ ከስራ መቅረታቸው የተረጋገጠ በመሆኑ፣በመደዲው ለአምስት የስራ ቀናት ያለበቂ ምክንያት ከስራ መቅረት ደግሞ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 27(1)(ለ) መሰረት ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውል ለማቋረጥ የሚያስችል ምክንያት በመሆኑ፣በዚህ ምክንያትም አመልካች የስራ ውላቸውን ከ30/10/2005 ዓ.ም በፉት በራሳቸው አነሳሽነት እንዲቋረጡ የሚቆጠር በመሆኑ እና ይህም ተጠሪው በ21/10/2005 ዓ.ም የሰጠው ማስጠንቀቂያ ከ01/11/2005 ዓ.ም ጀምሮ የአመልካችን የስራ ውል እንዲቋረጠው የሚያመለክት ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጥያቄ የማንሳትን እና የመመርመርን አላስፈላጊነት የሚያስከትል በመሆኑ ተጠሪው የስራ ውላን ከ01/11/2005 ዓ.ም ጀምሮ እንዲቋረጠው ሉቆጠር ይገባል በማለት አመልካች ያቀረቡት ክርክር ሕጋዊ መሰረት ያለው ሆኖ አልተገኘም።አንድ ሰራተኛ በመደዲው ለአምስት የስራ ቀናት ካለበቂ ምክንያት ከስራ መቅረቱ የተረጋገጠ እስከሆነ ድረስ አሰሪው በዚሁ ምክንያት ሰራተኛውን ካለማስጠንቀቂያ ከስራ ያሰናበተው ስለመሆኑ በደብዲቤ ሳይገልጽ መቅረቱ በአዋጁ አንቀጽ 27 (1) (ለ) መሰረት የስራ ውለ በሕግ አግባብ አልተቋረጠም ወደሚል መደምደሚያ የሚያደርስ አይደለም።በመሆኑም በዚህ ረገድ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተደረሰበትን የተሳሳተ መደምደሚያ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ማረሙ ሕጉን መሰረት ያደረገ ነው ከሚባል በቀር የሚነቀፍበት ሕጋዊ ምክንያት የለም።
ሲጠቃለል ይግባኝ ሰሚው ፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ የነበረውን ውሳኔ በማሻሻል የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ ስላልተገኘ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
የተሰጠውን ውሳኔ በማሻሻል የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ 12/12/2006 ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
እንዱያውቁት የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይላክ።
የሰበር ክርክሩ ያስከለተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቶአል።
No topics extracted.