በአንድ መተዳደሪያ ደንብ በማህበር አባላትና በድርጅቱ መካከል የሚነሱ አለመግባባቶች በመጀመሪያ በእርቅ መፈታት አለባቸው የሚል ድንጋጌ ሲኖር ይኸው ሥርዓት ሳይፈፀም ወደ ፍርድ ቤት ክስ ማቅረብ አግባብነትየልለው ስለመሆኑ ተዋዋይ ወገኖች በመካከላቸው የሚነሳ አለመግባባትን በተመለከተ ጉዳያቸው ፍርድ ቤት ከመቅረቡ በፊት በሽምግልና እንዲታይ ላሰማሙ ሥለመቻላቸው፣ የፍ/ሕ/ቁ. 1731(1)፣1732፣1736፣1738
No summary available.
የካቲት 06 ቀን 2007 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሀመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽላት ይመስል አመልካች፡- የከሰረው ሆላንድ ካር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጠበቃ ግርማ አለሙ ቀረቡ ተጠሪ፡- ዘመን ባንክ /አ.ማ/ ነገረ ፈጅ አቶ አዳም ሰገድ በላይ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የመዝገብ ግንቦት 5 ቀን 2006 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔና የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ ግንቦት 28 ቀን 2006 ዓ/ም የሰጠው ትእዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዳዩ የእግድ ትእዛዝ መነሳትን የሚመለከት ነው።
የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የስር ፍ/ቤት የዕግድ ትእዛዝ ተነስቶ ተጠሪ በመያዣነት የያዘውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/1990 በአዋጅ ቁጥር 216/1992 እንደተሻሻለው በተደነገገው መሰረት ንብረቶቹን በሀራጅ ሽጦ ለዕዳው መክፈያ ላያደርግ ይገባል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቅርቧል። ይግባኝ ሰሚው ችሎት የአመልካችን ይግባኝ በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁ. 337 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካች ሰኔ 9 ቀን 2006 ዓ/ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ አዋጅ ቁጥር 97/1990 እና አዋጅ ቁጥር 216/1992 ስለመክሰር የሚደነግግ ድንጋጌዎች የሉትም። በመክሰር ጉዳይ ተፈጻሚነት ላኖረው የሚገባው የንግድ ህጉ ነው። የከሰረው ድርጅት ንብረት በንግድ ህጉ መሰረት እንዲጣራና እንዲሸጥ መደረጉ፣ የሁሉንም ገንዘብ ጠያቂዎች መብትና ጥቅም የሚያስከብርና ተጠሪም በመያዣው ላይ አለኝ የሚለውን መብት የማያሳጣው በመሆኑ በተናጠል ንብረት ለመሸጥ ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ ላደረግ ይገባዋል። ባለዕዳው የተጠሪ እዳ ከመክፈሉ በፊት ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ላከፈሉ የሚገባ የሰራተኞች ደመወዝ ልሎች ክፍያዎችና የመንግስት ግብር በአግባቡ ተጣርቶ ባልተለየበት ሁኔታ፣ ተጠሪ መያዥያ በተናጠል እንዲሸጥ ያቀረበውን ጥያቄ መፍቀድ የህጉን ዓላማ የማያሳካ በመያዥያ ያልተያዙ የባለ እዳውን ንብረቶች ለብክነት የሚዳርግና ጥበቃው ከፍተኛ ወጪ እንዲያስወጣ የሚያደርግ ነው። ስለዚህ እግዱ እንዲነሳ የተሰጠው ውሳኔ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልን በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ ነሀሴ 27 ቀን 2006 ዓ/ም በተፃፈ መልስ አዋጅ ቁጥር 97/1990 እና አዋጅ ቁጥር 216/1990 አንድ የንግድ ድርጅት ሳይከስርም ሆነ መክሰሩ በፍርድ ከተረጋገጠ በኃላ ባንኮች ብድር ሲያበድሩ በመያዣነት የያዙትን ንብረት በሀራጅ ሽጠው የዕዳው መክፈያ እንዲያደርጉ ታስበው የታወጁ ህጎች ናቸው። ከዚህ አንጻር ተጠሪ ለከሰረው ሆላንድ ካር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ገንዘብ ሲያበድር በመያዣነት የያዘውን የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረት በሀራጅ ለመሸጥ ያቀረበውን ጥያቄ የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችሎት የሰጡት ትእዛዝ ስህተት የለበትም የሰራተኞች ደመወዝና የመንግስት ግብርን በተመለከተ ተጠሪ በሀራጅ ንብረቱን ሲሸጥ በራሱ የሚከፍላቸውና የሚፈጽማቸው ግድታዎች በመሆናቸው አመልካች መከራከሪያ አድርጎ ማቅረቡ የህግ መሰረት የለውም በማለት ተከራክሯል። አመልካች ተጠሪ በመያዥያነት ይዥዋለሁ የሚለውን ፋብሪካ ህንጻና ማሽነሪዎች በተናጥል ከሸጠ፣ ያልተገጣጠሙ መኪናዎችን ገጣጥሞ ለመሸጥና ለእዳው መክፈያ ለማድረግ የማያስችል ነው። የሰራተኞቹን የቀዳሚነት መብትና የመንግስትን ግብር በቀዳሚነት የመክፈል ግድታ ለመወጣት የማያስችል በመሆኑ የዕግድ ትእዛዝ ጸንቶ ላቆይ ይገባል በማለት መስከረም 30 ቀን 2007 ዓ/ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከስር የክርክር አመጣጥና በዚህ ሰበር ችሎት ግራ ቀኙ ያቀረቡት የጹሁፍ ክርክር ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤትና የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚው ችሎት የከሰረው ሆላንድ ካር መኪና መገጣጠሚያ ድርጅት የሚንቀሳቀስ ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት እንዳይሸጥ እንዳይለወጥና ለሶስተኛ ወገን እንዳይተላለፍ የስር ፍ/ቤት የሰጠው የእግድ ትእዛዝ ተነስቶ ተጠሪ በተናጥል በመያዥያ የያዘውን የፋብሪካ ህንፃና ማሽነሪ በሀራጅ እንዲሽጥ የሰጡት ውሳኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዳዩን መርምረናል።
ጉዳዩን እንደመረመርነው ባንኮች ያበደሩት የብድር ገንዘብ በወቅቱ ሳይከፈላቸው በሚቀርበት ጊዜ በመያዥነት የያዙትን ንብረት በሀራጅ በመሸጥ ብድራቸውን እንዲከፈል ለማድረግ የሚያስችላቸው ስልጣንና ስርዓት በአዋጅ ቁጥር 90/1997 በአዋጅ ቁጥር 216/1998 እንደተሻሻለ በአዋጅ ህግ አውጭው ደንግጓል። በልላ በኩል አንድ የንግድ ድርጅት መክሰሩ በፍርድ ተረጋግጦ ከተወሰነ በኃላ ከከሰረው የንግድ ድርጅት ገንዘብ የመጠየቅየቀዳሚነት መብት ያላቸው አበዳሪዎች እና ልሎች ገንዘብ ጠያቂዎች ጥያቄ ላስተናገድ የሚችልበት ዝርዝር አሰራር በንግድ ህጉ በአምስተኛው መፅሐፍ በዝርዝር ተደንግጓል።
በያዝነው ጉዳይ አመልካችንና ተጠሪ የሚከራከሩበት በጉዳዩ ተፈፃሚነት ላሰጠው የሚገባው አዋጅ ቁ.97/1990 እንደተሻሻለ መሆን ይገባል? ወይስ በንግድ ህጉ አምስተኛው መጽሐፍ የተደነገጉ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ላሆን ይገባዋል የሚለውን መከራከሪያ በማንሳት ነው የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስር ፍ/ቤት የሰጠው የእግድ ትእዛዝ እንዲነሳ ውሳኔ የሰጠው አዋጅ ቁጥር 97/1990 እና አዋጅ ቁጥር 216/1992 ከንግድ ህጉ አምስተኛ መጽሀፍ ከተደነገጉት ድንጋጌዎች በኃላ የወጡ ስለሆነ ተፈፃሚነትና ገዥነት አላቸው በማለት ነው። አመልካች የሚከራከረው ከአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና አዋጅ ቁጥር 216/1992 ስለመክሰር የሚመለከት ድንጋጌ የላቸውም የከሰረ የንግድ ድርጅት ንብረት ስለሚሸጥበትና የቀዳሚነት መብት ላላቸው ለልሎች የገንዘብ ጠያቄዎች የሚከፍልበትን ስርዓት የሚደነግጉ ልዩ ድንጋጌዎችን የያዘው የንግድህጉ አምስተኛው መጽሀፍ በመሆኑ፣ በዚህ ጉዳይ ተፈፃሚነት ላኖራቸው የሚገባው የንግድ ህጉ ልዩ ድንጋጌዎች ናቸው በማለት ነው። ይህም ተጠሪ በኃላ የወጣው ህግ በፊት ከወጣው ህግ ላይ የበላይነትና ተፈፃሚነት አለው የሚለውን የህግ አተረጓጎም መርህ መሰረት በማድረግ የሚከራከር መሆኑን ያሳያል። በልላ በኩል አመልካች ልዩ የህግ ድንጋጌዎች በጠቅላላ የህግ ድንጋጌዎች ላይ የበላይነትና ተፈጻሚነት አላቸው የሚለውን የህግ አተረጓጎም መሰረት በማድረግ የሚከራከር መሆኑን ተረድተናል።
በእኛ በኩል በዚህ መዝገብ አመልካችና ተጠሪ ለሚከራከሩበት ጉዳይ ተፈጻሚነት ያለው አዋጅ ቁጥር 97/1990 እንደተሻሻለ መሆን ይገባዋል ወይስ የንግድ ህጉ አምስተኛው መጽሀፍ የሚለው ምርጫ ከመምረጥና አመልካችና ተጠሪ ከጠቀሳቸው የአተረጓጎም መርሆች በላይ የሆኑ በርካታ ሁኔታዎቹን በመመርመር እና መመዘን የሚጠየቅ ሆኖ አግኝተነዋል ይኸውም ተጠሪ በተናጥል የከሰረውን የሆላንድ ካር የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ህንጻና ማሽነሪዎች በሀራጅ እንድሸጥ ቢደረግ የከሰረው የሆላንድ ካር ንብረት ተሸጦ በሚገኘው ገንዘብ ላይ ከተጠሪ በፊት የቀዳሚነት መብት ያላቸውን የሰራተኞችና የመንግስት የግብር ዕዳ ለማጣራትና ለመክፈል የማያስችል መሆኑን አለመሆናቸውን የከሰረው ድርጅት ንብረት ጠባቂና መርማሪ ዳኛ ተጣርቶ እንዲሸጥ መደረጉ ተጠሪ በመያዣነት በያዘው ንብረት ላይ ያለውን ልዩና የቀዳሚነት መብት የሚያሳጣ መሆኑን ወይስ አለመሆኑን እንደዚሁም የከሰረው ድርጅት ንብረት በንብረት ጠባቂና መርማሪ ዳኛ በኩል ተጣርቶ አስፈላጊ በሆነ ጊዜ በፍርድ ቤት ፈቃድና ትዕዛዝ መሰረት እንዲሸጥ መደረጉ የቀዳሚነት መብት የልላቸውን ገንዘብ ጠያቂዎች መብትና ጥቅም በተሻለ ሁኔታ ለማስከበርና ዕዳቸው እንዲከፈላቸው ለማድረግ የሚያስችል ነው ወይስ አይደለም?
የሚሉትን ነጥቦች ግንዛቤ ውስጥ ባስገባ መንገድ ላታይ የሚገባው ሆኖ አግኝተነዋል።
ከዚህ አንጻር ሲታይ፣ተጠሪ በመያዣነት የያዘውን የፋብሪካ ህንጻና የመኪና መገጣጠሚያ ማሽነሪ በተናጥል የሀራጅ ማስታወቂያ አውጥቶ እንዲሸጥ ቢደርግ የከሰረው ድርጅት ሰራተኞች በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 167 የተሰጣቸውን የቀዳሚነት መብት በተሟላ ሁኔታ ለማጣራትና የሰራተኞች ጥያቄ ከተጠሪ በፊት ተከፋይ እንዲሆን በማድረግ የሚያስችል አይደለም። ከዚህ በተጨማሪ ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 በተናጠል የሚያከናውነው የሀራጅ ሽያጭ፣ መንግስት ከከሰረው ሆላንድ ካር መኪና መገጣጠሚያ ድርጅት የሚጠይቀውን ትክክለኛ የግብር ዕዳ በተሟላ ሁኔታ ለማጣራትና ለመወሰን እንደዚሁም ከድርጅቱ ሰራተኞች ቀጥሎ ከተጠሪ በፊት መንግስት ያለውን የቀዳሚነት የግብር እዳ የመጠየቅ መብት የሚያረጋግጥ አይደለም። ከዚህ በተጨማሪ ተጠሪ በተናጥል የሚያከናውነው የሀራጅ ሽያጭ ለልሎች ገንዘብ ጠያቄዎች እዳ መክፈያ ላሆኑ የሚችሉ ያልተገጣጠሙ መኪናዎች እና ልሎች ንብረቶች ባለበት ሁኔታ በመጠበቅ ሽጦ የልሎች ገንዘብ ጠያቄዎቹን ዕዳ ለመክፈል የማያስችል መሆኑን ተጠሪ በመያዣነት ያልያዛቸውን የከሰረው ሆላንድ ካር ንብረቶች ለማጓጓዝና ለማስቀመጥ ተጨማሪ ወጪ የሚጠይቅና የልሎች ገንዘብ ጠያቂዎች መብትና ጥቅም የሚጎዳ መሆኑን ግራ ቀኙ ካቀረቡት ክርክር ተረድተናል።
በአንጻሩ ተጠሪ በመያዣነት የያዘው የፋብሪካ ህንጻና ማሽነሪዎች ከልሎች የከሰረው ሆላንድ ካር ንብረት ጋር ተጣርተው እንዲሸጡ ቢደረግ አመልካች በመያዣነት ይዟቸው የነበሩት ንብረቶች ተሸጠው በሚገኘው ገንዘብ ላይ ያለውን የቀዳሚነት መብት የማያሳጣው መሆኑን ከንግድ ህጉ አንቀጽ 104 እና ልሎች ተከታይ ድንጋጌዎች ለመረዳት ይቻላል።
ከዚህ በተጨማሪ በሂደቱ ከንብረት ጠባቂና መርማሪ ዳኛ በላይ የሆኑ ጉዳዮች ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት እየታዩ ውሳኔ እንዲሰጥባቸው ለማድረግ የሚያስችል አማራጭ እንደሆነ ከንግድ ህጉ አንቀጽ 989 እና አንቀጽ 990 ድንጋጌዎች ለመረዳት ይቻላል። ከላይ በዝርዝር በገለጽናቸው ምክንያቶች የማጣራትና የሽያጭ ሂደቱ፣ ተጠሪ በመያዣነት የያዘው የፋብሪካ ህንጻና የመኪና መገጣጠሚያ ማሽነሪ በተናጠል ይሆን ከልሎች የከሰረው የሆላንድ ካር ንብረቶች ጋር በአንድ ላይ የሚጣራበት የሚከናወነበትንና በመጀመሪያ ከተጠሪ በፊት የቀዳሚነት መብት ያላቸው የድርጅቱ ሰራተኞች ጥያቄና የመንግስት የግብር ዕዳ ተከፍለው የተጠሪ ቀዳሚነት መብት ተጠብቆ መያዣው ተሽጦ የተገኘው ገንዘብ እንዲከፈለው መደረጉ ከተጠሪ በፊት የቀዳሚነት መብት ያላቸውን ገንዘብ ጠያቂዎች የተጠሪንና የልሎች ገንዘብ ጠያቂዎች መብትና ጥቅም የሚያስከብርበመሆኑ የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤትና ይግባኝ ሰሚ ችሎት አዋጅ ቁጥር 97/1990 በንግድ ህጉ አምስተኛ መጽሀፍ በኃላ የታወጀ ነው በሚል ምክንያት የዕግድ ትእዛዝ እንዲነሳ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔና የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የሰጠው ትእዛዝ ተሽሯል።
ተጠሪ በመያዣነት በያዛቸው የፋብሪካ ህንፃና የመኪና መገጣጠሚያ ማሽነሪዎች በአዋጅ ቁጥር 97/1990 ለመሸጥና ለልላ ሰው ለማስተላለፍ የስር ፍ/ቤት የሰጠው የእግድ ትእዛዝ እንዲነሳለትያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት የልለው ነው በማለት ወስነናል። ንብረቶቹ እንዲከበሩየስር ፍ/ቤት የሰጠው ትእዛዝ ጸንቷል።
ተጠሪ በመያዣው ላይ ያለው መብት እንዲከበር የከሰረው ሆላንድ ካር ሂሳብ ተጣርቶ ንብረቶቹ ተሽጠው በመያዣው ላይ ያለው የቀዳሚነት መብት እንዲከበርለንብረት ጠባቂ ለመርማሪ ዳኛና ስልጣን ላለው ፍ/ቤት በህግ አግባብ የማቅረብ መብቱን ይህ ውሳኔ የሚገድበው አይደለም ብለናል።
ጉዳዩ የተጠሪ የመያዣያ መብት ያለበት በመሆኑ በተቀላጠፈ መንገድና በአጭር ጊዜ ውስጥ ላፈጸም ይገባል ብለናል ።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጡትን ውጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻሉ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ
No topics extracted.