የመንግሥት አካል ፉት ቀርቦ የተረጋገጠና የተመዘገበ ሰነድ በውስጡ የሚገኘው ይዘት ሙለ እምነት የሚጣልበት በቂ ማስረጃ ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 334/1995 አንቀጽ 27 /1/
No summary available.
ግንቦት 29 ቀን 2010 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካቾች፡-
ተጠሪዎች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
የነገሩ አመጣጥ የንግድ ማኅበር ክርክርን የሚመለከት ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የቀረበውና የታየው በግልግል ዲኝነት ነው። የአሁን ተጠሪዎች /የሥር አመልካቾች/ ህዲር 8 ቀን 2008 ዓ/ም ጽፈው ባቀረቡት የተሻሻለ የክስ አቤቱታ የሽርክና ውል በመፈራረም “ፕላዛ አዱስ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር” የተባለ ማኀበር ለማቋቋም በምንቀሳቀስበት ሂደት ውስጥ ተጠሪዎች በሽርክና ውል ለመሳተፍ የፈለጉ በመሆኑና አመልካቾችም በመስማማታቸው ይህንኑ አስመልክቶ መስከረም 15 ቀን 2006 ዓ/ም የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመናል፤ በፕላዛ አዱስ ትሬዱንግ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር ሥር ከሚጠቃለለት ንብረቶችና ፈቃድች ጭምር የህንፃው ሥራ ሙለ ለሙለwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ከተጠናቀቀና ለሆቴለ ሥራ የሚያስፈልጉ መሳሪያዎችና እቃዎች ሁለ ከተሟለ በኋላ አጠቃላይ የንብረቱ ዋጋ ብር 130,000,000 /አንድ መቶ ሰላሳ ሚሉዮን/ እንዱሆን እንደዚሁም ከዲሽን ባንክ የተወሰደ ብድር በተጠቀሰው የማኅበሩ ካፒታል ውስጥ የተካተተ መሆኑን ተዋዋይ ወገኖች ተስማምተናል፤ ከዚህ ካፒታል ውስጥ የተጠሪዎች ድርሻ 40% ወደ ገንዘብ ሲቀየር ብር 52,000,000 /አምሳ ሁለት ሚሉየን/ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የባንክ እዲው 40% ድርሻ ብር 24,000,000 /ሃያ አራት ሚሉየን/ ሲቀነስ ተጠሪዎች ቀሪውን ብር 28,664,000 /ሃያ ስምንት ሚሉየን ስድስት መቶ ስልሳ አራት ሺህ/ ለመክፈል ተስማምተው መስከረም 15 ቀን 2006 ዓ/ም በተደረገ የመግባቢያ ሰነድ ሲፈረም ከፉል ክፍያ ፈጽመው የሚፈለግባቸውን ቀሪ እዲ የመመሥረቻ ጽሁፈና መተዲደሪያ ደንብ ከመሻሻለ በፉት ለመክፈል ግዳታ ገብተዋል፤ ይሁንና ተጠሪዎች የሚቀርባቸውን እዲ የመመሥረቻ ጽሁፈና የመተዲደሪያ ደንቡ ከመሻሻለ በፉትም ሆነ በኋላ ለመክፈል ፈቃደኛ አልሆኑም፤ ተጠሪዎች በውለ መሰረት ሉከፍለ የሚገባቸውን በራሳቸው የታመነ ብር 6,399,782.07 /ስድስት ሚሉየን ሶስት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሺህ ሰባት መቶ ሰማኒያ ሁለት ብር ከዜሮ ሰባት ሳንቲም/፣ ለሆቴል አግልግልት ለሚውለ እቃዎች ግዢ ከትራንስፖርት ጭምር ብር 3,230,687.70 /ሶስት ሚሉየን ሁለት መቶ ሰላሳ ሺህ ስድስት መቶ ሰማኒያ ሰባት ብር ከሰባ ሳንቲም/ ውስጥ የተጠሪዎች 40% ድርሻ ብር 1,292,275.10 /አንድ ሚሉየን ሁለት መቶ ዘጠና ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሰባ አምስት ብር ከአስር ሳንቲም/ እና ለከስተም ክሉራንስ ኮንሰልታንሲ ከወጣ ብር 167,052.09 /አንድ መቶ ስልሳ ሰባት ሺህ ሃምሳ ሁለት ብር ከዜሮ ዘጠኝ ሳንቲም/ የተጠሪዎች ድርሻ ብር 66,820.83 /ስልሳ ስድስት ሺህ ስምንት መቶ ሃያ ብር ከሰማኒያ ሶስት ሳንቲም/ በድምሩ ብር 7,758,878.00 /ሰባት ሚሉየን ሰባት መቶ ሃምሳ ስምንት ሺህ ስምንት መቶ ሰባ ስምንት/ አልከፈለም፤ በመግባቢያ ሰነደ አንቀጽ 3 መሰረት የውለን አፈጻጸም ያሰናከለ ወይም ለማሰናከል የሞከረ ወገን የውለን ብር 130,000,000 /አንድ መቶ ሰላሳ ሚሉየን/ 10% የቅጣት ገንዘብ ውለን ላከበረ ወገን ለመክፈል ግዳታ መገባቱን ገልጸው በፍትሒብሓር ህግ ቁጥር 1731 እና 1971 መሰረት ለውለ አፈጻጸም የአንድነትና የነጠላ ኃላፉዎች መሆናቸው ተረጋግጦ ከላይ የተዘረዘረውን ብር 7,758,878.00 /ሰባት ሚሉየን ሰባት መቶ ሃምሳ ስምንት ሺህ ስምንት መቶ ሰባ ስምንት/ የመመሥረቻ ጽሁፈና የመተዲደሪያ ደንቡ ከተሻሻለበት ቀንwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድ፣ የጠበቃ አበል፣ የትርጉም፣ የዲኝነትና ልዩ ልዩ ወጪና ኪሳራ ጨምረው እንዱከፍለ ይወሰንልን በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
የአሁን ተጠሪዎች ታኅሳስ 20 ቀን 2008 ዓ/ም ጽፈው ባቀረቡት መልስ አመልካቾች በስምምነቱ መሰረት ህንፃውን ሙለ በሙለ የማጠናቀቅ፣ የሆቴለን እቃና መሳሪያ የማሟላት፣ የሆቴለ ይዞታ የነበረውን ቦታ በ241 ካሬ ሜትር አስቀንሰው በማስመዝገባቸው በገበያ ዋጋ ለተቀነሰው ቦታ ክፍያ የመፈጸምና በውል መሰረት ሉፈጽሟቸው የሚገቡ ግዳታዎች ስላለባቸው ግዳታዎቹን ፈጽመናል ሳይለ ወይም ለመፈጸም ዝግጁነታቸውን ሳይገልጹ መክሰስ እንዲይችለ የፍትሒብሓር ህግ ቁጥር 1757 የሚያግዲቸው ሲሆን ከዚህ ጋር ተያይዞ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ
ላይ አስገዲጅ ትርጉም ሰጥቶበታል፤ ይህ እንዲለ ሆኖ በሰነድች ምዝገባና ማረጋገጫ ጽ/ቤት ፉት መጋቢት 15 ቀን 2007 ዓ/ም ላይ የተፈረመው የማኅበሩ የተሻሻለው የመመስረቻ ጽሁፍ ላይ የማህበሩ ካፒታል ሙለ በሙለ በጥሬ ገንዘብ ተከፍሎል በማለት የተገለጸ በመሆኑ ተጠሪዎች ለ40 በመቶ ድርሻቸው የሚፈለግባቸውን የገንዘብ መዋጮ ለመክፈላቸው በቂ ማረጋገጫ ነው፤ በልላ በኩል ተጠቃሹን ገንዘብ ተከሳሾች ይከፍላለ ያሰኘው ከሳሾችና ተከሳሾች ከግልግል ዲኝነት ጉባኤው ውጪ ክርክራቸውን በሙግት ሳይሆን በእርቅ ይፈታ እንደሆነ ለመሞከር መግባባት ላይ በደረሱበት ወቅት አለመግባባት አስነስተዋል በተባለ ነጥቦች ላይ የከሳሾችን አመለካከት ወደ ቀና መንገድ ለመመለስ “ ሰጥቶ መቀበል” በሚል ቅን አስተሳሰብ ተከሳሾች ጥቅምት 20 ቀን 2008 ዓ/ም በጻፈት ማመልከቻ ተጠቃሹን ገንዘብ እንዱከፍለ ከሳሾችም ደግሞ የመስከረም 15 ቀን 2006 ዓ/ም ስምምነትን በመተግበር ግዳታቸውን በቅን መንፈስ እንዱወጡ ለማግባባት ይረዲል በሚል የገለጹት እንጂ ግዳታ የገቡበት አይደለም። ስለዚህ አዋዋይ በተገኘበት የተፈረመው ሰነድ ገንዘብ በተከሳሾች መከፈለ ግራ ቀኙ “ ሁለንም ተጠቃሚ ሉያደርግ” በሚችል የእርቅ ድርድር ወቅት እንከፍላለን ያለት ገንዘብ በፍርድ ቤት፣ በፍርድ ሰጭ አካል፣ በመንግሥት መሥሪያ ቤት እንደታመነ ወይንም በቃለ መኻላ እንደተረጋገጠ እዲ ተቆጥሮ ተጠያቂነት ያስከትላል የሚለው የከሳሾች አካሄድ ተቀባይነት የለውም ተብል ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ከዚህ በኃላ የአሁን ተጠሪዎች 14 ነጥቦችን በማንሳት የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ያቀረቡ ሲሆን የአሁን አመልካቾችም /የከሳሽ ተከሳሾችም/ ከሥልጣን ጋር ተያይዞ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እንዱሁም ለፍሬ ነገሩ መልስ ሰጥተው ተከራክረዋል።
ጉዲዩን የተመለከተው የግልግል ጉባኤ በተከሳሸ ከሳሽነት ከቀረቡት አስራ አራት ነጥቦች መካከል በተራ ቁጥር 1፣ 2፣ 3፣ 4፣ 7 እና 14 ላይ የቀረቡትን የዲኝነት ጥያቄዎችን ለመመልከት ሥልጣን እንዲላቸው፤ በልላ በኩል ደግሞ በተራ ቁጥር 5፣ 6፣ 11፣ 12 እና 13 ሥር ተጠቅሰው የቀረቡትን የዲኝነት ጥያቄዎችን መስከረም 15 ቀን 2006 ዓ/ም በተደረገው መግባቢያ ሰነድ መሰረት የግልግል ዲኝነት አካለ ለመመልከት ሥልጣን እንደላለው እንዱሁም በተራ ቁጥር 8፣ 9 እና 10 ሥር ተጠቅሰው የቀረቡትን የዲኝነት ጥያቄዎችን በተመለከተ የክስ ምክንያት የላላቸው መሆኑን ገልጾ ጥር 26 ቀን 2008 ዓ/ም ብይን ሰጥቷል።
ከዚህ በኃላ የግልግል ጉባኤው በፍሬ ነገሩ ላይ ግራ ቀኙን በማከራከርና ምስክሮችን በመስማት እንዱሁም ሰነድችን በመመርመር አመልካቾች ተጠሪዎች በጽሁፍ አምነዋል በማለት እንዱከፍሎቸው የጠየቁትን ብር 6,399,782.07 /ስድስት ሚሉየን ሶስት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሺህ ሰባት መቶ ሰማኒያ ሁለት ብር ዜሮ ሰባት ሳንቲም/ በተመለከተ ከዚህ ገንዘብ ውስጥ ብር 4,276,900 /አራት ሚሉየን ሁለት መቶ ሰባ ስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ/ የሚሆነው በመግባቢያ ሰነደ ላይ ተጠሪዎች ላይ ከተጣለው ግዳታ ጋር ግንኙነት የለውም በማለት ጉዲዩን ለማየት ሥልጣን የለኝም በማለት ሳይቀበለው የቀረ ሲሆን ቀሪውን ብር 2,122,882.00 /ሁለት ሚሉየን አንድ መቶ ሃያ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ሰማኒያ ሁለት/ ክፍያ ጥያቄን በተመለከተ ተጠሪዎች በመግባቢያ ሰነድ፣ በተለያዩ ደረሰኞች እንዱሁም ቼክ የሚፈለግባቸው ክፍያዎችን ከፍለው በሰነድች ምዝገባ ጽ/ቤት የተመዘገበ ስለሆነ አመልካቾች ገንዘብ አልተከፈለንም በማለት ያቀረቡትን ክርክር አልተቀበልንም፤ አመልካቾች ለሆቴለ አስፈላጊ የሆኑ እቃዎችና መሳሪያዎችን ለማሟላት አወጣን ያለትን ገንዘብ ተጠሪዎች እንዱከፍለ የጠየቁትን በተመለከተ መስከረም 15 ቀን 2006 ዓ/ም በተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ መሰረት አስፈላጊ የሆኑ እቃዎችና መሳሪያዎችን የማሟላት ግዳታ የአመልካቾች በመሆኑ የጠየቁትን ክፍያ በሚመለከት ይህ ክፍያ ሆቴለ በተገመተበት ሰላሳ ሚሉየን ብር ውስጥ የሚጠቃለልwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ከሚሆን በቀር ለብቻው ተነጥል በመውጣት በተጠሪዎች ክፍያ እንዱፈጸምበት ሉጠየቅ የሚችልበት ሆኖ አልተገኘም፤ አመልካቾች ያቀረቡት ለከስተምስ ኪሉራንስ እና ኮንሰልተንሲ የተከፈለ ብር 66,820.83 ይከፈለን ጥያቄ የውል ድጋፍ የለውም በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
በልላ በኩል የአሁን ተጠሪዎች ያቀረቡትን የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ በተመለከተ የግልግል ጉባኤው ሥልጣን አለኝ በማለት የተመለከታቸውን ነጥቦችን በተመለከተ 1ኛ/ ስፊቱ 1280 ካሬ ሜትር የሆነ ለመኖሪያነት በአሁን አመልካቾች ስም የተሰጠውን ይዞታ ካርታ ሲዘጋጅ ስፊቱ 1039 ሆኖ የተሰራ በመሆኑ የ241 ካሬ ሜትር ቦታ በሉዝ ሽያጭ ዋጋ ተመን ብር 6,319,261 /ስድስት ሚሉየን ሶስት መቶ አስራ ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ ስልሳ አንድ/ የአሁን አመልካቾች ይክፈለ በማለት የአሁን ተጠሪዎች የጠየቁትን በተመለከተ የግልግል ጉባዓው የተጠቀሰውን ቦታ በተመለከተ በቦላ ክፍላ ከተማ የይዞታ አስተዲደር የሽግግር ጊዜ አገልግልት ፕሮጀክት ጽ/ቤት ሚያዝያ 3 ቀን 2008 ዓ/ም በጻፈው ደብዲቤ የይዞታው ስፊት የቀነሰው በመንገድ ጥናት ምክንያት መንገድ የሚወስደው ተቆርጦ በመሆኑ ምክንያት እንደሆነ ገልጾ ተጠሪዎች ባቀረቡት የዲኝነት ጥያቄ የቀነሰው የይዞታ ስፊት በአካባቢው የሉዝ ዋጋ ተሰልቶ ድርሻቸው የይዞታ ዋጋ እንዱከፈላቸው የጠየቁትን ጥያቄ የግልግል ጉባኤው አልተቀበለውም በማለት ውድቅ አድርጓል፣ 2ኛ/ ከመተዲደሪያ እና መመሥረቻ ጽሁፍ ጋር ተያያዞ የተነሳውን ክርክር በተመለከተ መተዲደሪያ ደንቡ እና መመሥረቻ ጽሁፈ የተሻሻለ መሆኑ ማረጋገጡን፣ ተጠሪዎች በተሻሻለው ጽሁፍና ደንብ ውስጥ መካተት የሚገባቸው ጉዲዮች አልተካተቱም የሚለ ከሆነ በንግድ ህጉ እና በተሻሻለው የመመሥረቻ ጽሁፍ እና የመተዲደሪያ ደንብ መሰረት አጀንዲ አስይዘው እንዱካተቱ ለመጠየቅ የሚችለ ከሚሆኑ በስተቀር በመግባቢያ ሰነደ መሰረት መጋቢት 15 ቀን 2007 ዓ/ም ቃለ ጉባኤ ተይዞ የተሻሻለ መመሥረቻ ጽሁፍ እና መተዲደሪያ ደንብ የቀረበ በመሆኑ አልተሻሻለም የሚያስብል በቂ ምክንያት የላለ በመሆኑ በዚህ ረገድ የቀረበ የተጠሪዎች ክርክር ጉባኤው አልተቀበለውም በማለት አስቀምጧል። 3ኛ/ ከህንጻ ጋር በተያያዘ ህንጻው ጥራት የሚጎለው ከመሆኑ እንዱሁም አስፈላጊ መሳሪያዎችና እቃዎች ካለመሟላታቸው ጋር ተያይዞ የተነሳውን ክርክር በተመለከተ የህንፃው ሥራ ሙለ ለሙለ መጠናቀቅ አለመጠናቀቁን ለመረዲት ይቻል ዘንድ የግልግል ዲኝነት ጉባኤው በጉዲዩ ላይwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ከተጠሪዎች የተቆጠሩ ምስክሮችን አስቀርቦ ማዲመጡን እንዱሁም የሆቴለን ህንፃ ቦታው ድረስ ሄድ መመልከቱን ገልጾ አመልካቾች በክርክራቸው ሆቴለ ስለመጠናቀቁና እቃዎችና መሳሪያዎችም አለመሟላታቸው ሆቴለ ባለ4 ኮከብ የሚል ደረጃ የተሰጠው ስለመሆኑ አስረጅ ነው በማለት የተከራከሩ ቢሆንም በተለይም ሆቴለ የኮከብ ደረጃ ሲሰጠው ሆቴለ ሳያልቅ እንዲለቀ፣ ለሆቴለ ሥራ አስፈላጊ መሳሪያዎችና እቃዎች ሳይኖሩና ሳይሟለ እንዲለና እንደተሟለ ተደርጎ የተሰጠው መሆኑን የተጠሪዎች ምስክሮች በተለይም 2ኛ ምስክራቸው በማያሻማ መልኩ ያስረደ በመሆኑ አመልካቾች ሆቴለ ስለመጠናቀቁና አስፈላጊ እቃዎችና መሳሪያዎችም የተሟለለት ስለመሆኑ የተሰጠው ባለ4 ኮከብ ደረጃ ነው በማለት ያቀረቡትን መከራከሪያ ጉባኤው አልተቀበለውም ካለ በኋላ አመልካቾች መስከረም 15 ቀን 2006 ዓ/ም በተፈረመ የመግባቢያ ሰነድ መሰረት የሆቴለን ሥራ ሙለ ለሙለ ባለማጠናቀቃቸው እና ለሆቴለ የሚያስፈልጉ እቃዎችና መሳሪያዎችንም ባለማሟላታቸው በራሳቸው ወጪ የህንፃውን ሥራ ሉያጠናቅቁና አስፈላጊ እቃዎችና መሳሪያዎችንም ሉያሟለ ይገባል ሲል የግልግል ዲኝነት ጉባኤው ፍርድ ሰጥቷል። 4ኛ/ ተጠሪዎች አመልካቾች ከሆቴለ ከውል ወጪ ገንዘብ ወጪ አድርገዋል ተብል የቀረበውን በተመለከተ የግልግል ጉባኤው ተጠሪዎች ባቀረቡት ክርክር ካለፈቃዲችን ከሆቴለ የወጣ ወጪ ከነወለደ ተመላሽ ይደረግ ቢለም ምን ያህል ገንዘብ፣ መቼ እንደወጣ ግን በግልጽ በክርክራቸው አላመለከቱም፣ ይልቁንም አመልካቾች በጥሬ ገንዘብ ከሆቴለ ያወጡትን ያሳውቁን ማለታቸው በግልጽ ምን ያህል ገንዘብ እንደወጣ እየጠቀሱ ክርክራቸውን እያቀረቡ እንዲልሆነ ያሳያል፣ ይህ ብቻ ሳይሆን ከሆቴለ ያለፈቃዲቸው ገንዘብ ስለመውጣቱ ለማስረዲት ያቀረቡት አስረጅም የለም። ስለዚህ የግልግል ዲኝነት ጉባኤው በዚህ ረገድ የቀረበውን የተጠሪዎች የዲኝነት ጥያቄ ግልጽ ያልሆነና የማስረጃ ድጋፍም የላለው በመሆኑ አልተቀበልነውም በማለት ወስኗል። 5ኛ/ አመልካቾች ከተጠሪዎች እውቅና ውጪ ከዲሽን ባንክ በብድር የወሰደትን ብር 2,000,000.00 /ሁለት ሚሉየን/ በተመለከተ ተጠሪዎች ተጠያቂነት እንደላለባቸው ገልጸው ያቀረቡትን ክርክር በተመለከተ ምንም እንኳን የግልግል ዲኝነት ጉባኤው ጥር 26 ቀን 2008 ዓ/ም በመዝገቡ ላይ በሰጠው ብይን ከብር ሁለት ሚሉየን ጋር በተያያዘ የተነሳውን ክርክር ተመልክቶ ለመዲኘት ሥልጣን አለኝ ያለ ቢሆንም ግራ ቀኙ መጋቢት 12 ቀን 2008www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ዓ/ም ባስመዘገቡት ክርክር ለክስ መነሻ የሆነው ገንዘብ መግባቢያ ሰነደን መሰረት አድርጎ የተነሳ አለመሆኑን ከብይኑ በኃላ ያረጋገጡ በመሆኑ የግልግል ዲኝነት ጉባኤው ተጠሪዎች በዚህ ረገድ ያቀረቡትን ክርክር ተመልክቶ ለመዲኘት ሥልጣን የለኝም በማለት በፍትሒብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 9/2/ መሰረት በዚህ ረገድ የቀረበውን የተጠሪዎችን ክርክር ውድቅ አድርጓል ሲል ወስኗል።
በግልግል ጉባኤ 2ኛ ዲኛ የሆኑት አመልካቾች ተጠሪዎች እንዱከፍለ ያቀረቡት ብር 6,399,782.07 በተመለከተ በተጠሪዎች በጽሁፍ የታመነ እዲ ተቀባይነት ሉያገኝ የሚችለው እዲው የታመነበት ሁኔታ ግምት ውስጥ ገብቶ እንዱሁም ተጠሪዎች እዲ ከፍለናል በሚል ያቀረቧቸው ማስረጃዎች በጽሁፍ ከመታመኑ በፉት የተከፈለ ናቸው፤
በመሆኑም በቅርብ በጽሁፍ የታመነ እዲ ለማስተባበል በቂነት የላቸውም። ስለሆነም ተጠሪዎች ለአመልካቾች ሉከፍለ ይገባል በማለት ከአብላጫ ድምፅ ተለይተዋል።
የአሁን ተጠሪዎች 1ኛ/ የግልግል ጉባዓው አመልካቾች ግዳታቸውን ባልተወጡበት ሁኔታ ጉዲዩን ለማየት ሥልጣን የለውም ተብል የቀረበውን መቃወሚያ የግልግል ጉባዓው አልፍ ጉዲዩን መመልከቱ ያለአግባብ ነው፣ 2ኛ/ የ241 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የተሰጠውን ውሳኔ፣ 3ኛ/ የሥር መልስ ሰጪዎች /የአሁን አመልካቾች/ ለሆቴለ መኝታ ለተገለገለበትና ለሆቴለም ምግብ ለተጠቀሙበት ለሆቴለ ወይም ለማኅበሩ ገንዘቡን እንዱከፍለ ይወሰንልን በሚል የተጠየቀውን ዲኝነት ውድቅ በማድረግ የተሰጠው ውሳኔ ያለአግባብ እንደሆነ፣ 4ኛ/ ከማኅበሩ መተዲደሪያ ደንብ መሻሻል እና ከሆቴለ ስያሜ ጋር የተነሳውን ክርክር የግልግል ዲኝነት ተመልክቶ የሰጠው ውሳኔ ተገቢ አይደለም፣ 5ኛ/ የአሁን አመልካቾች ከዲሽን ባንክ የወሰደትን ብር 2,000,000 /ሁለት ሚሉየን/ ጋር በተያያዘ ግልግል ጉባኤው ሥልጣን አለኝ በማለት ካከራከረ በኋላ ተመልሶ ሥልጣን የለኝም ማለቱ ሥነ ሥርዓታዊ አይደለም። 6ኛ/ ውል ያላከበረ ወገን የ130,000,000 ብር 10% እንደሚከፍል መስከረም 15 ቀን 2006 ዓ/ም በተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ ላይ በተቀመጠው መሰረት የአሁን አመልካቾች ውለን ባለማክበራቸው በውለ የተጠቀሰውን ገንዘብ እንዱከፍለ የተጠየቀውን ዲኝነት የግልግል ጉባኤው በግልጽ ውሳኔ መስጠት ሲገባው በዝምታ ማለፈ ያለአግባብ ነው በማለት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበዋል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በልላ በኩል የአሁን አመልካቾች ያቀረቡት መስቀለኛ ይግባኝ 1ኛ/ ብር 7,758,878.07 የአሁን ተጠሪዎች እንዱከፍለ የጠየቁት ዲኝነት ውድቅ መደረጉን የሚመለከት ሲሆን 2ኛው ከሆቴለ አገልግልት አሰጣጥ እና እቃዎች አለመሟላት ጋር በተያያዘ የግልግል ጉባኤው የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ነው።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙ በየበኩላቸው ያቀረቡትን ይግባኝ ተቀብል ካከራከረ በኃላ የቀረቡትን ቅሬታዎችን መርምሮ የግልግል ጉባኤው የሰጠውን ውሳኔ በማጽናት እንዱሁም ከውል አለመፈጸም ጋር የተነሳውን የአንድ መቶ ሰላሳ ሚሉየን 10% ውሳኔ ሳይሰጥ በዝምታ ታልፎል የተባለውን በተመለከተ ጉባኤው በግልጽ የሰጠው ውሳኔ ባይኖርም በግራ ቀኙ መካከል ከተደረገው ውል ባህርይ፣ እንዱሁም መልስ ሰጪዎች /የአሁን አመልካቾች/ የሰጡት የውል ድንጋጌ የትኛው እንደሆነ ግልጽ ሆኖ የማይታወቅ ከመሆኑ አንጻር ሲታይ መልስ ሰጪዎች /የአሁን አመልካቾች/ ውለን ጥሰዋል ተብል ቅጣት ሉወሰን የሚችልበት ሁኔታ አይኖርም በማለት ውድቅ አድርጓል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም አመልካቾች ተጠሪዎች እንዱከፍለ የጠየቁትን ብር 6,399,782.07 በተመለከተ በተሰጠው ውሳኔ ላይ ቅር በመሰኘት ሲሆን አመልካቾች ተፈጽሞብናል ያሎቸውን ዝርዝር የቅሬታ ነጥቦችን አቅርበዋል።
የሰበር አቤቱታውን አጣሪው መርምሮ ተጠሪዎች በጽሁፍ ያመኑትን አይከፍለም የመባለን አግባብነት ለመመርመር ሲባል መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት ጉዲዩ ለሰበር ችልት ይቅረብ ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው በጠበቃቸው በኩል መስከረም 23 ቀን 2010 ዓ/ም የተጻፈ መቃወሚያ እና በአማራጭ ክፍያው ስለመፈጸሙ ዝርዝር መልስ አቅርበው የተከራከሩ ሲሆን የአመልካቾች ጠበቃም ጥቅምት 17 ቀን 2010 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ አቅርበው ተከራክረዋል።
የነገሩ አመጣጥና የክርክሩ ሂደት አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ እንደተመለከተው ሲሆን የአመልካቾችን የቅሬታ ነጥብ የግልግል ጉባዓው ከሰጠው ፍርድ እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰጠው ውሳኔ እንዱሁም በዚህ ችልት ከተደረገው ክርክር አንጻርwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
መርምረናል። በግልግል ጉባዓም ሆነ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተሰጡት ውሳኔዎች ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል ወይስ አልተፈጸመበትም?
የሚል ጭብጥ ተይዞ ጉዲዩ እንደሚከተለው ተመርምሯል።የአሁን አመልካቾች ካቀረቡት ዲኝነት መካከል ከብር 6,399,782.07 /ስድስት ሚሉየን ሶስት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሺህ ሰባት መቶ ሰማኒያ ሁለት ብር ዜሮ ሰባት ሳንቲም/ ውስጥ 4,263,460 /አራት ሚሉየን ሁለት መቶ ስልሳ ሶስት ሺህ አራት መቶ ስልሳ / ብር በተመለከተ በመግባቢያ ሰነደ ላይ በአሁን ተጠሪዎች ላይ ከተጣለው ግዳታ ጋር ግንኙነት የላለው ነው በማለት የግልግል ጉባኤው አልፍታል። ቀሪውን ገንዘብ በተመለከተ ግን የአሁን ተጠሪዎች በመግባቢያ ሰነድ፣ በተለያዩ ደረሰኞች እንዱሁም በቼክ ለአሁን አመልካቾች ከፍለዋል ሲል በማስረጃ አረጋግጦ የአሁን ተጠሪዎች ኃላፉነት የለባቸውም በማለት ወስኗል።
የግልግል ጉባዓው ውሳኔ ላይ በግልጽ እንደሰፈረው የግልግል ጉባዓው መመልከት አልችልም ካለው ገንዘብ ውጪ ያለው በተለያዩ ሰነድች ገቢ የሆነ መሆኑንና ይህም ገቢ ስለመደረጉ በሰነድች ምዝገባ ጽ/ቤት የተመዘገበ መሆኑን ነው። የግልግል ጉባኤው መስከረም 15 ቀን 2006 ዓ/ም ከተደረገው የመግባቢያ ሰነድ ውጪ ነው ያለውን ገንዘብ በተመለከተ አመልካቾች መብትና ጥቅም ካላቸው ለፍርድ ቤት አቅርበው ከሚያስወስኑ ውጪ መሰረታዊ የህግ ስህተት እንደተፈጸመ አድርገው ለዚህ ችልት ያቀረቡትን ስንመለከት ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም። እንዱሁም ተጠሪዎች ለመክፈል በጽሁፍ አምነው የነበረውን ገንዘብ በቃለ መኻላ ሥር ሆነው ስለመክፈላቸው ቃል በመስጠታቸውና በክርክር ሂደት ያቀረቡትን ማስረጃዎችን የግልግል ጉባዓው ተቀብል ውሳኔ መስጠቱ ተገቢ አይደለም በሚል የቀረበውን ቅሬታ በተመለከተ ተጠሪዎች የሚፈለግባቸውን ድርሻ ከፍለው ስለመክፈላቸውም በሰነድችና ምዝገባ ጽ/ቤት ከተመዘገበ በኋላ የምንከፍል ገንዘብ አለብን በማለት በጽሁፍ መተማመኛ ቢሰጡ ይህ ከአዋጅ ቁጥር 334/1995 አንጻር መታየት ያለበት ነው። በዚህ አዋጅ በሚመለከተው የመንግሥት አካል ፉት ቀርቦ የተረጋገጠና የተመዘገበ ሰነድ ደግሞ በውስጡ ስለሚገኘው ይዘት ሙለ እምነት የሚጣልበት በቂ ማስረጃ ስለመሆኑ በአንቀጽ 27/1/ ሥር ተደንግጎ ይገኛል። ስለሆነም የሥር ግልግል ጉባኤም ሆነ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከዚህ ጋር በተያያዘ የሰጡት ውሳኔ የሚነቀፍ ሆኖ አልተገኘም።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በአጠቃላይ ከላይ በዝርዝር የተመለከቱትን መሰረታዊ ነገሮችን የግልግል ጉባኤው ተመልክቶ እንዱሁም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ የቀረበለትን ጉዲይ አከራክሮ በሰጡት ውሳኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት ባለመኖሩ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
የግልግል ጉባኤው ጥር 26 ቀን 2008 ዓ/ም የሰጠው ብይን እና ሰኔ 13 ቀን 2008 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ እንዱሁም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍ/ይ/መ/ቁ. 130348 በ18/08/2009 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ በፍትሒብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 348 /1/ መሰረት ፀንቷል።
በግልግል ጉባኤውም ሆነ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተሰጡት ውሳኔዎች ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የለም ተብል ተወስኗል።
የዚህን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይድረሳቸው።
መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.