አንድ የመንግስት ሰራተኛ የጡረታ ዕድሜው ከደረሰ በኋላ አሰሪው መ/ቤት ፈቃድና ከየትኛውም አካል ተቃውሞ ሣይቀርብ የጡረታ ጊዜው ከተራዘመ ለተራዘመበት ጊዜ የሰራበት ለጡረታ ላያዝ የሚገባው ሥለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 714/2003፣ አዋጅ ቁጥር 515/99 አንቀጽ 85፣89 96833 የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ እና አሥፋው ደነቀ ታህሳስ 8/2007 345 81. በአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት የግልግል ተቋም ውስጥ አንድን ጉዳይ በግልግል እንዲያይ የተቀመጠ የግልግል ዳኛ ከተከራካሪ ወገኖች በአንዱ እንዲነሳ አቤቱታ በሚቀርብበት ጊዜ ይነሳ የተባለው ዳኛ የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት እና ታህሳስ 24/2007 348 አይገባም ብሎ ጥያቄውን ካነሳው ወገን ጋር ላከራከር የማይገባው ሥለመሆኑና ልነሳ አይገባም እያለ በሚከራከርበት ሆኔታም ጉዳዩን ገለልተኛ ሆኖ ያየዋል ተብሎ ሥለማይገመት መነሳት ያለበት ሥለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 9 እና 10 የፍ/ህ/ቁ.3342/ 3340/2/ የግልግል ተቋሙ የተሻሻለ ደንብ አንቀጽ 13 እና 15 አቶ በየነ ወልደገብርኤል 82. አንድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ላስተማራቸው ተማሪዎች ጊዜያዊ ዲፕሎማ ከሰጠ በኋላ ዋናው ዲፕሎማ ሳይሰጣቸው የማስተማር ፈቃዱ ቢነጠቅ እንኳ ፈቃዱን ተነጥቄያለሁ፣ ዋናውን ዲፕሎማ ልሰጥ አልችልም የማለት መብት የልለው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 650/2001፣ ደንብ ቁጥር 199/2003
No summary available.
ታህሳስ 24 ቀን 2007 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽላት ይመሰል አመልካች፡- ዶ/ር መኮንን ንዋይ የአዲስ አበባ ድንታል ሳይንስና ኮልጅ ባለቤትና ዲን - ጠበቃ ግርማ ኃይል ቀረቡ ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ ኦርጂናል ዲፕሎማ ይሰጠኝ ጥያቄ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪዎች በአሁኑ አመልካች ላይ በፍድራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው።የተጠሪዎች የክስ ይዘትም፡-አመልካች በ1999 ዓ/ም አዲስ አበባ ድንታል ሳይንስ ኮልጅውስጥ ለማስተማር ተቀብሎ ለሶስት አመታት የጥርስ ህክምና ትምህርት አስተምሮ በ2002 ዓ/ም ካስመረቀ በኋላ ትራንስክርቢትና ጊዚያዊ ዲፕሎማ የሰጣቸው ቢሆንም ኦርጂናል ዲፕሎማውን ለመስጠት ፈቃደኛ ያለመሆናቸውን ገልጸው ይህንኑ ማስረጃ እንዲሰጧቸው ይወሰን ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጡት መልስም ተጠሪዎች ትምህርቱን ጨርሰው ጊዜያዊ ዲፕሎማ መውሰዳቸውንአምነው ዋናውን ዲፕሎማ ለመስጠት ኮልጁ ዝግጅት ላይ እንዳለ የመንግስት ክልከላና የፈቃድ ስረዛ በማጋጠሙ የተነሳ ማህተምም ሆነ ፊርማ የሚፈርም ባለስልጣን ባለመኖሩ ለተጠሪዎች ኦርጂናል ዲፕሎማ እንዳልተሰጠና በፍርድ ቤት ቢወሰንም ላፈጸም የማይችል መሆኑን ገልጸው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክረዋል።ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማና ተገቢ ነው ባለው መንገድ ሁሉ ከሚመለከተው አካል ስለ ጉዳዩ አጣርቶ የተጠሪዎችን ኦርጂናል ዲፕሎማ አመልካች ላሰጥ የማይችልበት ሕጋዊ ምክንያት የለም ወደሚለው ድምዳሜ ደርሶ ማስረጃውን አመልካች ለተጠሪዎች ላሰጥ ይገባል ሲል ወስኗል።በዚህ ውሳኔ የአሁኑ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ጉዳዩን መርምሮ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ አፅንቶታል።የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።የአመልካቸ የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም በስር ፍርድ ቤት ያቀረባቸውን የክርክር ነጥቦችን የሚያሳይ ሁኖ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላሻር ይገባል በማለት መከራከሩን የሚያሳይ ነው።አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ችሎት እንዲታይ የተደረገ ሲሆን ተጠሪዎች ቀርበውም ግራ ቀኙ በፅሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል።
የክርክሩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች አንጻር እንደሚከተለው መርምሮታል።እንደመረመረውም በጉዳዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ለማለት ይቻላል ወይስ አይቻልም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሁኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪዎች በአመልካች ባለቤትነትና በሚታወቀውና አመልካቹ በዲንነት ያስተዳድሩት ኮልጅ ውስጥ ተመዝግበው በተገቢው መንገድ ትምህርታቸውን መከታተላቸውና መጨረሳቸው ተረጋግጦ ትራንስክርቢትና ጊዜያዊ ዲፕሎማ በአመልካቹ የተሰጣቸው መሆኑ ግራ ቀኙን ያላከራከረ ከመሆኑም በላይ ኮልጁ በመንግስት ክልከላና ፈቃድ ስርዛ ምክንያት ስራውን ያቆመ ቢሆንም ትምህርታቸውን በአግባቡ ተከታትለው ላጠናቀቁት ተማሪዎች ዋናውን ዲፕሎማ እንዳይሰጥ የሚከለክል መመሪያ የልለ መሆኑና ኮልጁ ዲፕሎማውን የመስጠት ግድታ ያለበት መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኤጂንሲ በቁጥር ኤ./4015/ተስጥመ/12/67 በቀን 17/10/2005 ዓ/ም ለስር ፍርድ ቤት በጻፈው ደብዳቤ መረጋገጡን ነው።በመሆኑም ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው የበታች ፍርድ ቤቶች የአመልካች ኮልጅ በመንግስት ስልጠና ለመስጠት መከልከሉና ፈቃድ መሰረዝ ከዚህ የመንግስት እርምጃ በፊት ስልጠናውን በአግባቡ ተከታትለው የጨረሱ ተማሪዎች ኦርጂናል ዲፕሎማ እንዳያገኙ የማያደርግ መሆኑን ከሚመለከተው አካል ምላሽ ተሰጥቷቸው በሚገባ አረጋግጠዋል።አመልካች ማህተም የልለው ስለመሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ ካለመረጋገጡም በላይ ማህተም ያለመኖሩ ወይም ቀድሞ ለተጠናቀቀ የትምህርት ስልጠና በፊርማ አረጋግጦ ማስረጃ ለመስጠት በወቅቱ የነበረው ኃላፊ ያለመኖሩ ተፈፃሚነትባላቸው ሕጎች መሰረት ኦርጂናል ዲፕሎማውን ለተጠሪዎች ላለመስጠት የሚያስችለው መሆኑን አላስረዳም።ይልቁንም አግባብነት ያለው አካል ኦርጂናል ዲፕሎማውን ማግኘት መብታቸው መሆኑን፣ማስረጃው መስጠት ደግሞ የአመልካች ግድታ መሆኑን በሚያስገነዝብ መልኩ አረጋግጧል።በመሆኑም አመልካች ከአዋጅ ቁጥር 650/2001፣ደንብ ቁጥር 199/2003 እና በልሎች አግባብነት ባላቸው ሕጎች የተጣለበትን ኃላፊነት ያልተወጣ መሆኑ በአንጻሩ ተጠሪዎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ለመማር የተቀመጡትን ቅድመ ሁኔታዎች አሟልተውና የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ስርዓቱን በተከተለ አግባብ ስልጠናውን ተከታትለው የጨረሱ መሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ ይህንኑ የሚያረጋግጥላቸውን ማስረጃ ከአመልካች የማግኘት መብት ያላቸው ስለሆነ የበታች ፍርድ ቤቶች ፍሬ ነገሩን በአግባቡ አጣርተውና አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በተጣጣመ መልኩ ተጠሪዎች ኦርጂናሉ ዲፕሎማ ላሰጣቸው ይገባል በማለት መወሰናቸው ሕጋዊ ነው ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት አልተቻለም።በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ውሣኔ
በፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ጥቅምት 18 ቀን 2006 ዓ/ም ተሰጥቶ በፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር143008 መጋቢት 23 ቀን 2006 ዓ/ም የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
አመልካች ለተጠሪዎች ኦርጂናል ዲፕሎማ የመስጠት ግድታ አለበት ተብሎ መወሰኑ በአግባቡ ነው ብለናል።
በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ
No topics extracted.