አንድ ባለሙያ በአሰሪው ቁጥጥር ሳይሆን በራሱ የሙያ ኃላፊነት የሙያ አገልግሎት ለመስጠት ከአንድ አሰሪ ጋር ውል ሲኖረው ጉዳዩ የሚገዛው በአሰሪና ሰራተኛ ህግ አዲስ አጠቃላይ ሆስፒታል እና ዶ/ር ምስራቅ ጥላሁን ታህሳስ 21/2007 55 -ከአንድ ባለሙያ ጋር የሙያ ግልጋሎት ውል ያለው አሰሪ ውሉን በማናቸውም ጊዜ ማፍረስ ሥለመቻሉ፣ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 3 ንዑስ አንቀስ /1//2/ የፍ/ህ/ቁ. 2140፣2646/1/፣ 2638/1/ 15. ከአሰሪና ሰራተኛ ክርክር ጋር በተነሳ ማንኛውም የሰራተኛ ክፍያ ጥያቄ ከማናቸውም የክፍያ ወይም የዕዳ ጥያቄ ቅድሚያ የሚኖረው ለሰራተኛ እንጂ ለስራ መሪዎች ስላለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 2(2)(ሐ) (3)፣167
No summary available.
የካቲት 17 ቀን 2007 ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽላት ይመሰል አመልካች፡- አቶ መላከ ሙሉጌታ - ጠበቃ ሙሉጌታ ወንድምአገኘሁ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- አቶ አበበ አቡራ - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ታህሳስ 21 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝና ታህሳስ 28 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ እንደዚሁም የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሰኔ 6 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠውየአፈፃፀም ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዳዩ በአፈፃፀም ሂደት የቀዳሚነት መብት ጥያቄን የሚመለከት ነው።
የፍርድ ባለዕዳ የሆነው ዲማክዶ መስማት የተሳናቸው የተባለ ድርጅት በመክሰስ አመልካችና ተጠሪ የፍርድ ባለመብት ሆነዋል። ተጠሪ የድርጅቱ የሥራ መሪ ስለነበረ በፍትሐብሕር ሕጉ መሰረት የፍትሐብሕር ክስ አቅርቦ የፍርድ ባለመብት ሆኗል። የፍርድ ባለዕዳውንም ንብረት አስቀድሞ በማስከበር በአፈፃፀም እንዲሸጥ አድርጓል። አመልካች በፍርድ ባለዕዳው ላይ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 መሰረት ክስ አቅርቦ የፍርድ ባለመብት ሆኗል። አመልካች በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 167 መሰረትየቀዳሚነት መብት ያለኝ ስለሆነ በቅድሚያ ለእኔ ላከፈለኝ ይገባል የሚል ጥያቄ አንስቷል። የሥር ፍርድ ቤት አመልካችም ሆነ ተጠሪ የፍርድ ባለዕዳው ሰራተኞች በመሆናቸው የቀዳሚነት መብት ያለው ንብረቱን ቀድሞ በአፈፃፀም የሸጠው /ተጠሪ/ ነው በማለት የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቧል። የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ሁለቱም የፍርድ ባለመብቶች የፍርድ ባለዕዳ ሰራተኞች በመሆናቸው ከይግባኝ ባይ /አመልካች/ የቀዳሚነት መብት የለውም በማለት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ትዕዛዝ አፅንቶታል።
አመልካች የፍርድ ባለዕዳው ንብረት ተሽጦ ከተገኘው ገንዘብ በቀዳሚነት ላፈፀምልኝ ሲገባ የበታች ፍርድ ቤቶች በሕግ የተሰጠኝን ልዩ የቀዳሚነት መብት አሳጥተውኛል በማለት የስር አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን ተጠሪ በበኩሉ እኔም የፍርድ ባለዕዳው ተቀጣሪ ሰራተኛ በመሆኔ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡትን አፈፃፀም ትዕዛዝ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክሯል። አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ትዕዛዝ የሕግ መሰረት ያለው ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዳዩን መርምረናል።
ጉዳዩን እንደመረመርነው ተጠሪ የፍርድ ባለዕዳውን ትምህርት ቤት ከስድስት ዓመት በላይ በወር 250 /ሁለት መቶ ሀምሳ የአሜሪካ ዶላር/ እየተከፈለው ያገለገለ መሆኑን፣ ተጠሪ የድርጅቱ የሥራ መሪ በመሆኑም ለፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቄራ ምድብ 2ኛ ፍትሐ ብሕር ችሎት ክስ አቅርቦበመዝገብ ግንቦት 29 ቀን 2004 ዓ.ም የፍርድ ባለዕዳው 12,000 /አስራ ሁለት ሺ የአሜሪካን ዶላር/ እንዲከፍለው ውሣኔ የሰጡለት መሆኑን ተረድተናል። አመልካች በበኩሉ የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቄራ ምድብ የሥራ ክርክር ችሎት ክስአቅርቦ የፍርድ ባለዕዳው ብር 28,173.33 /ሃያ ስምንት ሺህ አንድ መቶ ሰባ ሦሰት ብር ከሰላሳ ሦስት ሣንቲም / ለአመልካች እንዲከፍል በመዝገብ ሐምል 8 ቀን 2005 ዓ.ም ውሣኔ ሰጥቷል።
ከላይ እንደተገለፀው በተጠሪና በፍርድ ባዕዳው መካከል የሥራ ቅጥር ውል መኖሩ ግልፅ ቢሆንም የፍርድ ባለዕዳው አመልካችን የቀጠረው በሥራ መሪነት በርዕሰ መምህርነት እንደሆነ ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት ተረጋግጧል። በልላ በኩል በአመልካችና በፍርድ ባለዕዳው መካከል የነበረው ግንኙነት በአዋጅ ቅጥር 377/1996 መሰረት የተመሰረተ የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት መሆኑ ተረጋግጧል። አንድ የሥራ መሪ የሆነ ሰው በአሰሪው ድርጅት በፍትሐብሕር ሕጉ መሰረት ላከፍለው የሚገባውን ክፍያ እንዲከፍለው ክስ አቅርቦ የፍርድ ባለመብት መሆኑ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 መሰረት አሰሪው የሚያስተዳድራቸው ሰራተኞች በፍርድ እንዲከፈላቸው ያስወሰኑት ክፍያ ከመክፈሉ በፊት ፍርድ ተፈፃሚ ላሆንለት ይገባል ወይስ አይገባም? የሚለው የህግ ጥያቄ መታየት ያለበት ነው።
ይህም ጥያቄ በቅጥር ላይ ከተመሰረተ የሥራ ግንኙነት የሚመነጭ ማናቸውም የሰራተኛ ክፍያ ጥያቄ ከማናቸውም የክፍያ ወይም የዕዳ ጥያቄ ቅድሚያ ይኖረዋል በማለት የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 167 ድንጋጌ አንፃር መታየት ያለበት ነው። በአዋጅ ቁጥር 377/1996 ሰራተኛ ማለት በአዋጅ አንቀጽ 4 በተመለከተው መሰረት ከአሰሪው ጋር በቅጥር ላይ የተመሰረተ የሥራ ግንኙነት ያለው እንደሆነ በአዋጅ አንቀጽ 2 ንዑስ አንቀጽ 3 የተደነገገ ሲሆን የአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 2 ንዑስ አንቀጽ 2/ሐ/ በተገለፁት የሥራ መሪዎች ላይ ተፈሚነት የልለው መሆኑ ተደንግጓል። ከዚህ አንፃር ተጠሪ የሥራ መሪ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 167 የተደነገገው ልዩ የቀዳሚነት መብት የለውም። በመሆኑም ልዩ የቀዳሚነት መብት ያለው በአዋጅ ቁጥር 377/1996 መሰረት ከፍርድ ባለዕዳው ጋር የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ያለው አመልካች እንጅ ተጠሪ አይደለም።
በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች ተጠሪ የቀዳሚነት መብት አለው በማለት የሰጡት የአፈፃፀም ትዕዛዝ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀፅ 2 ንዑስ አንቀጽ 2፣ የአንቀጽ 2 ንዑስ አንቀጽ 2 እና አንቀጽ 167 የሚጥስና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ተሻሽሐል።
በአፈፃፀም የቀዳሚነት መብት ያለው ተጠሪ ነው በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት የውሣኔ ክፍል ተሽሯል።
በአፈፃፀም የቀዳሚነት መብት ያለው አመልካች ነው በማለት በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 167 መሰረት ወስነናል። የፍርድ ባለዕዳው ንብረት ተሽጦ ከተገኘው ገንዘብ፣ አመልካች በቅድሚያ ላከፈለው ይገባል በማለት ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻሉ።
በዚህ ፍርድ ቤት ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.