የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ ለይግባኝ ማቅረቢያና ተያያዥ ጉዲዮች የጊዜ ገደብ ቢያስቀምጥም በመታየት ላይ ያለ መዝገብ መዘጋቱ አስፈላጊ ሆኖ ከተዘጋ በኃላ እንደገና መከፈቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በምን ያህል ጊዜ ዉስጥ አቤቱታ ላቀርብበት እንደሚገባ በግልፅ ስላላስቀመጠ የጊዜ ገደቡ የሚወሰነው የጉዲዩን ሁኔታዎችና የአቤቱታዉን ዓይነት በመመልከት እንጂ መዝገቡን ለማንቀሳቀስ የቀረበዉ አቤቱታ ከተወሰነ ጊዜ በኃላ የቀረበ ነው በማለት አቤቱታውን አቶ ከበደ ተሰራ እና የፋዳራል ጠቅላይ ዐ/ሕግ ጥቅምት27/201 1 ዓ/ም 463www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. L ማድረግ የይግባኝ ባዩን መብት የሚጣብብ ስለመሆኑ በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 22(2)፤በወ/ሕ/አንቀጽ 6፣ 9(1) 79. በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 27/2/ መሰረት አንድ ተከሳሽ ለፖሉስ የሚሰጠው የእምነት ቃል ለምርመራ ዓላማ ሲባል በምርመራ ጊዜ የተገኘ ማስረጃ በመሆኑ የቀረበውን ክስ ለማስረዲት የሚችል ተቀባይነት ያለው ማስረጃ መሆን አለመሆኑ በፍ/ቤት ሉመረመር እና ሉመዘን የሚገባው እንጂ ከወዱሁ ተቀባይነት አለው ተብል ድምዲሜ የሚወሰድበት ስላለመሆኑ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 27/2/
No summary available.
ጥቅምት 8/2009 ዓ.ም.
ዳኞች- ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል ክፍለጽዮን ማሞ ሰናይት አድነው ጳውልስ አርሺሶ አመልካች- አቶ አህመድ ደርባቸው ጠበቃ ሬድዋን ከማል ተጠሪ- ፋዳራል ዐቃቤ ህግ- ሙለ ተስፊ ከበደ - ቀርበዋል።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የተጀመረው አመልካች በተጠሪው በቀረበባቸው የቼክ ማጭበርበር ወንጀል ጋር ተያይዞ ጉዲዩን የያዘው ፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ክሱ የሚሰማበት ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠቱና ተከሳሽ (የአሁን አመልካች) የዋስትና መብት ተጠብቆላቸው እንዱከራከሩ ለፍርድ ቤቱ በማመልከታቸው ነው።
ተጠሪ የአመልካችን የዋስትና መብት ጥያቄ ተቃውሟል ተጠሪ በመቃወሚያል አመልካች ቀደም ሲል በቂ ስንቅ የላለው ቼክ በማውጣት ወንጀል ተከስሰው የሦስት ወር እሰራት በ2 ዓመት ገደብ የተፈረደባቸው ሲሆን በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ላላ የቼክ ማጭበርበር ወንጀል ድርጊት ፈጽመዋል ተብል ክስ ቀርቦባቸዋል። ስለዚህ በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 67 (ለ) መሰረት የዋስትና መብት ጥያቄአቸው ውድቅ ላሆን ይገባዋል ሲል ተከራክሯል።
ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ አመልካች ቀደም ሲል የቅጣት ገደባቸው ሳያበቃ አሁን ከተከሰሱበት የወንጀል ድርጊት ጋር ተመሳሳይ የሆ ወንጀል ፈጽመው የተቀጡ መሆኑ በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 67 (ለ) መሰረት ላላ ወንጀል ይፈጽሙ ይሆናል ተብል የሚገመት በመሆኑ የዋስትና ጥያቄው አልተቀበልነውም ሲል ብይን ሰጥቷል።
ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው ፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የአመልካችን ቅሬታ ባለመቀበል ወስኖአል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
አመልካች የሥር ፍ/ቤቶች የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 67 (ለ) ን በተሳሳተ መንገድ ተርጉመውታል ይታረምልኝ ሲለ የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል።
አመልካች በሰበር አቤቱታቸው ቀደም ሲል የተቀጡበት ወንጀል በዚህ መዝገብ እያከረከረ ካለው የወንጀል ክስ ጋር የተለያየ ሆኖ እያለ በድጋሚ በተመሳሳይ ወንጀል ተከስሷል መባለ አለአግባብ መሆኑን ጠቅሰዋል።
አመልካች በማረፉያ ቤት እንዱቆዩ ቢደረግም እዚያው ሆነው የቼክ ማጭበርበር ድርጊት ከመፈጸም የሚያግዲቸው ነገር እንደማይኖር፣ ይልቁንም በዋስ ተለቅቀው ቼክ እንዱያንቀሳቅሱ መከልከለ አማራጭ መሆኑን ገልጸው በዋስ የመለቀቅ ሕገመንግስታዊ መብታቸው እንዱከበርላቸው ጠይቀዋል።
አመልካች በሰበር አቤቱታቸው በዋስ ቢለቀቁ ላላ ወንጀል ሉፈጽሙ የሚችል ስለመሆኑ ግምት ሉያስወስድ የሚችል ባህርይ ወይም የነገሮች ሁኔታ ሳይኖር የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.
67 (ለ) ን በመጥቀስ የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ ሲለ አመልክተዋል።
ተጠሪ በሰጠው መልስ ዋስትና በሕገመንግሥቱ ዔውቅና ያገኘ መብት ቢሆንም በሕግ ሉገደብ እንደሚቻል የታወቀ ነው ብሎል። አመልካች ከዚህ ቀደም በቼክ አታላይነት ወንጀል በብር 5000 መቀጮ የ3 ወር እስራት በ2 ዓመት ገደብ የተቀጡ ሲሆን አሁንም እንደገና የግል ተበዲይን እምነት በመጠቀም የወጡት ቼክ እንዲይከፈል ሂሳቡ እንዱዘጋ በማድረጋቸው በተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት በአንድ ዓይነት የሕግ ድንጋጌ ተከስሰው ቀርበዋል። አመልካች በዋስ ቢለቀቁ ላላ ወንጀል ይፈጽማለ ከሚል ግምት ከዚህ የበለጠ ማሳመኛ ምክንያት ሉኖር አይችልም ሲል ተጠሪ መቃወሚያውን አቅርቧል። በፍ/ቤቶች ውሳኔ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም በማለትም ተከራክሯል።
እኛም መዝገቡን መርምረናል። እንደመረመርነውም በከፍተኛው ፍ/ቤት ተሰጥቶ በጠቅላይ ፍ/ቤት በፀናው ውሳኔ የአመልካች የዋስትና ጥያቄ ውድቅ የተደረገበት ምክንያት ያለፈውን የወንጀል ሪከርድ በማየት አሁንም ተመሳሳይ ወንጀል ከመሥራቱ ይቆጠባል ተብል አይገመትም በሚል ነው።
ሆኖም በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 67 (ለ) ስር የተደነገገው የዋስትና መብት ገደብ በተከሳሹ ያለፈ የወንጀል ታሪክ ላይ የሚመሰረት አይደለም። ይልቁንም የድንጋጌው ዓላማ በእጅ ላይ ያለውን የክሱ ሂደት ሉያደናቅፍ ይችላል ተብል በሚገመትበት ጊዜ በዋስ የመለቀቅwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
መብቱን ለመገደብ ነው። የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 67 (ለ) ከንዐስ ቁጥሮች (ሀ) እና (ሐ) ጋር በአንድነት ሉነበብ ይገባል ሕጉ የተከሳሹን በዋስ የመለቀቅ መብት እየገደበ ያለው በዋስትና ወረቀት ላይ የሰፈሩትን ግዳታዎች አይፈጽምም ተብል ሲገመት ወይም ዋሶችን ሉያባብል ይችላል ወይም ሉያስፈራራ ይችላል ወይም ማስረጃዎችን ሉያጠፊ ይችላል ተብል ተከሳሹ ሲገመት ነው። የቁጥር 67 (ለ) ድንጋጌም ከንዐስ ቁጥሮች (ሀ) እና (ሐ) ጋር በጣምራ ሲነበብ “ላላ ወንጀል ሉሰራ ይችላል ተብል ሲገመት” የሚለው ድንጋጌ ከተያዘው ክስና ከተጀመረው የፍርድ ሂደት ጋር በተያያዘ ጠባብ የሕግ ትርጉም በተጣጣመ መልኩ እንደሆነ ግልፅ ነው።
ፍ/ቤቶቹ የተከሳሾችን ያለፈ የቅጣት ውሳኔ ካሁን ከተከሰሰበት ጉዲይ ጋር በማያያዝ በዋስ ቢለቀቅ ተመሳሳይ የቼክ ወንጀል ሉፈጸም ይችላል የሚል ግምት በመውሰድ የዋስትና ጥያቄውን አለመቀበላቸው አግባብ ያለው ሆኖ አላገኘነውም። ፍ/ቤቶቹ ተከሳሽ በዋስ ቢለቀቅ በተከሰሱበትን ጉዲይ ለማድበስበስ ማስረጃ ለማጥፊት፣ ወይም ራሱ ለመሰወርና ከፍርድ ለማምለጥ በአጭር የተያዘውን የፍርድ ሂደት ለማደናቀፍ የወንጀል ድርጊት ይፈጸማል ለማለት የሚያስችል አሳማኝ ማስረጃ ሳይቀርብላቸው የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 67 (ለ) ን የተሳሳተ ትርጉም በመስጠት መወሰናቸው ሉታረም የሚገባው ነው።
በልላ በኩል የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 138 (1) ሕጉ በግልጽ ካልደነገገ በቀር ተከሳሹ በፍርድ ዲኝነት በግልጽ እስከአልታወቀ ድረስ የቀድሞ ጥፊተኝነቱ አይገለጽም ሲል ደንግጓል።
ድንጋጌው የተከሳሽን ንጽሕ ሆኖ የመገመት ሕገመንግሥታዊ መብት የሚያመለክት ሲሆን በተጨማሪም ዳኞች የወንጀል ጉዲይ በሚመረምሩበት ጊዜ በተከሳሹ የጥፊተኝነት ሪከሪድ ጫና አድሮባቸው የተሳሳተ ውሳኔ እንዲይሰጡ ለማድረግ የሰፈረ ነው።
አሁን በያዝነው ጉዲይ ተጠሪ ስለአመልካች የቀድሞ የጥፊተኝነት መዝገብ ሲያቀርብ ፍ/ቤቶች ከላይ በተጠቀሰው የሕግ ድንጋጌ መሰረት እንዲልቀረበ በመቁጠር ሉወሰን ሲገባ ሕጉን በመጣስ በአመልካቹ የጥፊተኝነት መዝገብ ላይ በመመሥረት ማከራከራቸውን መወሰናቸውና መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ውሳኔ በመሆኑ ሉታረም የሚገባ ነው።
በዚህ መሰረት የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ው ሣ ኔ
127657 ያፀናው ውሳኔ ተሽሯል።
አመልካች የብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ዋስትና በማስያዝ በዋስ ተለቅቀው ጉዲያቸውን እንዱከታተለ ተወስኗል።
ከፍተኛው ፍ/ቤት ውሳኔውን እንዱያስፈጽም ታዟል፤ ይፃፍ።
No topics extracted.