በወንጀል የተከሰሰ ሰው ጉዳዩን በልለበት ለማየት ፍ/ቤቱ በመጀመሪያ ለተከሣሹ ህጉ ያስቀመጠውን ጥብቅ መስፈርት በተከተለ መልኩ በአግባቡ ጥሪ ላያደርግለት የሚገባ ስለመሆኑ፣ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ቁጥር 161(1)(2) እና 162 93577 አቶ ዘውድ ተስፋዬ ስመኝ እና የትግራይ ክልል ፍትህ ቢሮ ዐ/ህግ ህዳር 22/2007 198 47. አንድ ተጠርጣሪ ወይም ተከሳሽ በምርመራ ሒደትም ሆነ ክሱን ለሚሰማው ፍ/ቤት የሚሰጠው የእምነት ቃል ውጤት በራሱ በቃል ሰጪው ላይ ተወስኖ የሚቀር ከመሆኑ ውጪ ወንጀሉን አልፈፀምኩም ብሎ በሚከራከር ልላ ተከሣሽ ላይ ህጋዊ ውጤት ላያስከትል የማይችል ሥለመሆኑ፣ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ሥነ-ሥርዓት ቁጥር 27፣35 እና 134 96310 አቶ ጉደና ለማ ገዛኸኝ እና የደቡብ ብ/ብ/ህ/ክልል መንግስት የስ/ፀረሙስና ኮሚሽን ህዳር 26/2007 203 48. ከስር ተከሳሾች መካከል ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ ለአንዱየሚጠቅም በሆነ ጊዜና ይግባኝ ባዩ ጋር ተከሰውጥፋተኛ ተብለው የተቀጡ ሰዎች ይግባኝ ቢያቀርቡ ኖሮ በይግባኝ ሰሚው ፍቤት ውሣኔ ላጠቅሙ ይችሉ የነበረ መሆኑ ከተረጋገጠ ይግባኝ ሰሚዉ ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ ይግባኝ ላላቀረቡት ተከሳሾች ጭምር ተፈፃሚነት ላኖረው የሚገባ ሥለመሆኑ፣ የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 196/1/ /ሀ/ /ለ/ ጉምሩክ/ታክስ/ 216
No summary available.
ህዳር 25 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽላት ይመሰል አመልካች፡- ሀቢብ ጀማል ተጠሪ፡- የደ/ብ/ብ/ሕ/ብ/ክ/መንግስት ዐ/ሕግ - አቤቱታ አቅራቢዎች፡- 1.ረዳት ሳጅን መሐመድ እንድሪስ ጉዳዩን ተከታታዮች ተስፋዬ 2. አብዱ ኡመር አለሙ እና ወሰላ ከድር 3. ደግፍ አለሙ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ የወንጀል ክርክርን የሚመለከት ሲሆን መዝገቡ የተከፈተው በሀቢብ ጀማል አመልካችነት ሁኖ ከተጠሪ ጋር ክርክሩ ተካሂዶ ይህ ችሎት ጥቅምት 28 ቀን 2007 ዓ/ም በዋለው ችሎት ውሳኔ ሰጥቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው ጥቅምት 28 ቀን 2007 ዓ/ም በዚህ ችሎት የተሰጠው ውሳኔ በስር ፍርድ ቤት ከሀቢብ ጀማል ጋር ተከሳሽ የነበሩትን የአሁኑ አቤቱታ አቅራቢዎችንም የሚጠቅም በመሆኑ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 196 ድንጋጌ መሰረት የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ተግባራዊ ላሆን ይገባል በማለት ህዳር 02 ቀን 2007 ዓ/ም ማመልከቻ ስለአቀረቡ ነው። ይህ ችሎትም ይህንኑ የአቤቱታ አቅራቢዎችን ጥያቄ ለማስተናገድ ይቻለው ዘንድ ተጠሪ አስተያየት እንዲሰጥበት ያደረገ ሲሆን ተጠሪ ህዳር 19 ቀን 2007 ዓ/ም ባቀረበው አስተያየት አቤቱታ አቅራቢዎቹ ጥቅምት 28 ቀን 2007 ዓ/ም በተሰጠው የጥፋተኝነት ውሳኔ ተጠቃሚ መሆን ያለባቸው መሆኑን የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 196 ከአስቀመጠው ድንጋጌ የሚገነዘበው መሆኑን ዘርዝሮ አቤቱታ አቅራቢዎች አቶ ሀቢብ ጀማል ጥፋተኛ በተባሉበት በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 422(1) ድንጋጌ ስር ጥፋተኛ ተብለው በስር ፍርድ ቤት የቀረቡባቸው የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች መሰረት ተደርገው ቅጣት ላወሰንባቸው እንደሚገባ ገልፆ አስተያየቱን ሰጥቷል።
እኛም ጉዳዩን ከሕጉ ጋር አገናዝበን ተመልክተናል።
የጉዳዩ መነሻ በደ/ብ/ብ/ሕ/ብ/ክልላዊ መንግስት የስልጤ ዞን ዐ/ሕግ ጥቅምት 28 ቀን 2007 ዓ/ም በዋለው ችሎት ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት የጥፋተኝነት እና ተገቢውን የቅጣት ውሳኔ በሰጣቸው አቶ ሃቢብ ጀማልና በአሁኑ አቤቱታ አቅራቢዎች ላይ አራቱም ተከሳሾች በወ/ህ/ቁ 32/1//ሀ/፣ 37፣ 27/1/ እና 671/1/ሀ/ ሥር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ የማይገባቸውን ብልፅግና ለማግኘትና ለልላውም ለማስገኘት በማሰብ በስልጤ ወረዳ ውስጥ አሻኖ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ከወራቤ ወደ ቡታጅራ በሚወስደው አስፋልት መንገድ ላይ ሚያዚያ 08 ቀን 2005 ዓ/ም ከምሽቱ 5፡00 ሰኣት እስከ 7፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ የውንብድና ወንጀል ተግባር ለመፈፀም አስቀድመው በማሰብ በቡድን /ህብረት/ ሁነውና ተደራጅተው የጦር መሳሪያና ለዚሁ ተግባር የሚያግዛቸውን ተሽከርካሪ ጭምር በማዘጋጀት በመንገዱ ላይ ከአዲስ አበባ ወደ ወራቤ ምርጥ ዘር እና ሰዎችን ጭኖ ይጓዝ የነበረውንና በአቶ አብዱረዛቅ ዑመር አማካኝነት የሚሽከረከረውን ኤፍ.ኤስ.አር መኪና በማስቆም ከባድ የሆነ የውንብድና ወንጀል ለመፈፀም ሞክረዋል የሚል ሁኖ እያንዳንዱ ግብረ አበር በወቅቱ ፈፀመ የተባለውን ድርጊትም ክሱ ይዘረዝራል።
የአሁን አቤቱታ አቅራቢዎች በተከሳሻነታቸው ቀርበው ድርጊቱን አልፈፀምነም፤ ጥፋተኛም አይደለንም በማለት ክደው ተከራክረዋል። በአቃቤ ሕግ በኩል በማስረጃነት የሰው ማስረጃና የሰነድ ማስረጃዎች ቀርበዋል። ከዚህም በኋላ ሁሉም ተከሳሾች እንዲከላከሉ ተደርጎ የመከላከያ ማስረጃዎቻቸውን አሰምተዋል። ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ ተካሳሾቹ የወንጀል ድርጊቱን ስለመፈጸማቸው በአቃቤ ሕግ ተነግሮባቸው በመከላከያ ማስረጃዎቻቸው አላስተባበሉም በሚል ምክንያት በአቃቤ ሕግ በተጠቀሰው ድንጋጌ ስር ጥፋተኛ አድርጎአል። ቅጣቱን በተመለከተም የግራ ቀኙን አስተያየት ተቀብሎ ከቅጣት አወሳሰን መመሪያ ጋር አገናዝቦ መመርመሩን በማጣቀስ አቶ ሀቢብ ጀማልንና የአሁኑ አቤቱታአቅራቢ ከሆኑት 1ኛውን (የሥር 1ኛ ተከሳሽ) እና 2ኛውን (የሥር 2ኛ ተከሳሽን) እያንዳንዳቸውን በሰባት ዓመት፣ የስር 3ኛ ተከሳሽን (የአሁኑን ሶስተኛ አቤቱታ አቅራቢን) ደግሞ በስድስት አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አቶ ሀቢብ ጀማል ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት፣ የሰበር አቤቱታቸውን ደግሞ ለክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኘም። የአሁኑ አቤቱታ አቅራቢዎች ግን በዚህ አግባብ የይግባኝና የሰበር አቤቱታቸውን ስለማቅረባቸው የክርክሩ ሂደት አያሳይም።
ሆኖም ከአቤቱታ አቅራቢዎች ጋር በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ4ኛ ተከሳሽነት ተሰይሞ የነበረውና በበታች ፍርድ ቤቶች የጥፋተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ የተሰጠበት አቶ ሃቢብ ጀማል በሕጉ አግባብ በተዘረጋው ስርዓት መሰረት ለዚህ ችሎት የሰበር አቤቱታ አቅርቦ ጉዳዩ ተጠሪ ባለበት ከተጣራ በኋላ ተጠሪ አድራጎቱ የሚሸፈንበትን የሕግ ድንጋጌ በመለየትና የበታች ፍርድ ቤቶች የጥፋተኝነት ውሳኔ የሰጡበት ድንጋጌ ለስር ተከሳሾች አድራጎት አግባብነት የልለው መሆኑን ዘርዝሮ በሰጠው መልስ መነሻ ይህ ችሎት ጥቅምት 28 ቀን 2007 ዓ.ም በዋለው ችሎት የስር ተከሳሾች አድራጎት የሚያቋቁመው በወ/መ/ሕግ አንቀጽ 32(1(ለ)፣ 33 እና 422(1) ድንጋጌ መሆኑን ገልፆ አቶ ሀቢብ ጀማልን በዚሁ ድንጋጌ ስር ጥፋተኛ አድርጎ የቅጣት ውሳኔውንም በዚሁ ድንጋጌ አግባብ ወስኗል። ይህ ውሳኔ በሕግ አተገባበርና አተረጓጎም ረገድ የበታች ፍርድ ቤቶች የፈጸሙበትን ስህተት ከማረሙም በላይ በውጤቱ ደግሞ አቶ ሀቢብ ጀማልን የጠቀመ መሆኑ ግልጽ ነው። ከስር ተከሳሾች መካከል አንዱ ይግባኝ ጠይቆ የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ለይግባኝ ባዩ የሚጠቅም በሆነ ጊዜና ከይግባኝ ባዩ ጋር ተከሰው ጥፋተኛ ተብለው የተቀጡ ሰዎች ይግባኝ ቢያቀርቡ ኑሮ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሳኔ ላጠቀሙ ይችሉ የነበረ መሆኑ ከተረጋገጠ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ይግባኝ ላላቀረቡት ተከሳሾች ጭምር ተፈፃሚነት ላኖረው እንደሚገባ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 196(1(ሀ) እና(ለ) ድንጋጌዎች ስር በግልፅ ተመልክቷል። ይህ ድንጋጌ ለዚህ ችሎት የዳኝነት አሰጣጥ ስርዓትም ተፈፃሚነት ያለው ነው። ምክንያቱም ችሎቱ የሚመራበት የተለየ የወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ የለምና። ከዚህ አንፃር ጉዳዩን ስንመለከተው የአሁኑ አቤቱታ አቅራቢዎች ከአቶ ሀቢብ ጀማል ጋር ለዚህ ችሎት አቤቱታ ቢያቀርቡ ኑሮ የፍርዱ ተጠቃሚ ላሆኑ ይችሉ የነበረ መሆኑን ተገንዝበናል። በመሆኑም አቶ ሀቢብ ጀማልን በተመለከተ ይህ ችሎት ጥቅምት 28 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠው የጥፋተኝነት ውሳኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 196(1))(ሀ) (ለ) መሰረት ለአሁኑ አቤቱታ አቅራቢዎች ላይም ተፈጻሚነት አለው ብለናል።
ቅጣቱን በተመለከተ ግን አቶ ሀቢብ ጀማል ላይ የተሰጠው እንዳለ ተግባራዊ ይሁን የሚል ግልፅ ድንጋጌ ከወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 196 ድንጋጌ ስር አለ ለማለት ስለማይቻልና በመርህ ደረጃም እያንዳንዱ አጥፊ ላቀጣ የሚገባው በተሳትፎውና ግላዊ ሁኔታዎችን መሰረት በማድረግ ስለመሆኑ ከወ/መ/ሕጉ አንቀጽ 40 ድንጋጌ እና ከወንጀል ቅጣት አወሳሰን መርሆዎች የምንገነዘበው በመሆኑ የአሁኑ አቤቱታ አቅራቢዎች ላይ የሚጣለው የቅጣት መጠንን መመልከቱ ተገቢ ሁኖ ተገኝቷል። ከዚህ አንፃር ጉዳዩን ስንመለከተው ከአሁኑ ጥያቄ አቅራቢዎች ውስጥ 1ኛው ረዳት ሳጅን መሀመድ እንድሪስ፣ እና 2ኛው አብዲ አሙር ከሀቢብ ጀማል ጋር በተመሳሳይ ሁኔታ የተቀጡ በመሆኑ በአቶ ሀቢብ ጀማል ላይ በዚህ ችሎት የተጣለው ቅጣት ሙሉ በሙሉ ተፈፃሚነት ያለው ሁኖ አግኝተናል። ዐቃቤ ሕግ በጥያቄ አቅራቢዎች ላይ በቅጣት ማክበጃነት በስር ፍርድ ቤት የተያዙት ምክንያቶች እንዲያዙ የጠየቀ ቢሆንም ይህ ችሎት በአቶ ሀቢብ ጀማል ላይ የቅጣት ውሳኔ ሲሰጥ በከፊል ውድቅ ያደረጋቸው በመሆኑ በአሁኑ ጥያቄ አቅራቢዎች ላይም ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የሚያገኙበትን ሕጋዊ ምክንያት አላገኘም።
3ኛውን ጥያቄ አቅራቢ አቶ ደግፍ አለሙን በተመለከተ በስር ፍርድ ቤት የተያዙለት የቅጣት ማቅላያ ምክንያቶች ሁለት ናቸው። ይሄውም ሪኮርድ የልለበት መሆኑና የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆኑ ናቸው። ይህንኑ ይዘን የቅጣት እርከኑን ስንመለከተው በአንድ የቅጣት ማክበጃ ምክንያት ከእርከን 11 ወደ እርከን 12 ከፍ የሚል ሲሆን ጥያቄ አቅራቢው አቶ ደግፍ አለሙ ሁለት የቅጣት ማቅላያ ምክንያት ስላላቸው በመመሪያው አንቀፅ 13(5) መሰረት በጥያቄ አቅራቢው ላይ ላጣል ይችል የነበረው ቅጣት በአራት እርከን እንዲወርድ የሚያደርግ ነው። በዚህ ስልት መሰረትም ከእርከን 12 ወደ እርከን 8 የሚወርድ ሁኖ በዚሁ መጨረሻ እርከን ስር የተመለከተው የቅጣት አይነትና የመጠን ሬንጅ ከአንድ አመት ከሁለት ወር እስከ አንድ አመት ከስድስት ወርበመሆኑ ለፍ/ቤቱ በተሰጠው ፍቅድ ስልጣን መሰረት አቶ ደግፍ አለሙ ለፈፀሙት ጥፋት ተመጣጣኝ፣ ለመሰል አጥፊዎችን ደግሞ አስተማሪ ነው ብለን ያገኘነው አንድ አመት ከሁለት ወር ፅኑ እስራት ነው። ሲጠቃለልም የበታች ፍርድ ቤቶች በጥያቄ ባሁኑ ጥያቄ አቅራቢዎች ላይ የሰጡት የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ከላይ በተመለከቱት ሕጋዊ ምክንያቶች መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
በስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሰኔ 28 ቀን 2005 ዓ/ም የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 196/1/ /ሀ/ እና /ለ/ መሰረት ተሻሽሎ ጥያቄ አቅራቢ በሆኑት፡ሀ/ ረዳት ሳጅን መሐመድ እንድሪስ ለ/ አብዱ ኡመር ሐ/ ደግፍ አለሙ ይህ ችሎት ጥቅምት 28 ቀን 2007 ዓ/ም በአቶ ሀቢብ ጀማል በሰጠው የጥፋተኝነት ውሳኔ ተፈፃሚነት አለው ብለናል። ስለሆነም ጥያቄ አቅራቢዎቹ ላጠየቁ የሚገባው በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 33፣ 32(1(ለ) እና 422(1) ድንጋጌ ስር ነው ብለናል።
ቅጣቱን በተመለከተም ረዳት ሳጅን መሐመድ እና እንድሪስ አብዱ ኡመር እያንዳንዳቸው በጉዳዩ የታሰሩት ማናቸውም ጊዜ የሚታሰብላቸው ሁኖ ላቀጡ የሚገባው በአንድ አመት ከስድስት ወር ጽኑ እስራት ነው በማለት ወስነናል። ደግፍ አለሙን በተመለከተ ደግሞ የታሰሩት የሚታሰብላቸው ሁኖ በአንድ አመት ከሁለት ወር ፅኑ እስራት ነው ብለናል።
በዚህ ችሎት ውሳኔ መሰረት ተከታትሎ እንዲያስፈፅም ለወራቤ ማረሚያ ተቋም ይገለጽለት ብለናል።
No topics extracted.