ክሱ የቀረበው በአንድ ተለይቶ በታወቀ ጊዜ ወይም ቀን የተፈጠረ ክስተትን መሰረት በማድረግ ሳይሆን በተለያየ ጊዜ ተከስተዋል የተባሉ የተለያዩ ችግሮችን መሰረት አድርጐ ሲሆን የማህበር ይፍረስልኝ ጥያቄ ወይም ክስ በይርጋ ይታገዳል የሚባልበት አቶ ሐሰን መሀመድ እና ማጅ አግሮ ፎረስትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ሕዳር 11/2007 322 ሥላለመኖሩ፣ የን/ሕ/ቁ 218(1)፣541(1) የፍ/ሕ/ቁ 1835፣1845 ማህበር 76. ከውጪ አገር በዶላር የተላከ የውጭ ምንዛሬ ለተላከለት አላማ አልዋለም በሚል ገንዘቡ እንዲመለስ ክርክር ሲነሳ ገንዘቡ ላመለስ የሚገባውዶላር በተላከበት ጊዜ በኢትዮጵያ ብር ተመንዝሮ በተሰጠው ተመን መሰረት ስለመሆኑ፣ የፍ/ሕ/ቁ 1705፣1749፣1750፣1771 95069 እነ ስፍሜት አግሮ ቢዝነስ ኃ/የተ/ማህበር /ሁለት ሰዎች/ እና ወ/ሮ ኤልሳቤት ብረቱ ሕዳር 23/2007 325 አፈፃፀም 332 77. በፍርድ ባለዕዳው ሥም የሚታወቅ ቤት ቤቱ በህጋዊ መንገድ የተገነባና የፍርድ ባለዕዳው እስከሆነ ድረስ ካርታና ፕላን የልለው መሆኑ እና ለልላ ሶስተኛ ወገን ተሰጥቷል መባሉ ስጦታው ህጋዊ በሆነ መንገድ እስካልተከናወነ ድረስ ቤቱ ለፍርድ አፈፃፀም እንዳይውል ላያደረግው የሚችል ስላለመሆኑ፣ የፍ/ሕ/ቁ 276፣277 90722 ወ/ሮ መዓዛ መዝገቡ እና አቶ መሰለ ገላው ጥቅምት 11/2007 333 78. በፍርድ ውሣኔ በተሰጠበት ጉዳይ አፈፃፀምን ለማስቀረት በፍርድ ባለመብት እና በፍርድ ባለ ዕዳ የሚደረግ የእርቅ ውል በፍርድ ቤት ቀርቦ ካልፀደቀ በቀር አፈፃፀምን ላያስቀር የሚችል ስላለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 276፣277 98263 ወ/ሮ እናናይቱ ኢሳ እና ወ/ሮ አሲና ሁሴን ጥር 06/2007 336 79. የፍርድ ባለመብት ፍርዱን እንዲፈፀምለት ሲጠይቅ የፍርድ ባለዕዳው የፍርድ ባለመብቱ ተነፃፃሪ የሆነ ግድታውን እንዲወጣ ትዕዛዝ ይሰጥልኝ በማለት ጥያቄ ለማቅረብ የሚችለው በአንድ ፍርድ ቤት ውስጥ ሁለቱም ተከራካሪ ወገኖች የፍርድ ባለመብት መሆናቸው ተረጋግጦ ውሳኔ ተሰጥቶበት እንደሆነ ብቻ ስለመሆኑ፡አንድ የፍርድ ባለእዳ እንደ ፍርዱ እንዲፈጽም ሲጠየቅ ፍርድ ያላረፈበትን ቅድመ ሁኔታ በማቅረብ በአፈፃፃም ላከራከር ሥላለመቻሉ፣ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 398፣ 378
No summary available.
የሰ/መ/ ታህሳስ 24 ቀን 2007 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽላት ይመሰል አመልካች፡- የኢትዮጵያ ኤርፓርቶች ድርጅት - ጠበቃ አቶ ሚካኤል ጉንታ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- አቶ በየነ ወልደገብርኤል - ጠበቃ ኃይሉ ብርሃኑ ጋር ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥር 6 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ሰህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት አመልካች ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዳዩ የግልግል ጉባኤ ዳኛና ሰብሳቢ ሆኖ የተሰየመ ሰው ጉዳይን ከማየት ይነሳልኝ በሚል መንገድ በቀረበ ጥያቄ የተሰጠን ውሣኔ በመቃወም የቀረበ ነው።
የግልግል ተቁሙ የግልግል ዳኞች ጉባኤው በአመልካች ጥያቄ ላይ አስተያየት እንዲያቀርብ በማድረግ፣ የግልግል ዳኞች በአመልካች ማመልከቻ ላይ ዝርዝር አስተያየት ሰጥተዋል። የግልግል ተቋሙ፣ የግልግል የዳኝነት ጉባኤው ሰብሳቢ የሆኑት የአሁኑ ተጠሪ ጉዳዩን ከማየት እንዲነሳለት አመልካች ያቀረበውን ጥያቄ ያልተቀበለው መሆኑን በመግለጽ ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች ለፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርቧል። ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የአመልካችን ይግባኝ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካች ግንቦት 15 ቀን 2006 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪ ግልግል ዳኝነትና ከሰብሳቢነት ላነሳ ይገባል የሚልባቸውን ምክንያቶች በመዘርዘር የሰበር አቤቱታውን አቅርቧል። ከግልግል ዳኝነቱ እንዲነሳ የተጠየቀው ተጠሪ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም ከግልግል ዳኝነት አልነሳም የሚልበትን ዝርዝር ምክንያት በመግለፅ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርቧል። አመልካች ሐምል 8 ቀን 2006 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርበዋል።
የሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ሂደት ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ተጠሪ ከዚህ በኋላ የግልግል ዳኛና ሰብሳሲ ሆኖ ለመቀጠል ይችላል ወይስ አይችልም?
የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዳዩን መርምረናል።
ጉዳዩን እንደመረመርነው ከህዳር 16 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ የዋለው የአዲስ አበባ ንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የግልግል ተቋም የተሻሻለ የግልግል ደንብ ስለዳኞች መነሳትና መተካት በአንቀፅ 15 የደነገገ መሆኑን ተረድተናል። በግልግል ደንቡ አንቀፅ 15 ንዑስ አንቀፅ በአንደኛው ተከራካሪ ወገን አቤቱታ ወይም ጥቆማ መሰረት የግልግል ዳኛ እንዲነሳ ጥያቄ ሲቀርብ፣ ተዋዋዮችና ወይም የይነሳልን ጥያቄ ያልቀረበባቸው የግልግል ችሎት ልሎች አባላት የፅሑፍ አስተያየት ከተቀበለ በኋላ ተቋሙ ውሣኔ እንደሚሰጥ ይገልፃል።
አከራካሪው ጉዳይ ተቋሙ ከግልግል ችሎቱ እንዲነሳ ጥያቄ የቀረበበት ዳኛ፣ ከግልግል ችሎቱ መነሳት የለበትም በማለት በሰጠው ውሣኔ ላይ የአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀፅ 9 እና አንቀፅ 10 መሰረት የይግባኝና የሰበር አቤቱታ ሲቀርብበት ወይም በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 3342 መሰረት መቃወሚያ ሲቀርብበት የተቋሙን ውሣኔ በመደገፍ ተከራካሪ ሆኖ መቅረብ ያለበት ማን ነው? ከጉዳዩ እንዲነሳ ጥያቄ የቀረበበት ዳኛ፣ ጉዳዩን ከማየት እንዳልነሳ የተሰጠው ውሣኔ ተገቢነት ያለው ነው በማለት ጉዳዩን ለግልግል ዳኝነት ካቀረበውና ጥያቄውን ካነሳው ተከራካሪ ወገን ጋር መልስ ሰጭ ወይም ተጠሪ ሆኖ ቀርቦ ዝርዝር ክርክር ካቀረበ በኋላ፣ በፍርድ ቤት ተከራካሪ ሆኖ በቀረበበት ጉዳይና በተከራካራነት ቀርቦ ሲሞግተው የነበረውን ተከራካሪ ወገን ለግልግል ዳኞች የሚያቀርበውን ክርክርና ማስረጃ በገለልተኝነት ስምቶ ላወስን ይችላል ተብሎ በግልግል ዳኝነት እንዲሰየም ማድረግ የግልግል ዳኝነቱን ዓላማ የማያሳካ ነው ወይ? የሚለው ነጥብ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የአዲስ አበባ ንግድ ዘርፍ ማህበራት የግልግል ተቋም የግልግል ደንብ፣ ተቋሙ ጉዳዩን ከማየት እንዲነሳ ጥያቄ የቀረበበት የግልግል ዳኛ ጉዳዩን ከማየት አይነሳም በማለት በሰጠው ውሳኔ ላይ አንደኛው ተከራካሪ ወገን መቃወሚያ ፣ ይግባኝ ወይም የሰበር አቤቱታ በሚያቀርብበትና አቤቱታው ተቀባይነት አግኝቶ መልስ እንዲቀርብ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በሚሰጥበት ጊዜ ፣ የግልግል ተቋሙ ዳኛው ጉዳዩን ከማየት የሚነሳበት በቂ ምክንያት የለም በማለት የሰጠው ውሳኔ በዝርዝር ለማስረዳት ክርክሩን በማን በኩልና እንድት እንደሚያቀርብ በግልፅ ያስቀመጠው ስርዓት የለም። ሆኖም በመርህ ደረጃ የግልግል ተቋሙ ጉዳዩን በግልግል ዳኝነት (ሰብሳቢነት) ተሰይሞ ከማየት የሚከለክል በቂ ምክንያት የለም በማለት የሰጠውን ውሳኔ ለማስረዳት ከሚያቀርብ በስተቀር፣ጉዳዩን ከማየት እንዲነሳ ጥያቄ የቀረበበት የግልግል ዳኛ በተከራካሪነት ቢቀርብና፣የግልግል ዳኛውን ከዳኝነት የሚያስነሳው በቂ ምክንያት አለ ወይስ የለም በሚለው ጭብጥ ዙሪያ ተከራካሪ ሆኖ መሰለፍና ዝርዝር ክርክር የሚያቀርብበት ሁኔታ መኖር የለበትም።
ከዚህ አንጻር ስናየው ተጠሪ በጉዳዩ ተከራካሪ ሆነው መጠራታቸው ስህተት ነወ።
አመልካች ለግልግል ተቋሙ ተጠሪ ከግልግል ዳኛነትና ሰብሳቢነት እንዲነሳ ያቀርብኩት ምክንያት አላግባብ ውድቅ ተደርጎብኛል የሚል የሰበር አቤቱታ ሲደርሳቸው ተጠሪ በጉዳዩ የተለየ ጥቅምና ፍላጎት የልላቸው መሆኑንና ጉዳዩን በዳኝነት እንዳያይ ወይም ከግልግል ዳኝነት እንዲነሳ በህግ ስልጣን የተሰጣቸው አካላት ጉዳዩን አጣርተው የሚሰጡትን ውሳኔ በፀጋ እንደሚቀበሉ ከመግልጽ ማቆም ይገባዋል። ተጠሪም ጉዳዩን በግልግል ዳኝነት ተሰይሜ ማየት አለብኝ የሚል አቋም በመያዝ ሰፊና ዝርዝር ክርክር እንዳቀረቡ ለዚህ ሰበር ችሎት ካቀረቡት ክርክር ተርድተናል። ተጠሪ ከአመልካች ይዘት የቀረበውን ሙግት በመቃወም ፣ ተከራካሪ ሆነው ተሰልፈው ሰፊና ዝርዝር ክርክር ባቀረቡበት ሁኔታ የአመልካችንና በዚህ ክርክር ተሳታፊ ያልሆነውን “ቫርኔሮ” እየተባለ የሚጠራውን ድርጅት ጉዳይ ከዚህ በኋላ በግልግል ዳኝነት ተሰይመው እንዲያዩ መፍቀዱ ከመሰረታዊነትም ሆነ ከዕይታ አንጻር ሲመዘን ፣ የግልግል ዳኝነት ነጻነትና ገለልተኝነት መርህ የሚያስከበር ነው ብሎ ለመደምደም የሚያስችል ሆኖ አላገኘነውም።
ይህ ሁኔታ በራሱ በሶስተኛ ወገን የተመረጠ ዳኛ ባለማዳላቱ ወይም በነጻነቱ ላይ ጥርጣሬ ለማስገባት የሚችል አንድ አንድ የአካባቢ ሁኔታ ምክንያት በሚኖርበት ጊዜ ዳኛው ከግልግል ዳኛነቱ ላነሳ እንደሚችል በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 3340 ንዑስ አንቀጽ 2 የተደነገገውን የሚያሳይ ነው።
ው ሣ ኔ
ተጠሪ በግልግል ዳኝነትና ሰብሳቢነት መቀጠል እንደልለበት የተወሰነ መሆኑን አውቆ ተገቢውን እንዲፈፅም ለአዲስ አበባ ንግድ ዘርፍ ማህበራት የግልግል ተቋም ውሣኔው ይተላለፍለት።
ግራቀኙ በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ለየራሳቸው ይቻሉ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.