No summary available.
ጥቅምት 11 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ አልማው ወል ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽላት ይመሰል አመልካች፡- ወ/ሮ መዓዛ መዝገቡ - VC ሰላልሰራ መቅረባቸውን ማረጋገጥ አልተቻለም።
ተጠሪ፡- አቶ መሰለ ገላነው - VC ሰላልሰራ መቅረባቸውን ማረጋገጥ አልተቻለም።
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቶአል።
በዚህ መዝገብ አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት በስር የፍርድ ባለመብት (በአሁኑ ተጠሪ) እና በስር የፍርድ ባለዕዳ (የአሁኗ አመልካች የቀድሞ ባለቤት በአቶ ሰመረ ኃይሉ) መካከል በነበረው የአፈጻጸም ክርክር የአማራ /ብ/ክ/መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በስር ሁለቱ ፍርድ ቤቶች የተሰጠውን ውሳኔ ሽሮ በፍርድ ባለዕዳው ስም የሚታወቀው ቤት ካርታ እና ፕላን የልለው መሆኑ እና የቀድሞ ተጋቢዎች የፍቺ ውሳኔን ተከትሎ ቤቱን ለልጆቻችን ሰጥተናል በማለት በንብረት ክርክሩ መዝገብ ላይ ማስመዝገባቸው ቤቱ ለፍርድ አፈጻጸም እንዳይውል ላያደርገው የሚችል ባለመሆኑ አፈጻጸሙ በቤቱ ላይ ላቀጥል ይገባል በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ላታረም ይገባል በማለት ነው።
የጉዳዩን አመጣጥ በተመለከተ በስረ ነገሩ ክርክር ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ ተጠሪ በስረ ነገሩ 1ኛ ተከሳሽ እና የአሁኗ አመልካች ባለቤት ከነበሩት ከአቶ ሰመረ ኃይሉ ጋር በ22/06/2000 ዓ.ም.
ጋር አቋቁመውት በነበረው ውል መሰረት ባለመፈጸማቸው አቶ ሰመረ ኃይሉ ጉዳት አድርሰውብኛል በማለት ብር 270,926.50 እንዲከፍሐቸው በሁለቱ ተጋቢዎች ላይ በባህር ዳር ወረዳ ፍርድ ቤት ክስ መመስረታቸውን፣2ኛ ተከሳሽ የነበሩት የአሁኗ አመልካች በሰጡት መልስ በውሉ ተዋዋይ ወገን ባለመሆናቸው በውሉ አለመፈጸም ሳቢያ በከሳሽ ላይ ደርሷል ለተባለው ጉዳት በኃላፊነት ላጠየቁ የሚችሉበት የሕግ አግባብ አለመኖሩን በምክንያትነት በመጥቀስ ፍርድ ቤቱ ከክሱ እንዲያሰናብታቸው መጠየቃቸውን፣ፍርድ ቤቱም ጥያቄቸውን ተቀብሎ 1ኛ ተከሳሽ ለክሱ ኃላፊ የሚደረጉ ከሆነ 2ኛ ተከሳሽ ተጠያቂ ላደረጉ የሚችሉበት ሁኔታ መኖር አለመኖሩ በአፈጻጸም ጊዜ ከሚታይ በስተቀር 2ኛ ተከሳሽ በስረ ነገሩ ላከሰሱ የሚችሉበት አግባብ የለም ሲል 2ኛ ተከሳሽን አሰናብቶ 1ኛ ተከሳሽን ለክሱ ኃላፊ በማድረግ ብር 198,371.40 ለከሳሽ እንዲከፍሉ በመዝገብ በ30/04/2002 ዓ.ም. ውሳኔ መስጠቱን፣ከሳሽ በ1ኛ ተከሳሽ ላይ የተሰጠላቸውን ፍርድ ለማስፈጸም በዚያው የስረ ነገሩ መዝገብ የአፈጻጸም ማመልከቻ ባቀረቡበት ጊዜ ከስረ ነገሩ ክስ የተሰናበቱትን አመልካች በ2ኛ የፍ/ባለዕዳነት አካተው ማቅረባቸውን፣አመልካቿ በስረ ነገሩ ኃላፊ ተደርጌ የተሰጠብኝ ፍርድ ሳይኖር የፍ/ባለመብቱ በፍ/ባለዕዳነት ሰይሞ ያቀረበኝ አላግባብ በመሆኑ ከአፈጻጸሙ ልሰናበት ይገባል የሚል ክርክር በማቅረባቸው ፍ/ቤቱ ይህንኑ ተቀብሎ አመልካች ከአፈጻጸም ክስ ነፃ ናቸው በማለት በ05/05/2003 ዓ.ም. በተሰጠ ትዕዛዝ ያሰናበታቸው መሆኑን፣ከዚህ በኃላ የፍ/ባለመብቱ ለአፈጻጸሙ ይውል ዘንድ በባህር ዳር ከተማ በቀበል 16 የሚገኝ የፍ/ባለዕዳውን ቤት መምራታቸውን፣ቤቱ ተከብሮ እንዲቆይ ፍርድ ቤቱ ለሰጠው ትዕዛዝም የክፍሉ ቀበል ቤቱ የሚታወቀው በፍርድ ባለዕዳው በአቶ ሰመረ ኃይሉ ስም ቢሆንም የተገነባው በጊዜያዊ ይዞታ ላይ በመሆኑ እና ካርታ እና ፕላን የልለው በመሆኑ ምክንያት ለማስከበር እንደሚቸገር በ20/11/2002 በተጻፈ ደብዳቤ መግለጹን፣የቤቱ ሁኔታ ተጣርቶ እንዲቀርብለት እና ተከብሮ እንዲቆይ ፍርድ ቤቱ በድጋሚ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረትም የፍርድ ባለዕዳው እና ባለቤታቸው ፍቺ በፈጸሙበት ጊዜ ቤቱ ለልጆቻቸው እንዲሆን ለፍርድ ቤት አቅርበው ማስወሰናቸውን በመግለጽ የክፍሉ ቀበል በ15/06/2003 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ ምላሽ መስጠቱን፣ፍርድ ቤቱም ከቀበልው የተገለጹለትን ሁለት ምክንያቶች መሰረት በማድረግ የፍርድ ባለመብቱ ልላ ንብረት አፈላልገው ማቅረብ የሚችሉ ከመሆኑ ውጪ አፈጻጸሙ በቤቱ ላይ ላቀጥል የሚችልበት ሁኔታ አለመኖሩን ገልጾ በ21/06/2003 ዓ.ም.የአፈጻጸም መዝገቡን በብይን መዝጋቱን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።
በብይኑ ቅር በመሰኘት የአሁኑ ተጠሪ ባቀረቡት ይግባኝ ሳቢያ የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የወረዳውን ፍርድ ቤት ብይን ያጸናው ሲሆን ጉዳዩን በመጨረሻ የተመለከተው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በበኩሉ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ቤቱ የሚታወቀው በፍርድ ባለዕዳው ስም መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ ካርታ እና ፕላን የልለው መሆኑ ለፍርድ አፈጻጸም እንዳይውል ከማድረግ የማይከለክል መሆኑን እና የቀድሞ ተጋቢዎች ቤቱን ለልጆቻቸው ሰጥተዋል መባሉን በተመለከተም ስጦታው ሕጉ እንደሚያዘው በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2443 በተመለከተው ስርዓት መሰረት የተከናወነ መሆኑ እስካልተረጋገጠ ድረስ ተጋቢዎቹ በፍቺ ውሳኔ መዝገቡ ላይ ቤቱ ለልጆቻቸው እንዲሆን መስማማታቸው እና ስምምነታቸው የፍቺ እና የንብረት ውሳኔውን ባጸደቀው ፍርድ ቤት ተቀባይነት ማግኘቱ ቤቱ በሕጉ አግባብ በስጦታ ተላልፏል የሚያሰኝ አለመሆኑን እና ከፍቺ ጋር የተያያዘ ክርክር የቀረበለት ፍርድ ቤት ፍቺን እና የፍቺ ውጤቶችን ከመወሰን በቀር ስጦታን የማጽደቅ ስልጣን የልለው መሆኑን ገልጾ የሁለቱን የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በመሻር አፈጻጸሙ በቤቱ ላይ እንዲቀጥል ውሳኔ ሰጥቷል።
No topics extracted.
አመልካች የሰበር አቤቱታቸውን ለዚህ ችሎት ያቀረቡትም ይዘቱ ከላይ የተመለከተው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ላታረም ይገባል በማለት ነው።አቤቱታው ተመርምሮ ለሰበር ክርክር እንዲቀርብ የተደረገው በግራ ቀኙ መካከል ክርክር ሲካሄድበት ከነበረው ከሆነው መዝገብ ጋር ተጣምሮ እንዲታይ ተብሎ ቢሆንም በሁለቱ መዝገቦች ተከራካሪ ወገኖቹ ተመሳሳይ ቢሆኑም ለክርክር የቀረቡት ጭብጦች ግን የተለያዩ መሆናቸው በመረጋገጡ በሆነው መዝገብ የቀረበው ክርክር ተነጥሎ ውሳኔ የተሰጠበት ሲሆን በዚህ መዝገብ የቀረበውን አቤቱታ በተመለከተ ግን ለአፈጻጸሙ የተያዘው ቤት የተገነባው በጊዜያዊ ይዞታ ላይ መሆኑ እና በተጨማሪም በአመልካች እና በአቶ ሰመረ ኃይሉ መካከል የነበረው ጋብቻ ፈርሷል መባሉን ተከትሎ ቤቱ ለቀድሞ ተጋቢዎች ልጆች የተሰጠ መሆኑ በተገለጸበት ሁኔታ ቤቱ ለአፈጻጸሙ ላውል ይገባል ተብሎ የመወሰኑን አግባብነት ተጠሪው ባሉበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዳዩ ለሰበር ክርክር እንዲቀርብ በመደረጉ ተጠሪ የአቤቱታውን ግልባጭ ከመዝገቡ ወስደው መልስ እንዲሰጡበት በቪዲዮ ኮንፈረንስ በችሎት ተነግሯቸው መልስ ሳይሰጡ በመቅረታቸው የመከራከር መብታቸው እንዲታለፍ ተደርጓል።የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር መርምረናል።
በዚህም መሰረት ለአፈጻጸሙ የተያዘው ቤት በጊዜያዊ ይዞታ ላይ የተገነባ እና ካርታ እና ፕላን የልለው ቢሆንም በልላ በኩል ግን ተመዝግቦ የሚታወቀው በአቶ ሰመረ ኃይሉ ስም መሆኑን ጉዳዩ የሚመለከተው የአስተዳደር አካል ለወረዳው ፍርድ ቤት በጽሁፍ አረጋግጧል። በልላ አነጋገር ቤቱ ከሚመለከተው የአስተዳደር አካል ዕውቅና ውጪ በሕገወጥ መንገድ የተገነባ ስለመሆኑ የተገለጸ ነገር የለም።ይልቁንም አመልካች እና በፍቺ ተለያይተዋል የተባሉት የቀድሞ ባለቤታቸው አደረጉት በተባለው እና በፍርድ ቤት በተመዘገበው የፍቺ ስምምነት ቤቱ ለልጆቻቸው እንዲተላለፍ መስማማታቸው እና ጉዳዩ የሚመለከተው የአስተዳደር አካልም ቤቱ በቀድሞ ተጋቢዎች ስምምነት ለልጆቻቸው የተሰጠ በመሆኑ የፍርድ ቤቱን የማስከበሪያ ትዕዛዝ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚቸገር ገልጾ አፈጻጸሙን ለያዘው ፍርድ ቤት ምላሽ መስጠቱ ካርታ እና ፕላን የልለው ከመሆኑ ውጪ የቤቱ ሕጋዊነት ጉዳይ በአስተዳደር አካሉ ዘንድ ጥያቄ ያላስነሳ መሆኑን መገንዘብ የሚያስችል ነው።
ቤቱ ለቀድሞ ተጋቢዎች ልጆች ተሰጥቷል በማለት የቀረበውን ክርክር በተመለከተም አመልካች እና ፍቺ ፈጽመዋል የተባሉት የቀድሞ ባለቤታቸው የፍቺ ክርክሩን በተመለከተው ፍርድ ቤት ቤቱን ለሕጻናት ልጆቻቸው መስጠታቸውን ገልጸው የፍቺ ስምምነት ከማስመዝገባቸው ውጪ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በውሳኔው ላይ እንደገለጸው ስጦታውበሕጉ በተደነገገው ስርዓት መሰረት የተደረገ ነው የሚባል ካለመሆኑም በላይ የፍቺ ስምምነቱ በፍርድ ቤት ተመዝግቧል የተባለውም ተጠሪው ክስ ከመመስረታቸው ከአምስት ቀናት በፊት መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ የሚያመለክት በመሆኑ በዚህ ረገድ የቀረበው ክርክርም ሕጋዊ ተቀባይነት ላሰጠው የሚገባ ሆኖ አልተገኘም።
ሲጠቃለል የሁለቱን የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በመሻር በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ ስላልተገኘ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
ው ሳ ኔ1. በባህር ዳር ወረዳ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ21/06/2003 ዓ.ም. ተሰጥቶ በምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ29/05/2004 ዓ.ም.
የጸናውን ብይን በመሻር የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በመዝገብ በ07/09/2005 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ፀን~ል።2. እንዲያውቁት የዚህ ውሳኔ ግልባጭለባህር ዳር ወረዳ ፍርድ ቤት፣ለምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ይላክ።3. የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ።4. ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።