No summary available.
ሐምል 26 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ ነጋ ዱፊሳ አዳነ ንጉሴ አመልካች፡- ወ/ሮ ኪሮስ ገ/ማሪያም - ጠበቃ ዮሴፍ አእምሮ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ገብረ ስላሴ ሃይል- ወኪል ወርቅነሽ መንግስቱ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ የባልነት ማስረጃን መሰረት ያደረገ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁኑ አመልካች ባቀረቡት የመቃወም አቤቱታ መነሻ ነው።አመልካች የመቃወም አቤቱታ ላያቀርቡ የቻሉት የአሁኑ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት የሟች ወ/ሮ ኪሮስ ውቤ ባል ነኝ በማለት በሐሰት የወሰዱት ማስረጃ ያላግባብ ነው በማለት የተወሰደው ማስረጃ እንዲሰረዝላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል። የስር ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙን ከአከራከረና የምስክሮች ቃል ከሰማ በኋላ በተጠሪና በሟች ወ/ሮ ኪሮስ ውቤ መካከል ጋብቻ ስለመፈፀሙ በትዳር ሁኔታ ተረጋግጧል በሚል ምክንያት የአመልካችን አቤቱታ ባለመቀበል ቀድሞ ተጠሪ የሟች ወ/ሮ ኪሮስ ውቤ ናቸው በማለት የሰጠውን ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 360(2) መሰረት በማጽናት ወስኗል።ከዚህም በኋላ አመልካች የይግባኝ ቅሬታቸውን ለአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። ጉዳዩን ለከተማው ሰበር ሰሚ ችሎት አቅርበውም ተቀባይነት አላገኙም።የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።የአመልካች ሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም የባልነት ጉዳይ አከራካሪ በሆነበት ሁኔታ ጉዳዩ በበታች ፍርድ ቤቶች የታየው ያለስልጣናቸው መሆኑንና የተጠሪ የባልነት ማስረጃ ከመጀመሪያውም የተሰጠው ተገቢ ያልሆነ አቤቱታ ቀርቦና በሕግ አግባብ መቅረብ ያለበት ማስረጃ ሳይቀርብ ነው የሚል ሲሆን አቤቱታው ተመርምሮም ጉዳዩን የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ለማየት ስልጣን ያላቸው መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችሎቱ እንዲቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪም ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው በጉዳዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ ነው በማለት ተከራክረዋል።አመልካች በበኩላቸው የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።እንደመረመረውም የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ጉዳዩን የማየት የስረ ነገር ዳኝነት ሥልጣን አላቸው? ወይስ የላቸውም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላመረመር የሚገባው ሁኖ አግኝቶታል።
የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ሥረ ነገር ሥልጣን በአዋጅ ቁጥር 361/1995 እና 408/1996 ስር ተመልክቷል።በዚህም መሰረት በአዋጅ ቁጥር 361/1995 እና አዋጅ ቁጥር 408/1996 ከተሰጧቸው ስልጣኖች መካከል የወራሽነት ምስክር ወረቀት መስጠት፣የባልና ሚስትነት፣የሞግዚትነት ማስረጃ መስጠት ይገኙበታል።በዚህ ረገድ የተሻሻለውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ (ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር 408/1996 አንቀጽ 2 በአዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 41(1)(ሸ) ስር የተመለከተው ድንጋጌ ሰርዞ የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች የወራሽነት፣የባልና ሚስትነት እና የሞግዚትነት የምስክር ወረቀት ለማግኘት የሚቀርብ አቤቱታ ላይ የዳኝነት ሥልጣን ያላቸው መሆኑ ተደንግጓል።የድንጋጌው የእንግላዝኛው ቅጂም "application for certification of succession,marriage and guardianship."በሚል የተቀመጠ ነው።ከእነዚህ የድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ የሚቻለው የአዲስ አበባ ፍርድ ቤቶች ስለጋብቻ በሚሰጡት ማስረጃ ላይ በሚቀርብ ክርክር የሚኖራቸው የዳኝነት ሥልጣን አድማሱ እስከምን ድረስ መሄድ አለበት? የሚለው ጥያቄ የሚነሳ መሆኑን ነው።በልላ አገላለጽ የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ሥልጣን የባልና ሚስትነት ማስረጃ ለመስጠት ነው ተብሎ የተቀመጠው የሕጉ አገላለፅ ፍርድ ቤቶቹ የባልነት ወይም የሚስትነት ማስረጃ ከሰጡ በኃላ በማስረጃው ተቃውሞ ቢቀርብ እና የተቃውሞው መሰረት የሚሆኑት ምክንያቶች የባልነት ወይም የሚስትነት ማስረጃው የተሰጠው በቤተሰብ ሕጉ ስለጋብቻ መኖር ያለመኖር ላቀርቡ የሚገባቸው የማስረጃ አይነቶች ሳይቀርቡ ነው፣ጋብቻ ሳይኖር ነው፣የቀረበው አቤቱታ ከሕጉ ስርዓት ውጪ ነው፤ሕጉን በሚጻረር መልኩ ነው የሚል ከሆነ ማስረጃዎች በማስረጃነቱ ከመስጠት ባለፈ በተጠቀሱት ነጥቦች ክርክር እንዲካሄድ በማድረግ ዳኝነት ላሰጡ ይችላሉ? ወይስ አይችሉም?
የሚል ነው።ይህንኑ ጥያቄ ለመመለስ የባልነት ወይም የሚስትነት ማስረጃ ምንነት፣ማስረጃው የሚሰጥበትን ሁኔታ፣የማስረጃውን ይዘት፣አቤቱታው የሚስተናገድበትን ሥርዓት መመልከት አስፈላጊ ነው።
የጋብቻ ምስክር ወረቀት ስለሚሰጥበት ሁኔታና ስለይዘቱ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግአዋጅ ቁጥር 213/1992 ይደነግጋል። ይሄው ህግ ለጋብቻ መኖር መቅረብ ያለባቸውን የማስረጃ አይነቶች ቅደም ተከተል እንዲሁም በማስረጃው ላረጋገጡ ስለሚገባቸውሁኔታዎች አስፍሮ እናገኛለን።ከእነዚህ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ መገንዘብ የሚቻለው ፍርድ ቤቱ በሕጉ በተመለከተው አግባብ መረጋገጡን በቂ ነው ብሎ የገመተውን ያህል ማስረጃ ተቀብሎና መዝኖ ጋብቻ መኖር ያለመኖሩን የሚያረጋገጥ መሆኑን፣ጋብቻው አለ ወይም የለም ተብሎ ላሰጥ የሚችለውም በሕግ የተቀመጠውን መመዘኛ በማሟላታቸው በመለየት ስለሆነ ይህንኑ የሚገልፅ ወይም የሚያሳይ ምክንያት በመስጠት ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑን ነው።በአንፃሩ የባልነት ወይም የሚስትነት ማስረጃ መስጠት ግን ከላይ የተመለከቱት ሕጋዊ ክርክሮች በልሉበት ሁኔታ የሚሰጥ ማስረጃ እንጂ ጋብቻ ስለመኖሩ ያለመኖሩ ክርክር ተደርጎ የግራ ቀኙ ተከራካሪ ወገኖች ማስረጃ በሕጉ አይን ተመዝኖ የሚሰጥ አይደለም።ፍርድ ቤቱ ጥያቄው ሲቀርብ የሚሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ ስለውሳኔ የተቀመጠውን ትርጉም የሚያሟላ ነው ላባል የሚችል ሳይሆን የባልነት ወይም የሚስትነት የምስክር ወረቀቱን ስለሕጋዊ ማስረጃነቱ የሚያረጋገጥበት ነው።
ይህን አይነት ውሳኔ ለመስጠት ፍርድ ቤቱ ላከተለው የሚገባው ስነ ሥርዓት ሲታይም ተከራካሪ ወገን የልለበት፣አቤቱታ አቅራቢው ብቻ በማስረጃ በተደገፈ አቤቱታ መሰረት ይገባኛል የሚለውን መብት ወይም ጥቅም ትክክለኛነቱን፣ሕጋዊነቱን እንዲረጋገጥለት የሚያቀርብ በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 305 መሰረት የተፋጠነ ሥርዓት ነው ላባል የሚገባው ነው። ስለሆነም የባልነት ወይም የሚስትነት ማስረጃ ይሰጠኝ አቤቱታ ይዘቱና ፍርድ ቤቱ ላከተለው የሚገባው ስነ ሥርዓት ሲታይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች የማስረጃ ይሰጠኝ ጥያቄውን ተገቢነቱን፣ ትክክለኛቱንና ሕጋዊነቱን ከማረጋገጥ ባለፈ ጋብቻ አለ ወይስ የለም? የሚለውን ጭብጥ ይዘው በጉዳዩ ላይ የቀረቡትን ማስረጃዎችን በመስማት፣ጉዳዩን በማጣራት እና ልሎች ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ክርክር ሲኖር አቤቱታውን ተቀብሎ ለማስተናገድ የዳኝነት ሥረ ነገር ሥልጣን የልላቸው መሆኑን ያስገነዝባል።በጉዳዩ ላይ ሚስትነት ወይም ባልነት የለም የሚልና ተቃውሞውን ለማቅረብ መብትና ጥቅም ያለው ወገን ጋብቻው ያለመኖሩንና እና ተያያዥነት ያላቸውን ልሎች ሕጋዊ ክርክሮችን መሰረት በማድረግ ተቃውሞ በማቅረብ ሕጋዊ መፍትሕ ላያገኝ የሚገባው ጥያቄውን ወይም አቤቱታውን ለፍድራል ፍርድ ቤቶች ለማቅረብ እንጂ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች በማቅረብ አይደለም።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች በባልነት ወይም የሚስትነት ማስረጃ ወረቀት ላይ ውሳኔ ሰጥተዋል በሚል ምክንያት ብቻ ተቃውሞ ያለው ወገን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358"ን" መሰረት በማድረግ የተቃውሞ አቤቱታ ሲያቀርብና ፍርድ ቤቶቹም አቤቱታውን ተቀብለው የባልነት ወይም የሚስትነት ማስረጃ ትክክለኛነቱንና ሕጋዊነቱን ከማረጋገጥ ባለፈ ተከራካሪ ወገኖችን በማከራከር ስለጋብቻ መኖር ያለመኖር ላይ ማስረጃ ሳይሆን በጋብቻ ውጤት ላይ የራሱ የሆነ ትርጉም ያለውንና ላፈፀም የሚችል ውሳኔ ሲሰጡ በተግባር ይስተዋላል።ይሁን እንጂ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 መሰረት የተቃውሞ አቤቱታ የሚቀርበው በፍትሐ ብሕር ሥነ ሥርዓት ሕጉ በተሰጠው የውሳኔ ትርጉም(አንቀፅ 3 ይመልክቷል) መሰረት ላፈፀም የሚችል ውሳኔ ከተሰጠ እና ውሳኔው የክርክሩ ተካፋይ ያልሆነ ወገን መብትና ጥቅም የሚነካ መሆኑ ሲረጋገጥና አቤቱታው ውሳኔው ከመፈፀሙ በፊት ከቀረበ ነው።የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 አይነተኛ አላማ ማስረጃው ትክክለኛነቱና ሕጋዊነቱ ተረጋግጦ በማስረጃነቱ (Declaratory Judgement) በሚሰጠው ውሳኔ ላይ ሳይሆን ከላይ እንደተገለፀው ላፈፀም በሚችል ውሳኔ የክርክሩ ተካፋይ ያልሆነ ወገን መብትና ጥቅምን ማስከበር ነው።በአጠቃላይ የባልነት ወይም የሚስትነት ማስረጃ አቤቱታ ስለሚሰጥበት ሁኔታና ስለይዘቱ እንዲሁም በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁጥር 358 መሰረት ተቃውሞ የሚቀርብበት ሥርዓት በአንድነት ሲታዩ የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች በዚህ ረገድ የማስረጃው ይሰጠኝ ጥያቄ /አቤቱታ/ ትክክለኛነቱንና ሕጋዊነቱን በማረጋገጥ ለማስረጃነት ውሳኔ ከመስጠት ባለፈ ማስረጃውን ትክክለኛነቱንና ሕጋዊነቱን የሚቃወም ወገን አቤቱታ ሲያቀርብ ለተቃውሞው መሰረት ላሆኑ በሚችሉት ጋብቻ የለም፣ተገቢው ማስረጃ አልቀረበም፣የቀረቡት ማስረጃዎችም ሐሰተኛ ናቸው በሚሉት ነጥቦች ላይ ክርክር በመስማት ዳኝነት ለመስጠት በአዋጅ ቁጥር 361/1995"ም" ሆነ የዚሁ አዋጅ ማሻሻያ በሆነው አዋጅ ቁጥር 408/1996 መሰረት ሥልጣን ያልተሰጣቸው ሆኖ አግኝተናል።
ወደተያዘው ጉዳይ ስንመለስም ተጠሪ ለአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቤቱታ ሲያቀርቡ መሰረት ያደረጉት ከሟች ወ/ሮ ኪሮስ ጋር በጋብቻ ተሳስረው የነበሩ መሆኑን ጠቅሰው የባልነት ማስረጃ እንዲሰጣቸው ሲሆን ይህ ማስረጃ እንዲሰጣቸው ሲያመለክቱም አቤቱታቸውን በቃለ መሃላ ያስደገፉ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ለተጠሪ በተጠየቁት አግባብ ማስረጃ ከሰጠ በሁዋላ የአሁኗ አመልካች ተጠሪና ሟች ወ/ሮ ኪሮስ ውቤ ባልና ሚስት አይደሉም፣ጥያቄውና ማስረጃው የተሰጠበት አግባብ ሕጋዊ አይደለም የሚል ይዘት ያለው ተቃውሞ አቅርበዋል።ይህ በግልፅ የሚያሳየው የአመልካች የተቃውሞ አቤቱታ ተጠሪ ያገኙት የባልነት ማስረጃ ከማስረጃነቱ ባለፈ ልሎች የቤተሰብ ሕግ ክርክሮችን የሚያስነሳ መሆኑን ሲሆን ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የከተማው ፍርድ ቤትም የተሻሻለውን የፍድራሉን የቤተሰብ ሕግ ሁሉ በመጥቀስ ውሳኔ መስጠቱን ከውሳኔው ተመልክተናል።የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች በአዋጅ ቁጥር 361/1995 እና 408/1996 መሰረት ካገኟቸው ሥልጣኖች መካከል ከመሰረታቸው የፍድራል ጉዳዮች የሆኑት የሚገኙት ሲሆን እነዚህ ጉዳዮች ለእነዚህ ፍርድ ቤቶች ከፍድራል ፍርድ ቤቶች ሥልጣን ተቆርሰው ሲሰጡ በሕግ አውጪው የታሰበው በባሕርያቸው ውስብስብ ያልሆኑ ናቸው በሚል ነው።የጋብቻ መኖር ያለመኖር ውስብስብ ያልሆነ ክርክር የማይቀርብበት ሳይሆን ክርክር ተደርጎበት ውስብስብ የሕግ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥበት ነው።በመሆኑም የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች የጋብቻ መኖር ያለመኖርን ለመወሰን ሥረ ነገር ስልጣን ያልተሰጣቸው በመሆኑ ጉዳዩ በአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች መስተናገዱ ያላግባብ ነው።ተጠሪ ያገኙትን ማስረጃ አመልካች ላቃወሙት የሚገባቸው ስልጣን ባለው የፍድራል ፍርድ ቤት ነው።ስለሆነም የአዲስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአመልካች የቀረቡት ምክንያቶችን በመመልከት ጉዳዩን ለማስተናገድ ስልጣን የልለው መሆኑን ገልፆ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 9 እና 231(1(ለ)) መሰረት መዝገቡን መዝጋት ሲገባው ጉዳዩን ማስተናገዱም ሆነ የበላይ ፍርድ ቤቶች ይህንኑ ሳያረጋግጡ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በትእዛዝ ማፅናታቸው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ሁኖ አግኝተናል።በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 961/02 ጥቅምት 16 ቀን 2004 ዓ/ም ተሰጥቶ በከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በመ/ ሕዳር 25 ቀን 2004 ዓ/ም፣በከተማው ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ታህሳስ 13 ቀን 2004 ዓ/ም የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት በአብላጫ ድምፅ ተሽሯል።
የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች የባልነት ወይም የሚስትነት ማስረጃ በተመለከተ የቀረበው ጥያቄ ትክክለኛነቱንና ሕጋዊነቱን በማረጋገጥ በማስረጃነቱ ውሳኔ (Declaratory Judgement) ከመስጠት ውጪ ማስረጃው የተሰጠበትን ውሳኔ መሰረት በማድረግ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 መሰረት የተቃውሞ አቤቱታ መቀበልና ጋብቻ መኖር ያለመኖርን ልሎች ተያያዥነት ያላቸውን ክርክሮችን ለማስተናገድ የሥረ ነገር ሥልጣን የላቸውም ብለናል።
ተጠሪ አለኝ የሚሉትን ማስረጃ አመልካች በተጠሪና በሟች ወ/ሮ ኪሮስ ውቤ ጋር ጋብቻ የላቸውም የሚሉበትን ምክንያት መሰረት አድርገው ላቃወሙ የሚችሉት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 መሰረት ሳይሆን በልላ ክስ ሁኖ ስልጣን ባለው በፍድራሉ ፍርድ ቤት ነው ብለናል።
በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።
No topics extracted.