የአንድ ተከሳሽ ያለፈ የቅጣት ውሳኔ አሁን ከተከሰሰበት ጉዲይ ጋር በማያያዝ በዋስ ቢለቀቅ ተመሳሳይ ወንጀል ሉፈጸም ይችላል የሚል ግምት በመውሰድ የዋስትና ጥያቄን አለመቀበል አግባብነት የላለው አቶ አህመድ ደርባቸው እና ፋዳራል ዐቃቤ ህግ ጥቅምት8/2009 ዓ.ም. 473www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. LI በሕግ በግልጽ ካልተደነገገ በቀር አንድ ተከሳሽ በፍርድ ዲኝነት በግልጽ እስካልታወቀ ድረስ የቀድሞ ጥፊተኝነቱ የማይገለፅ ስለመሆኑ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 67 (ለ)፣138 (1) ልዩ ልዩ 477 81. የመጥፊት ዉሳኔ ከተሰጠና የጠፊው ሰው ንብረት ለወራሾቹ ከተላለፈ በኋላ የመጥፊት ዉሳኔ የተሰጠበት ሰዉ በህይወት ከተመለሰ ላላ ማረጋገጫ ሳያስፈልገዉ ንብረቶቹ በሚገኙበት አኳኋን መልሶ መዉሰድ ስለመቻለ የፍ/ብ/ህግ 168-173
No summary available.
መ/ቁ153418 ህዲር 28 ቀን 2011ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንደሻዉ አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች፡- አቶ ጉደታ አሰፊ ተጠሪዎች፡- 1ኛ/ወ/ት ወደሬ ጉደታ 2ኛ/ወ/ት ፊኖስ ጉደታ መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ በመሆኑ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
በዚህ መዝገብ የቀረበዉ ጉዲይ የመጥፊት ዉሳኔ ከተሰጠና ንብረቱ ለወራሾቹ ከተላለፈ በኋላ የመጥፊት ዉሳኔ የተሰጠበት ሰዉ ሲመለስ ንብረቶቹን የሚያገኝበት ሁኔታ በጊዜ የተገደበ ነዉ በማለት የስር ፍርድ ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ አግባብነት የሚመለከት ነዉ።የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ የአሁኑ አመልካች ጠፍቷል በሚል በፍርድ ቤት ዉሳኔ በማሰጠት ተጠሪዎች የአመልካቹን የመሬት ይዞታ በእጃቸዉ አድርገዉ ሲጠቀሙ ከቆዩ በኋላ አመልካች ቀርቦ የመጥፊት ዉሳኔ ተሰርዞ በተጠሪዎች እጅ የገባዉን ይዞታ እንዱመልሱ እንዱወሰን ዲኝነት የጠየቀ ሲሆን በተጠሪዎች በኩል የቀረበዉ መቃወሚያ ይዞታዉ በእጃቸዉ ከገባ 20 ዓመት በላይ ስለሆነ የአመልካች ጥያቄ በይርጋ ይታገዲል የሚል ሲሆን የወረዲዉ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ምስክር ሰምቶ አመልካች ጠፊ የተባለዉ በ15/09/1989 ዓ.ም ስለመሆኑ በመ/ቁ/126/99 ላይ በ25/05/1999 ዓ.ም ዉሳኔ ስለመሰጠቱ እና አመልካች አቤቱታ ያቀረበዉ በ24/08/2009 ዓ.ም በመሆኑ 10 ዓመት አልፍበታልwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በሚል በፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 172 እና 173/1/ መሰረት የአመልካች ጥያቄ በይርጋ ታግዶል በማለት ዉሳኔ ሰጥቷል።አመልካች በዚህ ዉሳኔ ቅር ተሰኝቶ ለሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና ለአማራ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም ተቀባይነት አላገኘም።
ለዚህ ሰበር ችልት አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ላይ ሲሆን የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘት ባጭሩ የይርጋ መቃወሚያ ላይ የተሰጠዉ ዉሳኔ ህጉን በአግባቡ ያላገናዘበ ነዉ የሚል ሲሆን ሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታዉን መርምሮ አቤቱታዉን ከፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 171 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች አግባብ ለመመርመር እንዱቻል ጭብጥ በመያዝ በጽሐፍ መልስ እንዱለዋወጡ ተደርጓል፡ የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ ባጭሩ የተገለጸ ሲሆን እኛም ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል ሲባል የተያዘዉን ጭብጥ መሰረት በማድረግ አግባብነት ካለዉ ህግ ጋር በማገናዘብ መርምረናል።ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል ሲባል የተያዘዉ ጭብጥ አመልካች ላይ የመጥፊት ዉሳኔ ከተሰጠ በኋላ ቀርቦ ንብረቶቹ እንዱመለሱለት ያቀረበዉ አቤቱታ በፍ/ብ/ህግ ቁ/171 እና 173 መሰረት በአስር ዓመት ይርጋ ቀሪ ነዉ በማለት የስር ፍርድ ቤት የሰጠዉ ትእዛዝ ተገቢነት ለመመርመር ነዉ።
በፍትሒብሓር ህግ ዉስጥ ስለሰዉና ስለሰዎች መብት በሚደነግገዉ አንደኛ መጽሒፍ ዉስጥ አንደ የተፈጥሮ ሰዉ ላይ የመጥፊት ማስታወቂያ ዉሳኔ የሚሰጥበትና ዉጤቱን የሚደነግገዉ አንቀጽ 154 እስከ 173 ድንጋጌዎች የሚመለከት ነዉ።አንድ የተፈጥሮ ሰዉ በህይወት መኖር አለመኖሩ አጠራጣሪ ሲሆንና በሕይወት ስለመኖሩ ወሬዉ ከጠፊ ሁለት ዓመት የሞላዉ እንደሆነ የመጥፊት ዉሳኔ የሚሰጥበት ስርዓትና በዚህም ፍርድ ቤቱ ተገቢዉን ማጣሪያ አድርጎ የጠፊዉ ሰዉ መሞት የሚመስል ሆኖ የታየዉ እንደሆነ ጠፍቷል ሲል እንደሚያስታዉቅ በፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 157/1/ ተመልክቷል።በዚህ ዓይነት ሁኔታ የሚሰጠዉ የመጥፊት ማስታወቂያ የሚያስከትለዉ ዉጤት እንደሞተ ሰዉ ተገምቶ መብትና ግደታዎቹ ለወራሾች የሚተላለፍ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህጉ አንቀጽ 154፣163 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ይዘት ያስገነዝባለ።በዚህ አግባብ የመጥፊት ማስታወቂያ ሲነገር ጠፊ የተባለዉ ሰዉ እንደሞተ ግምት ተወስድ ጋብቻዉ እንደሚፈርስ እናwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በእሱ መሞት መብት የሚተላለፍላቸዉ ሰዎች በመብታቸዉ ሉጠቀሙ እንደሚችለ የፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 163 እና 165 ላይ ተደንግጓል።በልላ በኩል ጠፊ የተባለዉ ሰዉ በህግ እንደሞተ ግምት የሚወሰድ ስለመሆኑና ነገር ግን ደግሞ ሰዉየዉ በህይወት ቢገኝ ወይም የሞተዉ ጠፊ ከተባለበት ቀን በኋላ ቢሆን ይህ ግምት ሉፈርስ እንደሚችል በማሰብ ንብረቶቹን በይዞታቸዉ ያደረጉ ሰዎች ዋስትና ወይም ግዳታ እንዱገቡ እንዱሁም ንብረቶቹን እንደመልካም አባት እንዱጠብቁ ህግ የሚያሥገድድ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 165፣166 እና 168 ድንጋጌዎች ይዘት ያስገነዝባለ።
ስለሆነም በአንድ በኩል የመጥፊት ዉሳኔ ሲሰጥ ጠፊ የተባለዉ ሰዉ እንደሞተ ተቆጥሮ መብቱ በህግ አግባብ ለባለመብቶች እንደሚተላለፍ በልላ በኩል ደግሞ ጠፊ የተባለ ሰዉ በህይወት ቢገኝ በሚል ወይም የመጨረሻ ወሬዉ የተሰማበት ላላ ጊዜ ቢሆን በሚል ህሳቤ መብቱ እንዲይጎዲ ህጉ ተገቢዉን ጥንቃቄ ማድረጉን እንገነዘባለን።ይህንንም ተከትል የመጥፊት ዉሳኔ ከተሰጠ በኋላ የመጥፊት ዉሳኔ ዉጤት የሚቀርበት ምክንያቶች በፍ/ብ/ህጉ አንቀጽ 170 ላይ ተዘርዝሯል።ከእነዚህ ዉስጥ አንደ ጠፊ የተባለዉ ሰዉ በሕይወት መገኘቱ ወይም መመለሱ ነዉ። ጠፊ የተባለዉ ሰዉ በህይወት ከተመለሰ ንብረቶቹ በሚገኙበት አኳኋን መልሶ መዉሰድ እንደሚችል የፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 171/1/ በግልጽ ይደነግጋል።ይህ ድንጋጌ የጊዜ ገደብ አላስቀመጠም።
በዚህ መዝገብ በተያዘዉ ጉዲይ አመልካች የመጥፊት ማስታወቂያ በመ/ቁ/126/99 ላይ በ25/05/1999 ዓ.ም የተሰጠ ሲሆን የመጨረሻ ወሬ ተሰማ የተባለዉ በ15/09/1998 ዓ.ም መሆኑ በዉሳኔዉ ላይ ተገልጧል።አመልካች ይህንን በመቃወም አቤቱታ ያቀረበዉ በ24/08/09 ዓ.ም ሲሆን አቤቱታዉም ተጠሪዎች የመጥፊት ማስታወቂያ ያሰጡት በድብቅ ስለመሆኑና መሬቱን እስከ 1996 ሲጠቀም ቆይቶ በአጋዞ ሰጥቶ ሲጠቀም የቆየና ስራ ፍለጋ ላላ ቦታ ለተወሰነ ጊዜ ሲሄድ ልጆቹ አጋዞ ከተሰጠዉ አቶ አሰፊ ገለታ ላይ ተቀብለዉ ለ 4ዓመት ከተጠቀሙ በኋላ አመልካች ተመልሶ ሲጠይቅ 10 ዓመት እንዲለፈዉ ተደርጎ መወሰኑ ስህተት ነዉ ህጉም ይህንን ገደብ አላስቀመጠም የሚል ነዉ።አመልካችም ይህንኑ መሰረት አድርጎ ንብረቶቹ እንዱመለሱለት ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን የስር ፍርድ ቤት የ10 ዓመት ጊዜ አልፍበታል በሚል የፍ/ብ/ህግ አንቀጽwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
172 ዋቢ በማድረግ የአመልካችን ጥያቄ ዉድቅ አድርጓል። የፍ/ብ/ህጉ አንቀጽ 172 ድንጋጌ ይዘት ሲታይ መጥፊቱን በሚወስነዉ ፍርድ ዉስጥ ከተወሰነዉ የመጨረሻ ወሬዎች ከተሰሙበት ጊዜ ወዱህ አስር ዓመት ያለፈ እንደሆነ መሞቱ የመጨረሻ ወሬዎች በተሰሙበት ሳይሆን በልላ ቀን ለመሆኑ ማስረጃ ለማቅረብ የሚችለዉ ጠፊ የተባለዉ ሰዉ ራሱ ወይም ስለመጥፊቱ የተሰጠዉ ፍርድ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን በኋላ ልዩ የሆነዉ ወኪል ብቻ ነዉ ይላል።የዚህ ድንጋጌ ይዘት ሲታይ የ10 ዓመት ጊዜ ገደብ የሚያያዘዉ ጠፊ የተባለዉ ሰዉ እንደሞተ ሰዉ ተገምቶ መብቶቹ ስለሚተላለፈ እና በመብቶቹ ሉሰሩ የሚችለ ወገኖች ላይ ይርጋና የመሳሰለት የጊዜ ጉዲዮች አከራካሪ በሆነ ጊዜ ትክክለኛዉን ጊዜ በሚመለከት መከራከሪያ ላቀርብበት የሚችለዉን ወገን ለማመላከት የተቀመጠ እንጂ ጠፊ የተባለዉ ሰዉ ራሱ ተመልሶ ቢመጣ ወይም በሕይወት ቢገኝ መብቱን ለመጠየቅ የሚገድበዉ ድንጋጌ ሆኖ የተቀረጸ አይደለም።በዚህ ረገድ ይህ ሰበር ችልት ጠፊ የተባለዉ ሰዉ ንብረት ዉርስ ጋር በተያያዘ ይርጋ ክርክር አስመልክቶ በሰበር መዝገብ ቁ/126975 ላይ የሰጠዉን ዉሳኔ ማገናዘብ ይቻላል።
ስለዚህም የሰዉየዉ መጥፊት ማስታወቂያ ወይም ዉሳኔ ተሰጥቶ 10 ዓመት ካለፈዉ በህይወት የመኖር ግምት ይበልጥ መሞቱ ስለሚያመዝን ንብረቱን በእጅ ያደረጉ ሰዎች ላይ በአንቀጽ 168 እና 169 ላይ የተጣለት ገደቦች እንደማይሰሩ አመላካች ድንጋጌ እንደሆነ ከአንቀጽ 173 ጣምራ ንባብ የምንገነዘበዉ ነዉ።በመሆኑም ጠፊ የተባለዉ አመልካች በሕይወት ከተመለሰ ላላ ማረጋገጫ ሳያስፈልገዉ ንብረቶቹ በሚገኙበት አኳኋን መልሶ መዉሰድ እንደሚችል የፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 171/1/ በግልጽ የተደነገገዉን መሰረት በማድረግ ዉሳኔ ሉሰጠዉ ይገባል።ስለዚህም የስር ፍርድ ቤት የፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 172 ተመርኩዞ የአመልካች ጥያቄ በ10 ዓመት ይርጋ ታግዶል በሚል የሰጠዉ ዉሳኔ የድንጋጌዉን ይዘትና ዓላማ በአግባቡ ያገናዘበ ሆኖ አላገኘንም።በዚሁ መሰረት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ በማለት ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
1ኛ/ የሲያ/ዋዩ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/0113197 ላይ በ29/02/2010 ዓ.ም የሰጠዉ ብይን እና ይህንኑ በማጽናት የአማራ ክልለ ሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 0125264 ላይ በ18/3/2010 ዓ.ም የሰጠዉ ፍርድ እና የአማራ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 030-9082 ላይ የሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁ 348/1/መሰረት ተሸሯል ።
2ኛ/ የአመልካች አቤቱታ በ10ዓመት ይርጋ አልታገደም ብለናል።
3ኛ/ የወረዲዉ ፍርድ ቤት ወደ ፍሬ ጉዲዩ ገብቶ በተጠሪዎች እጅ የገባዉን ንብረት አጣርቶ ተገቢዉን ዉሳኔ እንዱሰጥበት በማለት ጉዲዩን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁ.341/1/መሰረት መልሰንለታል። ይጻፍ 4ኛ/ በዚህ ፍ/ቤት ለተደረገዉ ክርክር ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.