አንድ በወንጀል ተጠርጥሮ የተከሰሰ ሰው ቅጣት በሚያከብድ የህግ ድንጋጌ ስለተከሰስኩ ክሱ ይሻሻልልኝ በማለት ተቃውሞ ካቀረበ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ፍ/ቤቱ የሚወስነው እንጂ ከጅምሩ ማስረጃ ሳይሰማ አቋም የሚወሰድበት እና ክሱ ይሻሻል ተብሎ የሚታዘዝ አቶ ጥዑም ተኬ ገብራይ እና የፍድራል ሥነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ ጥር 19/2007 170 42. በወንጀል የቅጣት አወሳሰን ጊዜ የቅጣት መነሻ ለማግኘት ቀላል የእስራት ቅጣትን ወደ ፅኑ እስራት መለወጥ የሚያሥፈልገው ወንጀለኛው ጥፋተኛ የተባለው በሁለት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ ወንጀሎች ሲሆንና አንዱ ወንጀል በቀላል እስራት ልላው ደግሞ በፅኑ እስራት የሚያስቀጣ በሆነ ጊዜ ብቻ ስለመሆኑ፡የተሻሻለው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ.2/2006 የወ/ሕ/አንቀፅ 184(1(ለ))
No summary available.
የሰ/መ/ቁ/ 99883 ጥር 19 ቀን 2007 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽላት ይመሰል አመልካች፡- አቶገ/ሥላሴ ገብሩ - ጠበቃ ገ/እግዚአብሕር ተስፋዬ ቀረቡ፣ ጠበቃ ሐና ዲግራንዲ ከመቀል በV.C. ቀረቡ።
ተጠሪ፡- የትግራይ ብ/ክ/መንግስት ፍትሕ ቢሮ - ዐ/ሕግ ገ/እግዚአብሕር ተወልደብርሃን ከመቀለ በV.C. ቀረቡ።
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
በዚህ መዝገብ እና በሆኑት በዛሬው ዕለት በዚሁ ችሎት ውሳኔ በተሰጠባቸው ልሎች ሁለት መዝገቦች ለቀረበው የሰበር ክርክር ምክንያት የሆነው ጉዳይ የተጀመረው ተጠሪ በ19/08/2003 ዓ.ም በተጻፈ የክስ ማመልከቻ በትግራይ ክልል በመቀል ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ በነበሩት የአሁኑ አመልካች እና 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች በነበሩት ልሎች ሁለት ተከሳሾች ላይ ስድስት የወንጀል ክሶችን በማቅረቡ ሲሆን ይዘታቸውም በአጭሩ፡-
2ኛ ተከሳሽ ወ/ት ብርኽቲ ተስፋይ ከ1999 ዓ.ም. እስከ 2000 ዓ.ም. ድረስ መክፈል ይገባቸው የነበረውን ግብር ብር 1,209,320.17 ባለመክፈላቸው፤
3ኛ ተከሳሽ አቶ ፍጹም አብርሃ ከ2000 ዓ.ም እስከ 2002 ዓ.ም ድረስ መክፈል ይገባቸው የነበረውን ግብር ብር 25,102.93 ባለመክፈላቸው ሕግን በመጣስ ግብር ያለመክፈል ወንጀል አድርገዋል፤
2ኛ ተከሳሽ ከሐምል 1999 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 2002 ዓ.ም. ድረስ ለመንግስት ገቢ ማድረግ ይገባቸው የነበረውን ብር 3,094,268.85 የተጨማሪ እሴት ታክስ ገቢ ባለማድረጋቸው፤እንዲሁም ከሐምል 1999 ዓ.ም. ጀምሮ ለተጨማሪ እሴት ታክስ መመዝገብ ሲገባቸው ባለመመዝገባቸው፤
3ኛ ተከሳሽ ከሐምል 2001 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 2002 ዓ.ም. ድረስ ለመንግስት ገቢ ማድረግ ይገባቸው የነበረውን ብር 199,334.17 የተጨማሪ እሴት ታክስ ገቢ ባለማድረጋቸው፤እንዲሁም ከሐምል 2001 ዓ.ም. ጀምሮ ለተጨማሪ እሴት ታክስ መመዝገብ ሲገባቸው ባለመመዝገባቸው፤ሕግን በመጣስ ታክስ ያለመክፈል ወንጀል አድርገዋል።
3 በሶስተኛ ክስ 1ኛ ተከሳሽ በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 በአንቀጽ 98(1)(ሀ) ስር የተደነገገውን በመተላለፍ በመቀል ከተማ ለሚያሰሩት ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ከቀረጥ ነጻ ያስገቡት የተለያየ መጠን ያለው የቀረጥ መጠኑ ብር 8,741,024.44 የሆነ ቴንዲኖ በባለሙያዎች ተፈትሾ ባለመገኘቱ ከቀረጥ ነጻ ሆኖ ወይም በቅናሽ ቀረጥ የገባን ዕቃ ከቀረጥ ነጻ መብቱ ከተሰጠበት ዓላማ ውጪ ለልላ አገልግሎት የማዋል ወንጀል አድረገዋል፤
4 በአራተኛ ክስ 1ኛ ተከሳሽ በንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 686/2002 በአንቀጽ 60(1) ስር የተደነገገውን በመተላለፍ መጀመርያ በሕንጻ ማከራየት የንግድ ዘርፍ ፈቃድ አውጥተው ከ2001 እስከ 2003 ዓ.ም. ድረስ ባለመክፈል እና ባለማደሳቸው፤በከብት ማድለብ የንግድ ዘርፍ ፈቃድ አውጥተው ከ2001 እስከ 2003 ዓ.ም. ድረስ ባለመክፈል እና ባለማደሳቸው፤ እንዲሁም በምግብ ቤት የንግድ ዘርፍ ፈቃድ አውጥተው ከ2001 እስከ 2003 ዓ.ም. ድረስ ሳይከፍሉ እና የጸና/የታደሰ/ የንግድ ፈቃድ ሳይዙ በንግድ ስራ ላይ ተሰማርተው በመገኘታቸው የጸና የንግድ ፈቃድ ሳይዙ በንግድ ስራ ላይ የመሰማራት ወንጀል አድርገዋል፤
5 በአምስተኛ ክስ 1ኛ ተከሳሽ በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 በአንቀጽ 50(3)(ለ) ስር የተደነገገውን ተላልፈው በክሱ ዝርዝር የተመለከተውን የወንጀል ድርጊት በመፈጸማቸው የሐሰት ወይም አሳሳች መረጃ የማቅረብ ወንጀል አድርገዋል፤
6 በስድስተኛ ክስ1ኛ ተከሳሽ በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 በአንቀጽ 97(3)(ለ) የተደነገገውን ተላልፈው በክሱ ዝርዝር የተመለከተውን የወንጀል ድርጊት በመፈጸማቸው የሐሰት ወይም አሳሳች መረጃ የማቅረብ ወንጀል አድርገዋል፤የሚሉ ናቸው።
1ኛ ተከሳሽ ያቀረቧቸው የመቃወሚያ ነጥቦች ውድቅ ከተደረጉ በኃላ ተጠይቀው ሶስቱም ተከሳሾች ወንጀሎቹን አላደረግንም በማለታቸው ፍርድ ቤቱ በተጠሪ በኩል የቀረቡ በሁሉም ክሶች ኦዲተሮችን ጨምሮ በድምሩ የአስራ ሰባት ምስክሮችን ምስክርነት ከሰማ እና የኦዲት ሪፖርትን ጨምሮ የተጠሪን የሰነድ ማስረጃ ከመረመረ በኃላ ተጠሪ በክሶቹ መሰረት አላስረዳባቸውም በማለት 1ኛ ተከሳሽን ከአምስተኛ እና ከስድስተኛ ክሶች በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ቁጥር 141 መሰረት በማሰናበት እና ቀሪዎቹን ክሶች በተመለከተ ግን ዐቃቤ ሕግ በክሱ መሰረት ያስረዳባቸው መሆኑን ገልጾ ሶስቱም ተከሳሾች መከላከያቸውን ማሰማት እንዲጀምሩ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ቁጥር 142 መሰረት ትዕዛዝ በመስጠቱ ሶስቱም ተከሳሾች የተለያዩ የመከላከያ ጭብጦችን በማስያዝ በጋራ እና በተናጠል በመሆን በድምሩ አስራ አምስት የመከላከያ ምስክሮችን አቅርበው ያሰሙ ከመሆኑም በላይ የተለያዩ ሰነዶችንም በመከላከያነት አቅርበዋል።
ፍርድ ቤቱም በሁለቱ ወገኖች የቀረበውን አጠቃላይ ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኃላ 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች በአንደኛ ክስ በተጠሪ የቀረበባቸውን ክስ እና ማስረጃ በመከላከያቸው ያስተባበሉ መሆኑን ገልጾ በአንደኛ ክስ ከተመለከተው የወንጀል ክስ በነጻ ያሰናበታቸው ሲሆን ይከላከሉ በተባሉባቸው በቀሪዎቹ ክሶች ግን ሶስቱም ተከሳሾች ባሰሟቸው የመከላከያ ምስክሮች በዐቃቤ ሕግ ማስረጃ የተመሰከረባቸውን ፍሬ ነገር ለማስተባበለል አልቻሉም በማለት በየክሶቹ በተጠቀሱባቸው ድንጋጌዎች ስር የጥፋተኝነት ውሳኔ በማስተላለፍ ግራ ቀኙ የቅጣት አስተያየት እንዲያቀርቡ አድርጓል። በመቀጠልም የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ካመዛዘነ በኃላ፡- 1ኛ ተከሳሽ በአንደኛ ክስ ስር በሁለት ዓመት ከስድስት ወር ጽኑ እስራት፤በሁለተኛ ክስ ስር በሶስት ዓመት ጽኑ እስራት፤በሶስተኛ ክስ ስር በአንድ ዓመት ከስድስት ወር ጽኑ እስራት፤በአራተኛ ክስ ስር በአራት ዓመት ጽኑ እስራት በብር 200,000 መቀጮ በድምሩ በአስራ አንድ ዓመት ከስድስት ወር ጽኑ እስራት እና በብር 200,000 መቀጮ፤
2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በሶስት ዓመት ጽኑ እስራት(የቅጣት መጠኑን በተመለከተ ብቻ በአብላጫ ድምጽ)፤እንዲቀጡ ውሳኔ ሰጥቷል።
በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ሶስቱም ተከሳሾች በአንድነት ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን ተጠሪ በበኩሉ በ1ኛ ተከሳሽ ላይ ከተሰጠው ውሳኔ መካከል በከፊሉ ቅር በመሰኘት በመዝገብ ይግባኝ አቅርቦአል። ፍርድ ቤቱም በከፍተኛ ፍርድ ቤት በሁለተኛ ክስ በተሰጠባቸው የጥፋተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ ቅር በመሰኘት ሶስቱም ተከሳሾች ያቀረቡትን ይግባኝ በትዕዛዝ የዘጋ ሲሆን በ1ኛ ተከሳሽ እና በተጠሪ መካከል በሁለቱም መዝገቦች የቀረበለትን ክርክር በተመለከተ ግን ክርክሩን በአንድነት ከመረመረ በኃላ በዐቃቤ ሕግ በኩል የቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አድርጎ የ1ኛ ተከሳሽን የይግባኝ ክርክር በመቀበል በከፍተኛ ፍርድ ቤት በአንደኛ፣በሶስተኛ እና በአራተኛ የወንጀል ክሶች ተሰጥቶባቸው የነበረውን የጥፋተኛነት እና የቅጣት ውሳኔ ሽሮ በነጻ አሰናብቷቸዋል።
ይህ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው በማለት ተጠሪ ባቀረበው አቤቱታ ሳቢያ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 በአንቀጽ 98(1)(ሀ) ተጠቅሶበት የቀረበው ሶስተኛው ክስ ሁለተኛ ይግባኝ ያለው በመሆኑ ምክንያት በሰበር ላያየው እንደማይችል ገልጾ በማለፍ በአንደኛ እና በአራተኛ የወንጀል ክሶች በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ይግባኝ ሰሚ ችሎት የተሰጠውን ውሳኔ ሽሮ በከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠውን የጥፋተኝነት ውሳኔ በማጽናት እና በ4ኛ ክስ በ1ኛ ተከሳሽ ላይ የተሰጠው የቅጣት መጠን አንሷል በሚል የቀረበውን የዐቃቤ ሕግ አቤቱታ በመቀበል እና ለ4ኛ የወንጀል ክስ ቅጣቱን በቅጣት አወሳሰን መመሪያው መሰረት በማስላት የመቀጮ ውሳኔውን ሳይነካ 1ኛ ተከሳሽ በሁለተኛ ክስ የተሰጠባቸውን የሶስት ዓመት ጽኑ እስራት ጨምሮ በድምሩ በአስራ አራት ዓመት ከስድስት ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ የሰጠ ሲሆን 1ኛ ተከሳሽ በዚህ ችሎት በመዝገብ አቤቱታ ያቀረቡትም ይህ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሰበር ችሎት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ላታረም ይገባል በማለት ነው። የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ጉዳይ በስር የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጣምረው ከቀረቡት ክሶች መካከል አንዱ የተጨማሪ እሴት ታክስን የሚመለከት ከመሆኑ አንጻር ጉዳዩን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ጉዳዩን አይቶ የመወሰን ስልጣን ያለው መሆን አለመሆኑን ተጠሪው ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዳዩ ለሰበር ክርክር እንዲቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል። የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር መርምረናል።
በዚህም መሰረት በአመልካቹ ላይ ከቀረቡት ስድስት የወንጀል ክሶች መካከል ሶስቱ ማለትም የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 49 ተጠቅሶበት የቀረበው ሁለተኛ ክስ፣ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 98(1)(ሀ) ተጠቅሶበት የቀረበው ሶስተኛ ክስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 50(3)(ለ) ተጠቅሶበት የቀረበው አምስተኛ ክስ በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 4(4) እና 15(1) ድንጋጌዎች መሰረት የሚወድቁት በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የስረ ነገር ስልጣን ስር መሆኑ፣እነዚህ ክሶች ለመቀል ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ላቀርቡ የቻሉትም በሕገ መንግስቱ በተሰጠው የስልጣን ውክልና መሰረት መሆኑ፣ቀሪዎቹ ሶስት ክሶች በክልሉ የወረዳ ፍርድ የስረ ነገር ስልጣን ስር የሚወድቁ ሆነው ነገር ግን በስልጣን ውክልና መሰረት ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ከቀረቡት ክሶች ጋር ተጠቃለው ለከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ የተደረገው በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 109(3) ድንጋጌ መሰረት መሆኑ እና ይህም ተገቢነት ያለው የክስ አቀራረብ ስርዓት መሆኑ ያላከራከረ ጉዳይ ነው። ይልቁንም አከራካሪ ሆኖ የቀረበው በአንድ ተከሳሽ ላይ ከቀረቡት ከአንድ በላይ ከሆኑ ክሶች መካከል ከፊሎቹ የሚወድቁት በፍድራል ፍርድ ቤት የስረ ነገር ስልጣን ስር፣ከፊሎቹ ደግሞ በክልል ፍርድ ቤት የስረ ነገር ስልጣን ስር በሆነ ጊዜ እና ነገር ግን በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 109(3) ድንጋጌ ስር በተመለከተው የክስ አቀራረብ መርህ መሰረት ተጠቃለው በቀጥታም ሆነ በውክልና በፍድራል ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲታዩ ተደርገው ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ በተመለከተው ፍርድ ቤት በአንድ ወይም በልላ አግባብ ውሳኔ ከተሰጠባቸው በኃላ ወደ ይግባኝ እና ወደ ሰበር የክርክር ደረጃ ሲደርሱ በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ እንደተደረገው ሁሉ ተጠቃለው የፍድራል ፍርድ ቤቶችን የይግባኝ እና የሰበር ስርዓት ተከትለው መጠናቀቅ አለባቸው ወይስ እንደየሚወድቁበት የስረ ነገር ስልጣን ሁኔታ ተነጣጥለው ከፊሎቹ የክልል ፍርድ ቤቶችን፣ከፊሎቹ ደግሞ በፍድራል ፍርድ ቤቶችን የይግባኝ እና የሰበር ስርዓት ተከትለው መጠናቀቅ አለባቸው? የሚለው ዓቢይ ነጥብ ነው። እንደሚታወቀው በስራ ላይ ያለው የወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ የወጣው በሀገሪቱ ውስጥ የፍድራል የአስተዳደር ስርዓት እና ይህንኑ ተከትሎ አዲስ የፍርድ ቤቶች አወቃቀር ስርዓት ከመዘርጋቱ ከበርካታ ዓመታት በፊት በመሆኑ የስነ ስርዓት ሕጉ ድንጋጌዎች በዚህ መዝገብ አከራካሪ ሆኖ ለቀረበው ነጥብ ምላሽ ላሰጡ የሚችሉ አይደሉም።
በመሆኑም የሀገሪቱን አዳዲስ ሁኔታዎች ያገናዘበ የወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ተቀርጾ ተግባራዊ እስከሚደረግ ድረስ አከራካሪ ሆኖ ከቀረበው ነጥብ ጋር ግንኙነት ያላቸው አሁን በስራ ላይ ያለው የወንጀል የስነ ስርዓት ሕግ ድንጋጌዎች ከፍድራላዝም ስርዓት እና ይህንኑ ተከትሎ ከተዘረጋው የፍርድ ቤቶች አወቃቀር ጋር በተቻለ መጠን ሁሉ ላጣጣም በሚችል ሁኔታ እየተተረጎሙ ተግባራዊ እንዲሆኑ ከማድረግ ውጪ የተሻለ አማራጭ አይኖርም።
በመሰረቱ በአንድ ተከሳሽ ላይ ከአንድ በላይ የሆኑ የወንጀል ክሶች በቀረቡ ጊዜ ክሶቹ በመርህ ደረጃ በአንድነት መታየት የሚገባቸው ስለመሆኑ በስነ ስርዓት ህጉ በቁጥር 116(2) ስር የተቀመጠው ድንጋጌ ዓይነተኛ ዓላማ በአንድ በኩል በተለያዩ ፍርድ ቤቶች እና መዝገቦች በአንድ ተከሳሽ ላይ ለየብቻ የቀረቡትን ከአንድ በላይ የሆኑ ክሶች በማስተናገድ ላባክን ይችል የነበረውን ጊዜ እና ሀብት በማዳን ለተከራካሪ ወገኖችም ሆነ ለምስክሮች ምቹ በሆነ ሁኔታ የተቀላጠፈ ፍትሕ እንዲሰጥ ለማስቻል እና በልላ በኩል ደግሞ በክሶቹ ተነጣጥሎ መታየት ሳቢያ በክሱ ክትትል ረገድም ሆነ የጥፋተኝነት ውሳኔ የሚሰጥ ከሆነ በቅጣት አጣጣል ረገድ በተከሳሽ ወገን ላይ ላደርስ የሚችለውን አላስፈላጊ ጉዳት በተቻለ መጠን ለማስወገድ እንደሆነ ይታመናል።
በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 109(3) ድንጋጌ ስር ከተመለከተው የክስ አቀራረብ መርህ አንጸር ከላይ የተጠቀሰው የቁጥር 116(2) ድንጋጌ ዓላማ ላሳካ የሚችለው ደግሞ ተጠቃለው የታዩት ክሶች ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ በተመለከተው ፍርድ ቤት በአንድ ወይም በልላ አግባብ ውሳኔ ከተሰጠባቸው በኃላ ወደ ይግባኝ እና ወደ ሰበር የክርክር ደረጃ ሲደርሱ በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ እንደተደረገው ሁሉ ተጠቃለው የፍድራል ፍርድ ቤቶችን የይግባኝ እና የሰበር ስርዓት ተከትለው እልባት እንዲያገኙ ሲደረግ ነው።
በተያዘው ጉዳይ የመቀል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክሶቹን አጠቃሎ የተመለከተው በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስልጣኑ መሆኑን በመግለጽ የክልሉ ሰበር ችሎት በፍድራል ፍርድ ቤቶች ስልጣን ስር የሚወድቅ ጉዳዮችን የማየት ስልጣን የልለው ስለመሆኑ ከአመልካች የቀረበለትን መቃወሚያ ሰበር ችሎቱ ሳይቀበል የቀረው በፍድራል ፍርድ ቤቶች ስልጣን ስር የሚወድቁ ናቸው ከተባሉት መካከል 2ኛውን ክስ አስመልክቶ የቀረበለት አቤቱታ አለመኖሩን እና 3ኛው ክስ ደግሞ የይግባኝ ስርዓቱ ያልተጠናቀቀ በመሆኑ ምክንያት በሰበር ላታይ የማይችል መሆኑን በመግለጽ ነው። ይህ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት አቋም ደግሞ ቀደም ሲል እንደተገለጸው ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ በተመለከተው ፍርድ ቤት ተጠቃለው እንዲታዩ የተደረጉት የወንጀል ጉዳዮች በይግባኝ እና በሰበር የክርክር ደረጃ ሲደርሱ እንደየሚወድቁበት የስረ ነገር ስልጣን ሁኔታ ከፊሎቹ የክልል ፍርድ ቤቶችን፣ ከፊሎቹ ደግሞ በፍድራል ፍርድ ቤቶችን የይግባኝ እና የሰበር ስርዓት ተከትለው እና ተነጣጥለው የሚታዩበትን አሰራር የሚፈጥር በመሆኑ እና የስነ ስርዓት ሕጉን ቁጥር 109(3) እና 116(2) ድንጋጌዎች ዓላማ የሚያሳካ ባለመሆኑ የተሻለ የክርክር አመራር አማራጭ ነው ላባል የሚችል አይደለም።
ሲጠቃለል የመቀል ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስልጣኑ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 109(3) እና 116(2) ድንጋጌዎች መሰረት አጠቃሎ በማየት በአንድ ወይም በልላ አግባብ ውሳኔ የሰጠባቸው ከፊሎቹ በክልል፣ከፊሎቹ ደግሞ በፍድራል ፍርድ ቤቶች የስረ ነገር ስልጣን ስር የሚወድቁ የወንጀል ጉዳዮች የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስልጣኑ በይግባኝ አይቶ በአንድ ወይም በልላ አግባብ ውሳኔ ከሰጠባቸው በኃላ ቀጥሎ ባለው የክርክር ሂደት መታየት የሚገባቸው በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ እንደተደረገው ሁሉ ተጠቃለው የፍድራል ፍርድ ቤቶችን የይግባኝ እና የሰበር ስርዓት ተከትለው መሆን ሲገባው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት የቀረበለትን መቃወሚያ ባለመቀበል በክልሉ ፍርድ ቤቶች የስረ ነገር ስልጣን ስር የሚወድቁ ናቸው በማለት የቀረበለትን የሰበር አቤቱታ ተቀብሎ በከፊሎቹ የወንጀል ጉዳዮች ላይ ውሳኔ መስጠቱ በክርክር አመራር ረገድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
የትግራይ ብ/ክ/መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በመዝገብ በ12/07/2006 ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔ ከላይ በተጠቀሰው ስነ ስርዓታዊ ምክንያት በአብላጫ ድምጽ ተሽሯል።
የክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ስልጣኑ ከፍድራል ጉዳይ ጋር በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 109(3) ድንጋጌ መሰረት አጠቃሎ ያየውን የክልል ጉዳይ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰበር የማየት ስልጣን የለውም በማለት ወስነናል።
በአንድ ተከሳሽ ላይ ከቀረቡት ከአንድ በላይ ከሆኑ ክሶች መካከል ከፊሎቹ የሚወድቁት በፍድራል ፍርድ ቤት የስረ ነገር ስልጣን ስር፣ከፊሎቹ ደግሞ በክልል ፍርድ ቤት የስረ ነገር ስልጣን ስር በሆነ ጊዜ እና ነገር ግን በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 109(3) ድንጋጌ ስር በተመለከተው የክስ አቀራረብ መርህ መሰረት ተጠቃለው በቀጥታም ሆነ በውክልና በፍድራል ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲታዩ ተደርጎ ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ በተመለከተው ፍርድ ቤት በአንድ ወይም በልላ አግባብ ውሳኔ ከተሰጠባቸው በኃላ ወደ ይግባኝ እና ወደ ሰበር የክርክር ደረጃ ሲደርሱ በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ እንደተደረገው ሁሉ የፍድራል ፍርድ ቤቶችን የይግባኝ እና የሰበር ስርዓት ተከትለው እና ተጠቃለው መታየት አለባቸው በማለት ወስነናል።
እንዲያውቀው የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ለትግራይ ብ/ክ/መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ይላክ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቶአል።
No topics extracted.