No summary available.
ግንቦት 28 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካቾች፡-
ወ/ሮ እላኒ ወ/አማኑኤል - ከጠበቃ አሰፊ ደሪብሳ ጋር ቀረቡ።
ህፃን ሰለማዊት ከበደ ሞግዚት 1ኛ አመልካች ወ/ሮ እላኒ ወ/አማኑኤል -ቀረቡ።
ተጠሪዎች፡-
ወ/ሮ ወርቅነሽ ብዙነህ - ቀረቡ።
ህፃን እፀገነት ከበደ ሞግዚት 1ኛ ተጠሪ ወ/ሮ ወርቅነሽ ብዙነህ - ቀረቡ።
ሰላም ሁለገብ አገልግልት ኃ/የተ/ህ/ስራ ማህበር -ጠበቃ እንዲልካቸው ሞላ ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካቾች የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍርድ ቤት የአሁን አመልካቾች ከሳሾች ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሾችwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ነበሩ። በስር ፍርድ ቤት ክርክሩ በተጀመረበት በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረቡት ክስ ይዘት፡- 1ኛ አመልካች ከሟች አቶ ከበደ ጌታቸው ጋር እንደባልና ሚስት አብረው በመኖራቸው፤ 2ኛ አመልካች ደግሞ የሟች ልጅ በመሆኗ በ3ኛ ተጠሪ ማህበር ውስጥ አቶ ከበደ ጌታቸው ያለው የእጣ ድርሻ 50% የሚገባቸው መሆኑን፤ እንዱሁም 2ኛ አመልካች ሟች ቦላ ክ/ከተማ ወረዲ 13 የቤት ቁጥር የላለው ቤት የአቶ ከበደ ጌታቸው ድርሻ 2ኛ አመልካች እና 2ኛ ተጠሪ እኩል እንዱካፈለ የየካ ምድብ ፍትሐብሕር ችልት በመ/ቁ.70021 በ8/7/2006 ዓ.ም በዋለው ችልት የቀረበውን የውርስ ሪፖርት በማጽደቅ ውሳኔ በመሰጠቱ በዚሁ መሰረት በተለይ የ3ኛ ማህበር ሂሳብ ተጣርቶ በሕብረት ስራ ማህበራት አዋጅ ቁጥር 147/1991 አንቀጽ 19/3/ መሰረት የእቃው ዋጋና ያስገኘው ጥቅም ሂሳቡ ተጣርቶ ክፍፍል እንዱደረግ እንዱወሰንላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል።
1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች በበኩላቸው በህዲር 8 ቀን 2008 ዓ.ም በተጻፈ መከላከያ መልስ ከሳሾች እንዱከፈላቸው የጠየቁት ቤት ሆነ የአክስዮን ድርሻ በእጃችን ያለ ስለመሆኑ ያቀረቡት ማስረጃ የላለ በመሆኑ ውድቅ እንዱደረግ፤1ኛ ከሳሽ ከሟች አቶ ከበደ ጌታቸው ጋር ልጅ ከመውለዲቸው በቀር እንደ ባልና ሚስት አብረው አልኖሩም፤ክስ የቀረበበት ቤትም በሟች ወላጆች አጥር ግቢ ውስጥ አንድ ጥግ ይዞ የተሰራ እንጂ ራሱን የቻለ የራሱ የከተማ ቦታ ይዞታ ማረጋገጫ የተሟላለት ቤት አይደለም። ይህ ቤት የለም እንጂ አለ የሚባል ከሆነ በተጣራው መሰረት ክፍፍል ቢደረግ ተቃውሞ የላላቸው መሆኑ፤የህብረት ስራ ማህበሩም ከ1ኛ ከሳሽ የምትወለደውን ልጅ እንጂ 1ኛ ከሳሽን የሚመለከት አይደለም፤ ስለሆነም ያለአግባብ የቀረበ ክስ በመሆኑ ውድቅ ተደርጎልን ወጪና ኪሳራ ተከፍልን መዝገቡ ተዘግቶ እንድንሰናብት በማለት ተከራክሯል። የአሁን 3ኛ ተጠሪ በበኩለ ለክሱ የሰጠው ምላሽ በተመለከተ 3ኛ ተከሳሽ የህብረት ስራ ማህበር እንጂ አክስዮን ማህበር አይደለም፤ ሟች አቶ ከበደ ጌታቸው የማህበሩ አባል የነበሩ መሆናቸው በመግለጽ የውርስ ሀብቱ ባለድርሻ ወገኖች ጉዲያቸውን በፍርድ ቤት ጨርሰው አስወስነው ቢመጡ 3ኛ ተከሳሽ በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እና በማህበሩ ደንብ መሰረት ከመፈፀም በስተቀር ባለድርሻ ነን ባዮች በሚያደርጉት ክርክር የሚሳተፍበት አግባብ የላለ በመሆኑ በ3ኛ ተጠሪ የቀረበው ክስ ውድቅ ተደርጎ እንዱወሰንላቸው ዘንድ ተከራክሯል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙ ክርክር መርምሮ ከሰላም ሁለገብ አገልግልት ኃ/የተ/የግ/ህብረት ስራ ማህበር ውስጥ ያለው ጥቅም ወይም ድርሻ እኩል እንዱካፈለ ተወስኗል፤እንዱሁም ከዚሁ ዔጣ የተገኘ የተጣራ ትርፍ ብር 45,895.81/ አርባ አምስት ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ብር ከሰማንያ አንድ ሳንቲም/ አመልካቾች፤1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች እኩል እንዱካፈለ፤በቦላ ክፍለ ከተማ ወረዲ 13 የቤት ቁጥር አዱስ የሆነው የውርስ ሀብት መሆኑ በፍርድ ቤት የተረጋገጠው ቤት 2ኛ ከሳሽ 1/4ኛ ድርሻ ያላቸው በመሆኑ ከተቻለ በዓይነት በስምምነት ግምቱን ይህ ካልተቻለ ቤቱ ተሸጦ ድርሻዋ እንዱከፈል ሲል የሰጠው ውሳኔ በመቃወም አመልካቾች ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙ ክርክር ከሰማ በኋላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ በማጽናት ወስኗል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። አመልካቾች ሰኔ 5 ቀን 2009 ዓ.ም በፃፈት አቤቱታ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶችን ዘርዝረው አቅርበዋል። የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ በመደረጉ ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት በታዘዘው መሰረት 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች በአንድ ላይ 3ኛ ተጠሪ ደግሞ ለብቻው ነሐሴ 22 ቀን 2009 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል። አመልካቾችም አቤቱታቸው በማጠናከር የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር መርምረናል። ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ሟች አቶ ከበደ ጌታቸው በ3ኛ ተጠሪ ህብረት ስራ ማህበር ውስጥ ያላቸው ድርሻ ውስጥ ለአራቱ ማለትም ለአመልካቾችና 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች እያንዲንዲቸው 1/4ኛ የሚደርሳቸው መሆኑን በውርስ ማጣራት ተረጋግጦ በፍርድ ቤት የጸደቀ ስለመሆኑ በግራ ቀኙ ተከራካሪ ወገኖች የተካደ ጉዲይ አይደለም። የሚያከራክረው የማህበሩ አባል ሲሞት ወደ ወራሾች የሚተላለፍ ምንድነው የሚለውን ጥያቄ ነው። በአመልካቾች በኩል ሟች ባለው የዔጣ ድርሻ የሚያስገኘው ትርፍ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የማህበሩን ካፒታለ/www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረቶች/ ተጣርቶ ሉከፈልን ይገባል የሚል ሲሆን በ3ኛ ተጠሪ ደግሞ በማህበራት አዋጅ 147/1991 አንቀጽ 32 መሰረት የማህበራት ንብረት ለአባላቱም ሆነ ለላላ ወገን የሚከፊፊል ባለመሆኑ የአመልካቾች ጥያቄ ተገቢ አይደለም የሚል ነው። ይህ ችልትም በስር ፍርድ ቤት የተካሄደው ክርክር እና የቀረቡትን ማስረጃዎችን ይዘት መመልከቱ አስፈላጊ ሁኖ ስለአገኘው የፋ/መ/ደ/ፍርድ ቤት ከየካ ምድብ ችልት የመ/ቁ. 104042 የሆነው መዝገብ እንዱቀርብ አድርጓል። ከስር መዝገብ መገንዘብ የተቻለው በቦላ ክፍለ ከተማ ወረዲ 13 ክልል ውስጥ የሚገኝ ቤት የውርስ ሀብት ከሆነው ቤት የተሰበሰበው የኪራይ ገንዘብ እንዱከፈል የቀረበው ጥያቄ በስር ፍርድ ቤቶች በዝምታ መታለፈ ተገቢ ሁኖ አልተገኘም። በመሆኑም ሉታረም የሚገባው ሁኖ አግኝተነዋል። ላላውን ነጥብ በተመለከተ ሟች አቶ ከበደ ጌታቸው በማህበሩ 155 ዔጣ ያንደ ዔጣ ዋጋ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ መሆኑን በዚሁ ስላት መሰረት የሟች ድርሻ የተጣራ ትርፍ ብር 45,895.81/ አርባ አምስት ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ብር ከሰማንያ አንድ ሳንቲም/ መሆኑን የሚገልጽ ሪፖርት መቅረቡን ተገንዝበናል። ተጣርቶ የቀረበው የተጣራ ትርፍ ድርሻ ሲሆን የአመልካቾች ዲኝነት ጥያቄ ከማህበሩ የሚገኘው የትርፍ ድርሻ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የማህበሩ ካፒታል የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረት ተጣርቶ ድርሻቸው እንዱከፈላቸው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት በማድረግ ተገቢውን ማጣራት ተደርጎ ውሳኔ የተሰጠ ውሳኔ ስለመሆኑ የስር ፍርድ ቤት መዝገብ አያሳይም። አንድ የመሰረታዊ ማህበር አባል ሲሞት ዔጣው ወይም ጥቅሙ በማህበሩ መዝገብ ውስጥ በወራሽነት ለሰየመው ወይም ሟቹ ወራሽ ያልሰየመ ከሆነ በሕግ ለመውረስ ለሚችል ወራሹ ይተላለፊል፡ ይህም የሚሆነው ወራሹ የማህበሩ አባል ከሆነ ወይም ለመሆን ፈቃደኝነቱን የገለጸ እንደሆነ ነው። ወራሹ የማህበሩ አባል ካልሆነ ወይም አባል ለመሆን የማይፈልግ ወይም የማይፈቀድለት ከሆነ የሟቹ የዔጣው ዋጋ እና ጥቅም እንደሚከፈለው በአዋጁ አንቀጽ 19 ስር ተመልክቷል።
በአጠቃላይ “የዔጣው ዋጋ እና ጥቅም ይከፈለዋል” የሚለውን የህጉ ድንጋጌ መሰረት በማድረግ አመልካቾች በማህበሩ የሚቀጥለ መሆናቸው አለመሆናቸው?፤ሉቀጥለ የማይፈልጉ ከሆነ ከማህበሩ ካፒታል /የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረት/ ተጣርቶ የሚሰጣቸው መሆን አለመሆኑ? በሚለት ነጥቦች ላይ ተገቢውን ጭብጥ ሳይመሰረትና ሳይጣራ በስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ የክርክር አመራርና የዲኝነት አሳጣጥwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ስርዓትን ያልተከተለ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሁኖ አግኝተናል።
ስለሆነም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 104042 ሰኔ 9 ቀን 2008 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 182433 መጋቢት 26 ቀን 2009 ዓ.ም በውሳኔ የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 348 /1/ መሰረት ተሻሽሎል።
ሟች በማህበሩ 155/አንድ መቶ ሃምሳ አምስት/ ዔጣዎች ያለት መሆኑን የተጣራ ትርፍ ብር 45,895.81 /አርባ አምስት ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ብር ከሰማንያ አንድ ሳንቲም/መሆኑን እንዱሁም የውርስ ሀብት ከሆነው በቦላ ክ/ከተማ ወረዲ 13 ክልል ውስጥ የሚገኘው ቤት 2ኛ አመልካች 1/4ኛ ድርሻ በተመለከተ የተሰጠ ውሳኔ ክፍል ፀንቷል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአጠቃላይ “የዔጣው ዋጋ እና ጥቅም ይከፈለዋል” የሚለውን የህጉ ድንጋጌ መሰረት በማድረግ አመልካቾች በማህበሩ የሚቀጥለ መሆናቸው አለመሆናቸው?፤ሉቀጥለ የማይፈልጉ ከሆነ ከማህበሩ ካፒታል /የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረት/ ተጣርቶ የሚሰጣቸው መሆን አለመሆኑ? በሚለት ነጥቦች ላይ አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ እና በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 136 መሰረት የሚመለከተው የህብረት ስራ ማህበራት ባለሙያ ምስክርነት /ማብራሪያ/ እንዱቀርብ በማድረግ ውሳኔ እንዱሰጥበት፤ እንዱሁም የውርስ ሀብት ከተባለው ቤት ኪራይ የተሰበሰበ መኖሩን አለመኖሩን አጣርቶ ውሳኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.343/1/ መሰረት ተመልሶለታል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።
No topics extracted.