አንድ ኢንሹራንስ ኩባንያ በውል የመነጨውን ግድታውን በወቅቱባለመወጣቱ ለተከሰተው ተጨማሪ ወጪ ተጠያቂ ላሆን የሚችል ስለመሆኑ የን/ሕ/ቁ 665
No summary available.
መስከረም 27 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወል ሱልጣን አባተማም መኰንን ገ/ህይወት ሙስጠፋ አህመድ ተኸላት ይመስል አመልካች፡- ወ/ሮ እመቤት መኰንን - ቀረቡ።
ተጠሪ፡-
ይህ ጉዳይ የተጀመረው በኦሮሚያ ክልል የአዳማ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች ተከሳሽ ሲሆኑ የአሁኑ 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ 2ኛ ተጠሪ ጣልቃ ገብ ነበሩ። ከሳሽ በቀረቡት ክስ ባለቤቴ ሟች ወንደሰን ከፍያለው በተከሳሽ መኪና የታርጋ በሆነው ላይ በአሽከርካሪነት ተቀጥሮ በወር 1000 እየተከፈለው ሲሰራ በደረሰው የመኪና አደጋ ህይወቱ አልፏል በአዋጅ 377/96 አንቀጽ 110/1/ ለከሳሽ እና የሟች ልጅ ለሆነው (ዳግም ወንድወሰን) ጭምር በድርጅታችን 60,000 (ስልሣ ሺ) ይከፈለኝ በተጨማሪም የጠበቃ አበል 10% እና ውጪ ኪሣራ ይከፈለኝ በማለት ጠይቀዋል። አመልካችም በሰጡት መልስ ተጠቃሹ መኪና የኢንሹራንስ ሽፋን ያለው መሆኑን በመግለፅ ግሎባል ኢንሹራንስ ጣልቃ ገብቶ እንዲከራከር በጠየቁት መሰረት ይኸው አካል ወደ ክርክሩ በመግባት እስከ 60,000 ብር ድረስ ሽፋን መስጠቱን በመጥቀስ ከውላቸው ውጭ የመክፈል ኃላፊነት የልለበት መሆኑን ገልፆ ተከራክሯል።
ጉዳዩን ያየው የወረዳው ፍ/ቤት ግሎባል ኢንሹራንስ በሰጠው ሽፋን ልክ ይክፈል። በወቅቱ ባለመክፈሉ ምክንያት ለደረሰው ወጪና ኪሣራ እና የጠበቃ አበል ይክፈል በማለት ወሰነ።
የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤትም ለደረሰው ጉዳት ይከፈል የተባለውን 60,000 በማጽናት የጠበቃ አበል፣ የወጪና ክሣራ አስመልክቶ ላከፍል አይገባም በማለት አሻሽሎ አፀና በመጨረሻም 1ኛ ተጠሪ ለክልሉ ሰበር ሰሚ ቅሬታዋን በማቅረብ የሰበር ሰሚውም ሽፋን ከተሰጠው በላይ የአሁን 2ኛ ተጠሪ /ግሎባል/ ላከፍል አይገባም ከሽፋኑ በላይ የሆነውን የአሁን አመልካች ተተክተው ላከፍሉ ይገባል ሲል አሻሽሎ አፅንቷል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታም ይህንኑ የሰበር ውሣኔ ለማሳረም ነው።
አመልካች ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ 2ኛ ተጠሪ (ግሎባል ኢንሹራንስ) ለደረሰ ጉዳት ተተክቶ ላከፍልእና በውላችን መሰረት ግድታውን ለመወጣት ተስማምቷል (ውል ገብቷል) ይሁን እንጂ 2ኛ ተጠሪ በፍርድ ካልተገደድኩ በማለት በወቅቱ ግድታውን ባለመወጣቱ ለቀረበዉ ክስ ሽፋንከሰጠው በላይ ልገደድ አይገባውም ተብሎ አመልካች የወጪ ኪሣራና የጠበቃ አበል ትክፈል ተብሎ መወሰኑ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ ላታረም ይገባዋል በማለት ጠይቀዋል።
በመሆኑም የግራ ቀኙ ለአመልካች አቤቱታ መልስ በፅሑፍ በማቅረብ ክርክራቸውን አድርገዋል።
በዚሁ መሰረት 2ኛ ተጠሪ ለአመልካች ከሰጠው ሽፋን በላይ የወጪ ኪሣራ እና የጠበቃ አበል ላከፍል አይገባም ተብሎ አመልካች እንዲከፍሉ የመወሰኑን አግባብነት በጭብጥነት ተይዞ ቀርቧል።
ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካለው ህግ አኳያ መርምረናል።
የጉዳዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተጠቀሰውን ይመስላል። እንግዲህ ለጉዳዩ መነሻ የሆነው የሥር ከሳሽ የአሁን 1ኛ ተጠሪ የሆኑት በባለቤታቸው ላይ በደረሰው የሞት አደጋ ምክንያት የአዋጅ 377/96 አንቀጽ 110(2) ሀ,ለ መሰረት 60,000 ብር እንድከፍላቸው በአሁኑ አመልካች ላይ ክስ በማቅረባቸው ምክንያት የአሁን 2ኛ ተጠሪ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ. 43 መሰረት ወደ ክርክሩ እንድገባ ተደርጐ ለደንበኛው በሰጠው የኢንሹራንስ ሽፋን መሰረት 60,00ዐ ብር እና የጠበቃ አበል 10% እና የወጪ ኪሣራ 1000 ብር እንዲከፍል በመወሰኑና በየደረጃው ባሉት የክልሉ ፍ/ቤቶች እያዩት የክልሉ ሰበር ሰሚ ደረሶ ግሎባል ኢንሹራንስ ከሰጠው የኢንሹራንስ ሽፋን በላይ የጠበቃ እና የወጪ ኪሣራ ልከፍል አይገባም የአሁን አመልካች ኢንሹራንስ ከከፈለው በላይ ያለውን 8000 ብር ይክፈሉ በመባሉ ነው። በዚህ ጉዳይ የክልሉ ሰበር አመልካች ላከፍሉ ይገባል ሲል የሰጠው የአሁን 2ኛ ተጠሪ (ግሎባል ኢንሹራንስ የንግድ ህጉን አንቀጽ 665(2) መሰረት ግድታው ከውላችን ላይ ካለው የሽፋን መጠን ልበልጥ አይገባውም የሚለውን ክርክር በመቀበል መሆኑ ግልፅ ነው። እንግዲህ የግራ ቀኙ መብትና ግድታ የሚመነጨው በመሀከላቸው ከተቋቋመው ውል መሆኑ ይህ ችሎትም የሚቀበለው ጉዳይ ነው።
ይሁን እንጂ በተያዘው ጉዳይ የአመልካች ደንበኛ (ግሎባል ኢንሹራንስ) በአመልካች መኪና በደረሰው የሞት አደጋ በወቅቱ አግባብነት ያለውን ክፍያ ባለመፈፀሙ ምክንያት የአሁን 1ኛ ተጠሪ የመኪናውን ባለቤት የሆኑትን አመልካች ለመክሰስ ተገደዋል። ስለሆነም ለተለያዩ (ላልታሰበ) ወጪ መዳረጋቸው ያልተካደና የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነው። በመሆኑም ግሎባል ኢንሹራንስ ምንም እንኳ የሰጠው የኢንሹራንስ ሽፋን የተገለፀ ቢሆንም ከውል የመነጨውን ግድታውን በወቅቱ ባለመወጣቱ ለተከሰተው ተጨማሪ ወጪ የአሁን አመልካች የሚቀጡበት የህግ አግባብ አይኖርም። በዚህ ሁሉ ምከንያት የሞት ካሣውን የገንዘብ መጠን 60,000 ብር ላይ የጠበቃ እና የወጪ ኪሣራውን ግሎባል ኢንሹራንስ ላከፍል የሚገባው ሆኖ አግኝተነዋል።
ባጠቃላይ የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የሥር ውሳኔዎችን በማሻሻል ከ60,000 ብር በላይ የተጠየቀውን ተጨማሪ ወጪ አመልካች ላከፍሉ ይገባል ማለቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት ተከታዩን ውሣኔ ሰጥተናል።
164154 በቀን 23/03/2006 የሰጡት ውሣኔዎች ተሻሽሎ ፀንቷል።
የሰበሩን ክርክር አስመልክቶ ግራ ቀኙ የወጪ ኪሣራ ይቻቻሉ። መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.