የዓመት ዕረፍት ክፍያ አስፈላጊው የገቢ ግብር ተቀንሶ ለሰራተኛው ላከፈለውየሚገባ ስለመሆኑ:-አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 27(ሐ)፣36፣37 የገቢ ግብር አዋጅ 286/94 እና ደንብ ቁጥር 78/94 አንቀፅ 3
No summary available.
መስከረም 27 ቀን 2007 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አልማው ወል ሡልጣን አባተማም መኮንን ገ/ሕይወት ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ አመልካች፡- አቶ አየለ መንግሥቱ ተጠሪ፡- የኢትዮጲያ እህል ንግድ ድርጅት መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዳይ የተጀመረው በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ነገል ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች ከሣሽ ሲሆን ተጠሪ ተከሣሽ ነበሩ አመልካች ባቀረበው ክስ ተጠሪ ያለምንም ምክንያት ያለማስጠንቀቂያ ከሥራ ስላሰናበተኝ የአገልግሎት ካሣና ጉዳት ፣የስድስት ወር ደሞዝ፣ የአመት ዕረፍት ክፍያ እና የሥራ ልምድ ጨምሮ 51,778 ብር እንዲከፈለኝ በማለት ጠይቋል። ተጠሪም በሰጠው መልስ አመልካች የመጋዘን ኃላፊ ሆነው ሲሰሩ 41.01 ኩንታል በቆሎ በጆንያ መሐከል ተደብቆ በፅዳት ሰራተኛ በኩል ተደረሶበት ይህንንም ያደረጉት ለራሳቸው ጥቅም ለማዋል በማሰብ ነው፣በድርጊቱም ተጠይቀው በቀን ሰራተኛ ሲጫን ተዛብቶ ይሆናል በማለት ተናግሯል።
ይሁንና ይህ ተግባራቸው ያለቅድሚያ ማስጠንቀቂያ የሚያሰናብት ነው በማለት ተከራክሯል፡ጉዳዩ የቀረበለት ፍ/ቤትም ተገኘ የተባለው በቆሎ ማን እንደደበቀው በግልፅ ባልተረጋገጠበት ያለማስጠንቀቂያ መሰናበቱ ህገ ወጥ ነው በመሆኑም በአዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 36፣37 ሣያሟላ እርምጃ መወሰዱ አግባብ ስላልሆነ በአዋጅ አንቀጽ 43(1) መሰረት ካሳና ደሞዝ ጋር ተያይዘው የሚመጡትን ክፍያዎች ጨምሮ በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 40(1-3) ባጠቃላይ 49,998.50 ይከፈለው ሲል ወሰነ ጉዳዩ በይግባኝ የቀረበለትም የከፍተኛው ፍ/ቤት በፍ/ህ/ስ/ስ/ቁ.337 ሰርዞታል።
የክልሉም የሰበር ሰሚ ችሎት ጉዳዩን በማየት ጠፋ የተባለው በቆሎ በመጋዘን ውስጥ ተደብቆ እና ቁልፉም ከተጠሪ ልላ ማንም እንማይዘው ተረጋግጧል፣ በመሆኑም ተጠሪ የማጭበርበር ድርጊት የፈጸመ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27(ሐ) መሰረት ያለማስጠንቀቂያ የሚያሰናብት ነው ሲል የስር ፍ/ቤቶችን ውሳኔ ሽሮታል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታም ይህንን ውሳኔ ለማስቀየር ነው። አመልካች ባቀረቡት አቤቱታ በስር ፍ/ቤት ተጠሪ በሰጠው መልስ በመጋዘን ውስጥ የተደበቀ በቆሎ በመገኘቱ እንዳሰናበተኝ ቢገልጽም የደረሰ ጉዳት የለም በማለት አጣርቶ ስንብቱ ህገ ወጥ ነው በማለት የተለያዩ ክፍያ እንዲከፈለኝ ቢወሰንም የክልሉ ሰበር ሰሚ ፍ/ቤት የአመልካችን የመጋዘን ኃላፊ መሆኑን በመገልጽና ቁልፉም በእኔው እጅ እንደሚቀመጥ በመጥቀሰ የማጭበርበር ድርጊት ተፈጸሟል በማለት በአዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 27(ሐ) መሰረት ስንብቱ ህጋዊ ነው በማለት የተወሰነልኝን የዓመት ዕረፍት ጭምር የሰረዘ ውሳኔን መሰጠቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ ላታረም ይገባል በማለት ጠይቋዋል።
በዚህ መሰረት ይህ ችሎትም የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ ስንብቱ ህጋዊ ነው ሲል ሲሽረው ወደ ገንዘብ ተቀይሮ እንዲከፈል የተወሰነውን የዓመት ዕረፍት ክፍያ ጭምር መሻሩን እንደ ጭብጥ በመያዝ የግራ ቀኙን አስቀርቦ መልስና የመልስ መልስ በማቀባበል እንዲከራከሩ ተደርጓል። ተጠሪ ለአመልካች የዓመት እረፍት ላከፈል እንደሚገባ ሳይክድ በትርፍነት የተከፈላቸውን ገንዘብ እንዲከፍሉ (እንዲመልሱ) በማለት ሲከራከር አመልካች በበኩላቸው የሚፈለግባቸው ገንዘብ የልለና አዲስ ክርክር ላነሳ አይገባም ሲሉ ክርክራቸውን አጠናክረዋል።
በመሆኑም የግራ ቀኙ ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና አግባብነት ካለው ህግ አኳያ አገናዝበን መርምረናል።
በመሆኑም የጉዳዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተጠቀሰውን ሲመስል እኛም ጉዳዩን እንዳየነው አመልካች በወረዳው ፍ/ቤት ከህግ ውጭ ተሰናበትኩ ሲል የዓመት ዕረፍትን ጨምሮ የተለያዩ ክፍያ እንዲከፈላቸው ጠይቀዋል።
በዚሁ መሰረት ግራ ቀኙን በማከራከር ስንብቱ ሕገ ወጥ በመሆኑ የስራ ከህግ ውጭ መሰናበት ውጤት የሆኑት ክፍያ እንዲከፈል ወስኗል።በይግባኝ ሰሚውም ይኸው ውሳኔ ጸንቷል።
በቀጣይነት የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የስር ውሳኔን በመሻር አመልካች የመጋዘን ኃላፊ ሆኖ በሚሰሩበት ወቅት ተደብቆየተገኘ በቆሎ መኖሩ የተረጋገጠ በመሆኑ ድርጊቱ በአዋጅ 377/96 አንቀፅ 27(1(ሐ) ስር የሚወድቅ የማጭበርበር ድርጊት በመሆኑ ስንብቱ ህጋዊ ነው ሲል ወስኗል።
ይህ ችሎትም የክልል ሰበር ሰሚ ችሎት ስንብቱ ህጋዊ ነው ሲል የደረሰበትን ድምዳሜ የሚቀበለው ሲሆን በስር ፍርድ ቤት የተጠየቀው የዓመት ዕረፍት ክፍያ ጥያቄን አስመልከቶ ሳይለይ በጠቅላላ መሻሩ ላታረም የሚገባ ሆኖ አግኝተናል።
በመሰረቱ የዓመት ዕረፍት ክፍያ ሰራተኛ በሥራ ዘመኑ ላጠበቁለት ከሚገቡ መብቶች መሀከል አንዱ ነው። በመሆኑም ይህ ክፍያ የሰራተኛው ውል በህግ ወይም ከህግ ውጭ እንዲሁም ሰራተኛው በራሱ ጊዜ ሲያቋርጥየዓመት ዕረፍትክፍያ ላታለፍበት (ላነፈግ) የሚችል አይደለም።
ይሁን እንጂ ጥያቄው ከሚቀጥለው ሁለት አመት በላይ ላራዘም እንደማይችል በአዋጅ አንቀጽ 79(5) ላይ ተመልክቷል። ይህም የሆነው ሰራተኛው ወደ ገንዘብ ተቀይሮ እንዲሰጠው ከሚጠይቅ ዕረፍቱን በአይነት ወስዶ በተሟላና አካሉን አሳርፎ በአዲስ ሀይል ሥራውን እንዲያከናውን ታስቦ እንደሚሆን ብዙ አያከራክርም። የህጉ አንቀጽ 76(1) ይህንኑ ሲያጠናክር በዚህ ረገድ ሰራተኛው የዕረፍት ጊዜውን ለመተው ላስማማ የማይችል መሆኑን ክልከላ ያስቀመጠው። ወደ ተያዘው ጉዳይ ስንመጣም የክልሉ የሰበር ሰሚ ችሎትም የአመልካችን የአመት እረፍት ክፍያ ውድቅ ያደረገበት ምክንያት ግልፅነት የጐደለው ሲሆንአመልካችም ውሳኔው ቢሻርም በሥር ፍ/ቤትየታመነው የአመት እረፍት ክፍያ የ85 ቀን (5468.5) ብር ላከፈለኝ ይገባል በማለት ይከራከራሉ። ተጠሪም በበኩሉ ይህ ክፍያ ለአመልካች ላከፈል እንደሚገባው በማመን መጠኑን አስመልክቶ የ48 ቀን ብቻ ነው ላከፍለው የሚገባው ሲል መነሻው ግብር ተቀንሶ ላከፍል ይገባዋል በማለት ይከራከራል። እንግዲህ የቀኑን ብዛት አስመልክቶ የተነሳው ክርክር በሥር ፍ/ቤት ጐልቶ መከራከሪያ ሆኖ ያልመጣ በመሆኑ አልተቀበልነውም ልላው ተጠሪ የሚያነሣው ክርክር የዓመት ዕረፍት ክፍያው ግብር ተቀንሶ ላከፈል ይገባል የሚል ነው። በዚሁ ውሳኔ ከፍ ሲል እንደተጠቀሰው የዓመት ዕረፍትን ለሰራተኛው መክፈል የማስፈለጉ አላማ ግልፅ ነው በመርህ ደረጃ በዓይነት የእረፍት ቀናትን ወስዶ እንዲወጣ ነው። በዚህን ጊዜ በህግ የተፈቀደለትን የዓመት ዕረፍቱን ወስዶ ከመውጣት በቀር ልላ ላያሟላ የሚጠበቅበት ነገር የለም። በልላበኩል በተለያዩ በህጉ በተቀመጡት ምክንያቶች የዓመት ዕረፍት ወደ ገንዘብ ተቀይሮ ሲከፈል እንደልሎች ከአሰሪና ሰራተኛ ህጉ የሚመነጩ መብቶች (ክፍያ) የዓመት ዕረፍት ክፍያም የገቢ ግብር ከተቀነሰ በኋላ የሚከፈል ክፍያ መሆኑን ይህ ችሎት የሚቀበለው ሆኖ ተገኝቷል። የገቢ ግብር የአዋጅ ቁ.286/94 እና ደንብ ቁ.78/94 አንቀፅ 3 የዓመት እረፍትን ያለማግለሉ ይህንኑ የሚያጠናክሩ ናቸው። በልላ በኩል አመልካች እንዲከፈላቸው የጠየቁትን የገንዘብ መጠን በሥር ውሳኔ በግልፅ ተጠቅሶ ባይቀመጥም ተጠሪ ለመጠንና ስልት ክርክር ውጭ አመልካች የአመት ዕረፍት ክፍያ የላቸውም የሚል ክርክር አላቀረቡም በመሆኑም በአዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 77፣78 እና 79 በተደነገጉት መሰረት አመልካች ያቀረቡትን የገንዘብ መጠን በልላ ማስረጃ አላስተባበለም።
በአጠቃላይ የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የሥር ውሳኔን ሲሽር የአመልካችን የአመት ዕረፍት ክፍያ ጭምር መሻሩ መሰረታዊ የህግ ሥህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
በመሆኑም የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
የአርሲ ነገል ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 20/12/05 የከፍተኛው ፍ/ቤት በመ/ በቀን 27/01/06 እና የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ በቀን 01/07/06 በማሻሻል ፀንቷል።
አመልካች የጠየቁትን የዓመት ዕረፍት ክፍያ በህጉ መሰረት አስፈላጊው የገቢ ግበር ተቀንሶ ይከፈላቸው ብለናል።
ተጠሪ ለአመልካች በትርፍነት ከወሰዱት ገንዘብ ላመልሱልኝ ይገባል የሚለውን በህግ አግባብ ከመጠየቅ ይህ ውሳኔ አያግድም።
የወጪና ኪሳራ የግራ ቀኙ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ውሳኔ አግኝቷል ይመለስ።