አንድ የሥራ ውለ በገዛ ፈቃደ የተቋረጠበት የሥራ መሪ ያልተጠቀመበት የአመት እረፍት በገንዘብ ተቀይሮ ስለሚከፈልበት የሕግ አግባብ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2563
No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 28 ቀን 2010 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካች፡- ሚ/ር አሂም ማርቲን ብራዉን- ጠበቃ ምንዲዬ አንጀል ቀረቡ ተጠሪ፡- ሜድሮክ ፊዉንዳሽን ስፔሻሉስት ኃ/የተ/የግ/ማህበር- ጠበቃ አብደላ ዓሉ ቀረቡ።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ አንድ የሥራ ውለ በገዛ ፈቃደ የተቋረጠበት የሥራ መሪ ያልተጠቀመበትን የአመት እረፍት በገንዘብ ተቀይሮ የሚከፈልበት የሕግ አግባብ መኖር ያለመኖሩን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረዉ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። በዚህ ፍርድ ቤት የአሁኑ አመልካች ከሳሽ፣ የአሁኑ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ የነበሩ ሲሆን የአመልካች የክስ ይዘትም፡- አመልካች ከተጠሪ ጋር የነበራቸዉን የስራ ዉል ከሚያዝያ 19 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ በገዛ ፍቃደ ያቋረጠ ቢሆንም ተጠሪ የተለያዩ ክፍያዎችን ያልፈጸመለት መሆኑን ገልፆ፣ ከ05/03/2004 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 19 ቀን 2004 ዓ.ም ድረስ ያለዉን የ5 ወር ደመወዝ ብር 1,243,758.34፣ የ280 ቀናት የዓመት እረፍት ክፍያ ብር 2,108,984.98፣ የአንድ ዓመት የቤት ኪራይ ብር 228,366.67፣ የልጆች ትምህርት ቤት ክፍያ ብር 242,894.00፣ ቀሪ የአየር ጉዞ ትኬት ብር 1,140,000.00፣ ለስራ ጉዞ ያወጡትን ወጪ ብር 192,925.59፣ የተለያዩ ክፍያዎች ብር 69,881.87፣ የ3 ወር ደመወዝ በፍትሐብሕር ሕጉ መሰረት ብር 652,148.20፣ በድምሩ ብር 5,686,034.00 ተጠሪ እንዱከፍላቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የአሁኑ ተጠሪ ለክሱ በሰጠው መከላከያ መልስም፡- በግራ ቀኝ መካከል በተደረገዉ ዉል ተፈፃሚነት ያለዉ ህግ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ መሆኑን የተስማሙ መሆኑን እና ጉዲዩ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ የሚታይ ከሆነ ደግሞ የቀረበዉ የተለያዩ ክፍያዎች ጥያቄ በይርጋ ቀሪ የሚሆኑ መሆኑን እንደ መጀመሪያ መቃወሚያ ካነሳ በኋላ ፍሬ ነገሩን በተመለከተም አመልካች ለሰሩባቸዉ ጊዜያት ደመወዝ ሲከፈላቸዉ የነበረ መሆኑን፣ አመልካች ከደመወዝ ጋር በተያያዘ በፈጸሙት ህገ ወጥ ተግባር ለ6,000.00 ዩሮ የጀርመንና የኢትዮጵያ መንግስታት የገቢ ግብር እንዲያገኙ ያደረጉ መሆኑን፣እንዱሁም ስራዉን ያቋረጡረት በራሳቸው ፍቃድ በመሆኑ የ3 ወር ደመወዝ ክፍያ በካሳ መልክ ሉከፈላቸዉ የማይገባ መሆኑን፣ የዓመት እረፍት ክፍያም በሁለት ዓመት ባለመጠየቁና በሚመለከተዉ አካል ፍቃድ ያልተላለፈለት በመሆኑ ሉከፈላቸው የማይገባ መሆኑን፣ በዉለ መሰረት አመልካች በራሳቸዉ ቤት እየኖሩ ስለሆነ በዉለ መሰረት ሉከፈላቸዉ የሚገባ ደመወዝ አለመኖሩን፣ የት/ቤት ክፍያ የሚከፈለዉ ዔድሜያቸዉ ከ14 ዓመት በታች ለሆኑት ሕፃናት በመሆኑ እና ለእነማን እንደሚከፈል በክሱ በግልጽ ያልተመለከተ በመሆኑ ለት/ት ቤት ክፍያ በሚል የቀረበዉ ተቀባይነት የላለዉ መሆኑን፣ አመልካች ለእረፍት ወይም ለስራ መሄዲቸዉ ባልተገለጸበት ሁኔታ የጉዞ ትኬት በማለት የጠየቁትም ተገቢነት የላለዉ መሆኑን እና ልዩ ልዩ ክፍያዎች በሚል ያቀረቡትም አግባብነት የላለው ነው የሚለትን ምክንያቶችን በማንሳት ክሱ ውድቅ እንዱሆን ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በዚህ መልኩ የቀረበዉን የግራ ቀኝ ክርክር ከሰማ በኋላ፤ ለአመልካች ደመወዝ ስለመከፈለ ተጠሪ በማስረጃዉ ያላስረዲ በመሆኑና መጠኑንም በተመለከተ ስላልተከራከረ ብር 1,243,758.34፣ የ280 ቀናት የዓመት እረፍት አመልካች መዉሰዲቸውን ገልጾ ተጠሪ ባለመከራከሩ ብር 2,108,984.98፣ አመልካች የቤት ኪራይ ሲከፍል የነበረ መሆኑ በመረጋገጡ ብር 228,366.67፣ አመልካች ከአዱስ አበባ ፍራንክፈርት የደርሶ መልስ የአዉሮፕላን ትኬት እንደሚሰጣቸዉ በቅጥር ዉለ ላይ በተመለከተዉ እና በአመልካች በቀረበዉ ትኬት መሰረት ብር 1,140,000.00፤ በድምሩ ብር 4,721,109.99 ተጠሪ ለአመልካች እንዱከፍል በማለት ሲወስን ቀሪዎቹን የክፍያ ጥያቄዎችን ግን ዉድቅ በማድረግ ወስኗል። ከዚህም በኋላ የአሁኑ ተጠሪ ይግባኙን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቦ ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ የአሁኑ አመልካች የጠየቁትን የ 5 ወር ደመወዝ የከፈለ መሆኑን በተመለከተ አመልካች ተገቢ ክርክርና ማስረጃ ያቀረበ ባለመሆኑ ይሄዉ እንዱከፈል በስር ፍርድ ቤት የተሰጠ ዉሳኔ የሚነቀፍ ሆኖ ያለመገኘቱን፣ የዓመት እረፍት ወደ ገንዘብ ተቀይሮ እንዱሰጠዉ አመልካች ያቀረቡትን ጥያቄ በተመለከተም ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ባቀረበዉ ክርክር አመልካች የዓመት እረፍት ወስደው መጠቀማቸውን ገልፆ ያልተከራከረ በመሆኑ አመልካች የዓመት እረፍቱን በየዓመቱ ሲጠቀሙበት ቆይተዋል በማለት በይግባኝ ክርክር ደረጃ የሚያቀርበዉ ክርክር በፍ/ሥ/ሥ/ ህጉ አንቀጽ 329(1) መሰረት ተቀባይነት ያለዉ ክርክር ያለመሆኑን፣ አዋጅ ቁጥር 377/96 ለጉዲዩ ተፈፃሚነት የላለዉ በመሆኑ አመልካች የዓመት ፍቃድ ጠይቀው እንዱተላለፍላቸው ባላስፈቀደበት ሁኔታ የዓመት እረፍት ወደ ገንዘብ ተቀይሮ እንዱከፈል መጠየቅ አይችልም በማለት የአዋጁን አንቀጽ 79 በመጥቀስ የሚያቀርበዉ ክርክርም ተቀባይነት የለላለው ቢሆንም አመልካች ያልተጠቀሙበት የዓመት እረፍት የ280 ቀናት ወደ ገንዘብ ተቀይሮ እንዱከፈል በስር ፍርድ ቤት የተሰጠ ዉሳኔ የህግ መሰረት የላለው ነው በማለት በዚህ ረገድ የተሰሰጠውን የውሳኔ ክፍል ውድቅ ያደረገው አድርጎታል። እንዱሁም የኪራይ ቤት ክፍያና የአየር ትኬት ለአመልካች እንዱከፈል ተብል መወሰኑም ያላግባብ መሆኑን ጠቅሶ በዚህ ረገድ የተሰጠውን የውሳኔ ክፍል በመሻር በአጠቃላይ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ አሻሽል ተጠሪ ለአመልካች የ5 ወር ከ15 ቀን ደመወዝ ብር 1,243,758.34 (አንድ ሚሉዮን ሁለት መቶ አርባ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሀምሳ ስምንት ከ34/100) ብቻ ከየካቲት 05 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ ገንዘቡ ተከፍል እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር እንዱከፍል በማለት ወስኖል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም የአመልካች የዓመት ፍቃድ የተሰጣቸዉ ስለመሆኑ ተጠሪ ባላስረዲበት ሁኔታ ወደ ገንዘብ ተቀይሮ የማይከፈልበት ምክንያት የላለ መሆኑን፣ የቤት ኪራይና የጉዞ ትኬት ክፍያ ዉሳኔም ዉለን መሰረት ያደረገ ሁኖ እያለ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት መሻሩ ያላግባብ መሆኑን በመግለጽ በአጠቃላይ በእነዚህ ነጥቦች ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጠው ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆኑን ዘርዝሮ ውሳኔው ታርሞ በእነዚህ ነጥቦች ላይ የስር ፍርድ ቤትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የሰጠው ውሳኔ ሉጸና ይገባል በማለት ዲኝነት መጠየቁን የሚያሰይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም የአመት እረፈት በገንዘብ ተቀይሮ ላሰጥ የሚችል መሆኑን በፍትሃብሓር ሕጉ አልተመለከተም ተብል የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ተብል ጉዲዩ ለዚህ ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ ቀርቦም ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጎአል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተመለከተዉን የሚመስል ሲሆን፣ ይህ ችልትም የግራ ቀኝን ክርክር ለሰበር አቤቱታው ምክንያት ከሆነዉ ዉሳኔ እንዱሁም ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን ለዚህ ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር ብቻ እንደሚከተለዉ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መረዲት ለመሆኑ ላይ ግራ ቀኝ ያልተካካደ መሆኑን፣ አመልካች ያቀረቧቸዉን የተለያዩ ክፍያዎች ላለመክፈል የአሁኑ ተጠሪ ካቀረባቸዉ ክርክሮች ዉስጥ አንደ በግራ ቀኝ መካከል በተደረገዉ የቅጥር ዉል ላይ ተፈፃሚነት ያለዉ ህግ አዋጅ ቁጥር 377/96 መሆኑ በዉለ የተመለከተ በመሆኑ አመልካች ያቀረቧቸዉ የክፍያ ጥያቄዎች በአዋጁ መሰረት በይርጋ ቀሪ የሚደረጉ ናቸዉ የሚል የነበረ ቢሆንም አመልካች የተቀጠሩበት ስራ በባህርዉ የስራ መሪ በሚል በአዋጅ ቁጥር 377/96 ስር የተመለከተዉ ዓይነት በመሆኑ ላይ ግራ ቀኝ ክርክር የላላቸው ቢሆንም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት አዋጅ ቁጥር 377/96 የስራ መሪን በሚመለከቱ ጉዲዮች ላይ ተፈፃሚነት እንደላለዉ ይሄዉ አዋጅ በአንቀጽ 3(2-ሐ) ስር በግልጽ መደንገጉን፣ በአዋጁ አንቀጽ 3 ስራ የተመለከተዉ የአዋጁ ተፈፃሚነት ወሰን በህግ አዉጭዉ አካል የተወሰነ፤
መወሰንም የሚገባዉ በመሆኑ የአዋጁን ተፈፃሚነት የመወሰን ጉዲይ በተዋዋይ ወገኖች በድርድር የሚወሰን ላሆን እንደማይችል በምክንያትነት ይዞ በግራ ቀኝ መካከል በተደረገዉ የቅጥር ዉል አንቀጽ 10 በቅጥር ዉለ ተፈፃሚነት ያለዉ የአሰሪና ሰራተኛ ህግ ነዉ በሚል የተመለከተ ቢሆንም፣ ይህ የዉል ቃል የአፈፃፀም ወሰኑን በተመለከተ በአዋጁ አንቀጽ 3(2-ሐ) ስር ከተመለከተዉ ድንጋጌ ጋር የሚጋጭ በመሆኑ ተቀባይነት የላለዉ ነው ወደሚለው ድምዲሜ ይሄንኑን በምክንያትነት በመጥቀስ የቀረበዉ ክስ በይርጋ ይታገዲል በማለት የአሁኑ ተጠሪ የሚያቀርበዉ መከራከሪያ ተገቢነት የለውም በማለት ማለፈን እና በዚህ ረገድ በአሁኑ አመልካችም ሆነ በተጠሪ በኩል የቀረበ የሰበርwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ቅሬታ የላለ መሆኑ ነው። እንዱሁም የዓመት እረፍት ወደ ገንዘብ ተቀይሮ እንዱሰጠዉ አመልካች ያቀረቡትን ጥያቄ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ባቀረበዉ ክርክር አመልካች የዓመት እረፍት ወስደው መጠቀማቸውን ገልፆ ያልተከራከረ በመሆኑ አመልካች የዓመት እረፍቱን በየዓመቱ ሲጠቀምበት ቆይቷል በማለት ተጠሪ በይግባኝ ሰሚው ችልት ያቀረበው ክርክር አዱስ ክርክር ነው ተብል ውድቅ የሆነ ከመሆኑም በላይ አዋጅ ቁጥር 377/96 ለዚህ ጉዲይ ተፈፃሚነት የላለዉ በመሆኑ አመልካች የዓመት ፍቃድ ጠይቀው እንዱተላለፍለት ባላስፈቀደበት ሁኔታ የዓመት እረፍት ወደ ገንዘብ ተቀይሮ እንዱከፈል መጠየቅ አይችልም በማለት የአዋጁን አንቀጽ 79 በመጥቀስ ተጠሪ የሚያቀርበዉ ክርክርም በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተቀባይነት ያለማግኘቱን ተገንዝበናል።
በዚህ ችልት እንዱታይ ወደ ተያዘው መሰረታዊ ጭብጥ ስንመጣም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት አመልካች ያልተጠቀሙበት የዓመት እረፍት የ280 ቀናት ወደ ገንዘብ ተቀይሮ እንዱከፈል በስር ፍርድ ቤት የተሰጠ ዉሳኔ የህግ መሰረት ያለው አይደለም በማለት የሰጠው ውሳኔ ተገቢ መሆን ያለመሆኑን ተመልክተናል። ይግባኝ ሰሚው ችልት እንደገለጸው የዓመት እረፍት አንደ ዓላማዉ ሰራተኛዉ የእረፍት ጊዜ ተጠቅሞ ብቁ በሆነ የአእምሮና የአካል ሁኔታ ወደ ስራዉ እንዱመለስ ማድረግ ነዉ። ከዚህም የምንረዲዉ የዓመት እረፍት ሰራተኛዉ የሚያርፍበት ጊዜ እንጅ የእረፍት ጊዜዉን በስራ ላይ አሳልፍ እረፍቱ ወደ ገንዘብ ተቀይሮ እንዱሰጠዉ መጠየቅ አይደለም። ይህ በመሆኑም በመርህ ደረጃ የእረፍት ጊዜ ወደ ገንዘብ ሉቀየር የማይችል ስለመሆኑ እና ወደ ገንዘብ የሚቀየሩት በየህጎቹ በተመለከቱት ሁኔታዎች ብቻ ስለመሆኑ የአሰሪና ሰራተኛን ግንኙነት በሚገዙ በተለያዩ አዋጆች ተቀባይነት ያገኘ መርህ ነዉ። በተያዘዉ ጉዲይ ላይ ተፈፃሚነት ያለዉ ህግ በፍትሐብሕር ህጉ የስራዎች አገልግልት ለመስጠት የሚደረጉ ዉልች በሚል ርዔስ ከአንቀጽ 2512 ጀምሮ የተደነገገዉ ሲሆን፣ በዚህ ርዔስ ከአንቀጽ 2560-2565 ስር የተመለከቱት ስለ የዓመት እረፍት በተለይ የሚደነግጉ ሲሆን፣ የዓመት እረፍት ከዓመት ዓመት ሉተላለፍ ስለሚችልበት ሁኔታ እንዱሁም የዓመት እረፍት ሲተላለፍ ወደ ገንዘብ ተቀይሮ ሉከፈል የሚቻል መሆን አለመሆኑ በእነዚህ ድንጋጌዎች ስር አልተመለከተም። ለክርክሩ መነሻ በሆነዉ የቅጥር ዉል ስለ የዓመት እረፍት የሚደነግገዉ የዉለ አንቀጽ 5(ሀ እና ለ) ለአሁኑ አመልካች በዓመትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የ42 ቀን የዓመት እረፍት የሚሰጣቸዉ መሆኑን እና የዓመት እረፍት የሚሰጥበትም ጊዜ በግራ ቀኝ መካከል በሚደረግ ስምምነት የሚወሰን መሆኑን የሚደነግግ ቢሆንም፣ የአሁኑ አመልካች ያልተጠቀሙበት የዓመት እረፍት ወደ ገንዘብ ተቀይሮ ላሰጥ ስለሚችልበት ሁኔታ በተለይ የማይደነግግ መሆኑን ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ያረጋገጠው ጉዲይ መሆኑን ተገንዝበናል። ይህ ማለት ግን አመልካች ሳይጠቀሙበት ከዓመት ዓመት የተላለፈ የእረፍት ጊዜ ወደ ገንዘብ ተቀይሮ እንዱሰጣቸው ለመጠየቅ የሚያስችል ከህግም ሆነ ከዉል የመነጨ መብት የላቸውም ወደሚል ድምዲሜ የሚያደርስ አይደለም። ምክንያቱም ይግባኝ ሰሚው ችልት ጉዲዩን ይገዛለ ብል ከጠቀሳቸው የፍትሃብሓር ሕግ ድንጋጌዎች መካከል ለጉዲዩ ቀጥተኛ ተፈጻሚነት ያለው የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2563 ድንጋጌ ውለ በተቋረጠ ጊዜም ሰራተኛው የሚገባውን የእረፍት ጊዜ ለማግኘት መብት አለው የሚል ይዘት ያለው መሆኑ ይህ መብት ተግባራዊ የሚሆነው በገንዘብ ተቀይሮ ነው ተብል ከሚተረጎም በስተቀር ላላ ሰራተኛው የመብቱ ተጠቃሚ አይሆንም የሚል ትርጉም የሚያሰጥ አይደለም። ስለሆነም ለአመልካች የመብት ጥያቄ ሕግ ጥበቃ አድርጎ እያለና የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2563 ድንጋጌም ይዘትና መንፈሱ ሲታይ ውለ መቋረጡ እስከተረጋገጠ ድረስ የአመት እረፍትን የማግኘት መብቱን የጠበቀ መሆኑን የሚያስገነዝብ ሁኖ እያለ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ድንጋጌው ተግባራዊ የሚሆንበትን አግባብ ሳያገናዘብ የአመልካች ጥያቄ የሕግ መሰረት የለውም በማለት የሰጠው የውሳኔ ክፍል ተቀባይነት ያለው ሁኖ አልተገኘም። እንዱሁም ተጠሪ አመልካች የእረፍት ጊዜአቸውን መጠቀማቸውን ወይም በሕጉ አግባብ የተጠቀሙ መሆኑን ሳያስረዲ የገንዘብ መጠኑ ከፍተኛ መሆኑን በመጥቀስ በተጠሪ ላይ ኪሳራ ሉያደርስ የሚችል በመሆኑ የአመልካች ጥያቄ ተቀባይነት የለውም በማለት የአቀረበው ክርክር የሕግ መሰረት የላለው በመሆኑ አልተቀበልነውም። በእነዚህ ሁለ ምክንያቶች ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የአመት እረፈትን በተመለከተ የሰጠው የውሳኔ ክፍል የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2563 ድንጋጌን የጣሰ እና መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ ስለአገኘውም ተከታዩን ወስነናል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/138726 በቀን 18/04/09 ዓ.ም በዋለዉ ችልት ተሰጥቶ በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ በ22/01/2010 ዓ/ም የተሻሻለው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
የዓመት እረፍትን በተመለከተ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የተጠው የዉሳኔ ክፍል ተሸሮ በዚህ ረገድ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁጥር 348 መሰረት ፀንቷል
የመኖሪያ ቤት ኪራይ እና ቀሪ የጉዞ ትኬት ክፍያን በተመለከተ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የተሰጠው የውሳኔ ክፍል በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁጥር 348 መሰረት ጸንቷል።
የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ለተጠሪ የ5 ወር ከ15 ቀን ደመወዝ ብር 1,243,758.34 (አንድ ሚሉዮን ሁለት መቶ አርባ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሀምሳ ስምንት ከ34/100) እና የ280 ቀናት የዓመት እረፍት ብር 2,108,984.98 እንዱከፍል ተብል የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ጸንቷል።
በዚህ ችልት በተደረገዉ ክርክር የወጣዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ ብለናል።