የአንድ ድርጅት የበላይ ኃላፊ ለሰራተኞች ለጡረተኞች የክፍያ ጭማሪን በተመለከተ በስሩ ለሚገኙ እንደየገቢያቸው መጠን እያስወሰኑና እያስፀደቁ የጭማሪ ክፍያ እንዲያደረጉ ያስተላለፈው ውሣኔ በሙሉ በስር በሚገኙት ድርጅቶች ላይ ተፈፃሚ ላሆን የሚገባው እነ አቶ ገ/መድህን አስፋው እና ትንሳኤ ጉባኤ ማተሚያ ቤት ሕዳር 24/2007 76 21. የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰራተኛ ጉዳይ ወሣኝ ቦርድ የወሰነውን ጉዳይ በይግባኝ ሲያይ የህግ ስህተት መኖሩን እና አለመኖሩን ከማረጋገጥ ባለፈ የፍሬ ጉዳይ እና የማስረጃ ምዘናን በተመለከተ የማየት እና የማረም ስልጣን የልለው ስለመሆኑ፣ አንድ አሰሪ የሰራተኛ ቅነሳ በሚል ምክንያት ሰራተኞችን ከሥራ ሲያሰናብት በአዋጁ የሰራተኛን ቅነሳ በተመለከተ የተቀመጡትን ድንጋጌዎች መሰረት ማድረግ ያለበት ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 28(2)(ሐ) ፣29፣140 102512 እነ ብርሀኑ ቢኒ (ሰላሳ አራት ሰዎች) እና የአርባ ምንጭ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ታህሳስ 10/2007 81 22. አንድ ሰራተኛ የስራ ግድታውን በአግባቡ ባለመወጣት በአሰሪው ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ላይ ጉዳት ያደረሰ ከሆነ የስራ ውሉን ያለማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ በቂ ምክንያት ሥለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 377/96 (1)(ሸ)፣ 12(2)(7)
No summary available.
ቀን 29/07/2007 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽላት ይመሰል አመልካች፡- ሐግቤስ ኃ/የተ/የግል/ማህበር - ነ/ፈጅ ፀጋዬ መካሻ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ በላይ ገ/ማሪያም - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የቀረበው በፍድደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአመልካች የስንብት እርምጃ ህገ ወጥ ነው ተብሎ የተሰጠው ውሳኔ በፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመጽናቱ በውሳኔው ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልካች ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዳዩ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 “ን” መሰረት ያደረገ የግል የስራ ክርክር ሁኖ አንድ ሰራተኛ ከአሰሪው ንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል ተብሎ ከስራ ያለማስጠንቀቂያ የሚሰናበትበትን የህግ አግባብ ነው።
በስር ፍርድ ቤት የቀረበው የተጠሪ ክስ አመልካች ተጠሪን በጨረታ እንዳይሳተፍ የተደረገውን ጥፋት ሳይፈጽም ይህንኑ ጥፋት ፈጽመሃል በሚል ምክንያት የስራ ውል አላግባብ ያቋረጠ በመሆኑ የተለያዩ ክፍያዎችን እንዲከፍል ይወሰንልኝ የሚል ነው። የአሁኑ አመልካች በተከሳሽነቱ ቀርቦ በሰጠው መልስ የተጠሪ የስራ መዝርዝር በግልጽ የሚያሳየው የጨረታ ሰነድ አዘጋጅተው የጨረታውን ሂደት በመከታተል ሪፖርት ማቅረብ መሆኑን ፣ ተጠሪ ይህንኑ የስራ ግድታ በመተላለፍ የጨረታ ሰነድ ሳያስገቡ በቀሩት የማሽን ጉልበት አመልካች ድርጅት ከጨረታ እንዲሰረዝ በመደረጉ ለተጠሪ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ቢሆንም አመልካች ድርጅት ተሳታፊ እንዲሆን በወሰነበት የትግራይ የውሃስራዎች ኮንስትራክሽን መጋቢት 05 ቀን 2005 ዓ/ም ባወጣው ጨረታ ጨረታውን ሳይከታተሉ በመቅረታቸው ድርጅቱ በጨረታው እንዳይሳተፍ አድርገው የጥቅም ማጣት እንዲደርስበት ያደረጉ መሆኑን ዘርዝሮ ስንብቱ በህጉ አግባብ የተደረገ ነው በማለት ተከራክሯል።
የስር ፍ/ቤት ተጠሪ በፈጸሙት ከባድ ቸልተኝነት ምክንያት አመልካች ድርጅት በጨረታው ላይ ሳይሳተፍ የቀረ መሆኑ ቢረጋገጥም በዚህ ጥፋት ምክንያት በአመልካች ድርጅት ላይ የደረሰ ጉዳት መኖሩ አልተረጋገጠም የሚል ምክንያት አስፍሮ የአመልካች የስንብት እርምጃ ህገ ወጥ ነው በማለት አመልካች ለተጠሪ የተለያዩ ክፍያዎችን ላከፍል ይገባል በማለት የክፍያዎችን አይነትና መጠን በመዘርዘር በድምሩ ብር 72,000.00 (ሰባ ሁለት ሺህ) እንዲከፍል፣ የስራ ልምድ የምስክር ወረቀት አዘጋጅቶ እንዲሰጠው ሲል ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ሲሆን የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- ተጠሪ በስራ መዘርዝራቸው መሰረት ግድታቸውን ያለመወጣታቸውና ከባድ ቸልተኝነት የነበረባቸው መሆኑን የስር ፍርድ ቤት አረጋግጦ ጉዳት ስለመድረሱ አልተረጋገጠም በሚል ምክንያት ብቻ ስንብቱ ህገ ወጥ ነው በማለት የወሰነው ከህጉ ይዘትና መንፈስ ውጪ ነው ፣ አመልካች በጨረታው ላይ ባለመሳተፉ ከብር ሃያ ሶስት ሚላዮን በላይ የጥቅም ማጣት ደርሶበታል በማለት መከራከሩን የሚያሳይ ነው።
አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ችሎት እንዲታይ በመደረጉ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው ግራ ቀኙ በጽሁፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል። ተጠሪ በፅሁፍ በሰጡት መልስም በአመልካች ድርጅት ላይ ጉዳት ያለመደረሱን ፣ በስራቸው የፈጸሙት ጥፋትም የልለ መሆኑን ዘርዝረው ተከራክረዋል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ጉዳዩን መርምረናል። ጉዳዩን እንደመረመርነው የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች የተጠሪን የስራ ውል ያቋረጠው ከህግ ውጭ በመሆኑ ፣ ለተጠሪ የተለያዩ ክፍያዎችን እንዲከፍል የሰጠው ውሳኔ ተገቢ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ጭብጥ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ጉዳዩን እንደመረመርነው የተጠሪ የስራ መዝርዝር በግልጽ የሚያሳየው የጨረታ ሰነድ አዘጋጅተው የጨረታውን ሂደት በመከታተል ሪፖርት ማቅርብ መሆኑንና ይህንኑ የስራ ግድታ ባለመወጣታቸው አመልካች ቀድሞ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው እንደገና አመልካች ድርጅት ተሳታፊ እንዲሆን በወሰነበት የትግራይ የውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን መጋቢት 05 ቀን 2005 ዓ/ም ባወጣው ጨረታ ጨረታውን ሳይከታተሉ በመቅረታቸው ድርጅቱ በጨረታው እንዳይሳተፍ ያደረጉ መሆኑ በበታች ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል። ተጠሪም ይህንን ጥፋት ያልፈጸሙ መሆኑን በማስረጃዎቹ ያላስረዱ መሆኑን ከስር ፍርድ ቤቶች የውሳኔ ይዘት ተገንዝበናል። ተጠሪ በዚህ የሰበር ክርክር ደረጃ ባቀረቡት መልስ በአመልካች ድርጅት ላይ በጨረታ ባለመሳተፉ የደረሰ ጉዳት የለም በማለት ከገለፁ በኋላ በአማራጭ ደግሞ ከባድ ቸልተኝነት እንዳልነበራቸውና ጥፋት እንዳልፈጸሙ ዘርዝረው በዚሁ በአማራጭ ባቀረቡት ክርክር መሰረት የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላጸና ይገባል በማለት ተከራክረዋል። ሆኖም ተጠሪ ከባድ ቸልተኘነት እንዳልነበራቸው ፣ ጥፋት እንዳልፈጸሙ የሚያቀርቡት ክርክር በሰበር መልሳቸው የተገለፀ እንጂ ስርዓቱን ጠብቆ የቀረበ ነው ላባል የሚችል ካለመሆኑም በላይ የስር ፍርድ ቤት ፍሬ ነገሩን አጣርቶና ማስረጃን መዝኖ የደረሰበት ድምዳሜ በመሆኑ በዚህ ችሎት ላለወጥ የሚችል ሆኖ አልተገኘም። በመሆኑም ተጠሪ በከባድ ቸልተኝነት አመልካች ድርጅት በጨረታው ላይ እንዳይሳተፍ ያደረጉ መሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ ነው በሚል የምንቀበለው ነጥብ ነው።
አመልካች ተጠሪን ለቀደመው ጥፋታቸው በማስጠንቀቂያ ያለፋቸው ቢሆንም መጋቢት 05 ቀን 2005 ዓ/ም በወጣው ጨረታ እንዳይሳተፍ የተደረገው በተጠሪ ጥፋት መሆኑ በመረጋገጡ ተጠሪን ከስራ ላያስናብታቸው ችሐል። አመልካች በዚህ ጨረታ ያልተሳተፈው በተጠሪ ከባድ ቸልተኝነት መሆኑ በበታች ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል። ተጠሪ የሚሰሩበት የስራ ባህርይ የጨረታ ሰነድ አዘጋጅተው የጨረታውን ሂደት በመከታተል ሪፖርት ማቅረብ መሆኑንም በስር ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ በመሆኑ ተጠሪ አመልካች ድርጅትን ጥቅም ለማስጠበቅ ከፍተኛ ጥንቃቄና ትጋት በማድረግ ግድታቸውን መወጣት የሚገባቸውና የድርጅቱ ኢኮኖሚ ጥቅም ጉዳት እንዳይደርስበት የማድረግ የስራ ግድታ አለባቸው። ተጠሪ ይህንን የስራ ተግባሩን በአግባቡና በጥንቃቄ ባለመፈጸማቸው አመልካች ድርጅት ከጨረታ መሰረዙ በድርጅቱ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ላይ ጉዳት አላደረሰም ላባል የሚችል አይደለም። ተጠሪ ጉዳዩን ጨረታን መሰረት ያደረገና በውድድር ላይ የተመሰረት መሆኑን ግልጸው የአመልካች ድርጅት የጨረታ ሰነድ ከልሎች ተጫራቾች ጋር ሲነጻጸር ጨረታውን ላያሽነፍ ይችል ያልነበረ መሆኑን ጠቅሰው ያቀረቡት ክርክር የለም። በጨረታው ውደድር በአመልካች ድርጅት ጥቅም የሚገኝበት አግባብ መኖሩ ግልጽ ከሆነና አመልካች በተጠሪ የስራ ግድታቸውን በአግባቡ ባለመወጣት ከውድድሩ ውጪ መሆኑ ከተረጋገጠ በአመልካች ድርጅት ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ላይ ጉዳት ያለመደረሱን የማስረዳት ግድታ የተጠሪ ነው። በዚህ ጉዳይ ግን ተጠሪ በአመልካች ላይ ጉዳት አልደረሰም ከማለት ውጪ ይህንኑ የሚያስረዳ ማስረጃ ያለማቅረባቸውን ከክርክሩ ሂደት ለመገንዘብ ችለናል።
ተጠሪ የፈጸሙት ጥፋት በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27 ንዑስ አንቀጽ 1/ሸ/ የሚሽፈንና የተጠሪን የስራ ውል ያለማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ የሚያስችል በቂ ምክንያት ሆኖ እያለ የበታች ፍርድ ቤቶች በተጠሪ ከባድ ቸልተኝነት ምክንያት በአመልካች ላይ የደረሰ ጉዳት የለም በማለት ስንብቱ ህገ ወጥ ነው በማለት የሰጡት ውሳኔ የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27(1)ሸ እና አንቀጽ 12(2)(7) ድንጋጌ መሰረታዊ ይዘት ፣ መንፈስና አላማ ያላገናዘብ ሆኖ አግኝተነዋል።
ከዚህ አንጻር ሲታይ አመልካች የተጠሪን ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ በድጋሚ ጥፋት ሲፈጽሙ የስራ ውሉን ያለማስጠንቀቂያ ማቋረጡ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27(1)(ሸ) እና 12(2)(7) ድንጋጌዎች መሰረት ህጋዊ እንጂ ህገ ወጥ ተግባር ሆኖ አላገኘነውም። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች የተጠሪን የስራ ውል ያቋረጠው ከህግ ውጭ ነው በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ ስለአገኘነው ተከታዩን ወስነናል።
በፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ሚያዚያ 30 ቀን 2006 ዓ/ም ተሰጥቶ በፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሐምል 25 ቀን 2006 ዓ/ም የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የአመልካች እርምጃ ህጋዊ ነው፣ አመልካች ለተጠሪ ካሳም ሆነ የሰራ ስንብት ክፍያ ላከፍል አይገባም ብለናል። የስራ ልምድ ምስክር ወረቀት ግን ይስጣቸው ብለናል።
በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.