No summary available.
የሰ/መ/ቁ/89676 ጥር 4 ቀን 2007 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽላት ይመሰል አመልካች፡- የፍድራል ዐቃቤ ሕግ - ዐቃቤ ሕግ ምርምር ጥጋቡ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ሣሙኤል ፈቃዱ ኃይል-ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
በዚህ መዝገብ አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረበው ተጠሪው በተከሰሰበት በሕጻናት ልጆች ላይ የሚፈጸም የግብረ ስጋ ድፍረት በደል ወንጀል ክስ ባሰማው የመከላከያ ማስረጃ የዐቃቤ ሕግን ክስ እና ማስረጃ ከጥርጣሬ ላይ የጣለ በመሆኑ በወንጀሉ ጥፋተኛ አይደለም በማለት የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው እና በፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተቀባይነት ያገኘው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ላታረም ይገባል በማለት ነው።
አመልካች በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጠሪው ላይ በ04/07/2004 ዓ.ም.አዘጋጅቶ ያቀረበው ክስ ይዘት ባጭሩ፡-ተከሳሹ በኢ.ፍ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 627(1) ስር የተደነገገውን በመተላለፍ በ08/06/2004 ዓ.ም. ከቀኑ በግምት ከ10፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ በአራዳ ክፍለ ከተማ በቀበል 03/09 ክልል ልዩ ቦታው ደጃች ውቤ ሰፈር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ውስጥ ሣህላት ብርሃን የተባለችውንየሁለት ዓመት ከስምንት ወር ዕድሜ ያላትን የግል ተበዳይ ሕጻን የለበሰችውን ልብስ ዝቅ በማድረግ እግሩ ላይ አስቀምጦ የግብረ ስጋ ግንኙነት በመፈጸም የክብረ ንጽህናዋ የታችኛው የቀኝ ክፍል እንዲቀደድ ያደረገ በመሆኑ በሕጻናት ልጆች ላይ የሚፈጸም የግብረ ስጋ ድፍረት በደል ወንጀል አድርጓል የሚል ሲሆን አመልካች ተጠይቆ መቃወሚያ እንደልለው ገልጾ ወንጀሉን አላደረግሁም በማለቱ ፍርድ ቤቱ በተጠሪ በኩል የቀረቡ የግል ተበዳይ ሕጻንን ጨምሮ የአራት ምስክሮችን ምስክርነት ከሰማ እና በ09/06/2004 ዓ.ም. ከየካቲት 12 ሆስፒታል የተሰጠ የሕክምና ማስረጃ ከመረመረ በኃላ ዐቃቤ ሕግ በክሱ መሰረት ያስረዳበት መሆኑን ገልጾ አመልካች መከላከያውን ማሰማት እንዲጀምር በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ቁጥር 142 መሰረት ትዕዛዝ ሰጥቷል።
በዚሁ መሰረት አመልካች በ08/06/2004 ዓ.ም. ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ላይ ከእናቱ፣ከሕጻን ልጁ እና ከሰራተኞቹ ጋር ከእህቱ ቤት መጥተው ምሳ ከበሉ በኃላ ሰራተኛዋ ቡና አፍልታ እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ መቆየታቸውን፣ተከሳሽ በ11፡00 ሰዓት ወጥቶ ወደ ቤተክርስቲያን የሄደ መሆኑን፣በዚህ መሀል የግል ተበዳይ ሕጻን ወደ ቤቱ አለመምጣቷን፣በአካባቢው ሣሙኤል በሚባል ስም የሚጠራ ልላ ሰው መኖሩን ያስረዱልኛል በማለት ሶስት የመከላከያ ምስክሮችን አቅርቦ ያሰማ ሲሆን የመከላከያ ምስክሮቹም እናውቃለን ስላሐቸው ፍሬ ነገሮች በጭብጡ ከተገለጸው በተጨማሪ በተከሳሽ እና በግል ተበዳይ ቤተሰቦች መካከል የቆየ ቂም በቀል መኖሩን እና የግል ተበዳይ ሰራተኛ አባት የግል ተበዳይ ቤተሰቦችን ልጄን በሀሰት አስመስክራችኃል በማለት ተከሳሽ ከተያዙ በኃላ መጥተው ልጃቸውን የወሰዱ መሆኑን ጭምር እና እነዚህኑ ፍሬ ነገሮች ላያውቁ ስለቻሉበት ሁኔታ በዝርዝር በመግለጽ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።የግል ተበዳይ በጋንዲ ሆስፒታል በድጋሚ እንድትመረመር ተጠሪው በጠየቀው እና ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረትም ምርመራው ተከናውኖ የሕጻኗ የድንግልና አካል የሆነው ክፍል የተጎዳ እና ጉዳቱም የቆየ መሆኑን የሚገልጽ ከሆስፒታሉ በ11/10/2004 ዓ.ም. የተጻፈ ማስረጃ ቀርቦ ተያይዟል።
ፍርድ ቤቱም በሁለቱ ወገኖች የቀረበውን አጠቃላይ ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኃላ ተጠሪው ባሰማቸው የመከላከያ ምስክሮች በዐቃቤ ሕግ ማስረጃ የተመሰረበትን ፍሬ ነገር ከጥርጣሬ ላይ በሚጥል ሁኔታ አስተባብሐል በማለት በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ቁጥር 149(2) ድንጋጌ መሰረት በነፃ እንዲሰናበት ውሳኔ ሰጥቷል።አመልካች አቤቱታውን ለዚህ ችሎት ያቀረበው ይግባኙን የተመለከተው የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኙን በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 195(1) ድንጋጌ መሰረት ዘግቶ በማሰናበቱ ሲሆን የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ጉዳይ ተጠሪው የመድፈር ወንጀል አልፈጸመም ተብሎ በነጻ የመለቀቁን አግባብነት ከወንጀል ሕግ አንቀጽ 23 አንጸር ተጠሪው ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዳዩ ለሰበር ክርክር እንዲቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር መርምረናል።
በዚህም መሰረት አመልካች በክሱ መሰረት ያስረዱልኛል በማለት ያሰማቸው አራት ምስክሮች በተሰሙበት በቅደም ተከተል መሰረት የግል ተበዳይዋ ሕጻን፣የሕጻኗ እናት፣የሕጻኗ የእናት ወገን አክስት እና የሕጻኗ ሞግዚት ሲሆኑ የምስክርነታቸው ይዘት ጠቅለል ተደርጎ ሲታይም የሕጻኗ ቤተሰቦች እና ተከሳሹ ጎረቤታሞች መሆናቸውን፣ሕጻኗ በ08/06/2004 ዓ.ም. ከቀኑ በግምት ከ10፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ከተከሳሹ መኖሪያ ቤት ቆይታ ወደ ቤቷ የተመለሰች መሆኑን፣የተመለሰችውም እያለቀሰች መሆኑን፣ምን ሆና እንዳለቀሰች ሞግዚቷ የጠየቀቻት ቢሆንም ሕጻኗ አልናገርም ያለቻት መሆኑን፣በወቅቱ እናቷ ከቤት ያልነበረች መሆኑን፣ማታ ላይ አሞኛል በማለት ወደ ሀኪም ቤት እንድትወስዳት እናቷን የጠየቀቻት መሆኑን፣እናቷም ሕጻኗ እንደዚህ ያለቻት ቀደም ሲል ሀኪም ቤት ትወስዳት ስለነበረ እንደሆነ በመገመት ደህና ነሽ አላመመሽም ተኚ ያለቻት መሆኑን ሰውነቷን እንድትጠርግላት እና ተከሳሹ በጣቱ ወይም በሽንት መሽኛው ከሽንት መሽኛዋ ላይ የወጋት መሆኑን ሕጻኗ በነጋታው የጠየቀቻት እና የነገረቻት መሆኑን፣እናቷ ገልጣ ስትመለከት በሕጻኗ ብልት አካባቢ ቁስል እና የደረቀ የወንድ የዘር ፍሬ ያየችመሆኑን፣ወዲያውኑ ይዛት እህቷ ወደ ሆነችው 3ኛ ምስክር ወስዳ ያሳየቻት እና በመቀጠልም ወደ ሆስፒታል ወስደው ያስመረመሯት እና ውጤቱም መደፈሯን ያረጋገጠ መሆኑን፣ተከሳሹ የስድስት ወር ሕጻን ልጅ ያለው መሆኑን፣የግል ተበዳይ ሕጻን የተከሳሹን ልጅ ለማጫወት ሁልም ወደተከሳሹ ቤት ትሄድ የነበረ መሆኑን፣ቤታቸው ቅርብ ለቅርብ በመሆኑ የምትሄደው ብቻዋን መሆኑን፣ድርጊቱ ተፈጸመ በተባለበት ዕለትም ሕጻኗ የሄደችው በዚሁ ሁኔታ መሆኑን፣ሕጻኗ ወደ ተከሳሹ ቤት ሄዳ እዚያው በነበረችበት ጊዜ ሞግዚቷ የሆነችው 4ኛ ምስክር የሕጻኗን መኖር ለማረጋገጥ ወደ ተከሳሹ ቤት ሄዳ በሩን ስታንኳኳ ተከሳሹ እንደከፈተላት እና የሕጻኗን መኖር ስትጠይቀው መኖሯን የነገራት መሆኑን፣በወቅቱም ከተከሳሹ ቤት ውስጥ ከእርሱ እና ከግል ተበዳይዋ ህጻን በቀር ልላ ሰው ያልነበረ መሆኑን እና መሰል ፍሬ ነገሮችን የሚገልጽ ነው።ከየካቲት 12 ሆስፒታል በ09/06/2004 ዓ.ም. የተሰጠው የሕክምና ማስረጃም የሕጻኗ ድንግልና የታችኛው የቀኝ ክፍል ትኩስ መቀደድ የታየበት መሆኑን የሚያመለክት ነው።
ቀደም ሲል እንደተገለጸው ሕጻኗ ድርጊቱ ተፈጽሞባታል በተባለበት ጊዜ የሁለት ዓመት ከስምንት ወር ዕድሜ የነበራት ሲሆን በፍርድ ቤት ቀርባ ምስክርነቷን የሰጠችውም ድርጊቱ ተፈጸመ ከተባለበት ቀን አንስቶ ሁለት ወር ባልሞላው ጊዜ ውስጥነው።በማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያ እርዳታ እና በተመሳሳይ ዕድሜ አካባቢ ለሚገኙ ሕጻናት በሚያመች ሁኔታ በተዘጋጀ የችሎት ፋሲላቲ በመታገዝ ሕጻኗ የሰጠችው ምስክርነት በተለይ ሲታይ አዋቂ ሰዎች በሚጠቀሙበት ዓይነት አነጋገር እና አገላለጽ የተሰጠ ባይሆንም የተፈጸመባትን ድርጊት ዓይነት፣ድርጊቱን የፈጸመባትን ሰው ማንነት፣ፈጻሚው ድርጊቱን የፈጸመው በየትኛው የአካል ክፍሉ በመጠቀም እና በየትኛው የአካል ክፍሐ ላይ መሆኑን በግልጽ መገንዘብ በሚያስችል ሁኔታ የተሰጠ መሆኑን እና ድርጊቱን ፈጽሞብኛል ያለችውን ሰው ለይታ እንድታሳይ ተጠይቃም ወደ ችሎቱ አዳራሽ በመምጣት የአሁኑን ተጠሪ ለይታ ያሳየች መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።
ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት አጠቃላይ ይዘቱ ከላይ የተመለከተውን የግራ ቀኙን ማስረጃ ከመረመረ በኃላ ተጠሪው ባሰማቸው የመከላከያ ምስክሮች በዐቃቤ ሕግ ማስረጃ የተመሰከረበትን ፍሬ ነገር ከጥርጣሬ ላይ በሚጥል ሁኔታ አስተባብሐል በማለት በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 149(2) ድንጋጌ መሰረት በነፃ እንዲሰናበት ለሰጠው ውሳኔ በመከላከያ ምስክሮች ከተሰጠው ምስክርነት ውስጥ መሰረታዊ ምክንያቶች አድርጎ የወሰደው፡-
የግል ተበዳይዋ ሕፃን ቤተሰቦች እና ተከሳሹ በሚኖሩበት አካባቢ ከተከሳሹ ጋር በተመሳሳይ ስም የሚጠራ በሃያ ዓመት ዕድሜ አካባቢ የሚገኝ ልላ ሰው አለ መባሉን በተመለከተ በመሰረቱ የድርጊቱን ፈጻሚ ማንነት በተመለከተ በአመልካች ምስክሮች የተሰጠው ምስክርነት ድርጊቱን የፈጸመው ሣሙኤል የሚባል በሕጻኗ ቤተሰቦች መኖሪያ አካባቢ የሚኖር ሰው ነው ተብሎ በደፈናው እና የድርጊቱን ፈጻሚ ማንነት ለይቶ ለማረጋገጥ በማያስችል ወይም በሚያጠራጥር ሁኔታ የተሰጠ ሳይሆን ድርጊቱን የፈጸመው የአሁኑ ተጠሪ ስለመሆኑ በስም፣በመኖሪያ ቤቱ ማለትም ድርጊቱ በተፈጸመበት ቤት ልዩ አድራሻ እና በአካላዊ መለያው ጭምር ተለይቶ እና ተረጋግጦ የተሰጠ መሆኑን ይዘቱ ከላይ የሰፈረው የምስክርነቱ ይዘት በግልጽ የሚያመለክት በመሆኑ በአካባቢው ከተከሳሹ ጋር በተመሳሳይ ስም የሚጠራ ልላ ሰው የመኖሩ ወይም ያለመኖሩ ጉዳይ ለክርክሩ አግባብነት ያለው የመከላከያ ፍሬ ነገር ነው ላባል የሚችልበት የሕግ አግባብ የለም።ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት ለዚህ ዓይነቱ ለክርክሩ አግባብነት ለልለው የመከላከያ ፍሬ ነገር ዋጋ ሰጥቶ ተጠሪው ባሰማው መካለከያ ማስረጃ በአመልካች ማስረጃ የተመሰከረበትን ፍሬ ነገር ከጥርጣሬ ላይ በሚጥል ሁኔታ አስተባብሐል ከሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱም ሕጋዊ ተቀባይነት ላሰጠው የሚገባ አይደለም።
በተከሳሽ ቤተሰቦች እና በግል ተበዳይ የእናት ወገን ቤተሰቦች መካከል የቆየ ቂም በቀል አለ መባሉን በተመለከተ የግል ተበዳይ እናት የሆኑት 2ኛ ምስክር ተጠይቀው በሁለቱ ቤተሰቦች መካከል የቆየ ጥል ነበረ መባሉን እህታቸው ከሆኑት 3ኛ ምስክር የሰሙት ድርጊቱ ከተፈጸመ በኃላ እንደሆነ፣ልሎች የምስክሯ ቤተሰቦች በተለያየ ምክንያት አካባቢውን የለቀቁ መሆኑን እና አሁን በአካባቢው የቀሩት ምስክሯ ብቻ መሆናቸውን እና ድርጊቱ ከመፈጸሙ በፊት ነበረ ስለተባለው ጠብ የሚያውቁት ነገር ስላልነበረ ከከሳሹ ጋር በክፉ እና በደስታ ቀን ይደራረሱ እንደነበረ በመግለጽ የመሰከሩ ሲሆን 3ኛ ምስክር በበኩላቸው ጠቡ ተከስቶ የነበረው ከ35 ዓመታት በፊት መሆኑን እና የጠቡን መንስኤ ጭምር በመግለጽ መስክረዋል።ተጠሪው እና የግል ተበዳይ ቤተሰቦች ጨርሰው የማይነጋገሩ እና 3ኛ ምስክር በገለጹት መሰረት በክፉ እና በደስታ ቀን የማይደራረሱ ስለመሆኑ በተጠሪው ምስክሮች የተነገረ ነገር የለም።ምስክርነት በሰጡበት ጊዜ የ2ኛ እና የ3ኛ ምስክሮች ዕድሜ እንደቅደም ተከተሉ 30 እና 44 ዓመት መሆኑንም የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።ተጠሪው በሁለቱ ቤተሰቦች መካከል የቆየ ቂም በቀል አለ በሚል ጭብጥ ዙሪያ መከላከያ ምስክሮችን ያሰማው የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች የቆየውን ቂም በቀል መሰረት በማድረግ በሀሰት የመሰከሩበት መሆኑን ግምት ለማስወሰድ እንደሆነ የሚታመን ነው።ይሁን እንጂ በተጠሪው ላይ ዋነኛ እና የዓይን ምስክር ሆና የቀረበችው የግል ተበዳይ ስለቂም በቀል ልታውቅ የማትችል የ2 ዓመት ከ8 ወር ሕጻን በመሆኗ እና የአካባቢ ማስረጃ የሆነችው የሕጻኗ ሞግዚት 4ኛ ምስክርም የ14 ዓመት ዕድሜ ያላት እና በግል ተበዳይ እናት ቤት የቆየችው ለጥቂት ዓመታት ብቻ እንደሆነ መዝገቡ የሚያመለክት በመሆኑ እነዚህ ሁለቱ ምስክሮች ምስክርነት የሰጡት በቂም በቀል ላሆን የሚችልበት ዕድል ፈጽሞ አለመኖሩን ከምስክርነታቸው አጠቃላይ ይዘት መገንዘብ የሚያዳግት አይደለም። ምስክርነታቸውም በተጨባጭ የሀኪም ማስረጃ የተደገፈ ጭምር ነው።በመሆኑም የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች የሰጡት ምስክርነት የተሰጠው በቂም በቀል ስለመሆኑ ምንም ዓይነት አመላካች ፍንጭ በልለበት ሁኔታ የስር ፍርድ ቤቶች ለደረሱበት ድምዳሜ ይህንን ያልተረጋገጠ ፍሬ ነገር መሰረት ማድረጋቸው አጠቃላይ የማስረጃ ምዘና መርህን መሰረት ያደረገ ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም።
የግል ተበዳይ ሰራተኛ አባት የግል ተበዳይ ቤተሰቦችን ልጄን በሀሰት አስመስክራችኃል በማለት ተከሳሽ ከተያዙ በኃላ መጥተው ልጃቸውን ወስደዋል መባሉን በተመለከተ በዚህ ረገድ ምስክርነት የሰጠችው 3ኛ የመከላከያ ምስክር ስትሆን የምስክርነቷ ይዘትም የሰራተኛዋ አባት ወደግል ተበዳይ እናት ስልክ ደውለው ልጃቸውን በሀሰት እንደዳስመሰከሯት ልጃቸው የነገረቻቸው መሆኑን እና የግል ተበዳይ እናትም የምትመሰክረው ነገር ስላለ መስክራ ትመጣልሃለች ብለው መመለሳቸውን የሚገልጽ ነው።በመሰረቱ የመከላከያ ምስክሯ የመሰከረችው የስልክ ንግግሩን በቀጥታ ሰምቻለሁ በማለት ሳይሆን የስልክ ንግግሩን ከሰሙት የግል ተበዳይ ጎረቤቶች ሰማሁ በማለት ነው።ተጠሪው ይህንን የስልክ ንግግር በቀጥታ ሰምተናል ያሉትን ጎረቤቶች አቅርቦ ማሰማት ያልቻለበት ምክንያትም ሆነ የጎረቤቶቹ ማንነት አልተገለጸም።በልላ በኩል ሰራተኛዋ በፍርድ ቤት ቀርባ ምስክርነቷን የሰጠችው የስልክ ንግግሩ ተደረገ ከተባለበት ጊዜ በኃላ ሲሆን በተጠሪው ጠበቃ ለቀረበላት መስቀልኛ ጥያቄ ምስክርነቷን እንድትሰጥ በግል ተበዳይ ቤተሰቦች በኩል የደረሰባት ምንም ዓይነት ተጽዕኖ አለመኖሩን በማረጋገጥ መመስከሯን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።
ሲጠቃለል ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት ከላይ በዝርዝር በተመለከተው አግባብ በከሳሽ የሰው እና የሰነድ ማስረጃ የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር ወደጎን ትቶ በመከላከያ ምስክሮች የተነገሩ ነገር ግን ለክርክሩ አግባብነት የልላቸውን እና ያልተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች በዐቃቤ ሕግ የዓይን፣የአካባቢ እና የሀኪም ማስረጃ ከተረጋገጠው ፍሬ ነገር ጋር በመመዘን ተጠሪው ባሰማቸው የመከላከያ ምስክሮች በዐቃቤ ሕግ ማስረጃ የተመሰከረበትን ፍሬ ነገር ከጥርጣሬ ላይ በሚጥል ሁኔታ አስተባብሐል በማለት የደረሰበት ድምዳሜም ሆነ ይህንን ድምዳሜ መሰረት አድርጎ ተጠሪን በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 149(2) ድንጋጌ መሰረት በነፃ በማሰናበት የሰጠው እና በይግባኝ ሰሚው ፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተቀባይነት ያገኘው ውሳኔ የማስረጃ ምዘና መሰረታዊ መርሆዎችን መሰረት ያላደረገ እና መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ30/11/2004 ዓ.ም. ተሰጥቶ በፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ28/05/2005 ዓ.ም. የጸናውን ውሳኔ በመሻር ዐቃቤ ሕግ በክሱ መሰረት በዓይን፣በአካባቢ እና በሀኪም ማስረጃ ያስረዳበትን የወንጀል ፍሬ ነገር በመካለከያው ያላስተባበለ በመሆኑ ተጠሪው በተከሰሰበት በሕጻናት ልጆች ላይ የሚፈጸም የግብረ ስጋ ድፍረት በደል ወንጀል ጥፋተኛ ነው በማለት በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 195(2)(ሀ) መሰረት ወስነናል።
ተጠሪው ጥፋተኛ የተባለ በመሆኑ በቁጥጥር ስር አቆይቶ እንዲያቀርበው ለአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ይጻፍ።
ግራ ቀኙ የቅጣት አስተያየታቸውን በቅጣት አወሳሰን መመሪያ መሰረት በቀጣይ ቀጠሮ በጽሁፍ ያቅርቡ።
ግራ ቀኙ የሚያቀርቡትን የቅጣት አስተያየት ለመቀበል 20/05/07 ዓ.ም ተቀጠረ።
No topics extracted.