በሕገወጥ ዔቃዎች መረጃ አሰጣጥ፤አያያዝ እና አመዘጋገብ እና የወሮታ ክፍያዎችን ለመወሰን ተሻሽል በወጣው መመሪያ ቁጥር 78/2004 መሰረት ለኢትዮጲያ ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለሥልጣን ጥቆማ ሲቀርብ ወሮታ ስለሚከፈልበት አግባብ መመሪያ ቁጥር 78/2004 አንቀጽ 16/1እና2፤17 www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. LIV
No summary available.
መስከረም 24 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች:- አቶ ስንዳው ታደሰ - አልቀረቡም ተጠሪ፡- የኢትዮጲያ ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለሥልጣን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ነ/ፈጅ ዲኛቸው ጌቴ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ላቀርብ የቻለው አመልካች የካቲት 05 ቀን 2010 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው አቤቱታ በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወል መስተዲድር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. ሰኔ 28 ቀን 2009 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ.37 ሕዲር 29 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አቤቱታ በማቅረቡ ነው።
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ምክንያት የወሮታ ክፍያን የሚመለከት ሲሆን አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። የአሁን አመልካች በሥር ፍ/ቤት ባቀረበው ክስ የቀረጥ እና ታክስ እንዱሁም ወለድ እና ቅጣት መጠናቸው በግምት ብር 2,475,000 /ሁለት ሚልዬን አራት መቶ ሰባ አምስት ሺህ / የሆኑwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ከቀረጥ ነጻ የገቡ የፎበል ደቄት ፊብሪካ ማሽነሪዎች ያላግባብ ለሶስተኛ ወገን ተላልፈዋል በማለት ለተጠሪው መስሪያ ቤት ጥቆማ የሰጠ መሆኑን፤በጥቆማው መሰረት ምርመራ ተደርጎ ንብረቶቹ ለሶስተኛ ወገን መተላለፊቸው የተረጋገጠ መሆኑን በመግለጽ ከዚሁ የገንዘብ መጠን ላይ ብር 495,000 / አራት መቶ ዘጠና አምስት ሺህ ብር / እንዱከፈለው ይወሰንለት ዘንድ ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው።
ተጠሪ በሰጠው መልስ ባልሰበሰበው ቀረጥ እና ታክስ የወሮታ ክፍያ እንዱፈጽም የማይገደድ መሆኑን፤ከቀረጥ ነጻ የገቡትን ዔቃዎች ድርጅቱ ለብድር ዋስትና በማስያዝ ከዲሸን ባንክ ብድር ተበድሮ ድርጅቱ ብድሩን መመለስ ባለመቻለ ባንኩ በአዋጅ 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በሕጋዊ ጨረታ ለቅን ልቦና 3ኛ ወገን ያስተላለፊቸው መሆኑን፤በመመሪያ ቁጥር 78/2004 ከቀረጥ ነጻ የገባን ዔቃ በማስተላለፍ የቀረበን ጥቆማ ክፍያ የሚፈጸመው ዔቃው ከተያዘ በኋላ ቀረጥ እና ታክስ ተሰልቶ ከሚገኘው ገንዘብ ሆኖ ሳለ ባልተያዘ ንብረት እና ባልተሰበሰበ ቀረጥ እና ታክስ ላይ ወሮታ እንዱከፈል የቀረበው ክስ ሕጋዊ አለመሆኑን እና በክሱ የተገለጸው የገንዘብ መጠን ያልታወቀ እና ምንም ዓይነት ማስረጃ ያልቀረበበት መሆኑን በመግለጽ የአመልካች ክስ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍ/ቤት የግራቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ ዔቃዎቹ ለብድር በያዘው ዲሸን ባንክ ተሸጠው ለ3ኛ ወገን የተላለፈ በመሆኑ ንብረቶቹን በመያዝ እና በመሸጥ ቀረጥ እና ታክስ ለመሰብሰብ የሚቻል አይደለም፤ድርጅቱም ስራ ስላቆመ ላልች ንብረቶችን ማግኘት አልተቻለም፤በመመሪያ ቁጥር 78/2004 መሰረት ወሮታ የሚከፈለው ዔቃው ከተያዘ በኋላ ተሰልቶ ከሚገኘው ገንዘብ ላይ ነው፤ባንኮች ብድራቸውን ለማስመለስ ቀዲሚ መብት ስላላቸው ዔቃው የተሸጠ በመሆኑ ባልተያዘ እና ባልተሰበሰበ ቀረጥ እና ታክስ ላይ የሚከፈል ወሮታ የለም በማለት ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም አቤቱታው ተቀባይነት አላገኘም። የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- አመልካች በሰጠሁት ጥቆማ መሰረት ምርመራ ተጣርቶ ማሽነሪዎቹ ለላላ ሶስተኛ ወገን መተላለፊቸው ተረጋግጧል፤www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
አመልካች በሕግ የተፈቀደልኝን 20% የወሮታ ክፍያ ተጠሪ እንዱከፍለኝ የጠየቅኩ ቢሆንም ተጠሪ መስሪያ ቤት ንብረቶቹን ገቢ ማድረግ ሲኖርበት ሀላፉነቱን ሳይወጣ ባንኮች ንብረቱን ለመሸጥ መብት አላቸው የሚል ምክንያት በመስጠት ለመክፈል ፈቃደኛ አይደለም፤ጥቆማ የቀረበባቸው ማሽነሪዎች ከቀረጥ እና ታክስ ነጻ መግባታቸው እና ቀረጥ እና ታክሳቸው ሳይከፈል ወደ 3ኛ ወገን የተላለፈ መሆኑ አልተካደም፤
ከቀረጥ ነጻ ሆኖ ወደ ሀገር ውስጥ የገባ ዔቃ ቀረጥ እና ታክሱ ሳይከፈልበት ተመሳሳይ የቀረጥ ነጻ መብት ለላለው ማንኛውም ሰው ማስተላለፍ ወይም የቀረጥ ነጻ መብት ከተሰጠበት ዓላማ ውጪ መገልገል ወይም በላልች ሰዎች ይዞታ እና አገልግልት እንዱውል ማድረግ የተከለከለ ሲሆን ይህንኑ የተላለፈ ማንኛውም ሰውም የወንጀል ሀላፉነት አለበት፤ባንኮች የቀረጥ ነጻ መብት በሕጉ ከተቀመጠው ዓላማ ውጪ እንዱያውለ አልተፈቀደላቸውም፤ባንኩ ንብረቶቹን በዋስትና ሲይዝ ከቀረጥ ነጻ የገቡ መሆናቸውን ያውቃል፤ተጠሪ ጥቆማው ከደረሰው በኋላ ምርመራውን በአግባቡ ባለማከናወኑ መጠኑ ሉታወቅ ያልተቻለ ቢሆንም አመልካች ተገቢውን ጥቆማ የሰጠሁ በመሆኑ ወሮታው ሉከፈለኝ ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ከቀረጥ ነጻ የገባው ዔቃ ለባንክ ብድር መያዣበመዋለ ምክንያት አመልካች በአዋጅ ቁጥር 622/2008 እና አዋጅ ቁጥር 859/2008 መሰረት የጠየቁት የወሮታ ክፍያ ሉያገኙ አይገባም ተብል በስር ፍ/ቤቶች የመወሰኑን አግባብነት ለማጣራት ሲባል ጉዲዩ በዚህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል።
ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የተጠሪ መልስ ይዘት በአጭሩ፡- የንጋት ጸሐይ ደቄት ፊብሪካ ከዲሸን ባንክ ጋር ለፈጸመው የብድር ውል ማሽነሪዎቹን በዋስትና ያስያዘው ጥቅምት 29 ቀን 1999 ዓ.ም በመሆኑ ለጉዲዩ አግባብነት ያለው አዋጅ ቁጥር 622/2001 እና 859/2006 ሳይሆን በወቅቱ የነበረው አዋጅ ቁጥር 60/90 ነው፤ድርጅቱ ዔቃዎቹን በዋስትና ባስያዘበት ጊዜ በስራ ላይ የነበረው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 60/89 / እንደተሻሻለው / ከቀረጥ ነጻ የገቡ ዔቃዎችን ለባንኩ ብድር በመያዣነት ሉውለ እንደሚችለ በግልጽ የሚፈቅድም ሆነ የሚከለክል ድንጋጌ የለውም፤ዔቃዎቹም ከቀረጥ ነጻ የገቡ ስለመሆናቸው ባልተረጋገጠበት እና በማስረጃ ባልተደገፈበት ሁኔታ የጠቋሚ ወሮታ የሚከፈልበትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
አግባብ የለም፤መመሪያ ቁጥር 78/2004 የወጣውም አዋጅ ቁጥር 622/2001 ለማስፈጸም ሲሆን ድርጊቱ ተፈጸመ የተባለው ደግሞ አዋጅ እና መመሪያው ከመውጣቱ በፉት በመሆኑ ጠቋሚው ከመጀመሪያውኑ ወሮታ የማግኘት መብት አልተጎናጸፈም፤ድርጅቱ ምን ዓይነት ዔቃዎችን እንዲስገባ? መቼ እዲስገባ? ምን ያህል ቀረጥ እና ታክስ መክፈል እንደነበረበት? ያልተረጋገጠ በመሆኑ ይህ ሳይረጋገጥ ወሮታ የሚከፈልበት ሕጋዊ ምክንያት የለም፤ዔቃዎቹ በቀረጥ ነጻ የገቡ ናቸው የሚባል ቢሆን እንኳን ከቀረጥ ነጻ የገቡ ዔቃዎችን ባንክ ዋስትና ይዞ በሚሸጥበት ጊዜ ወሮታ ይከፈላል የሚል ሕግ የለም፤ግለሰቡ ከመጀመሪያውም የሰጠው መረጃ እንጂ ጥቆማ አይደለም፤በመመሪያ ቁጥር 78/2004 አንቀጽ 5/1/ሀ በህዝብ የሚታወቁ ሕገወጥ ዔቃዎች የሚገኙባቸውን ቦታዎች መጠቆም ባለመብት የሚያስደርግ ጥቆማ አይደለም፤ከቀረጥ ነጻ የገቡ ቢሆንም በሕጋዊ ሁኔታ ወደ 3ኛ ወገን የሚተላለፈበት ሁኔታ አለ፤ይህ በሕግ የተቀመጠ ልዩ ሁኔታ እያለ ለመንግስት ተጨባጭ ማስረጀ ባልሰጠበት እና መንግስት ከጥቆማው ያገኘው ጥቅም በላለበት ሁኔታ ወሮታ ሉከፈል አይገባም፤በመመሪያ ቁጥር 78/2004 አንቀጽ 16/1 እና 2 አንድ ጠቋሚ ወሮታ ሉሰጠው የሚችለው ሕገወጥ ዔቃው ከተያዘ እና ለባለስልጣኑ ገቢ ከተደረገ ነው፤ወሮታ ማግኘት የሚችለውም ለባለስልጣኑ ገቢ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ ነው፤የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር በባንክ በዋስትና የተያዙ ንብረቶች ሲሸጥ የተገኘው ገቢ በቅድሚያ የባንክ እዲ ለመሸፈን በማዋል ቀሪ ገንዘብ ካለ ብቻ ለመንግስት ዔዲ ክፍያ እንዱውል የወሰነ በመሆኑ አቤቱታው ተቀባይነት የለውም የሚል ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። እኛም እንዱጣራ የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረነዋል።
አመልካች ከቀረጥ ነጻ ሆነው ወደ ሐገር ውስጥ የገቡ የፎበል ደቄት ፊብሪካ ማሽነሪዎች አላግባብ ለሶስተኛ ወገኖች ተላልፈዋል በማለት ለተጠሪው መስሪያ ቤት ጥቆማ የሰጠ መሆኑን፤ንብረቶቹ የተላለፈለት የንጋት ጸሐይ ደቄት ፊብሪካ ከዲሸን ባንክ ጋር ለፈጸመው የብድር ውል ጥቅምት 29 ቀን 1999 ዓ.ም ማሽነሪዎቹን በዋስትና ያስያዘ መሆኑን፤ተበዲሪው ድርጅት ከባንኩ የተበደረውን ገንዘብ መክፈል ስላቃተው ባንኩwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በአዋጅ 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ንብረቶቹን በሕጋዊ ጨረታ ለቅን ልቦና 3ኛ ወገን ያስተላለፊቸው መሆኑን፤ከቀረጥ ነጻ ገብተዋል የተባለት ዔቃዎች ምን ዓይነት ዔቃዎች እንደሆኑ? መቼ እንደገቡ? የቀረጥ እና ታክስ መጠናቸው ምን ያህል እንደሆነ የማይታወቅ መሆኑን እና ተጠሪው መስሪያ ቤት ከንብረቶቹ የሰበሰበው የቀረጥ እና ታክስ ክፍያ የላለ መሆኑን ከክርክሩ ሑደት መገንዘብ ችለናል።
የሕገወጥ ዔቃዎች መረጃ አሰጣጥ፤አያያዝ እና አመዘጋገብ እና የወሮታ ክፍያዎችን ለመወሰን ተሻሽል የወጣው መመሪያ ቁጥር 78/2004 አንቀጽ 16/1እና2 ድንጋጌ ለባለሥልጣኑ በሚቀርብ ጥቆማ ወይም ያለጥቆማ ሕገወጥ ዔቃው ከተያዘ እና ለባለስልጣኑ ገቢ ከተደረገ ጠቋሚው፤ያዥው፤ትብብር እና ድጋፍ ያደረጉት በሙለ በመመሪያው መሰረት ወሮታ የሚከፈላቸው መሆኑን፤የወሮታው ክፍያ የሚከፈለውም ሕገወጡ ዔቃ በመመሪያው አንቀጽ 17 መሰረት ለባለስልጣኑ ገቢ ከሆነበት ቀን ጀምሮ መሆኑን በመግለጽ ይደነግጋል።
በያዝነው ጉዲይ አመልካች ከቀረጥ ነጻ ሆነው ወደ ሐገር ውስጥ የገቡ የፎበል ደቄት ፊብሪካ ማሽነሪዎች አላግባብ ለሶስተኛ ወገኖች ተላልፈዋል በማለት ለተጠሪው መስሪያ ቤት ጥቆማ የሰጠ መሆኑን በመግለጽ የወሮታ ክፍያው ሉከፈለኝ ይገባል በማለት የሚከራከር ቢሆንም ከቀረጥ ነጻ ገብተዋል የተባለት ንብረቶች የተላለፈለት የንጋት ጸሐይ ደቄት ፊብሪካ ከዲሸን ባንክ ጋር በፈጸመው የብድር ውል ጥቅምት 29 ቀን 1999 ዓ.ም ማሽነሪዎቹን በዋስትና አስይዞ ከባንኩ የተበደረውን ገንዘብ መክፈል ስላቃተው ባንኩ በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ንብረቶቹን በሕጋዊ ጨረታ ለቅን ልቦና 3ኛ ወገን ገዢ በሽያጭ ያስተላለፊቸው በመሆኑ፤ከቀረጥ ነጻ ገብተዋል የተባለት ዔቃዎች ምን ዓይነት ዔቃዎች እንደሆኑ? መቼ እንደገቡ? የቀረጥ እና ታክስ መጠናቸው ምን ያህል እንደሆነ የማይታወቅ ከመሆኑም ባሻገር ተጠሪው መስሪያ ቤት ከንብረቶቹ የሰበሰበው የቀረጥ እና ታክስ ክፍያ የለም።
የሕገወጥ ዔቃዎች መረጃ አሰጣጥ፤አያያዝ እና አመዘጋገብ እና የወሮታ ክፍያዎችን ለመወሰን ተሻሽል የወጣው መመሪያ ቁጥር 78/2004 አንቀጽ 16/2 የወሮታው ክፍያ የሚከፈለው ሕገወጡ ዔቃ በመመሪያው አንቀጽ 17 መሰረት ለባለስልጣኑ ገቢ ከሆነበት ቀን ጀምሮ ነው በማለት የሚደነግግ በመሆኑ እና አመልካች ጥቆማ ሰጥቸበታለሁwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የሚለው ከቀረጥ ነጻ ሆኖ የገባው ዔቃ ባንኩ ላበደረው ብድር መክፈያ ይውል ዘንድ በሽያጭ የቅን ልቦና ገዢ ለሆነ 3ኛ ወገን የተላለፈ እና ለተጠሪው መስሪያ ቤት ያልገባ እና ቀረጥ እና ታክስ ያልተሰበሰበበት በመሆኑ በመመሪያው መሰረት ለአመልካች ሉከፈል የሚችል የወሮታ ክፍያ ስለማይኖር የስር ፍ/ቤቶች ይህንኑ መሰረት በማድረግ አመልካች ወሮታ እንዱከፈለው ያቀረበውን ክስ ውድቅ በማድረግ የሰጡት ውሳኔ በአግባቡ ነው ከሚባል በቀር የተፈጸመ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥሕተት አላገኘንበትም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወል መስተዲድር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. ሰኔ 28 ቀን 2009 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ.37 ሕዲር 29 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥሕ/ቁ 348/1 መሰረት ጸንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ግራቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።