አንድ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት (ሰበር ሰሚ ችሎት )የሥር ፍ/ቤት ጉዳዮን አግባብነት ባላቸው ማስረጃዎች ሁሉ አጣርቶ እንዲወስን ብሎ አንድን ጉዳይ ሲመልስ ስለማስረጃ አቀራረብ በህጉ የተመለከቱትን ድንጋጌዎችን ሁሉ ባላገናዘበ መልኩ ማስረጃ ይቅረብ ማለት ስላለመሆኑ፡ለአንድ ጉዳይ አግባብነት ያላቸው ማስረጃዎች መቅረብ ያለባቸው ለህጉ የተዘረጋውን ሥርዓት ጠብቀው ላሆን የሚገባ ስለመሆኑና ተገቢውን የማስረጃ አቀራረብ ሥርዓት ሳይጠብቅ የሚቀርብ ማስረጃ ግን ዋጋ ላሰጠው የማይገባና ውድቅ ላደረግ የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 137(3) እና 256
No summary available.
ጥቅምት 28 ቀን 2007 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽላት ይመስል አመልካች፡- ወ/ሮ ሐዋ በከር አቶ ጀማል የሱፍ ቀረቡ ተጠሪ፡-
ጉዳዩ የቀረበው አመልካች በሐዋ በከር የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችሎት በመዝገብ ጥቅምት 18 ቀን 2006 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይወሰንልኝ በማለት የሐዋ በከር ጠበቃ ነኝ በማለት አቶ ራጅ ገመቹ በአመልካች ስም ፅፈውና ፈርመው ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዳዩ በመጀመሪያ የታየው በሐሮማያ ወረዳ ፍርድ ቤት ነው። የአውዳይ ፍርድ ቤት ጥር 30 ቀን 2004 ዓ.ም በሀዋ በከር ስም የቀረበለት ክስ ላይ የተከሳሾችን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ ተከሳሾች በከሳሽ የይዞታ ቦታ ላይ ግንባታ በማከናወን ሁከቱ የፈጠሩበት ስለሆነ ሀከቱ እንዲወገድ በማለት በመዝገብ ታህሣሥ 15 ቀን 2005 ዓ.ም. ውሣኔ ሰጥቷል።
ተጠሪዎች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለምስራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል። ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካችን (ሀዋ በከርን) በመልስ ሰጭነት በመሰየምና መልስ ሰጭ በወኪሐ በኩል መልሷንና ክርክሯን እንዳቀረበች በማስፈር የወረዳው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በመዝገብ ግንቦት 19 ቀን 2005 ዓ.ም. በሰጠው ውሣኔ አፅንቶታል። ተጠሪዎች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበዋል። የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችሎት ሀዋ በከርን በተጠሪነት በመሰየምና ተጠሪ በወኪል በኩል እንደተከራከረች በውሣኔው ውስጥ በማስፈር የወረዳው ፍርድ ቤትና የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ ሽሮታል።
ይህንን ውሣኔ በማስለወጥ በሀዋ በከር ስም ህዳር 30 ቀን 2006 ዓ.ም. የተፃፈ የሰበር አቤቱታና መጋቢት 15 ቀን 2006 ዓ.ም. የተፃፈ የመልስ መልስ ለዚህ ሰበር ችሎት ጠበቃው ራጅ ገመቹ ያቀረቡ ሲሆን ሐምል 15 ቀን 2006 ዓ.ም ሀዋ በከር በህይወት የልለች መሆኑ ለፍርድ ቤቱ በመግለፅ፣የሀዋ በከር ወራሽ የወራሽነት ማስረጃውን እንዲያያይዙ ትዕዛዝ ተሰጥቷል። በዚህ ትዕዛዝ መሰረት አቶ ጀማል ዮሱፍ ጥቅምት 12 ቀን 2007 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የሃረሚያ ወረዳ ፍርድ ቤት በመዝገብ መጋቢት 6 ቀን 2004 በተፃፈ መሸኛ ሀዋ በከር ህዳር 15 ቀን 2004 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለየች መሆኑን በማረጋገጥ የሰጠውን ፍርድና የወራሽነት ማስረጃ ቀርቧል።
ተጠሪዎች በበኩላቸው ለወረዳው ፍርድ ቤት ክስ የቀረበውና እስካሁን ክርክሩ በሀዋ በከር ስም የቀጠለው ሟች ከሞተች በኋላ በመሆኑ ጉዳዩ ላሰረዝልን ይገባል በማለት ጥቅምት 18 ቀን 2007 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ ጠይቀዋል።
ይህችሎትሀዋበከር ህዳር 15 ቀን 2004 ዓ.ም በሞት ከተለየች በኋላ በሀዋ በከር ስም ከወረዳ ፍርድ ቤት ጀምሮ እስከ ሰበር እንድት ክርክር እንደ ቀረበ ለማጣራት ግራ ቀኙን በቃል እንዲከራከሩ በማድረግ አጣርቷል። ጠበቃው አቶ ራጅ ገመቹ በመጀመሪያ ፋይሉን የከፈተው ጀማል ዮሱፍ ነው። እኔ ክርክሩ ከተጀመረ በኋላ ነው ጉዳዩን የያዝኩት በማለት መልስ የሰጠ ሲሆን አቶ ጀማል ዮሱፍ በሟች ስም ለወረዳው ፍርድ ቤት ክስ ያቀረብኩት እኔ ነኝ። ባለማወቅ ነው ክሱን ያቀረብኩት በማለት መልስ ሰጥቷል።
አጠቃላይ የጉዳዩ አመጣጥ ከላይ የተገለፀ ሲሆን፤ እኛም ጉዳዩን እንደመረመርነው በሀዋ በከር ስም ከወረዳ ፍርድ ቤት ጀምሮ እስከ እዚህ ሰበር ችሎት ክርክር ሲደረግ የነበረው ሀዋ በክር ከዚህ አለም በሞት ከተለየች ከህዳር 15 ቀን 2004 ዓ.ም በኋላ ነው። ሀዋ በከር በህይወት እያለች ለአቶ ጀማል ዮሱፍ የሰጡት ውክልና ሀዋ በከር ህዳር 15 ቀን 2004 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በኋላ ውጤት እንደማይኖረውበፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 2232(1) ተደንግጓል። ከዚህ አንፃር ጀማል ዮሱፍ ሟች ሀዋ በከር በሕይወት እያለች የሰጠችውን ውክልና በመጠቀም ጠበቃ ወክሎ ሟች በህይወት እንዳለች በማስመሰል ለወረዳው ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስና ክፍያ ከዚያም በኋላ በይግባኝና በሰበር ያቀረበው ክርክር የሞተችው ሀዋ በክር በህይወት እያለች ሆኖ የቀረበ፣እስከ ሐምል 15 ቀን 2006 ድረስ ለልሎች ፍርድቤቶችም ሆነ ለዚህ ችሎት ያልተገለፀና፣ ሀዋ በክር በህይወት እንዳለች ጀማል ዮሱፍ ወኪሐ እንደሆነና ወኪሐ ደግሞ ጠበቃ እንደወከለ ተደርጐ የቀረበ መሆኑን በመዝገቡ የቀረቡ ውሳኔዎችንና ልሎች ክርክሮችን በመመርመር ተገንዝበናል።
በአንድ ሰው ስም ፍርድ ቤት ቀርቦ ክስ ለማቅረብና ለመከራከር የሚችለው ዋናውባለጉዳይ ወይም ለዋናው ባለጉዳይ የወኪልነት፣የጠበቃነት ወይም የነገረ ፈጅነት ሥልጣን ያለው ሰው እንደሆነ የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 57 ይደነግጋል።በያዝነው ጉዳይ ጀማል የሱፍ የሟች ወራሽ መሆኑን ገልፆ በወራሽነቱ ያቀረበው ክስና ክርክር የለም።ጀማል የሱፍ ሀዋ በከር በህይወት እያለች የሰጠችውን የውክልና ሰነድ በመጠቀም የሀዋ በከር ወኪል በመሆንና ጠበቃ በመቅጠር በሀዋ በከር ሥም ሟች ከሞተች በኃላ ክስ አቅርቧል።ይህም ጀማል የሱፍ ሀዋ በከር በመሞቷ ምክንያት የተሰጠው የውክልና ሥልጣን ቀሪ ከሆነ በኃላ በወኪልነት ሥልጣኑ በመጠቀም ጠበቃ ያቆመ በመሆኑና ጠበቃውም ሀዋ በከርን በመወከል ጠበቃ ለመወከል ሥልጣን በልለው ሰው ተወክሎ ክርክሩ ያቀረበ በመሆኑ ከወረዳው ፍርድ ቤት ጀምሮ በሀዋ በከር ስም እስከዚህ ችሎት ያቀረቡት ክርክር የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2232/1/ እና የፍታሐብሕር ሥነ -ሥርዓት ሕግ ቁጥር 57 ድንጋጌዎችን የሚጥስና ህጋዊ ዕውቅናና ውጤት ላሰጠው የማይገባው ነው።
በመሆኑም ህዳር 15 ቀን 2004 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት በተለየችው ሀዋ በከር ስም ለሥር ፍርድ ቤት የቀረበ ክስና ከዚያም በኃላ ፍርድ ቤቶቹ ሀዋ በከር በህይወት እንዳለች በመገመትና በውሣኔያቸው በመግለፅ የሰጡት ውሣኔና ህጋዊ ዕውቅና ውጤት ላሰጠው የማይገባ በመሆኑ በአመልካች ስም የቀረበውን ክርክርና የተሰጠውን ውሣኔ ሙሉ በሙሉ ሰርዘናል።
ው ሣ ኔ
ክሱ የተጀመረውና እስከዚህ ሰበር ችሎት ክርክሩ የተደረገው ሀዋ በከር ህዳር 15 ቀን 2004 ዓ.ም በሞት ከተለየች በኃላ በሀዋ በከር ስም በመሆኑ ይህም የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2232/1 እና የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 57 ድንጋጌን የሚጥስ በመሆኑ በሟች ሀዋ በከር ስም የቀረበውን ክርክርና በየደረጃው ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ ሙሉ በሙሉ ተሰርዟል።
ሀዋ በከር በሞት ከተለየች በኃላ በስሟ የቀረበው ክስ፣ክርክር እንዳልቀረበና በየደረጃው የተሰጡት ፍርዶች ሁሉ እንዳልተሰጡ ይቆጠራሉ ብለናል።
በሞት በተለየችው ሃዋ በከር ሥም ክርክር በማቅረብ በተጠሪዎች ላይ ለደረሰው መጉላላትና ኪሣራ አቶ ጀማል የሱፍ ብር 2000/ሁለት ሺ ብር/ ኪሣራ ተጠሪዎች ይክፈል በማለት ወስነናል።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.