No summary available.
መጋቢት 18 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽላት ይመሰል አመልካች፡- 1.መፍትሃ ሙሜ 2. ናቶላ መሃመድ ነጂብ የቀረበ የለም 3. ሐናን መሃመድ ነጂብ ተጠሪ፡- አቶ ዑስማን ዓላ - ጠበቃ ይማጅ ዮኒስ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅን መሰረት ያደረገ ሁኖ የጉዳት ካሣ ክፍያን የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካቾች ባቀረቡት የክስ ማመልከቻ የ1ኛ አመልካች ህጋዊ ባለቤት የልሎች አመልካቾች ወላጅ አባት የሆኑት ሟች መሃመድ ነጂብ በተጠሪ በሰራተኛነት ተቀጥረው በማገልግል ላይ እያሉ የተጠሪ ንብረት የሆነውንና የሻንሲ ቁጥር JAAKP- 34HbB7P5165፣የሞተር ቁጥሩ 4HG1-865627 የሆነና የሰልዳ ቁጥር ያልወጣለትን አይሱዙ ተሸከርካሪ ከድሬዳዋ አዲስ አበባ ለማድረስ በማሽከርከር ላይ እንዳሉ ተጠሪ በእሩምታ ጥይት ተተኮሶባቸው ሕይወታቸው በማለፉየጉዳት ካሳ 903.000.00(ዘጠኝ መቶ ሰለሳ ሺህ) ብር እንዲከፈላቸው ይወሰንላቸው ዘንድ በፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የአሁኑ ተጠሪም በተከሣሽነት ቀርበው ከሟች ጋር የስራ ቅጥር ውል የልላቸው መሆኑንና ሟቹ በራሳቸው ኃላፊነትና መሪነት ለተለያዩ ሰዎች የሙያ አገልግሎት የሚሰጡ እንጂየተጠሪ ተቀጣሪ ያለመሆናቸውን፣ግንኙነቱ የሙያ አገልግሎት በመሆኑ ላገዛ የሚገባው በፍትሐ ብሕር ሕጉ ድንጋጌዎች ነው በማለት ክሱ ውድቅ እንዲሆንላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል።
የስር ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን የቃል ክርክር እና ማስረጃዎችን ከሰማ በኋላ በተጠሪ በኩል በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት የቀረቡትን የክርክር ነጥቦች ውድቅ በማድረግ በሟችና በተጠሪ መካከል የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት የነበረ መሆኑ ተረጋግጧል የሚል ድምዳሜ ደርሶ የጉዳት ካሣውን መጠንን በተመለከተም የሟቹ የወር ደመወዝ ብር 12,000.00(አስራ ሁለት ሺህ) መሆኑን መገንዘቡን ጠቅሶ በዚሁ ወርሃዊ የደመወዝ መጠን በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 110(3) የሞት ጉዳት ካሳው ሲሳላ ብር 720,000.00 (ሰባት መቶ ሃያ ሺህ) እንደሚሆንና የቀብር ማስፈጸሚያም የሁለት ወር ደመወዝ ብር 24,000.00 ላያዝ እንደሚገባ ገልፆ በድምሩ ብር 744,000.00(ሰባት መቶ አርባ አራት ሺህ ብር) ካሳ ለአመልካቾች ላከፈል እንደሚገባ፣ አከፋፈሉን በተመለከተም ከዚሁ ገንዘብ ውስጥ 50% የሟች ሚስት ለሆኑት ለአሁኗ 1ኛ አመልካች፣ ቀሪው 50% ደግሞ ለሟች ተወላጆች ለአሁኑ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ላከፈል ይገባል በማለት ወስኗል።በጉዳት ካሳ መጠኑ ላይ 10% ደግሞ ለጠበቃ አበል እንዲከፈል ሲል ወስኗል። በዚህ ውሣኔ የአሁኑ ተጠሪ ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፍድራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ጉዳዩን መርምሮ በሟች እና በተጠሪ መካከል ያለው ግንኙነት የአሰሪና ሰራተኛ አይደለም፣ ሟች በራሳቸው ኃላፊነትና መሪነት ስራውን ሲሰሩ የነበሩ ናቸው በማለት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ ሽሮታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ የበታች ፍ/ቤቶችን ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካቾች ጠበቃ መስከረም 27 ቀን 2007 ዓ.ም በፃፉት 4/አራት/ ገፅ የሰበር አቤቱታ በፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈፅሟል የሚሉባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡-ሟች ሹፍር ሁነው ለተጠሪ ሲሰሩ የነበሩ መሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ በራሳቸው ኃላፊነትና መሪነት የሙያ አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ ናቸው ተብሎ ግንኙነቱ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ህግ አይገዛም ሲባል የተወሰነው ውሳኔ ስለሙያ አግባብነት ባላቸው ሕጎች የተቀመጠውን መስፈርት ያላገናዘበ በመሆኑ ላታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ችሎት እንዲታይ በመደረጉ ተጠሪ ቀርበው ግራ ቀኙ በፅሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን የጽሑፍ እና የቃል ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ከላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር አገናዝቦ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የዚህን ችሎት ምላሽ የሚያስፈልጋቸው አበይት ጭብጦች፡-
በተጠሪ እና በሟች መካከል የነበረው ግንኙነት በአዋጅ ቁጥር 377/96 ድንጋጌዎች አግባብ የሚገዛ ነው? ወይስ አይደለም?
ከተባለስ የጉዳት ካሳ መጠኑ ምን ያህል ላሆን ይገባል? የሚሉት ሁነው አግኝተናል።
የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ፡ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ሟች ህይወታቸው ያለፈው በሹፍነታቸው የተጠሪ ንብረት የሆነውን መኪና ከድሬዳዋ ወደ አዲስ አበባ በማሽከርከር ላይ እንዳሉ በተከፈተባቸው እሩምታ ተኩስ መሆኑን፣ሟች አንድ ጊዜ መኪና ሲያደርስ ብር 800.00 (ስምንት መቶ) ብር ለመከፈል ተጠሪ መስማማታቸውን ተጠሪ ባቀረቡት ክርክርም ሆነ የአመልካቾች ምስክሮች መረጋገጡን የስር ፍርድ ቤት በውሳኔው ላይ በግልጽ ያሰፈረው ጉዳይ መሆኑን ነው። በሟችና በተጠሪ መካከል እንደዚህ አይነት ስምምነት የተደረገው ከሚያዚያ ወር 2002 ዓ/ም ጀምሮ መሆኑንና የሞት አደጋው የደረሰው ደግሞ የካቲት 08 ቀን 2003 ዓ/ም ስለመሆኑ በአመልካቾች ማስረጃዎች የተነገረ መሆኑንም ከስር ከበታች ፍርድ ቤቶች የውሳኔ ይዘት ተመልክተናል።
ይህንኑ ለመመለስም በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አሰሪና ሰራተኛ ማን ነው የሚለውን ጉዳይ መመልከቱ የግድ ይላል። ይህ ጥያቄ ምላሽ ላያገኝ የሚችለውም በአዋጁ የሚገዙት የትኞቹ አሰሪዎች እና ሰራተኞች ናቸው? የሚለው ጥያቄ መሰረት በማድረግ መሆኑ ይታመናል።
በመሰረቱ አዋጅ ቁጥር 377/1996 በአንቀፅ 2/3/ ስር ሰራተኛ ማለት በዚህ አዋጅ አንቀፅ 4 ስር በተመለከተው መሰረት ከአሰሪ ጋር በቅጥር ላይ የተመሰረተ የስራ ግንኙነት ያለው ግለሰብ ነው በማለት በግልፅ ያስቀምጣል። በመሆኑም ይህ ሰራተኛ ለአሰሪው በአሰሪው ቁጥጥር ስር ሁኖ አሰሪው በሚከፍለው ደሞዝ በራሱ የጉልበት ወይም የእውቀት አገልግሎት ለተወሰነ ጊዜ ወይም ስራ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ የሚሰጥ መሆኑን አዋጅ ያስገነዝባል። በልላ በኩል አዋጁ በአንቀፅ 2/1/ ስር አሰሪ ማለት አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ሰዎችን በዚህ አዋጅ አንቀጽ 4 በተመለከተው መሰረት ቀጥሮ የሚያሰራ ግለሰብ ወይም ድርጅት ላሆን እንደሚችል በመግለፅ ድርጅት የሆነውን አሰሪ በማየት አሰሪ ማን ነው? የሚለውን ጥያቄውን ለመፍታት የሚያስችል መሆኑ የሚያስረዳ ነው። ከዚህ አንፃር ጥያቄውን ስንመለከተውም አሰሪው ግለሰብ ወይም ድርጅት ሲሆን የስራ ውሉ ግንኙነት በአዋጅ የሚገዛ መሆኑን፣ አሰሪው ከነዚህ ውጭ ከሆነ እንደሁኔታው የልሎች ህጎች ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት የሚኖራቸው መሆኑን ሕጉ የሚያመለክት መሆኑን መረዳት የምንችለው ጉዳይ ይሆናል። በአዋጁ ስለሰራተኛ የተቀመጠው ትርጉም የሚያሳየው በአዋጁ አንቀጽ 4 በተመለከተው መሰረት ከአሰሪ ጋር በቅጥር ላይ የተመሰረተ የስራ ግንኙነት ያለው ግለሰብ መሆኑን አንቀጽ 2(3) በግልጽ ያሳያል። በዚህ ድንጋጌ ይዘት አንድን ሰው ሰራተኛ ነው ለማለት በቅጥር ላይ የተመሰረተ የስራ ግንኙነት መኖሩና በአዋጁ አንቀጽ 4 ድንጋጌ አግባብ መሰረት ሰራተኛው አገልግሎት ለመስጠት መስማማቱ፣ሰራተኛው አገልግሎት የመስጠት ግድታ ያለበት መሆኑንና ሰራተኛው ላሰጥ የሚገባውን አገልግሎት አይነት፣ የት አገልግሎቱን መስጠት እንደአለበት፣አገልግሎቱን መቼ ላያከናውነው እንደሚገባና እንድት ማከናወን እንደሚኖርበት አሰሪው የመቆጣጣር ስልጣን ያለው መሆኑ መረጋገጥ ያለባቸው መሆኑን ነው። አሰሪው ሰራተኛውን በዚሁ በህጉ በተቀመጠው አግባብ ተቆጣጥሮ ስራውን የሚያሰራ መሆኑ መረጋገጡ አንድ ተዋዋይ ወገን ዋጋ እየተከፈለው የንግድ ስራ ወይም በራሱ የሙያ ኃላፊነት የሚሰራ ስራ ከሚያከናውን ወገን በትክክል ለመለየት የሚረዳ መሆኑም ተቀባይነት ያለው መለኪያ ነው።በአዋጁ ለቅጥር ውሉ ከተሰጠው ትርጉም መካከል አንዱ የደመወዝ ጉዳይ ሲሆን ሰራተኛው ለአሰሪው በገባው ለአሰሪው ጥቅምና በአሰሪው ቁጥጥር ችሎታውንና ጊዜውን በመጠቀም ተገቢውን አገልግሎት ለአሰሪው ለመስጠት ግድታ የሚገባው አሰሪው ለሰራተኛው ተገቢውን የድካም ዋጋ በደመወዝ መልክ የመክፈል ግድታ ሲገባነው።
ደመወዝ ደግሞ በጥሬ ገንዘብ ወይም በአይነት ላሆን የሚችል ሁኖ የአከፋፈሉ ጊዜም አንደነገሩ ሁኔታ በየቀኑ፣በየሁለት ቀኑ፣ በየሁለት ሳምንቱ፣በየወሩ፣በተሰራው ሰራ መጠን……ወዘተ ላሆን እንደሚችል ከአዋጁ አንቀጽ 4 እና 58 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዳይ ነው።በመሆኑም በእነዚህ የአከፋፈል ጊዜያት ወይ ዘድዎች ደመወዝ የመከፈሉ ሁኔታ በአሰሪና ሰራተኛ መካከል በተመሰረተው የቅጥር ሁኔታ ላይ በሕጉ ረገድ ለውጥ የማያስከትል መሆኑን መገንዘብ ይቻላል።
ወደተያዘው ጉዳይ ስንመለስም ሟች ተጠሪ ግለሰብ ከውጪ ከሚያስመጣቸው ተሽከርካሪዎች ውስጥ ከድሬዳዋ ወደ አዲስ አበባ በማመላለስ አገልግሎት ሲሰጡ እንደነበርና ስራውን የሚሰራው ጊዜና ቦታ መኖሩን፣ይህም በተጠሪው መሪነት ወይም ቁጥጥር ሲከናወን የነበረ መሆኑን የክርክሩ ሂደት ያሳያል።ተጠሪ ሟቹ ሲከፈላቸው የነበረው ደወመዝ በቁርጥ መሆኑን ጠቅሰው ከመከራከራቸው ውጪ ሟቹ የሚሰጡትን አገልግሎት በራሳቸው ቁጥጥር ስር ያልነበረ መሆኑን አላስረዱም። የደመወዝ አከፋፈል በቁርጥ መሆኑ ደግሞ የቅጥር ግንኙነት ከላይ በተመለከቱት የአዋጁ ድንጋጌ ስለ ሰራተኛ ማንነት የተቀመጠውን ትርጉም ላለመቀበል የሚያስችል አይደለም።
ከዚህ አንፃር ጉዳዩን ስንመለከተው ሟች በተጠሪ ቁጥጥር ስር ሁነው የሹፍርና አገልግሎት ሲሰጡ የነበረ መሆኑ በሚገባ የተረጋገጠ ሁኖ እያለ የፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሟች በራሱ የሙያ ኃላፊነት ሲሰሩ የነበሩ ናቸው በማለት ግንኙነቱ በአዋጅ ቁጥር 377/96 የሚገዛ አይደለም በማለት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ መሻሩ በሕጉ ስለሰራተኛ ማንነት የተቀመጡ መለኪያዎችን በአግባቡ ባላገናዘበ መልኩ ሁኖ አግኝተናል። በመሆኑም ውሳኔው የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 2(1)(2)፣3(2(ረ))፣ 4 እና 58 ድንጋጌዎችን ይዘትና መንፈስ የጣሰ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ አግኝተናል።
ሁለተኛውን ነጥብ በተመለከተ፡-ሟች የተጠሪ ሰራተኛ ናቸው ከተባለ በስራ ላይ እያሉ ሕይወታቸው ማለፉ ግራ ቀኙን ያላከራከረ ጉዳይ ነው። በስራ ምክንያት ለሚመጡ ጉዳቶች አሰሪው ሀላፊነት አለበት። ስለዚህ በስራ ምክንያት የሚመጣ ጉዳት ከሆነ አሰሪው ኃላፊነቱን እንዲወስድ የተደረገ ሲሆን በአዋጁም በስራ ላይ የሚደርስ ጉዳት ማለት በስራ ላይ የሚደርስ አደጋ ወይም በስራ ምክንያት የሚመጣ በሽታ መሆኑን በቁጥር 95(2) ደንግጓል በአዋጅ አንቀጽ 96(1) ”አሰራው ጥፋት ባይኖረውም…..” ተብሎ መመልከቱ የአሰሪው የኃላፊነት ዓይነት ጥፋት ሣይኖር ኃፊነት /Strict Liability or Liability in the absence of Fault/ መሆኑን የሚያሣይ ነው። አሰሪው ከዚህ ዓይነት ኃላፊነት የሚድነው ጉዳት የደረሰበት ሰራተኛ ሆነ ብሎ በራሡ ላይ ያደረሰው ጉዳት መሆኑን ማስረዳት ሲችል ስለመሆኑ አንቀጽ 98(2) ያስገነዝባል።ሆነ ብሎ ያደረሰው ጉዳት የሚባሉት ሁኔታዎችም ሰራተኛው አስቀድሞ በግል የተሰጡትን የደህንነት መጠበቂያ መመሪያዎችን መጣስ ወይም የአደጋ መከላከያ ደንቦችን መተላለፍ ወይም አካሉን ወይም አእምሮውን በሚገባ ለመቆጣጠር በማይችልበት ሁኔታ በመጠጥ ወይም በአደንዛዥ እፅ ሰክሮ በሥራ ላይ መገኘት መሆናቸውን ህጉ በቁጥር 96(2(ሀ እና ለ)) ስር አመላክቷል።
የአዋጁ አንቀጽ 97(1) ድንጋጌ ሲታይም አንድን አደጋ በስራ ላይ የደረሰ ነው ለማለት ሰራተኛው ስራውን በማከናወን ላይ እያለ ወይም ከስራው ጋር ግንኙነት ባለው ሁኔታ ከራሡ ውጭ በሆነ ምክንያት ወይም ስራውን ለማከናወን ባደረገው ጥረት ምክንያት በአካሉ ወይም በአካሉ በማንኛውም ክፍል ተፈጥሯዊ እንቅስቃሴ ላይ በድንገት የደረሰበት ጉዳት ስለመሆኑ መርሁን ያስቀመጠ ሲሆን ይኽው ድንጋጌ ከፊደል (ሀ) እስከ ፊደል (መ) በተመለከቱት ንዑስ ድንጋጌዎች የተመለከቱት ምክንያቶች በስራ ላይ የደረሰ አደጋ ተብለው የሚጨመሩ ስለመሆኑ ያሣያል። ስለሆነም በመርሁ መሰረት ሰራተኛው የጉዳት ካሣ ለማግኘት ማሣየት የሚጠበቅበት አደጋው ስራውን በማከናወን ላይ እያለ የደረሰ መሆኑን፣ ወይም ደግሞ በራሡ ባልሆነ ምክንያት ግን ከሥራው ጋር ግንኙነት ባለው መልኩ የደረሰበት አደጋ መሆኑን ነው ።ከላይ እንደተገለፀው ከስራ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሁኔታዎች ምን እንደሆኑ ህጉ አስቀምጧል። ለዚህ ጉዳይ ቀጥተኛ አግባብነት ያለው ድንጋጌ በአንቀጽ 97(1(ሐ)) ስር የተመለከተው ሲሆን በዚህ ድንጋጌ መሰረት አሰሪው በመደበው የመጓጓዝ አገልግሎት ሰራተኛው ሲጠቀም ጉዳት ከደረሰ አደጋው በስራ ላይ እንደደረሰ ተቆጥሮ ኃፊነቱን ከአሰሪው ላወሰድ የሚገባ መሆኑ ተመልክቷል። ይኽው ድንጋጌ አሰሪው የመደበው የመጓጓዝ አገልግሎት አደጋው ከደረሰበት በአሰሪው ስር ባለው ልላ ሰራተኛ ወይም 3ኛ ወገን ከሆነ አሰሪው ለተጐጂው ሰራተኛ የጉዳት ካሣ ኃፊነት የልለበት ስለመሆኑ አያሣይም ይልቁንም ድንጋጌው በአዋጁ አንቀጽ 96(1) ስር ከተመለከተው የአሰሪ አላፊነት ዓይነት ጋር ተዳምሮ ሲታይ አሰሪው አላፊነት ያለበት መሆኑን የሚያጠናክር ነው በልላ አገላለፅ በሰራተኛው ላይ ጉዳት ያደረሰው ሰራተኛው ወደ ስራ ሲሄድና ከስራ ወጥቶ ወደ ቤቱ ሲመለስ አሰሪው በመደበው የመጓጓዠ አገልግሎት ሲጠቀም አደጋ የደረሰበት መሆኑ ከተረጋገጠ 3ኛ ወገኖች ለአደጋው ያደረጉት አስተዋጽኦ ለአሰሪው መከላከያ ላሆን አይችልም። በመሆኑም ሟች የተጠሪን መኪና በወቅቱ ሲያሽከረክሩ የነበሩ መሆኑ መረጋገጡ ተጠሪን ነፃ ላያደርገው የሚችልበት ህጋዊ ምክንያት ስለልለ ተጠሪ ለጉዳቱ ኃላፊነት ያለባቸው ናቸው።
ተጠሪ ለጉዳቱ ኃላፊ ናቸው ከተባለ የጉዳት ካሣ መጠኑ ምን ያህል ላሆን ይገባል?፣ ካሳው መክፈል ያለበት ለየትኞቹ የተጐጂ ጥገኞች ነው? የሚለው ጥያቄም በህጉ አግባብ መታየት ያለበት ነው። ለዚህጥያቄ ምላሽ የሚሰጠው ድንጋጌም በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 107(1(ሐ) ስር ተመልክቷል። በዚህ ድንጋጌ መሰረት ማንኛውም በስራ ላይ የሚመጣ ጉዳት የደረሰበት ሰራተኛ የሞተ እንደሆነ ለጥገኞች የጡረታ አበል ወይም ዳረጐት ወይም ካሣ የማግኘት መብት ያለው ስለመሆኑ ተመልክቷል።የአዋጁ አንቀጽ 110 ድንጋጌ ሲታይም ለሟች ሰራተኛ ጥገኞች የሚከፍሉትን የክፍያ ዓይነቶችንና ጥገኛ የሚባሉትን ወገኖች በንዑስ ቁጥር አንድና ሁለት በግልፅ ዘርዝሯል። በዚህም መሰረት ማንኛውም ሰራተኛ ወይም ለማጅ ሰራተኛ በስራ ምክንያት በደረሰበት ጉዳት የተነሣ የሞተ እንደሆነ የጉዳት ካሣ ለጥገኞች፣ የቀብር ሥነ ሥርዓት ወጪ እንደሚከፈልና ጥገኞች የሚባሉትም የሟች ህጋዊ ባል ወይም ሚስት፣ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ የሟች ልጆችና በሟች ሰራተኛ ድጋፍ ይረዱ የነበሩ የሟች ወላጆች ስለመሆናቸው ተመልክቷል።
ወደ ተያዘው ጉዳይ ስንመለስም 1ኛ አመልካች የሟች ሚስት፣ ልሎች ተጠሪዎች ደግሞ ተወላጅ ናቸው። በመሆኑም አመልካቾች በህጉ አግባብም የሟች ጥገኛ መሆናቸው ስለተረጋገጠ የጉዳት ካሣ የሚገባቸው ሆኖ ተገኝቷል።
የጉዳት ካሳ መጠኑም በሰራተኛው በስራ ላይ እያለ የሞተ እንደሆነ የሰራተኛው የዓመት ደሞዝ በአምስት ተባዝቶ የሚከፈል እንደሆነ አንቀፅ 110(3) ተመልክቷል።ይህንኑ ለመወሰን ደግሞ የሰራተኛው ደመወዝ መጠኑ በትክክል ላታወቅ ይገባል።በተያዘው ጉዳይ የፍድራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሟችን ደመወዝ መጠን በወር 12,000.00 ያደረገው በወር ውስጥ አስራ አምስት ቀናትን ለተጠሪ አገልግሎት ለመስጠት ይችላሉ በሚል መነሻ ነው። ይሁን እንጂ በዚህ ረገድ በግልጽ የቀረበ ማስረጃ የለም።በፍሬ ነገር ደረጃ በሚገባ የተረጋገጠው ሟች ከድሬዳዋ ወደ አዲስ አበባ ለሚያደርሱት አንድ ተሸከርካሪ ብር 800.00(ስምንት መቶ ) የሚከፈላቸው መሆኑ ነው።ይህ ደግሞ ሟች በወር አስራ አምስት ቀናት ሙሉ ስራውን ይሰራሉ ተብሎ ስላልተረጋገጠ የወርሃዊ ደመወዝ መጠን በብር 800.00 ላታሰብ የሚገባው ሁኖ አልተገኘም።በመሆኑም ይህ ችሎት የሟች ወርሃዊ ደመወዝ ከብር 3200.00 ላበልጥ የሚችልበትን አግባብ አላገኘም።
ይኼው የደመወዝ መጠን መሰረት ተደርጎ አመታዊ ደመወዝ ሲሰላ ደግሞ ብር 38,400.00(ሰላሳ ስምንት ሺህ አራት መቶ ብር) ሁኖ በአዋጁ አንቀጽ 110(3) መሰረት የአምስት ዓመቱ ሲሰላ ብር 192,000.00(አንድ መቶ ዘጠና ሁለት ሺህ ብር) የጉዳት ካሳ ላሆን የሚገባው ሁኖ አግኝተናል።
የቀብር ሥርዓት ማስፈፀሚያ ክፍያ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 110(1(ለ) መሰረት ሲሰላም የሁለት ወር ደመወዝ ብር 6,400.00(ስድስት ሺህ አራት መቶ ብር) መሆን ያለበት ሁኖ አግኝተናል።
በአጠቃላይ 198,400.00 (አንድ መቶ ዘጠና ስምንት ሺህ አራት መቶ ብር) የሟች ጥገኛ ለሆኑት ለአሁኑ አመልካቾች በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 110(3) እና (4) ስር በተመለከተው አግባብ የሚከፈል የጉዳት ካሣ መጠን ሁኖ አግኝተናል። ሲጠቃለልም የፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ሙሉ በሙሉ፣ የፍድራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔ ደግሞ በከፊል መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለባቸው በመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፍድራሉ ከፍ/ፍ/ቤት በመ/ ሐምል 23 ቀን 2006 ዓ/ም ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
በፍድራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/መ/ ጥር 26 ቀን 2006 ዓ.ም እና መጋቢት 29 ቀን 2006 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሻሽሐል።
በሟች እና በተጠሪ መካከል የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ውል አለ፣ ሟቹ የሞቱት በስራ ላይ እያሉ በመሆኑ ለሟቹ ጥገኞች የሞት ጉዳት ካሳ የሟቹ የአምስት አመት ደመወዝና የሁለት ወር ደመወዝ ለቀብር ስነ ስርዓት ማስፈፀሚያ ተጠሪ የመክፈል ኃላፊነት አለባቸው ብለናል።
ተጠሪ ለአመልካቾች የሚከፍሉት የካሳ መጠንም ብር 198,400.00(አንድ መቶ ዘጠናስምንት ሺህ አራት መቶ) ሁኖ አከፋፈሉም በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 110(3(ሀ) ((ለ)) በተመለከተው አግባብ 50% ለ1ኛ አመልካች (የሟች ሚስት) ቀሪው 50% ደግሞ ለሟች ልጆች (2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች) ላሆን ይገባል ብለናል። የጠበቃ አበል በዚህ ችሎት በተወሰነው የገንዘብ መጠን 10% ተጠሪ ለአመልካቾች ላተኩ ይገባል ብለናል።
ልሎች ወጪና ኪሳራዎች የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።
No topics extracted.