አንድ ኢንሹራንስ ኩባንያ በውል የመነጨውን ግድታውን በወቅቱባለመወጣቱ ለተከሰተው ተጨማሪ ወጪ ተጠያቂ ላሆን የሚችል ስለመሆኑ የን/ሕ/ቁ 665
No summary available.
ታህሳስ 21 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኸላት ይመሰል አመልካች፡- አዲስ አጠቃላይ ሆስፒታል ጠበቃ አብደላ ዓላ ቀረቡ ተጠሪ፡- ዶ/ር ምስራቅ ጥላሁን ጠበቃ አቶ ስመኘው አራጌ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል
ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሐምል 9 ቀን 2005 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ግንቦት 18 ቀን 2006ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዳዩ የሥራ ውል ከሕግ ውጭ በአሰሪው ተቋርጣል በማለት ያቀረቡትን ጥያቄየሚመለከት ነው።
አመልካች ተከሣሽ ሆኖ ቀርቦ ከከሳሽ/ተጠሪ/ጋር የሥራ ቅጥር ውል ግንኙነት የለንም።ከሳሽ ጋር ያለን ግንኙነት፣ከሳሽ በትርፍ ሰዓታቸው የሙያ ግልጋሎት እየሰጡ ክፍያ የሚያገኙበት የውል ግንኙነት ነው።ተከሳሽ ይህንን በትርፍ ሰዓት የሚሰጥ የሙያ ግልጋሎት ውል አላቋረጠም። ከሳሽ የሙያ ፈቃዳቸውን ከጤና ጥበቃ ሚኒስትር ያላሳደሱ በመሆኑ ፈቃዳቸውን አድሰው ሲቀርቡ ሥራ የሚጀምሩ ፤መሆኑን ተገልፆላቸዋል ከሳሽ በድርጅታችን ውስጥ በቀን ሁለት ሰዓት የሚሰራ ሲሆን በጡረታ የተገለሉ በመሆኑ ከከሳሽ ጋር ቋሚ የሆነ የአሰሪና የሰራተኛ ግንኙነት የላቸውም በማለት ተከራክረዋል።
የሥር ፍ/ቤት ግራ ቀኙ ያቀረቡትን ክርክር ከመረመረ በኃላ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የከሳሽን ስም በመጥቀስ ጥቅምት 5 ቀን 2002 ዓ.ም የፃፈው ደብዳቤና ልሎች የፅሑፍ ሰነዶች በማስረጃነት ያቀረቡለት መሆኑን ጠቅሶ በከሳሽ እና በተከሳሽ መካከል የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት አለ ከሳሽ የተከሳሽን የሥራ ውል ያቋረጠው ከሕግ አግባብ ውጭ ነው በማለት ከሳሽ ለተከሳሽ የሥራ ስንብት ክፍያ የማስጠንቀቂያ ክፍያ የካሣ ክፍያና ክፍያ ለዘገየበት ክፍያና የፅሁፍ ክፍያ እንዲከፍል ውሳኔ ሰጥቶበታል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቧል። የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አፅንቶታል።
አመልካች ግንቦት 28 ቀን 2005 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ተሰጥቷቸው ከአመልካች ዘንድ በቀን ሁለት ሰዓት ብቻ የሚያገለግሉራዲዮሎጂስት ናቸው። ይህ ፍሬ ጉዳይ በተጠሪ አልተካደም ይህም በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀፅ 3 ንዑስ አንቀጽ 2(1) የሚሸፈንና በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የአሰራና እና ሰራተኛ ግንኙነት የልለ መሆኑን የሚያሳይ ሆኖ እያለ የበታች ፍርድ ቤቶች የሥራ ውል አላግባብ ተቋርጧል በማለት የተለያዩ ክፍያዎች እንድከፍል መወሰናቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪ ሐምል 17 ቀን 2005 ዓ.ም በተፃፈ መልስ እኔ በራሴ ኃላፊነት ሳይሆን በአመልካች ኃላፊነትና ቁጥጥር ሥር ሆኜ ሥራ የምሰራ ሰራተኛ ነኝ። ሬዲዮሎጅስት አገልግሎት የሚሰጥበት የሙያ ዘርፍ ነው።
አመልካች ከሚገኘው ደመወዝ በየወሩ የሥራ ግብር 2,433.65(ሁለት ሺ አራት መቶ ሰላሣ ሶስት ብር ከስልሣ አምስት ሣንቲም ) እየቀነሰ ያስቀራል እንጅ በቀን ሁለት ሰዓት መስራት የአመልካችና የእኔን የስራ ውል ስምምነት የሚያሳይ እንጂ የአመልካች ሰራተኛ አለመሆኔን የሚያሳይ አይደለም። ስለዚህ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ ይጽናልኝ በማለት ተከራክረዋል። አመልካች ሐምል 29 ቀን 2006 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የበታች ፍርድ ቤቶች በአመልካችና በተጠሪ መካከል በአዋጅ ቁጥር 377/1996 የሚሸፈን የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት አለ፣ አመልካች ከሕግ አግባብ ውጭ የሥራ ውሉን አቋርጧል በማለት የተለያዩ ክፍያዎች አመልካች ለተጠሪ እንዲከፍል የሰጠው የሕግ መሰረት ያለው ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዳዩን መርምረናል።
ጉዳዩን እንደመረመርነው ተጠሪ “በሬድዮሎጂ” የሕክምና ሙያ የስልጠና በቂ ዕውቀትና ክህሎት ያለውና የደንብ ቁጥር 76/1994 አንቀፅ 20 በሚደነግገው መሰረት በሕግ ሥልጣን ከተሰጠው አካል በሙያው የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለው የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የተሰጠው ባለሙያ መሆኑ በግራ ቀኙ ክርክርና ማስረጃ ተረጋግጧል። ከዚህ በተጨማሪ ተጠሪ ከጥር 1 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ በአመልካች ድርጅት በቀን ለሁለት ሰዓት ያህል በመገኘት ከአመልካች ጋር በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2641 በሚደነግገው መሰረት የሆስፒታል ውል ከተዋዋሉ የአመልካች ደንበኞች የሙያ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ መሆኑና ተጠሪ ለሚሰጠው አገልግሎት አመልካች በየወሩ ብር 8000 /ስምንት ሺ ብር/ክፍያ ሲከፍለው የኖረ መሆኑ በግራ ቀኙ ክርክርና ማስረጃ ተረጋግጧል።
አመልካች እና ተጠሪ ከላይ የተገለፀው አይነት የውል ግንኙነት የነበራቸው መሆኑ አያከራክርም። አከራካሪው ጉዳይ ይኽ በአመልካችና በተጠሪ መካከል ፀንቶ የኖረው ግንኙነት የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ነው ወይስ የዕውቀትና የሙያ ሥራ ለማከራየት የተደረገ የውል ግንኙነት ነው? የሚለው ነጥብ ነው። ይህንን ጭብጥ ለመወሰን በአመልካች ተጠሪና የሕክምና አገልግሎት በሚሰጣቸው ህሙማን /የአመልካች ደንበኞች መካከል የሚኖረውን ግንኙነት መመልከት ያስፈልጋል። ከላይ እንደተገለፀው አመልካች በደንብ ቁጥር 76/94 አንቀጽ 20 እና ተከታይ ድንጋጌዎች መሰረት በሙያው የሕክምና ግልጋሎት ለመስጠት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው ባለሙያ ነው።ከዚህ በተጨማሪ አመልካች የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2140 በሕክምና ባለሙያዎች ላይ የሚጥለው ግድታና በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2646(1) መሰረት ለሚሰጠው አገልግሎት የአመልካች ደንበኛ ከሚከፍለው ክፍያ ተጠሪ ምን ያህል ገንዘብ በወር ላከፈለው እንደሚችል በውል በመስማማት፣ሙሉ በሙሉ በአመልካች ተቆጣጣሪነትና አሰሪነት እየተመደበ ሳይሆን ፣በቀን ለሁለት ሰዓቶች ሙያዊ አገልግሎትየሚሰጥ ባለሙያ መሆኑን የግራ ቀኙ ክርክርና በበታች ፍርድ ቤቶች የተረጋገጡት ፍሬ ጉዳዮች ያሳያሉ።
የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ የተፈፃሚነት ወሰን በዝርዝር የሚደነግገው በአዋጅ ቁጥር 397/96 አንቀፅ 3 ፣ንዑስ አንቀፅ (1) አዋጅ በአሰሪና ሰራተኛ መካከል በሚደረግ በቅጥር ላይ የተመሰረተ የሥራ ግንኙነት ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆን በመርህ ደረጃ ደንግጓል። አዋጅ በዚህ ጠቅላላ መርህ የማይካተቱና የቅጥር ላይ የተመሰረቱ የሥራ ግንኘነቶች በአዋጅ ቁጥር 377 አንቀጽ 3 ንዑስ አንቀጽ 2 በልዩ ሁኔታና በዝርዝር ደንግጓል። የአዋጅ አንቀፅ 3 ንዑስ አንቀፅ 2 ድንጋጌ ቃል በቃል ሲነበብ ‹‹ይህ አዋጅ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት በቅጥር ላይ በተመሰረቱ የሥራ ግንኙነቶች ላይ ተፈፃሚ አይሆንም ›› የሚል ይዘት ያለው ሲሆን በአዋጅ አንቀጽ 3 ንዑስ አንቀጽ 2 በዝርዝር ከተደነገጉ አዋጅ ተፈፃሚነት ከማይሆንባቸው ግንኙነቶች ውስጥ፤አንድ ተዋዋይ ወገን ዋጋ እየተከፈለው በራሱ የንግድ ሥራ ወይም በራሱ የሙያ ኃላፊነት የሚሰራ ስራ የሚያከናውን ሲሆን፣አዋጅ ቁጥር 377/96 ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት የልላቸው መሆኑ በአዋጅ አንቀጽ 3 ንዑስ አንቀጽ 2(1) ተደንግጓል።
ከላይ እንደተገለፀው ተጠሪ ሙሉ በሙሉ በአመልካች መሪነትና ቁጥጥር ሣይሆን በአመልካች ድርጅት ውስጥ በቀን ለሁለት ሰዓት ያክል ከአመልካች ጋር የሆስፒታል ውል ለተዋዋሉ የአመልካች ደንበኞች የራድዮሎጅ የሙያ ግልጋሎት በራሱ የሙያ ኃላፊነት የሚሰጥ ነው። አመልካች ተጠሪ ይህንን የሙያ ግልጋሎቱን ልላ ቦታ የሚገኝ የህክምና ተቋም ወይም ከአመልካች ጋር ምንም አይነት የሆስፒታል ውል ግንኙነት ለልላቸውና የአመልካች የህክምና ካርድ ላልያዙ ሰዎች እንዲሰጥናየሥራ ስምሪት መስጠትና አመልካችን ተቆጣጥሮ ማሰራት አይችልም። ከዚህ በተጨማሪ ተጠሪ የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 61 እና ተከታታይ ድንጋጌዎች መሰረት በቀን ሥምንት ሰዓት በሣምንት አርባ ሥምንት ሰዓት ከሥራ ቦታ እንዲገኝ ለማስገደድና ተቆጣጥሮ ማሰራት እንደማይችል የግራ ቀኙ ክርክርና ከበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ ተረድተናል።
የሥር ፍ/ቤት ተጠሪ በቀን ለሁለት ሰዓት ብቻ አገልግሎት መስጠቱ፤ ከአመልካች ጋር በአዋጅ ቁጥር 377/96 የሚሸፈን የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ከመመስረት አይገድበውም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። ሆኖም ይህ የስር ፍርድ ቤት የሰጠው የሕግ ትርጉምና ውሳኔ የአዋጅ ቁጥር 377/1996 ከአንቀፅ 61 እስከ አንቀፅ 64 የተደነገጉትን ድንጋጌዎች ይዘትና ውጤት ያገናዘበ ካለመሆኑም በላይ ፣በአዋጅ አንቀጽ 65 ልዩ ድንጋጌ ያገናዘበ ሆኖ አላገኘነውም። በአዋጅ አንቀጽ 65 መሰረት በሥራ ውሉ ወይም በህብረት ስምምነት በልላ አኳኃን ካልተወሰነ በስተቀር ፣የአዋጁ የስራ ሰዓት የሚመለከቱት ከአንቀጽ 61 እስከ አንቀጽ 64 የተደነገጉት ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት የማይኖራቸው በንግድ መልዕክተኞች በንግድ ወኪሎች ላይ እንደሆነ በግልፅ ተደንግጎአል። ከዚህ አንፃር የሥር ፍርድ ቤት የአዋጅ የሥራ ሰዓት ድንጋጌዎች ተጠሪ የአመልካች ቅጥር ሰራተኛ ነው ብሎ ለመወሰን ተፈፃሚነት እንደልላቸው በመግለፅ የሰጠው ትርጓሜ የአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀፅ 65 ልዩ ድንጋጌ ያላገናዘበና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ከላይ በዝርዝር የተገለፁት ምክንያቶች ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 3 ንዑስ አንቀፅ 2/1) መሰረት ከአመልካች ቁጥጥርና የሥራ አለመረዳት ሣይገደብ በራሱ የሙያ ኃላፊነት በቀን ለሁለት ሰዓት የራዲዮሎጅ የሙያ አገልግሎት የሚሰጥ ባለሙያ እንጅ የአመልካች ሰራተኛ አይደለም። ተጠሪ ለአመልካች የሚሰጠው የእውቀት ግልጋሎት እና ሥራ ውል በመሆኑ አመልካች በማናቸውም ጊዜ ውሉን ለማፍረስ የሚችል መሆኑን በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 2638 ንዑስ አንቀጽ 1 ተደንግጓል። ይህም በመሆኑ አመልካች አግባብነት ያለውንና ተፈፃነሚነት ያለውን የህግ ድንጋጌ መሰረት በማድረግ አለኝ የሚለውን መብትና ጥቅም ከሚጠይቅ በስተቀር ተጠሪ የአዋጅ ቁጥር 377/1996 ድንጋጌዎች መሰረት የተለያዩ ክፍያዎች እንዲከፍለው የመጠየቅ መብት የለውም ።
በመሆኑም የበታች ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ከላይ በዝርዝር የጠቀስናቸውን የሕግ ድንጋጌዎች የሚጥስና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሳኔ ተሸሯል ።
ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 3 ንዑስ 2(1) መሰረት በራሱ የሙያ ኃላፊነት በቀን ለሁለት ሰዓት የሙያ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ የአመልካች ቅጥር ሰራተኛ ሣይሆን የዕውቀት ሥራና ግልጋሎት ለመሰጠት የተዋዋለ ባለሙያ ነው በማለት ወስነናል።
አመልካች ከተጠሪ ጋር የነበረውን የሙያ (ዕውቀት)ሥራ ግልጋሎት ውል ያቋረጠው በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2637 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት ነው በማለት ወስነናል።
ይኽ ውሣኔ ተጠሪ የሙያ ግልጋሎት ውሉ በመቋረጡ ምክንያት አለኝ የሚለውን የመብት ጥያቄ ከማቅረብ የሚገድበው አይደለም ብለናል።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጣውን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻሉ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።