አንድ ጠበቃ ደንበኛው ላይ በቀረበ ክስ “በተመሳሳይ ጉዲይ ሁለት ፍርድ ቤት ክስ ላቀርብ አይገባም ” በሚል በህግ የተፈቀደን መቃወሚያ ማቅረቡ የጥብቅና ሙያን የሚያጎድፍ ተግባር ፈፅሟል ተብል በዱስፕሉን የሚያስቀጣው ተግባር ስላለመሆኑ የትግራይ ክልል የጥብቅና ፈቃድ አሰጣጥና አስተዲደር አዋጅ ቁ/ 262/2007 አንቀጽ 30/23/ www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. LV
No summary available.
መ/ቁ154371 ህዲር 28 ቀን 2011ዓ.ም ዳኞች፡ ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንደሻዉ አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች፡- አቶ አስፊዉ ተኽለ በሽሩ ተጠሪ፡- የትግራይ ክልል ፍትህ ቢሮ መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ በመሆኑ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
በዚህ መዝገብ የቀረበዉ ጉዲይ የጥብቅና ሙያ የዱስፕሉን ጥፊት የሚመለከት ነዉ። አመልካች አዋጅ ቁ/262/07 አንቀጽ 30/23/ ተላልፍ የጥብቅና ሙያ የሚያጎድፍ ተግባር ፈጽሟል በሚል የክልለ የጠበቆች የዱስፕሉን ጉባኤ የጥፊተኛነት ዉሳኔ ሰጥቶ በዚህም ብር ሶስት ሺህ የገንዘብ መቀጮ የወሰነበት ሲሆን የክልለ ፍትህ ቢሮ ሃላፉ ይህንኑ በማጽናታቸዉ አመልካች ለክልለ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ ያቀረቡ ቢሆንም ተቀባይነት አላገኘም።
ለዚህ ሰበር ችልት አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ላይ ሲሆን የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘት ባጭሩ ሲታይ የአመልካች ደንበኛ ተከሳሽ ፍፁም ገ/መድህን በተከሰሰበት ቀላል ስርቆትና በቸልተኛነት የመሸሸግ ወንጀል በሐድነት ክ/ከ ክርክር ላይ መሆኑን በመግለጽ መቃወሚያ ማቅረብ የጥብቅና ሙያ የሚያጎድፍ ነዉ ተብል የቅጣት ዉሳኔ መሰጠቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለሆነ እንዱታረም የሚል ነዉ።የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በአመልካች ደንበኛና በአቃቤ ህግ መካከል በተመሳሳይ ጉዲይ በልላ ፍርድwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ቤት ቀጠሮ ላይ መሆኑን ገልጾ መከራከሩ ፍትህን የሚያዛባ ተግባር ነዉ ተብል ጥፊተኛ የመባለን አግባብነት ለመመርመር እንዱቻል ጭብጥ ተይዞ ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ ተደርጓል።በተጠሪ በኩል ያቀረበዉ መልስ ባጭሩ የአመልካች ደንበኛ በኩሒ ክ/ከ/ወረዲ ፍርድ ቤት የተከሰሰዉ ንብረትነቱ የአቶ ሃይላይ ገ/ሕይወት የሆነ የብልኬት ማምረቻ ዱናሞ ሸሽጎ በመገኘቱ ስለመሆኑ፤በልላኛዉ ጉዲይ በሒድነት ክ/ከ/ ወረዲ ፍ/ቤት የተከሰሰዉ ንብረትነቱ የአቶ ሃይለ ግርማይ የሆኑ ሁለት ስላተርሽ የሚባል ማሽን ሸሽጎ በመገኘቱ ስለመሆኑና በሁለቱም መዝገብ የአመልካች ደንበኛ የተከሰሰዉ በመሸሸግ ወንጀል ቢሆንም ንብረቶቹ የተለያዩና ባለቤቶቹም የተለያዩ ስለሆነ ይህንን ሒቅ እያወቀ መቃወሚያ ማቅረቡ ፍትህን የሚያሳስት ተግባር ስለሆነ የጥብቅና ሙያ የሚያጎድፍ ተግባር ነዉ ተብል መቀጣቱ ተገቢ ነዉ በማለት ተከራክሯል።አመልካችም አቤቱታዉን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥና የግራቀኙ ክርክር ይዘት ከላይ ባጭሩ ተገለጸ ሲሆን እኛም አቤቱታዉ ለሰበር ያስቀርባል ሲባል የተያዘዉን ጭብጥ መሰረት በማድረግ አግባብነት ካለዉ ህግ ጋር በማገናዘብ መርምረናል።መዝገቡን መርምረን እንደተገነዘብነዉ የአመልካች ደንበኛ በሁለት ፍርድ ቤቶች በተመሳሳይ ጉዲይ ክስ ላቀርብባቸዉ አይገባም በማለት አመልካች ያቀረቡት መቃወሚያ የክስ ክርክር የጥብቅና ሙያ የሚያጎድፍ ተግባር ነዉ በሚል የተሰጠዉ ቅጣት ዉሳኔ ተገቢ መሆን አለመሆኑ ከአዋጁ አንጻር መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተናል።የትግራይ ክልል የጥብቅና ፈቃድ አሰጣጥና አስተዲደር አዋጅ ቁ/262/2007 ላይ የድስፕሉን ጥፊቶች ዓይነትና የሚወሰደ እርምጃዎችን አስመልክቶ በክፍል ሶስት አንቀጽ 30 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ላይ በዝርዝር ተደንግጓል።በዚህ መዝገብ በተያዘዉ ጉዲይ አመልካች ጥፊተኛ የተባለት የአዋጁን አንቀጽ 30/23/ተላልፈዉ የጥብቅና ሙያ የሚያጎድፍ ተግባር ፈጽመዋል በሚል ነዉ።የአዋጁ አንቀጽ 30 የሚደነግገዉ ከባድ የዱስፕሉን ጥፊቶችን በመዘርዘር ሲሆን ንኡስ አንቀጽ 23 ስር የተመለከተዉ የጥብቅና ሙያን የሚያጎድፍ ተግባር በደንበኛዉ ወይም በልላ ሰዉ ላይ መፈጸም ከባድ የዱስፕሉን ጥፊት መሆኑን የሚደነግግ ነዉ።ከዚህ ድንጋጌ አንጻር የጥብቅና ሙያ የሚያጎድፍ ተግባር ምንነት አመላካች ቃል ወይም ትርጉም በግልጽ በአዋጁ ላይ የተመለከተ ባይሆንም አመልካች ደንበኛቸዉ በተመሳሳይ ጉዲይ በሁለት ፍርድ ቤት ክስ ላቀርብበት አይገባም በማለትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
መቃወሚያ ማቅረባቸዉ የጥብቅና ሙያ የሚያጎድፍ ተግባር ነዉ በሚል መቀጣታቸዉ ተገቢ መሆን አለመሆኑን መርምረናል።
በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበዉ ክስ መነሻዉ የአመልካች ደንበኛ አቶ ፍጹም ገ/መድህን በሁለት ፍርድ ቤቶች በተመሳሳይ ሁኔታ በመሸሸግ ወንጀል መከሰሳቸዉን ተከትል አመልካች በደንበኛቸዉ ላይ በተመሳሳይ ጉዲይ ሁለት ፍርድ ቤት ክስ ላቀርብ አይገባም በሚል መቃወሚያ ማቅረባቸዉ የአዋጁን አንቀጽ 30/23/ በሚያሟላ ሁኔታ የጥብቅና ሙያ የሚያጎድፍ ተግባር ነዉን? የሚለዉ መታየት ያለበት ነዉ።የአመልካች መቃወሚያ ነጥብ ደንበኛቸዉ በመሸሸግ ወንጀል በሒድነት ክ/ከ/ወረዲ ፍርድ ቤት ተከሰዉ ቀጠሮ ላይ ስለሆነ በተመሳሳይ የመሸሸግ ወንጀል በኩሒ ክ/ከ/ወረዲ ፍርድ ቤት ክስ መቅረቡ ተገቢ ስላልሆነ መዝገቡ እንዱዘጋ የሚል ስለመሆኑ መዝገቡ ያስረዲል።በአቃቤ ህግ በኩል የተሰጠዉ ምላሽ ሁለቱም ክሶች የመሸሸግ ወንጀል ቢሆኑም የግል ተበዲይ እና ንብረቱ የተለያየ ስለሆነ አንድ ዓይነት ክስ አይደለም የሚል ነዉ።
በወ/መ/ስ/ስ/ህግ ቁ/130 ላይ እንደተመለከተዉ የክሱ ማመልከቻ ላይ ተከሳሹ መቃወሚያ ሉያቀርብ ከሚችልባቸዉ ምክንያቶች አንደ በዚሁ ነገር ክስ በልላ ፍርድ ቤት ተጀምሮ በቀጠሮ ላይ ያለ መሆኑን መሰረት በማረጋገጥ ሲቻል ነዉ።የአመልካች ጠበቃ በሁለት ፍርድ ቤቶች በመሸሸግ ወንጀል ክስ የቀረበበት መሆኑ አላከራከረም። ስለሆነም በሁለቱ ፍርድ ቤቶች የተያዘዉ ክስ አንድ ነዉ ወይስ አይደለም የሚለዉን እና የቀረበዉ መቃወሚያ በህግ ተቀባይነት አለዉ ወይስ የለዉም የሚለ ነጥቦች መዝገቡን ለያዘዉ ፍርድ ቤት የተተወና ፍርድ ቤቱ አጣርቶ ብይን የሚሰጥበት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ አመልካች በዚህ መልክ ያቀረቡት መቃወሚያ በህግ የተፈቀደ ስለመሆኑ ከወ/መ/ስ/ስ/ህግ ቁ/130/2/ሀ ድንጋጌ ይዘት የምንገነዘበዉ ነዉ።በዚህ መዝገብ በተያዘዉ ጉዲይ የአመልካች ደንበኛ በሁለት የተለያዩ ፍርድ ቤቶች የተከሰሱት በመሸሸግ ወንጀል መሆኑን መሰረት አድርገዉ አመልካች መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን እንደአቃቤ ህግ ክርክር የክሶቹ ዝርዝር ይዘት ሲታይ የተሸሸገዉ ንብረት ዓይነትና የንብረቶቹ ባለቤቶች የተለያዩ መሆንን መሰረት አድርጎ የክሱ ነገር አንድ ነዉ ወይሥ አይደለም የሚለዉን ለይቶ መቃወሚያዉ የወ/መ/ስ/ስ/ህግ ቁ130 2/ሀ ድንጋጌ ይዘት ያሟላል ብል መቀበል ወይም ዉድቅ ማድረግ ፍርድ ቤቱ ዉሳኔ የሚሰጥበት ስለመሆኑ ከወ/መ/ስ/ስ/ህግwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ቁ/131 ድንጋጌ ይዘት መገንዘብ ይቻላል። በመሆኑም የአመልካች ደንበኛ ላይ በሁለት ፍርድ ቤቶች በመሸሸግ ወንጀል ክስ ቀርቦ ያለ መሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ አመልካች በህግ የተፈቀደዉን መቃወሚያ ማቅረባቸዉን የሚያሳይ እንጂ አመልካች የጥብቅና ሙያ የሚያጎድፍ ተግባር መፈጸማቸዉን የሚያረጋግጥ ባለመሆኑ የአመልካች ተግባር በአዋጅ ቁ/262/07 አንቀጽ 30/23/ስር የሚያሥቀጣ ሆኖ አላገኘንም።ስለዚህም በዚህ ጉዲይ ላይ የተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል ብለናል።
በዚህ ጉዲይ አመልካች ያቀረቡት መቃወሚያ ክርክር የጥብቅና ሙያ የሚያጎድፍ ተግባር ፈጽመዋል በሚል የትግራይ ክልል የጠበቆች ዱስፕሉን ጉባኤ በ06/01/2010 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና ይህንኑ በማጽናት የትግራይ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/101364 ላይ በ06/06/2010 ዓ.ም የሰጠዉ ትእዛዝ ተሽሯል።ይጻፍ።
አመልካች በደንበኛቸዉ ላይ ለቀረበዉ የወንጀል ክስ ያቀረቡት መቃወሚያ ምክንያት በህግ የተፈቀደ በመሆኑ ፍርድ ቤት መርምሮ ዉሳኔ የሚሰጥበት እንጂ የጥብቅና ሙያ የሚያጎድፍ ተግባር ነዉ ተብል በዱስፕሉን የሚያስቀጣ ተግባር አይደለም ብለናል።
No topics extracted.