ከቅጅ መብት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ክርክሮች የሚጣሩበት አግባብም ሆነ ክርክሮቹን መሰረት በማድረግ የሚሰጡ ዉሳኔዎች የቅጅ መብት ጥበቃ አጠቃላይ ዓላማ እነ አረቡ አብደላ ( 3 ሰዎች) እና www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. LIII በማድረግ የቅጅ እና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ ለማግኘት ስራዎቹ ማሟላት የሚጠበቅባቸዉ መመዘኛዎች መሟላታቸው አለመሟላታቸውን ስለ ቅጅ መብት ዔዉቀትና ልምድ ያላቸዉ ባለሙያዎች የተካተቱበትን አጣሪ ቡድን በማቋቋም እንዱያጣሩ በማድረግ የቅጅ መብት ጥሰት የተፈፀመ መሆን አለመሆኑን በማጣራት መወሰን ያለበት ስለመሆኑ በኢፋዱሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 91(3) ፤አዋጁ ቁጥር 410/96 አንቀጽ 2(8)፣2(30)፣ 4(1)(ለ)፣ 6(1) አደኛ ጓዳ
No summary available.
ቀን - 28/01/2011ዓ.ም ዳኞች፡- ዲኜ መላኩ ተኽሉት ይመሰል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራዉ አመልካቾች፡-
ተጠሪ፡- አደኛ ጓዳ- ከጠበቃ ሰለሞን ጋር ቀርበዋል።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ክርክሩ የተጀመረዉ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን፤ ተጠሪ ከሳሽ፣ አመልካቾች ደግሞ፣ በቅደም ተከተል፣ ከ1-3ኛ ተከሳሾች በመሆን ተከራክረዋል። ተጠሪ በቀን 01/07/07 ዓ.ም አዘጋጅተዉ ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት ክስ፡- ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በገበያ ላይ የነበሩ እና እንደገና ተሻሽለዉ በ2006 ዓ.ም ታትመዉ በአእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ከተመዘገቡት አድቫንስድ ዎርሉድ ኢንግሉሽ ቡክ 1 እና 2 መጽሀፍችን አዘጋጅተዉ መጽሐፍቹም በ 15,000 ኮፒ ታትመዉ ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ ገበያ ላይ መዋላቸዉን እና በገበያ ተቀባይነት አግኝተዉ ኮፒዎቹ ሙለ እንደተሸጡ፤ ይሁንና ያለ ከሳሽ ፈቃድ 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ምሳላዎችን፣ አገላለፆቹን እና ማብራሪያዎቹን ቃል በቃል እና በማመሳሰል በቀጥታ ከከሳሽ መጽሐፍች በመቅዲት ኢክስትሪም ስሪዬስ እንግሉሽ ፍር ግሬድ 11-12 በሚል ርዔስ አዘጋጅተዉ መሸጣቸዉን እና 1ኛ ተከሳሽም መጽሐፍቹን ማሳታሙን፤ ከሳሽ ያዘጋጃቸዉ 8,000.00 መጽሐፍችም በዚህ ምክንያትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ገዥ አጥተዉ በከሳሽ ላይ የብር 200,000.00 ኪሳራ መድረሱን ጠቅሰዉ ብር 100,000.00 የሞራል ኪሳራን ጨምሮ ብር 300,000.00 ተከሳሾች እንዱከፍለ፣ እንዱሁም የታተሙት እንዱወገደ እና ለወደፉትም እንዲይታተሙ ይወሰንላቸዉ ዘንድ ዲኝነት ጠይቀዋል።
1ኛ አመልካች ለክሱ በሰጡት መልስ፤ ከከሳሽ መጽሐፍ አልተገለበጠም እንጂ ተገልብጧል ቢባል እንኳ ከሳሽ የስራዬ አካል ናቸዉ የሚላቸዉ ጽንሰ ሃሳቦች ከብሓራዊ ፈተና የተወሰደ ጥያቄዎች እና ምሳላዎች፣ ማብራሪያዎች እና አገላለፆች የህዝብ ንብረት መሆናቸዉን፤ በመጽሐፍቹ መካከል መመሳሰል አለ ቢባል እንኳ ስራዎቹ የእንግሉዘኛ መማሪያ መፅሀፍት፣ ካሪኩለም፣ ሀገር አቀፍ ፈተናዎችን መሰረት በማድረግ የታወቁ ሳይንሳዊ የቋንቋ አፃፃፍ መርሆ ስርዓትና ህግ በመከተል ተቀራራቢ የእንግሉዘኛ ትምህርት ዝግጅት ባላቸዉ መምህራን የተዘጋጁ በመሆናቸዉ ምክንያት መሆኑን ጠቅሰዉ ከሳሽ የቅጅ መብት እንደላላቸዉ፣ የተጠየቀዉ የጉዲት ካሳ መጠንም ማስረጃን መሰረት ያላደረገ መሆኑን ጠቅሰዉ የተከራከሩ ሲሆን፤ 2ኛ ተከሳሽም 1ኛ ተከሳሽ ካቀረቡት ጋር ተመሳሳይ ይዘት ያለዉ ክርክር በማንሳት ተከራክረዋል። 3ኛ ተከሳሽ ባለመቅረባቸዉ ክርክሩ በላለበት ታይቷል።
ጉዲዩ በመጀመሪያ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ከግራ ቀኝ በዚህ መልኩ የቀረበዉን ክርክር ከሰማ በኋላ፣ ተጠሪ ያቀረቧቸዉ ማስረጃዎች አመልካቾች ከተጠሪ መጽሀፍ ቃል በቃል ወስደዋል ከማለት ዉጪ ምን ያህል ፏርሰንት እንደተወሰደ፣ የትኛዉ አገላለጽ፣ የትኛዉ ምሳላ እና ማብራሪያ በቀጥታ እንደተወሰደ እንዱሁም የቋንቋ አፃፃፍ መርሆዎች እና ጽንሰ ሃሳቦቹ በአገላለጽ፣ ማብራሪያ እና ምሳላዎቹ በተለያየ አገላለጽ እና ዘይቤያዊ አነጋገር፣ የአሰራር ሂደቱ እና ዘዳዉ፣ ተጠሪ ያወጣዉ ማዉጫ እና ምዔራፍ በተለየ ሲስተም የተብራራ እና የተተነተነ መሆኑ እንዱሁም ከግራመር አጠቃቀም ሁኔታ አንፃር ሲታይ የአመልካች ስራ በቀጥታ ከተጠሪ የተወሰደ መሆኑን በአግባቡ የሚያስረዲ ማስረጃ አለመቅረቡን ጠቅሶ የቀረበዉን ክስ ዉድቅ በማድረግ ወስኗል።
ተጠሪ በዚህ ዉሳኔ ባለመስማማት ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በበኩለ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ተጠሪ ካዘጋጃቸዉ መጽሐፍት የእንግሉዝኛ ቋንቋ ማሳያ ምሳላዎችንና ማብራሪያዎችን በቀጥታ ምንጭwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ሳይጠቅሱ ወስደዉ በጽሐፊቸዉ የተጠቀሙ ስለመሆኑ ተጠሪ ካቀረባቸዉ የሰዉ ምስክሮች በተጨማሪ የኮተቤ ዩንቨርሲቲ ኮላጅ ለቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሉስ የወንጀል ምርመራ ዱቪዝዮን በላከዉ ደብዲቤ የተረጋገጠ መሆኑን፤ ይህም በአገራችን የቅጅ መብት ጥበቃ የተደረገዉ ለሃሳብ አገላለጽ ቅርጽ ከመሆኑ እና ከቅጅ መብት ጥበቃ አስፈላጊነት አንፃር ሲታይ የተጠሪ የቅጅ መብት በተጠሪ የተጣሰ መሆኑን የሚያሳይ መሆኑን በመጥቀስ አመልካቾች ኃላፉነት አለባቸዉ በሚል የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤትን ዉሳኔ ሽሮ በአመልካቾች ላይ ሉወሰድ የሚገባዉን እርምጃ በተመለከተ የግራ ቀኝን ክርክር በመስማት ተገቢዉን እንዱወስን ሲል መዝገቡን ወደ ስር ፍርድ ቤት በመመለስ ወስኗል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበዉም በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ሲሆን፣ አመልካቾች በቀን 07/06/2010 ዓ.ም አዘጋጅተዉ ባቀረቡት 8 ገጽ የሰበር አቤቱታ የተጠሪ ስራዎች በአዋጅ ቁጥር 410/96 አንቀጽ 6(1)(ሀ) ስር የተመለከተዉን የወጥነት መመዘኛ የማያሟላ መሆኑን፣ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፖሉስን የምርመራ መዝገብ በማስረጃነት ያስቀረበበት ሂደትም የአመልካቾችን የመከራከር መብት የሚያጣብብ መሆኑን፣ 1ኛ አመልካች የመጽሐፍቹ አሳታሚ ወይም አዘጋጅ ስለመሆናቸዉ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ “አረቡ አብደላ ኤክስትሪም ቡክ ሲሪየስ” የሚል በስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያልነበረዉን አዱስ ስያሜ በመስጠት 1ኛ አመልካች ኃላፉነት እንዲለባቸዉ መወሰኑን እና ላልችንም ነጥቦች በመዘርዘር ታርሞ ይወሰንላቸዉ ዘንድ ዲኝነት ጠይቀዋል። አቤቱታዉ ተመርምሮ አመልካቾች የቅጅ መብት ጥሰት ፈጽመዋል ተብል የመወሰኑን አግባብነት ግራ ቀኝ በተገኙበት አከራክሮ ለመወሰን ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ በተደረገለት ጥሪ መሰረት ቀርበዉ ግራ ቀኝ ክርክራቸዉን በጽሐፍ ተለዋዉጠዋል።
ከስር ጀምሮ የክርክሩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ሲታይ ከፍ ሲል የተመለከተዉን ሲመስል ይህ ችልትም ለሰበር አቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉን ዉሳኔ ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመረዉም፡-www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ተጠሪ ለክሱ መሰረት ባደረጋቸዉ ሁለቱ መጽሐፍች ላይ የቅጅ መብት አላቸዉ ወይስ የላቸዉም? መብት አላቸዉ የሚባል ከሆነ አመልካቾች የቅጅ መብት ጥሰት ፈጽመዋል አልፈጸሙም?
1ኛ አመልካች ለተጠሪ ስለሚኖረዉ ኃላፉነት ተለይቷል ወይስ አልተለየም?
የሚለ የዚህን ችልት ምላሽ የሚያስፈልጋቸዉ ጭብጦች ሆነዉ ተገኝተዋል።
በመሰረቱ የቅጅ መብት አጠቃላይ ዓላማ የፈጠራ ባለሞያዎች የፈጠራ ስራዎቻቸዉን ለማከናወን ያፈሰሱትን ዔዉቀት፣ ጊዜና ሀብት እንዱያካክሱና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ ሆነዉ ለተጨማሪ የፈጠራ ስራ እንዱነሳሱ በማድረግ ቀጣይ የፈጠራ ስራን በማበረታት ኢንቨስትመንት እንዱበረታታ አቅም ለመፍጠር ሲሆን፤ ኢ- ቁሳዊ ከሆኑ የንብረት መብቶችም አንደ ገጽታ ነዉ። በመሆኑም መንግስት በኢፋዱሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 91(3) ስር የተመለከተዉን ኪነጥበብን፣ ሳይንስና ቴክኖልጅን ለማስፊፊት ባለበት ግዳታ መሰረት፣ የቅጅ እና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 410/96 አወጥቶ ስራ ያዋለ ሲሆን፤ ለአዋጁ መዉጣት አስፈላጊ ከሆኑት ምክንያቶች ዉስጥም አንደ የስነ ጽሐፍ፣ የኪነ ጥበብ እና ተመሳሳይ የፈጠራ ስራዎች የአንድ አገር ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ሳይንሳዊ እና ቴክኖልጂያዊ ልማት በማፊጠን ረገድ ትልቅ ሚና የሚጫወቱ በመሆናቸዉ የሚበረታቱበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ስለመሆኑ ከአዋጁ መግቢያ ላይ ከተመለከተዉ መረዲት ይቻላል። ይህን አጠቃላይ ዓላማ ለማሳካት ይቻል ዘንድም አዋጁ የቅጅ መብትን የሚያስገኙ ስራዎች፣ ጥበቃ የማይደረግላቸዉ ስራዎች ዓይነት፣ የቅጅ መብት ጥበቃ ለማግኘት የሚያስፈልጉ መመዘኛዎችን ጨምሮ የተለያዩ ድንጋጌዎችን ያስቀምጣል። አዋጁ የስራዉ አመንጪ በስራዉ ላይ የሚኖራቸዉን ኢኮኖሚያዉ እና የሞራል መብቶችን የሚደነግግ ሲሆን፤ ኢኮኖሚያዊ መብት ስራዉን የማባዛት፣ የመከወን፣ ብሮድካስት የማድረግ፣ ወደ ላልች ስራዎች የመለወጥና ላልች ብቸኛ መብቶችን የሚያካትት ሲሆን፤ የሞራል መብቱ ደግሞ የፈጠራ ስራዉ አመንጪ የመባል፣ ስራዎቹ እንዲይዛቡ የማድረግና መሰል መብቶችን የሚያካትት ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 7 እና 8 ከተመለከቱት ድንጋጌዎች መረዲት ይቻላል። ይህ በመሆኑም ያለፈቃደ በአዋጁ አንቀጽ 7(1) ስር የተመለከቱት ተግባራት በልላ ሰዉ እንዲይፈጸሙ የስራዉ አመንጪ የመከልከል መብት ያለዉ ሲሆን፤ በዚህ ስር ከተመለከቱት ዉስጥም አንደ ስራን ማመሳሰል፣ ማቀናበር ወይም ወደ ላላ ዓይነት መቀየር የማይቻል መሆኑንwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በተመለከተ በአንቀጽ 7(1)(ሐ) ስር የተመለከተዉ ነዉ። የተጠሪ የዲኝነት ጥያቄም ይህኑን መሰረት ያደረገ ሆኖ በመጽሐፍቼ ላይ የተመለከቱትን ምሳላዎች፣ አገላለጾችን እና ማብራሪያዎችን አመልካቾች ያለ ተጠሪ ፈቃድ ወስደዉ ኢክስትሪም እንግሉሽ ፍር ግሬድ 11-12 በሚል መጽሐፍ አካተዉ አሳትመዋል የሚል ሲሆን፤ አመልካቾች በበኩላቸዉ ኃላፉነት የለብንም ሲለ አጥብቀዉ የሚከራከሩት የተጠሪ መጽሐፍቶች የትምህርት ሚኒስቴር ያዘጋጀዉን ካሪኩለም፣ ሲለበስ፣ የተማሪዎች መማሪያ መጽሐፍት፣ የመምህር መምሪያን ይዘትና ዓላማን መሰረት በማድረግ የታወቀና ሳይንሳዊ የእንግሉዘኛ ቋንቋ አፃፃፍ ስርዓትን እና ሰዋሰዉ መርህን እና ጽንሰ ሃሳቦችን መሰረት በማድረግ በመሆኑ የተጠሪ ስራ በቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ የተመለከተዉን የወጥነት መመዘኛ የማያሟላ መሆኑን፤ እንዱሁም በመጽሐፍቹ መካከል መመሳሰል አለመኖሩን ስለመሆኑ የግራ ቀኝ ክርክር ይዘት ያስገነዝባል።
የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኝን የሰዉ ምስክር የሰማ ሲሆን፣ በመጨረሻ የተጠሪን የዲኝነት ጥያቄ ዉድቅ በማድረግ ሲወስን እንደ ምክንያት የጠቀሰዉ የተጠሪ መጽሐፍች መርሆዎቹ እና ጽንሰ ሃሳቦቹ በአገላለጽ፣ ማብራሪያ እና ምሳላዎች በተለያየ አገላለጽ እና ዘይቤያዊ አነጋገሩ፣ የአሰራር ሂደቱ፣ የአሰራር ዘዳዉ፣ ማዉጫዉ እና ምዔራፈ፣ እንዱሁም የግራመር አጠቃቀሙ የተጠሪ ስራ ስለመሆኑ፤ እንዱሁም የተጠሪዎች መጽሐፍች ቀጥታ ከተጠሪ ስራዎች የተገለበጡ ስለመሆኑ በማስረጃ አልተረጋገጠም በሚል ሲሆን፤ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በበኩለ አመልካቾች ኃላፉነት አለባቸዉ በሚል ድምዲሜ ላይ የደረሰዉ አመልካቾች ያዘጋጁት መጽሐፍ ተጠሪ ካዘጋጃቸዉ መጽሐፍች ጋር ከፍተኛ መመሳሰል ያለ ስለመሆኑ የኮቴቤ ዩኒቨርሲቲ ቀደም ሲል ለወንጀል ምርመራ ዓላማ ለፖሉስ ጽ/ቤት ጽፍ የነበረዉ ደብዲቤ የሚያስረዲ መሆኑን በመጥቀስ ስለመሆኑ ከየዉሳኔዎቹ ይዘት መገንዘብ ይቻላል።
ከቅጅ መብት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ክርክሮች የሚጣሩበት አግባብም ሆነ ክርክሮቹን መሰረት በማድረግ የሚሰጡ ዉሳኔዎች፣ ከፍ ሲል የተመለከተዉን፣ የቅጅ መብት ጥበቃ አጠቃላይ ዓላማ መሰረት ሉያደርጉ የሚገባ በመሆኑ፤ የተጠሪ ስራ ወጥነት ያለዉ መሆን አለመሆኑ እንዱሁም የአመልካቾች ስራዎች ከተጠሪ ስራዎች የተወሰደ መሆን አለመሆኑ ይህኑን ግምት ባስገባ መልኩ መጣራት አለበት የሚል እምነት አለን።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
አዋጅ ቁጥር 410/96 አንቀጽ 2(30) የቅጅ መብት ጥበቃ የሚደረግላቸዉን ስራዎች ዓይነት ሲዘረዝር፣ የአዋጁ አንቀጽ 6 በስራዎቹ ላይ የቅጅ መብት ጥበቃ ለማግኘት አስፈላጊ የሆኑ መመዘኛዎችን ይደነግጋል። በዚህም መሰረት አንድ ሰዉ የቅጅ እና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ ለማግኘት፣ ስራዎቹ ሁለት መመዘኛዎቹን ማሟላት የሚጠበቅባቸዉ ሲሆን፤ የመጀመሪያዉ ወጥ (original) መሆኑ ሲሆን፣ ሁለተኛዉ ግዙፍነት ያለዉ መሆኑ ነዉ። ወጥነት በስራ አመንጪዉ የተሰራዉ ስራ ሙለ በሙለ ከላልች ስራዎች ያልተቀዲ መሆን እንዲለበት የሚገልጽ ሃሳብ ሲሆን፤ ስራዎቹ ከላልች ስራዎች ጋር በፍጹም መመሳሰል የለባቸዉም ማለት እንዲልሆነ ግን መገንዘቡ ተገቢ ነዉ። ይልቁንም ስራዉ ወጥነት ያለዉ መሆን አለመሆኑን በማረጋገጥ ረገድ መታየት የሚገባዉ ነጥብ፣ በስራዉ ላይ የተለየ የባለ ስራዉ ችልታ (skill)፣ ጉልበት (labour) ስራ ላይ መዋለ፤ እንዱሁም፣ በተለይም በአዋጁ አንቀጽ 4(1)(ለ) ስር ከተመለከተዉ አንፃር ሲታይ፣ የስራዉ ባለቤት ስራዉን ሲሰራ የራሱ የሆነ የአገላለጽ መንገድ፣ ዘዳ እና ስታይል የተጠቀመ መሆን አለመሆኑ ስለመሆኑ መገንዘቡ ተገቢ ነዉ። ግዙፊዊ መሆን አለበት ሲልም፣ ስራዉ በሃሳብ ደረጃ የቀረ ሳይሆን በወረቀት ላይ የሰፈረ ላሆን ይገባል ለማለት እንደሆነ ከድንጋጌዉ ይዘት እና መንፈስ መገንዘብ ይቻላል። በአጠቃላይ በአዋጁ የተመለከቱት የወጥነት እና የግዙፊዊነት መስፈርቶች መሰረተ ሃሳብ ከላይ የተመለከቱ ሲሆኑ፣ የስራዉ አመንጪ የሰራዉ ስራ እነዚህን መስፈርቶች ማሟላቱ ከተረጋገጠ ያለ ምንም ላላ ቅድመ ሁኔታ የቅጅ መብት ጥበቃ የሚሰጠዉ ስለመሆኑም አዋጁ ያመለክታል።
ከፍ ሲል እንደተመለከተዉ፣ አመልካቾች የተጠሪ ስራ የወጥነትን መስፈርት አላሟላም በማለት የሚከራከሩት፣ የተጠሪ መጽሐፍቶች የትምህርት ሚኒስቴር ያዘጋጀዉን ካሪኩለም፣ ሲለበስ፣ የተማሪዎች መማሪያ መጽሐፍት፣ የመምህር መምሪያን ይዘትና ዓላማን መሰረት በማድረግ የታወቀና ሳይንሳዊ የእንግሉዘኛ ቋንቋ አፃፃፍ ስርዓትን እና ሰዋሰዉ መርህን እና ጽንሰ ሃሳቦችን መሰረት ያደረጉ መሆኑን ነዉ። በርግጥ ተጠሪ መጽሐፍቹን ሲያዘጋጅ፣ እነዚህኑን መሰረት አድርጎ ላሆን ይችላል። ይሁንና፣ እላይ እንደተመለከተዉ፣ ተጠሪ የራሱን የተለየ ችልታ እና ጉልበት እንዱሁም የአፃፃፍ ስታይል እና የአፃፃፍ ዘዳ በመጠቀም መጽሐፍቹን ማዘጋጀታቸዉ ከተረጋገጠ፤
መጽሐፍቹ ትምህርት ሚኒስቴር ያዘጋጀዉን ካሪኩለም፣ ሲለበስ፣ የተማሪዎች መማሪያwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
መጽሐፍት፣ የመምህር መምሪያን ይዘትና ዓላማን መሰረት በማድረግ የታወቀና ሳይንሳዊ የእንግሉዘኛ ቋንቋ አፃፃፍ ስርዓትን እና የሰዋሰዉ መርህን እና ጽንሰ ሃሳቦችን መሰረት በማድረግ ማዘጋጀታቸዉ ብቻ፣ በአዋጁ አንቀጽ 6(1) መሰረት፣ ስራቸዉ የወጥነትን መስፈርት አያሟላም ወደሚል ድምዲሜ የሚወስድ አይሆንም። በልላ አገላለጽ ተጠሪ ከላይ የተመለከቱትን ስራዎች፣ ጽንሰ ሃሳቦችን እና መርሆዎችን መሰረት በማድረግ ያዘጋጁት ለክርክሩ መነሻ የሆኑት መጽሐፍች ይዘት፤ ተጠሪ በዝግጅቱ ሂደት የራሳቸዉን የተለየ ችልታ፣ ጉልበት፣ የአፃፃፍ ዘዳ እና ስታይል መጠቀማቸዉን የሚያሳይ ከሆነ በመጽሐፈ ላይ የቅጅ መብት የማያገኙበት ምክንያት አይኖርም። ስለሆነም የተጠሪ መጽሐፍች የወጥነትን መስፈርት የሚያሟላ መሆን አለመሆኑን በመወሰን ረገድ በፍ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 246(1) መሰረት ተይዞ በማስረጃ ተጣርቶ እልባት ማግኘት የነበረበት ትክክለኛ ጭብጥ፣ ለክርክሩ መነሻ የሆኑት የተጠሪ መጽሐፍች ቀደም ሲል የተሰሩ ስራዎችን እንዱሁም የእንግሉዘኛ አፃፃፍ መርሆዎችን እና ጽንሰ ሃሳቦችን መሰረት ያደረጉ መሆን አለመሆናቸዉ ሳይሆን፣ መጽሐፍቹ በይዘታቸዉ የተጠሪን የተለየ ችልታ፣ የአፃፃፍ ዘዳ እና ስታይል የሚያሳዩ መሆን አለመሆናቸዉ ነዉ። ይሁንና የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ አስፈላጊዉን ማጣሪያ ሳያደርግ አመልካቾች በዚህ መልኩ ያቀረቡትን ክርክር በደፈናዉ በመቀበል የተጠሪን የዲኝነት ጥያቄ ዉድቅ ማድረጉን ተመልክተናል፤ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ቢሆን፣ አመልካቾች ያዘጋጁት መጽሐፍች ተጠሪ ካዘጋጃቸዉ መጽሐፍች ጋር የሚመሳሰለ መሆን አለመሆኑን መሰረት በማድረግ ጉዲዩን የተመለከተ ሲሆን፣ የተጠሪ ስራ በአዋጁ አንቀጽ 6(1) ስር የተመለከተዉን የወጥነት መስፈርት የሚያሟላ መሆን አለመሆኑን ከግራ ቀኝ ክርክር አንፃር ያልመረመረ ስለመሆኑ የዉሳኔዉ ይዘት ያስገነዝባል። በመሆኑም ለክርክሩ መነሻ የሆኑት የተጠሪ መጽሐፍች የወጥነት መስፈርት የሚያሟለ መሆን አለመሆኑ በስር ፍርድ ቤቶች በጭብጥነት ተይዞ በማስረጃ ተጣርቶ እልባት ያልተሰጠዉ ሆኖ አግኝተንዋል።
የተጠሪ መጽሐፍች ከላይ በተመለከተዉ ጭብጥ መሰረት ተጣርተዉ የወጥነትን መስፈርት የሚያሟለ መሆናቸዉ ከተረጋገጠ፣ ቀጥል የሚመጣዉ ጥያቄ 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች ባዘጋጁት መጽሐፍ በተጠሪ መጽሐፍች የተመለከቱትን አገላለፆች፣ ምሳላዎች እና ማብራሪያዎች ወስደዉ የመጽሐፍቹ አካል ማድረግ አለማድረጋቸዉwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ነዉ። በዚህ ረገድ የተጠሪ ክርክር በመጽሐፍቹ መካከል መመሳሰል የለም እንጂ አለ እንኳ ቢባል ስራዎቹ የእንግሉዝኛ መጽሐፍት፣ የመምህር መመሪያ፣ አገር አቀፍ ፈተናዎችን መሰረት በማድረግ የታወቁ ሳይንሳዊ የቋንቋ አፃፃፍ መርሆ፣ ስርዓትና ህግ በመከተል ተቀራራቢ የእንግሉዝኛ ትምህርት ዝግጅት ባላቸዉ መምህራን የተዘጋጀ በመሆኑ ምክንያት እንደሚሆን በመግለጽ የሚከራከሩ ስለመሆኑ መዝገቡ ያስረዲል።
በመሰል ጉዲይ የቅጅ መብት ጥበቃ መብት የሚሰጠዉ ሃሳቡ ሳይሆን፣ ሃሳቡ የተገለጸበት ቅርጽ፣ የተገለጸበት መንገድ እና ዘዳ ስለመሆኑ በቅጅ መብት ጥበቃ ተቀባይነት ያገኘ መርህ ነዉ። አንድ ሰዉ አንድን መጽሐፍ ሲያዘጋጅ፣ መጽሐፈ ተነባቢ እንዱሆን እና አንባቢዉ በቀላለ ሉረዲ እንዱችል ሃሳቡን የሚገልጽበት የራሱ የሆነ ዘዳ እና ስታይል ይጠቀማል። የስራ አመንጪዉ ይህን ሲያደርግም ለስራዉ ጊዜ ሰጥቶ፣ የተለየ ችልታዉን (skill) እና ጉልበቱን (labor) ተጠቅሞ በመሆኑ በቅጅ እና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ አንቀጽ 2(8) መሰረት በስራዉ ላይ የቅጅ መብት ባለቤት ይሆናል። ከዚህ አንፃር ሲታይ፣ ተጠሪ መጽሐፍቹን ሲያዘጋጅ የእንግሉዝኛ መጽሐፍት፣ የመምህር መመሪያ እንዱሁም ሳይንሳዊ የቋንቋ አፃፃፍ መርሆዎችን መሰረት በማድረግ ሆኖ ግን የራሱን የተለየ ችልታ በመጠቀም፤ አንባቢ (ተማሪ) በቀላለ እንዱረዲዉ ማድረግ በሚያስችል መልኩ፣ በመጽሐፍቹ ለተጠቀማቸዉ አገላለፆች፣ ምሳላዎች እና ማብራሪያዎች የቅጅ መብት ጥበቃ ያገኛል። በመሆኑም አመልካቾች ለተገቢ አሰራር እና ዓላማ የስራዉን ምንጭ እና የተጠሪን ስም በመጥቀስ ስራዉን መጠቀም ከሚችለ በስተቀር (የአዋጁ አንቀጽ 10 ይመለከቷል)፣ ተጠሪ በመጽሐፈ ያካተታቸዉን አገላለፆች፣ ምሳላዎች እና ማብራሪያዎችን እንዲለ በመዉሰድ የመጽሐፍቻቸዉ አካል ማድረግ ይችለ ዘንድ የቅጅ መብት አዋጁ አይፈቅድላቸዉም።
ይህን ማድረጋቸዉ ከተረጋገጠ በተጠሪ ላይ ለደረሰ ጉዲት ኃላፉ የማይሆኑበት ምክንያት የለም። በመሆኑም፣ አመልካቾች በመጽሐፍቹ የተጠቀሙባቸዉ ምሳላዎች፣ አገላለፆች እና ማብራሪያዎች ከተጠሪ መጽሐፍ የተወሰደ መሆን አለመሆናቸዉ በጭብጥነት ተይዞ በማስረጃ ተረጋግጦ መወሰን የሚገባዉ ነዉ። ይሁንና፣ ከላይ እንደተገለጸዉ፣ የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዚህ መልኩ አላጣራም፤ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይህኑን በጭብጥነት በመያዝ የቅጅ መብት ተጥሷል በሚል ድምዲሜ ላይ ሲደርስ በዋነኛነት የጠቀሰዉ ማስረጃ ከኮተቤ ዩኒቨርሲቲ ተልኳል የተባለን ደብዲቤ ነዉ። ይህwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ለወንጀል ምርመራ ዓላማ የተፃፈ ከመሆኑም በላይ አመልካቾች በማስረጃዉ ላይ አስተያየት ያልሰጡበት በመሆኑ ብቻዉን እምነት የሚጣልበት አይደለም። በመሆኑም አመልካቾች ከተጠሪ መጽሐፍ ምሳላዎችን፣ ማብራሪያዎችን እና አገላለፆችን ወስደዉ በመጽሐፍቻቸዉ በመጠቀም የቅጅ መብት ጥሰት የፈጸሙ መሆን አለመሆኑ በአግባቡ ተረጋግጧል ለማለት አይቻልም።
ወደ ሁለተኛዉ ጭብጥ ስንመለስ፣ ተጠሪ 1ኛ አመልካችን 1ኛ ተከሳሽ አድርገዉ ክስ ሲያቀርቡ መጽሐፍቹን አሳትሟል በሚል ነዉ። 1ኛ አመልካች በበኩለ መጽሐፍቹን አለማሳተሙን ገልፆ ተከራክሯል። የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዉሳኔ መጽሐፍቹን ያሳተመ መሆን አለመሆኑን በጭብጥነት ይዞ ወደ ማጣራቱ አልሄደም። የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም በዚህ ረገድ አላጣራም።
በአጠቃላይ ከፍ ሲል በዝርዝር ከተመለከቱት ዝርዝር ምክንያቶች አንፃር ሲታይ፣ በስር በከፍተኛ እና ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተሰጡት ዉሳኔዎች መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ ሆኖ ስላገኘን ተከታዩ ተወስኗል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ በቀን 02/02/2010 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ፤ እንዱሁም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 21/05/2010 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተዘግቶ የነበረዉን መዝገብ በማንቀሳቀስ የግራ ቀኝ ክርክር እና ማስረጃ እንዱሁም ስለ ቅጅ መብት ዔዉቀትና ልምድ ያላቸዉ ባለሙያዎች የተካተቱበትን አጣሪ ቡድን በማቋቋም እንዱያጣሩ በማድረግ ተገቢዉን ዉሳኔ እንዱሰጥበት መዝገቡ በፍ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 343(1) መሰረት የተመለሰለት ሲሆን፣ መጣራት ያለባቸዉ ጭብጦቹም፡- 2.1. የተጠሪ መጽሐፍቶች የትምህርት ሚኒስቴር ያዘጋጀዉን ካሪኩለም፣ ሲለበስ፣ የተማሪዎች መማሪያ መጽሐፍት፣ የመምህር መምሪያን ይዘትና ዓላማን መሰረት በማድረግ የታወቀና ሳይንሳዊ የእንግሉዘኛ ቋንቋ አፃፃፍ ስርዓትንwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
እና ሰዋሰዉ መርህን እና ጽንሰ ሃሳቦችን መሰረት በማድረግ የተዘጋጀ ሆኖ ግን በዝግጅቱ ሂደት የራሳቸዉን (የተጠሪን) የተለየ ችልታ፣ ጉልበት፣ የአፃፃፍ ዘዳ እና ስታይል የተጠቀሙ መሆን አለመሆኑን በማረጋገጥ የተጠሪ ስራ ወጥነት ያለዉ መሆን አለመሆኑን፤
2.2. የተጠሪ ስራ የወጥነትን መስፈርት የሚያሟላ ከሆነ አመልካቾች ተጠሪ በመጽሐፍቻቸዉ የተጠቀሙባቸዉ ምሳላዎች፣ ማብራሪያዎች እና አገላለፆች ከተጠሪ መጽሐፍች የተወሰደ መሆን አለመሆናቸዉን፤
2.3. 1ኛ አመልካች ለተጠሪ ኃላፉነት ያለበት መሆን አለመሆኑ ናቸዉ።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።
ይህ ችልት በቀን 21/10/2010 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል፤ ይፃፍ።