ተከራካሪ ወገኖች ለፍ/ቤት የሒሳብ አጣሪ ይሾምልን የሚል አቤቱታ ሲያቀርቡ በሒሳብ አጣሪዎች ሪፖርት አለመስማማት ቢኖር እንኳ ጉዳዩ የንግድ ህጉንና የፍትሐብሕር ሥነ-ስርዓቱን መሰረት በማድረግ ውሣኔ በዛው በኩል እንደሚሰጥ በግልጽ ከተስማሙ ይህ ግልጽ ስምምነት ባለበት ሁኔታ የሒሳብ አጣሪዎች የስራ ክንውን ግድፈት አለበት በማለት ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት የሚያቀርቡበት የአቶ አበበ ክብረት ሚስትና ወራሾች እና አቶ ነጋ ቦንገር (አስር ሰዎች) ጥቅምት 25/2007 5 ምክንያት የልለ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 277(1)(2) ፣የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 3312 3. በህግና በሚመለከተው መንግስት አካል እውቅና የተቋቋሙ ማህበራት የተቋቋሙበትን ዓላማ ለማሳካት፣የአባላታቸውን መብትና ጥቅም ለማስከበርፍ/ቤት፣ለግልግል ተቋም ወይም ለልሎች የዳኝነት ሥልጣን ለተሰጣቸው አካላት የዳኝነት ጥያቄ የማቅረብ መብት ያላቸው ስለመሆኑ፣ የፍትሐ ብሕር ህግ ቁጥር 454(1) የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 35 አዋጅ ቁጥር 62/2001 አንቀፅ 55፣110
No summary available.
ጥር 19 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽላት ይመስል አመልካች፡- ሮፓክ ነዋሪዎች ልማት ማህበር - ጠበቃ አቶ ማርሻል ፍቅረ ማርቆስ ቀረቡ ተጠሪ፡- ሮፓክ ኢንተርናሽናል ኃላፊነቱ የተወ.የግል ማህበር -ጠበቃ አቶ ያለለት ተሾመ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥር 30 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔና የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት መዝገብ ሚያዝያ 22 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዳዩ በመጀመሪያ የታየው በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ነው።
በስር ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። ጉዳዩ የግልገል ዳኛ እንዲሰየም ትእዛዝ ይስጥልኝ በሚል መንገድ የቀረበ የዳኝነት ጥያቄ ነው።
የክርክሩ መነሻ አመልካች ለስር ፍርድ ቤት ያቀረበው ማመልከቻ ነው። ከሳሽ (አመልካች) ተከሳሽ(ተጠሪ) ከአባላቱ ጋር በተለያየ ጊዜ በተዋዋለው የመኖሪያ ቤት ግንባታ ውል ቤቶቹ ለሚሰሩበት መንደር የመሰረተ ልማት ግንባታና ልማት ስራ ለማከናወን ለነዋሪዎቹ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግየውል ግድታ ገብቷል። ሆኖም ተከሳሽ (ተጠሪ) በውሉ በገባው ግድታ መሰረት የመሰረተ ልማት ግንባታ እንዲያከናውን ሲጠየቅ፤የግንባታ ስራውን ለመስራት ፍቃደኛ አልሆነም።ተከሳሽ ከከሳሽ አባላት ጋር ባደረገው ውል በአፈፃፀም ሂደት የሚፈጠር አለመግባባት ለግልግል ዳኛ የሚቀርብ ስለመሆኑ ተመልክቷል። ሆኖም ተከሳሽ የግልግል ዳኛ እንድንሰይም ባቀረባቸው ጥያቄ መሰረት የግልግል ዳኛ ለመሰየም ፍቃደኛ ባለመሆኑ ፍርድ ቤት ተከሳሽ የግልግል ዳኛ እንዲሰይምና ስብሳቢ ዳኛ ላሰየም በሚችልበት ሁኔታ ትእዛዝ እንዲሰጥልኝ በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ በተከሳሽነት ቀርቦ፤ ከከሳሽ (አመልካች) ጋር ያደረኩት የውል ግንኙነት የለም። ከሳሽ አባላቱን ለመወከል በግልግል ጉባኤ ለመከራከር የሚያስችለው ልዩ ውክልና በአባላቱ አልተሰጠውም። ከሳሽ በተከሳሽ ላይ ክስ ለማቅረብ የሚያስችለው መብትና ጥቅም ወይም የውክልና ስልጣን የለውም። ስለዚህ ከሳሽ ያቀረበውን ክስ ውድቅ በማድረግ እንዲያሰናብተኝ በማለት ተከራክሯል። የስር ፍርድ ቤት የተከሳሽን መቃወሚያ ውድቅ በማድረግና ከሳሽ የተቋቋመበት አላማ በተከሳሽ ላይ ክስ ለማቅረብ የሚያስችለው በመሆኑ ተከሳሽ የግልግል ዳኛ እንዲሰይም በማለት ትእዛዝ ሰጥቷል።
ተጠሪ የስር ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቧል። የሥር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙ ክርክር ከሰማ በኃላ መልስ ሰጭ(አመልካች) አባላቶችን በመወከል ክስ ለማቅረብ የሚያስችለው የውክልና ማስረጃ ያላቀረበ በመሆኑ፤
ይግባኝ ባይ (ተጠሪ) የግልግል ዳኛ እንዲሰይም ጥያቄ ለማቅረብ አይችልም በማለት የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ ሽሮታል። አመልካች ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በሰጠው ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቅርቧል። ይግባኝ ሰሚው ችሎት የአመልካች ይግባኝ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 377 መሰረት ሰርዞታል።
ተጠሪ በበኩሉ አመልካች በተጠሪ ላይ የግልግል ዳኛ እንዲሰየምለት ጥያቄ ለማቅረብ የሚያስችለው ውክልና ወይም ከሕግ ወይም ከውል የመነጨ መብትና ጥቅም የልለው በመሆኑ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችሎት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም የሚል ይዘት ያለው መልስ ሐምል 22 ቀን 2006 ዓ/ም በፅሁፍ አቅርቧል። አመልካች ነሐሴ 13 ቀን 2006 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና ግራ ቀኙ ለዚህ ችሎት ያቀረቡትን የፅሁፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችሎት አመልካች ለተጠሪ የግልግል ዳኛ እንዲሰይም ክስ ለማቅረብና ለመጠየቅ የሚችልበት ሕጋዊ ምክንያት የለም በማለት የሰጡት ብይን (ውሳኔ) የህግ መሰረት አለው ወይስ የለውም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዳዩን መርምረናል።
ከላይ የተያዘውን ጭብጥ ለመወሰን በመጀመሪያ አመልካች ህጋዊ ህልውና ሲያገኝ ላያሳካቸው የሚችላቸው መሰረታዊ ዓላማዎችና አመልካች አላማዎቹን ለማሳካት ላፈፅማቸው ስለሚችላቸው ህጋዊ ተግባራት መመርመር አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
ጉዳዩን እንደመረመርነው አመልካች በኦሮሚያ ክልል በፊንፍኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ ሮፓክ ቀበል ውስጥ በሚኖሩ ሰዎች የተመሰረተና የአካባቢ ብክለትና የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል፤ጎርፍለመከላከል፤ የአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ ስራ ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር፤ የልማት ስራ የመስራትና የመሰረተ ልማትና የማህበሩ የአገልግሎት ተቋማት በፕላን መሰረት መገንባታቸውን በአባላቶቹ ስም ለመከታተልና ይህ ግድታ ያለበት ሶስተኛ ወገን በሕጉ መሰረት ግድታውን እንዲወጣ ለማድረግ በአባላቱ ስም አስፈላጊውን ለመፈጸም ለማስፈፀምና ልሎች አላማዎችን ለማሳካት የተቋቋመ ማህበር መሆኑን ከማህበሩ መመስረቻ ፅሑፍ አንቀጽ 5 የተዘረዘረ መሆኑን የበታች ፍርድ ቤቶች ከሰጡት ውሳኔና ግራ ቀኙ ካቀረቡት ክርክር ይዘት ለመረዳት ችለናል።
ይህም ከተጠሪ ጋር በተናጠል የቤት ግንባታና የማዘዋወር ውል የተዋዋሉ ግለሰቦች፣ተጠሪ በተናጠል በገባላቸው የውል ግድታ በአንቀጽ 1 በተደነገገው መሰረት የመሰረተ ልማት ተቋማትን የመገንባትና የአገልግሎት ሰጭ ማዕከላትን የመገንባት ግድታውን ያልተወጣ በመሆኑ፣ ተጠሪን ከውል ወይም በሕግ ስልጣን ለተሰጠው አካል በማቅረብ የውል ግድታውን እንዲወጣ ክስ የማቅረብና ተከታትሎ የማስፈፀም ዓላማና ልሎች አላማዎችን የሚያሳካ ማህበር በመፍጠር፣ የፈጠሩት ማህበር፣ የማህበሩ አባላት በተናጠል ከውል የመነጨ መብታቸውን፣ለማስከበር ቢንቀሳቀሱ፣ የሚያወጡትን ወጭዎችና ጊዜ በሚቆጥብ ሁኔታ በተደራጀ መንገድ ማህበሩ ጥያቄ እንዲያቀርብላቸው ሙሉ ፈቃድና ስምምነታቸውን ሥልጣን ባለው የመንግሰት አካል ፊት በመቅረብና የማህበሩን መመስረቻ ፅሑፍ በፊርማቸው በማፅደቅ የሰጡ መሆኑን የበታች ፍርድ ቤቶች በውሣኔያቸው ካሰፈሩትና ከደረሱበት የፍሬ ጉዳይና የማስረጃ ምዘና መደምደሚያ ለመረዳት ይቻላል።
አመልካች የተቋቋመበት አንደኛው መሰረታዊ ጉዳይ የማህበሩ አባላት አመልካችን ከማቋቋማቸው በፊት በተናጠል ከተጠሪ ጋር ባደረጉት የመኖሪያ ቤት ግንባታና የማዘዋወር ስምምነት መሰረት ተጠሪ ግድታውን እንዲወጣ አባላቱን በመወከል አስፈላጊ የሆኑ ተግባራትን ክስና ልሎች የዳኝነት ጥያቄዎችን በማቅረብ ኃላፊነት ያለበት ሶስተኛ ወገን /ተጠሪ/ ግድታውን እንዲፈጽም ለማድረግ መሆኑ በአመልካች መመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 5 ንኡስ አንቀጽ 11 በግልጽ ተደንግጓል። አመልካች ይህንንና ልሎች ዓላማዎችን ለማሳካት እንዲንቀሳቀስ ዕውቅና ፈቃድ ስልጣን ባለው የመንግስት አካል ተሰጥቶታል።ይህም አመልካች በአላማነት ይዟቸው የተነሱ ተግባሮች ለመፈጸም የሚያስችልን ህጋዊ ተግባራት እንዲፈጽም አባላቱ ማህበሩን ሲመሰርቱ በሰጡት ፍቃድና ስምምነት መሰረት የመንቀሳቀስ ኃላፊነት ያለበት መሆኑ ከአዋጁ ቁጥር 621/2001 አንቀጽ 55 ድንጋጌዎችና ከአዋጅ ድንጋጌ ጋር የሚቃረን ይዘትና ውጤት ያላቸው የልሎች ህጎች ተፈጻሚነት የልላቸው መሆኑን ከሚደነግገው የአዋጁ አንቀጽ 110 ድንጋጌዎች መሰረታዊ ይዘት ህጋዊ ውጤት በማገናዘብ ለመረዳት ይችላል።
ለዚህም ምክንያቱ የአዋጅ ቁጥር 621/2001 አንቀጽ 110 ድንጋጌ፣ ከአዋጅ ጋር የማይቃረኑ የፍትሐብሕር ሕጉና የልሎች ሕጐች ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት የሚከለክል ይዘትም ሆነ ሕጋዊ ውጤት የልለው መሆኑ ነው። ይህም ስለ ማህበራት “ችሎታ” የሚደነግገው የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 454 ንዑስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ እንድናገናዝብ የሚጠይቅ ሆኖ አግኝተነዋል። ስለማህበራት ችሎታ የሚደነግገው የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 454 ንዑስ አንቀጽ 1 “ማህበሩ ከዓይነቱ ጋር የሚያስማማበትን ብሕራዊ የኑሮ ተግባሮች ሁሉ ለመፈፀም ይቻላል” የሚል ይዘት ያለው ነው። ከዚል አንፃር ሲታይ፣ አመልካች የተቋቋመበትን መሰረታዊ ዓላማ ለማሳካት የሚያስችለውን የዳኝነት ጥያቄ የአባላቱን መብትና ጥቅም ለማስከበር በሚያስችለው አግባብ ለመጠየቅ ከአዋጅ ቁጥር 621/2001 አንቀጽ 55፣አንቀጽ 110 እና በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 454 ንዑስ አንቀጽ 1 ድንጋጌዎች የሚፈቅድለት መሆኑን ለመረዳት ይቻላል።
ከዚህ በተጨማሪ የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 35 ድንጋጌ፣ ከአንድ ሰው አንድ አይነት መብትና ጥቅም የሚጠይቁ ካሉ ከሳሾች፣ መብትና ጥቅማቸውን እነሡን በመወከል የሚጠይቅ በህግ ዕውቅና የተሰጠውና ህጋዊ ህልውና ያለው ማህበር በማቋቋም፣ በማህበሩ መብታቸውን እንዲጠይቅላቸው በማህበሩ መመሥረቻ ፅሑፍ በሙሉ ፈቃድና ስምምነት በማፅደቅ የሚሰጡትን ስምምነት ዋጋ በሚያሳጣ ሁኔታ መተርጐም ያለበት ሆኖ አላገኘነውም። በአንፃሩ የህግ ህልውና ያገኙ የሲቪል ማህበራት ፣የተቁቋሙለትን ዓላማ ለማሣካትና፣ ሲያከራክሩት የሚፈልጉትን የአባላታቸውን መብትና ጥቅም ለማሰከበር፣ ለፍርድ ቤት ለግልግል ተቋም ወይም ለልሎች የዳኝነት ሥልጣን ለተሰጣቸው አካላት ጥያቄዎችን ለማቅረብ በሚያስችል መንገድ የሕጉን ድንጋጌዎች መተርጐም በግልና በተናጠል እንዲሁም በራሳቸው ችሎታ ተከራክረው መብትና ጥቅማቸውን ለማስከበር ከፍተኛ ወጭና ጊዜ የሚጠይቃቸው ግለሰቦች፣ ለዚህ ዓላማ በመሰረቱት ማህበር በኩል መብትና ጥቅማቸውን በቀላሉ ለማስከበር የሚችሉበትን ዕድል በሚያሰፋና የሰዎችን ፍትህ የማግኘት መብት የሚያረጋግጥ አግባብ መተርጐም ያለበት ሆኖ አገኘተነዋል። ከዚህ አንፃር ተጠሪ በሕግና በሚመለከተው የመንግስት አካል ዕውቅና የተቋቋሙ ማህበራት፣ የተቋቋመበትን አላማ ለማሳካት፣ የሚያስችላቸው የዳኝነት ጥያቄ የማቅረብ መብት የላቸውም በማለት ያቀረበው መቃወሚያ ከላይ በዝርዝር የጠቀስናቸውን የሕግ ድንጋጌዎች ይዘትና ተግባራዊ ተፈፃሚነት ያላገናዘበ በመሆኑ አልተቀበልነውም።
የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤትና የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ከላይ በዝርዝር የገለጽናቸውን ድንጋጌዎች ይዘትና ተግባራዊ ውጤት ሣያገናዝቡ አመልካች የግልግል ዳኛ እንዲሰየምለት ለማቅረብ አይችልም በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ውሣኔ
የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔና የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የሰጠው ትእዛዝ ተሽሯል።
የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ
No topics extracted.