በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 74(2) መሰረት ፍ/ቤቱ የተዘጋን የይግባኝ አቤቱታን እንደገና ስለሚያይበት እነ ወ/ሮ ብዙ ሰንበታ (ሁለት ሰዎች) እና አቶ ታደሰ ሰንበታ
No summary available.
30/01/2007 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አልማው ወል ሡልጣን አባተማም መኮንን ገ/ሕይወት ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ አመልካቾች፡-
በዚህ መዝገብ አመልካቾች የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ይግባኙ ላሰማ በተቀጠረበት ዕለት በቀጠሮው ሰዓት ለመድረስ ያልቻሉት ለጠበቃቸው የሰጡት የውክልና ስልጣን ማስረጃ በእጃቸው በመቅረቱ እና የሚመጡትም ከርቀት አካባቢ በመሆኑ ምክንያት መንገድ በመዘጋጋቱ በመሆኑ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 73 መሰረት የተዘጋው የይግባኝ መዝገብ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 74(2) መሰረት ተከፍቶ እንዲታይላቸው ያቀረቡት አቤቱታ በበቂ ምክንያት ላይ የተመሰረተ ባለመሆኑ ተቀባይነት የለውም በማለት በኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ተሰጥቶ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሰበር ችሎት በውሳኔ የጸናው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ላታረም ይገባል በማለት ነው።
የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ጉዳይ አመልካቾቹ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በነበራቸው ክርክር መዝገቡ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ አመልካቾቹ በዚያኑ ቀን በ4፡30 ሰዓት በፍርድ ቤቱ የደረሱ መሆናቸውን እና በሰዓቱ ለመድረስ ያልቻሉትም በመንገድ ስራ ምክንያት መንገድ በመዘጋጋቱ መሆኑን ገልጸው በሚከራከሩበት ሁኔታ አመልካቾቹ ያቀረቡት ምክንያት በቂ ምክንያት የሚባል አይደለም በማለት የስር ፍርድ ቤቶች የአመልካቾቹን አቤቱታ ውድቅ የማድረጋቸውን አግባብነት "በቀዳሚው ቀነ ቀጠሮ ሳይቀርብ የቀረው በቂ ሆኖ በሚገመት እክል ምክንያት መሆኑን ፍርድ ቤቱ የተረዳው እንደሆነ" በሚል በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 74(2) ስር ከተመለከተው ሐረግ ይዘት እና ተፈጻሚነት አንጻር ተጠሪው ባሉበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዳዩ ለሰበር ክርክር እንዲቀርብ በመደረጉ ተጠሪ መልስ እንዲሰጡ የተላከላቸውን መጥሪያ ፈርመው ለመቀበል ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸው በስርዓቱ መሰረት በመረጋገጡ የመከራከር መብታቸው እንዲታለፍ ተደርጓል። የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር መርምረናል።
በዚህም መሰረት የአሁኖቹ አመልካቾች ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ይግባኝ ሳቢያ የግራ ቀኙን የይግባኝ ክርክር ለመስማት ለ18/03/2005 ዓ.ም. ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ተይዞ በነበረው ቀጠሮ በይግባኝ ባዮቹ በኩል የቀረበ ሰው ባለመኖሩ ተጠሪው ያቀረቡትን ክርክር በመቀበል ፍርድ ቤቱ መዝገቡን በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 73 መሰረት የዘጋው መሆኑ፣አመልካቾቹ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ቀርበው በሰዓቱ በቀጠሮ ላገኙ ያልቻሉት ለጠበቃቸው የሰጡት የውክልና ስልጣን ማስረጃ በእጃቸው በመቅረቱ፣የሚመጡትም ራቅ ካለ አካባቢ በመሆኑ እና አዲስ አበባ ከተማ ከገቡ በኃላም ፍርድ ቤቱ የሚገኝበትን አካባቢ እና የታክሲ መያዣ ቦታውን በትክክል ባለማወቃቸው መሆኑንበመግለጽ መዝገቡ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 74(2) መሰረት ተከፍቶ ክርክሩ እንዲቀጥል ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው በጽሁፍ የጠየቁ መሆኑ በክርክሩ የተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች ሲሆኑ ፍርድ ቤቱ በአቤቱታቸው ላይ የልላኛውን ተከራካሪ ወገን አስተያየት ከተቀበለ በኃላ መዝገቡ ተከፍቶ ክርክሩ እንዲቀጥል አመልካቾቹ ያቀረቡትን ጥያቄ ሳይቀበል የቀረው ይዘቱ ከላይ የተመለከተው በአመልካቾቹ በኩል የቀረበው ምክንያት በቂ ላባል የሚችል አይደለም በማለት ነው።
በመሰረቱ በአንድ ነገር ክስ ያቀረበ ሰው ክርክሩ እንዲሰማ በተወሰነው ቀነ ቀጠሮ ሳይቀርብ የቀረ እንደሆነ እና ተከሳሹ ቀርቦ የተከሰሰበትን ነገር በሙሉም ሆነ በከፊል ያመነ እንደሆነ ከሳሹ በልለበትም ቢሆን ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ በሙሉ ወይም በከፊል ላመነው ጉዳይ የፍርድ ውሳኔ ለመስጠት እንደሚችል እና ከሳሹ የካደ እንደሆነ ግን መዝገቡን በመዝጋት እንደሚያሰናብተው በፍትሐብሄር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 73 ላይ የተመለከተ ሲሆን ይህ ድንጋጌ በይግባኝ ክርክር ጉዳዮች ላይ ጭምር ተፈፃሚነት ያለው መሆኑም በቁጥር 32(2) ድንጋጌ ተመልክቷል። በልላ በኩል በቀነ ቀጠሮው ሳይቀርብ የቀረበትን ምክንያት በመግለጽ ይግባኝ ባዩ መዝገቡ በተዘጋ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ መዝገቡ ተከፍቶ ክርክሩ እንዲቀጥል ጥያቄውን ለፍርድ ቤቱ ላያቀርብ የሚችል ስለመሆኑ እና ይግባኝ ባዩ በቀዳሚው ቀነ ቀጠሮ ሳይቀርብ የቀረው በቂ ሆኖ በሚገመት እክል ምክንያት መሆኑን ፍርድ ቤቱ የተረዳው እንደሆነ ስለኪሳራው እና ስለ ማናቸውም ወጪ አከፋፈል ተስማሚ መስሎ የታየውን ውሳኔ ከሰጠ በኃላ የተዘጋው መዝገብ እንደገና ተከፍቶ ነገሩ እንዲቀጥል ትዕዛዝ መስጠት የሚችል ስለመሆኑ በቁጥር 74(2) ተደንግጓል።እንደሚታየው ይህ ድንጋጌ ይግባኝ ባዩ በቀነ ቀጠሮው ሳይቀርብ የቀረበት ምክንያት በቂ ሆኖ የሚገመት እክል መሆን እንደሚገባው ከመግለጽ ውጪ በቂ ሆኖ በሚገመት እክል ውስጥ የሚካተቱት ሁኔታዎች ምን ምን እንደሆኑ የሚጠቁመው ነገር የለም።ይህም በዚህ ረገድ የሚቀርብላቸውን አቤቱታ ከድንጋጌው ይዘት እና ዓላማ አንጻር መርምሮ ተገቢውን ዳኝነት የመስጠት ኃላፊነት የፍርድ ቤቶች መሆኑን የሚያመለክት ነው።
በተያዘው ጉዳይ አመልካቾቹ ጉዳዩ እንዲንቀሳቀስላቸው አቤቱታ ያቀረቡት መዝገቡ በተዘጋ አንድ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መሆኑ እና ለጠበቃቸው የውክልና ስልጣን የሰጡትም ቀጠሮው ከመድረሱ ከስምንት ቀናት በፊት በ10/03/2005 ዓ.ም. በወልመራ ወረዳ ፍትሕ ጽ/ቤት በኩል መሆኑ ተረጋግጧል።አመልካቾቹ ለጠበቃቸው የሰጡት የውክልና ስልጣን ማስረጃም በእጃቸው የቀረ መሆኑን በመግለጽ የተከራከሩ ሲሆን በአንጻሩ የውክልና ስልጣን ማስረጃው አስቀድሞ ለጠበቃቸው ተሰጥቶ የነበረ ስለመሆኑ በተጠሪው በኩል የቀረበ ክርክር እና ማስረጃ የለም።የስር ፍርድ ቤቶች አመልካቾቹ ያቀረቡት ምክንያት በቂ ላባል የሚችል አይደለም ከማለት ውጪ በቂ ተደርጎ ላወሰድ ያልቻለው በምን ምክንያት እንደሆነ በውሳኔአቸው ላይ በግልጽ አላሰፈሩም።
በዚህ ሁኔታ የሚሰጥ ውሳኔ ደግሞ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 182(1) ስር በአስገዳጅነት የተቀመጠውን የውሳኔ አሰጣጥ ስርዓት የተከተለ ባለመሆኑ ሕጋዊ ተቀባይነት ላሰጠው የሚገባ አይደለም። ይልቁንም አመልካቾቹ ጉዳዩ እንዲንቀሳቀስላቸው አቤቱታ ያቀረቡት
በመከታተል ላይ የነበሩ መሆኑን እና በሰዓቱ በቀጠሮው ሳይገኙ የቀሩትም በቂ ሆኖ በሚገመት እክል ምክንያት መሆኑን መገንዘብ የሚያስችል በመሆኑ አመልካቾቹ መዝገቡ ተከፍቶ ክርክሩ እንዲቀጥል ያቀረቡት አቤቱታ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 74(2) መሰረት ሕጋዊ ተቀባይነት ላሰጠው ይገባ እንደነበረ ከክርክሩ አጠቃላይ ይዘት መገንዘብ ይቻላል።ሲጠቃለል በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 73 መሰረት የተዘጋው የይግባኝ መዝገብ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 74(2) መሰረት ተከፍቶ እንዲታይላቸው አመልካቾቹ ያቀረቡት አቤቱታ በበቂ ምክንያት ላይ የተመሰረተ ባለመሆኑ ተቀባይነት የለውም በማለት በኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ተሰጥቶ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሰበር ቸሎት በውሳኔ የጸናው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
የተዘጋው የይግባኝ መዝገብ ተከፍቶ ክርክሩ እንዲቀጥል አመልካቾቹ ያቀረቡት አቤቱታ በበቂ ምክንያት ላይ የተመሰረተ ባለመሆኑ ተቀባይነት የለውም በማለት በኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ በ09/04/2005 ዓ.ም. ተሰጥቶ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሰበር ችሎት በመዝገብ በ13/01/2006 ዓ.ም. በውሳኔ የጸናው ትዕዛዝ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
አመልካቾቹ በሰዓቱ በቀጠሮው ሳይገኙ የቀሩት በቂ ሆኖ በሚገመት እክል ምክንያት መሆኑን መገንዘብ የተቻለ በመሆኑ መዝገቡ ተከፍቶ ክርክሩ እንዲቀጥል ያቀረቡት አቤቱታ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 74(2) መሰረት ሕጋዊ ተቀባይነት ላሰጠው የሚገባው ነው በማለት ወስነናል።
መዝገቡን አንቀሳቅሶ ክርክሩን ቀጥሎ በመስማት ተገቢውን ውሳኔ ይሰጥበት ዘንድ ጉዳዩ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት እንዲመለስ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 341(1) መሰረት ወስነናል።
በዚሁ መሰረት መፈጸም ያስችለው ዘንድ የውሳኔው ግልባጭ ለኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይላክ።
የሆነው መዝገብ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይመለስ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ አመልካቾች የራሳቸውን ይቻሉ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.