አንድ ተከሳሽ በአንድ ቸልተኝነትና በአንድ ድርጊት በደረሱ ጉዲቶች በተደራራቢ ወንጀልች ሲከሰስ ላላ የተለየ ሀሳብና ድርጊት መኖሩ እስካልተረጋገጠ ድረስ አንደን በቸልተኝነት ላላዉን ደግሞ ሆን ተብል ታስቦ በተፈጸመ ወንጀል ጥፊተኛ የሚደረግበት አግባብ አቶ ሀብታሙ ደስታ እና የፋዳራል ጠቅላይ ዐ/ሕግ www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XLVIII ቅጣትን በሚመለከት ተደራራቢ ወንጀልች ተፈጽመዉ ሲገኙ ቅጣት ሉወሰን የሚገባዉ ለእያንዲንደ ወንጀል መነሻ ቅጣት ከተያዘ በኃላ እነዚህን በመደመር ድምሩ የቅጣት መጠን የሚያርፍበትን ዝቅተኛ የቅጣት እርከን በመለየት ስለመሆኑ የተሻሻለዉ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 02/2006 አንቀጽ 22(1/ሀ)
No summary available.
ጥቅምት 27/2011 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ኃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች:- አቶ ከበደ ተሰራ ጠበቃ ሚሉዮን አሰፊ ቀረቡ ተጠሪ፡- የፋዳራል ጠቅላይ ዐ/ሕግ ዮሐንስ ግርማ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
የጉዲዩ መነሻ አመልካች ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረቡት አቤቱታ በ25 ዓመት ጽኑ እሥራት እንዱቀጡ ተወስኖ ቅጣቱን በመፈጸም ላይ የሚገኙ መሆኑን ገልጸዉ ጥፊተኛ የተባለበትን ሕግ የተካዉ የፋዳራል የታክስ አስተዲደር አዋጅ ቅጣቱን አሻሽል የወጣ በመሆኑ ከሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 22(2)፣ ከወንጀል ሕጉ አንቀጽ 6(9) እና ከአዱሱ አዋጅ አኳያ ታይቶ ቅጣቱ እንዱቀነስላቸዉ ማመልከታቸዉ ነዉ። የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የአመልካችን አቤቱታ መርምሮ በአመልካች ላይ በመጨረሻ የቅጣት ዉሳኔ የሰጠዉ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ለእያንዲንደ ጥፊት መነሻ ቅጣት በመያዝ ዉሳኔ ባለማስተላለፈ ይህ ፍቤት ቅጣቱን በአዱሱ አዋጅ ድንጋጌ መሰረት እንደገና ለማስላት መቸገሩን ገልጾ አመልካች አቤቱታዉን ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርቦ መስተናገድ ይኖርባቸዋል በማለት በአብላጫ ድምጽ አቤቱታዉን ባለመቀበል ወስኗል።
በዚህ ዉሳኔ ቅር ተሰኝተዉ አመልካች ባቀረቡት ይግባኝ መነሻነት ጉዲዩን የተመለከተዉ ፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኙ ያስቀርባል በማለት በክርክርwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ሂደት ላይ እያለ አመልካች በይቅርታ በመለቀቃቸዉ መዝገቡን ዘግቶታል። ሆኖም ለአመልካች የተሰጠዉ ይቅርታ በስህተት ነዉ ተብል በመሰረዙና አመልካች ወደ ማረሚያ ቤት የተመለሱ በመሆኑ የተዘጋዉ መዝገብ ተከፍቶ እንዱንቀሳቀስ አመልካች ጠይቀዋል።
ተጠሪ በአመልካች በአቤቱታ ላይ መልስ እንዱሰጥበት የተደረገ ሲሆን አመልካች በራሳቸዉ የተዉትን ይግባኝ መልሰዉ እንዱንቀሳቀስ ማድረግ አይችለም። አመልካች የይግባኝ ቅሬታዉ መሰረዙን ካወቁና ወደ እስር ቤት ከተመለሱ ከ9 ወር በላይ የሆነዉ በመሆኑ አመልካች መዝገቡ እንዱንቀሳቀስ ያቀረቡት ምክንያት በቂና አሳማኝ ባለመሆኑ ጥያቀዉ ዉድቅ ይደረግልን በማለት ተከራክሯል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ጉዲዩን መርምሮ የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ ለሁለም ጉዲዮች የጊዜ ገደብና በቂ ምክንያት ያለዉ መሆኑ ሲታይ የተዘጋዉ መዝገብ እንዱንቀሳቀስ ለማድረግ በጊዜ ገደቡና በበቂ ምክንያት ተደግፍ ላቀርብ የሚገባዉ በመሆኑ አመልካች መዝገቡ ከተዘጋ ከ8 ወር በላይ ቆይቶ የተዘጋዉ መዝገብ ይንቀሳቀስልኝ በማለት ያቀረበዉ ጥያቄ በቂ ምክንያት በላለዉ ሁኔታ የቀረበ በመሆኑ ተገቢነት የለዉም በማለት የአመልካችን አቤቱታ ዉድቅ በማድረግ መዝገቡን ዘግቶታል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ትዕዛዝ በመቃወም ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘት፡- የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በትዔዛዙ ላይ እንዲሰፈረዉ በዚህ አግባብ የተዘጋ መዝገብ በምን ያህል ጊዜ መከፈት እንዲለበት በሥነሥርዓት ሕጉ ላይ አልተመለከተም። አመልካች ይቅርታዉ ከተሰረዘባቸዉ በኃላ ያለአግባብ የተሰረዘባቸዉ መሆኑን በመጥቀስ የይቅርታ አዋጁ ባስቀመጠዉ አግባብ አቤቱታ ለሚመለከተዉ አቅርበዉ ዉጤቱን ሲጠባበቁ ብዙ ጊዜ ወስድባቸዋል። አቤቱታ የቀረበለት አካል ፈጥኖ መልስ ሰጥቷቸዉ ቢሆን ኖሮ የይግባኙ መዝገብ እንዱንቀሳቀስ ወዱያዉኑ ማመልከት ይችለ ነበር። የሥነ-ሥርዓት ሕግ በራሱ ግብ ካለመሆኑም በላይ በጭፍጫፋ የሥነ-ሥርዓት ጉዲዮች መሰረታዊ የሆነ የተከሳሽ መብት ሉነካ አይገባም።
ስለሆነም ፍ/ቤቱ የፈጸመዉ መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ ዉሳኔዉ ተሽሮ ይግባኙን ተመልክቶ እንዱወስን ይመለስለት የሚል ነዉ።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 96 እና 97(3)ን ተላልፈዉ ወንጀል ፈጽመዋል ተብል የጥፊተኝነትና የቅጣት ዉሳኔ ከተላለፈባቸዉ በኃላ ጥፊተኛ የተባለበት አዋጅ በአዋጅ ቁጥር 983/2008 ስለተሻሻለ በወ/ሕ/አንቀጽ 6 እና 9(1) እንዱሁም በኢ.ፋ.ዳ.ሪ. ሕገ-መንግስት አንቀጽ 22(2) መሰረት የተወሰነባቸዉ ቅጣት እንዱሻሻልላቸዉ ለስር ፍ/ቤት አቤቱታ አቅርበዉ ዉድቅ ሲደረግባቸዉ አመልካች ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበዉ በመታዬት ላይ እያለ አመልካችን መንግስት በይቅርታ የፈታቸዉ በመሆኑ የይግባኝ መዝገቡ እንዱዘጋላቸዉ ባቀረቡት አቤቱታ መነሻነት መዝገቡ ከተዘጋ በኃላ መንግስት ለአመልካች ሰጥቶ የነበረዉን ይቅርታ በማንሳቱ እና አመልካች ወደ እስር በመግባታቸዉ ምክንያት የተዘጋዉ የይግባኝ መዝገብ ተከፍቶ እንዱታይላቸዉ ያቀረቡትን አቤቱታ ይህን የሚከለክል ግልጽ ሕግ መኖሩ ሳይገለጽ አቤቱታዉ ዉድቅ የተደረገበትን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል የተባለ ሲሆን ግራቀኙ መልስና የመልስ መልስ በጽሁፍ በማቅረብ ተከራክረዋል።
ተጠሪ የሰጡት መልስ ይዘት በአጭሩ፡- አመልካች መዝገቡን ያስዘጉት ይቅርታ ስለተደረገላቸዉ ሲሆን በሳምንት ዉስጥ ይቅርታዉ በስህተት የተሰጠ መሆኑ ተገልጾ ወደ እስር እንዱመለሱ ተደርጓል። አመልካች ይቅርታዉ መሰረዙን ካወቁ ከ8 ወር በኃላ አቤቱታ ሉያቀርቡ የቻለበት ምክንያት ስለመኖሩ አላቀረቡም። አመልካች በወ/ሕ/አንቀጽ 6፣ 9(1) እና በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 22(2) የተቀመጠዉን መብት ማስጠበቅ የሚችለት በስነ-ስርዓት ሕጉ የተቀመጠዉን መርህ ተከትል አቤቱታ በስርዓቱ ሲቀርብ ነዉ። የአመልካች አቤቱታ ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ ዉስጥ ያልቀረበ በመሆኑ አቤቱታዉ ተቀባይነት ማጣቱ የሚነቀፍ አይደለም። አመልካች በሰበር አቤቱታቸዉ ላይ ይቅርታዉ ቀሪ መደረጉን እንዲወቁ መዝገቡ እንዱንቀሳቀስ ያላመለከቱት በይቅርታ አዋጁ መሰረት አቤቱታ ለሚመለከተዉ አካል አቅርበዉ ዉጤቱን ሲጠባበቁ መሆኑን ቢገልጹም በስር ያልተነሳ በመሆኑ ተቀባይነት የለዉም። ስለሆነም በስር የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት ባለመኖሩ ይጽናልን የሚል ነዉ። አመልካች የሰበር አቤቱታቸዉን በሚያጠናክር መልኩ የመልስ መልስ አቅርበዋል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የግራ ቀኙ ክርክር በአጭሩ ከላይ የተመለከተዉን የሚመስል ሲሆን ከስር ፍ/ቤት ዉሳኔ እና ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል ተብል ከተያዘዉ ጭብጥ ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
መርምረን እንደተረዲነዉ አመልካች በስር ፍ/ቤት ያቀረቡት አቤቱታ ቀደም ብል ጥፊተኛ የተባለበትን ሕግ የተካዉ አዱሱ አዋጅ ለጥፊቱ የተቀመጠዉን ቅጣት አሻሽል የወጣ በመሆኑ በኢ.ፋ.ዳ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 22(2) መሰረት ቅጣቱ አዱስ በወጣዉ አዋጅ ድንጋጌ አግባብ እንደገና እንዱሰላለት ነዉ። የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አቤቱታዉን ተቀብል ከመረመረ በኃላ ተፈጻሚ በመሆን ላይ ያለዉን ቅጣት የወሰነዉ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ቅጣቱን ሲወስን መነሻ ቅጣት በመያዝ ባለማስላቱ አዱሱን ሕግ ተፈጻሚ ለማድረግ እንደሚቸገር ገልጾ አመልካች አቤቱታዉን ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርበዉ መስተናገድ እንዲለባቸዉ በመጥቀስ ወስኗል። አመልካች በዚህ ዉሳኔ ቅር ተሰኝቶ ያቀረቡት ይግባኝ ያስቀርባል ተብል በመታየት ላይ ባለበት ወቅት አመልካች በይቅርታ በመለቀቃቸዉ የጉዲዩ መታየት አስፈላጊ ሆኖ ባለመገኘቱ መዝገቡ ተዘግቷል። ይህ በእንዱህ እንዲለ ይቅርታዉን የሰጠዉ አካል ይቅርታዉ በስህተት የተሰጠ መሆኑን በመግለጽ ይቅርታዉን በማንሳቱና አመልካች ቅጣቱን መፈጸም እንዱጀምሩ ከተደረገ ከ8 ወር በኃላ አመልካች የተዘጋዉ መዝገብ እንዱንቀሳቀስላቸዉ ቢጠይቁም የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ዘግይቶ የቀረበ አቤቱታ ነዉ በማለት ሳይቀበላቸዉ ቀርቷል። የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አመልካች መዝገቡ እንደገና ተከፍቶ እንዱንቀሳቀስላቸዉ ያቀረቡትን አቤቱታ ከ8 ወር በላይ ዘግይቶ የቀረበ ነዉ በማለት ዉድቅ ማድረጉ በአግባቡ ነዉ? ወይስ አይደለም? የሚለዉን ቀጥለን እንመልከት።
በመሰረቱ የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ ለይግባኝ ማቅረቢያና ተያያዥ ጉዲዮች የጊዜ ገደብ ቢያስቀምጥም በመታየት ላይ ያለ መዝገብ መዘጋቱ አስፈላጊ ሆኖ ከተዘጋ በኃላ እንደገና መከፈቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በምን ያህል ጊዜ ዉስጥ አቤቱታ ላቀርብበት እንደሚገባ በሕግ የጊዜ ገደብ አልተቀመጠም። ይህ በሚሆንበት ወቅት የጊዜ ገደቡ የሚወሰነዉ የጉዲዩን ሁኔታዎችና የአቤቱታዉን ዓይነት በመመልከት እንጂ ከተወሰነ ጊዜ በኃላ የቀረበዉ አቤቱታ ተቀባይነት የለዉም በሚል ድምዲሜ ላይ በመድረስ አይደለም።
በተያዘዉ ጉዲይ መዝገቡ እንዱዘጋ ምክንያት የሆነዉ የአመልካች ጥፊት ወይም ይግባኙን አለመፈለግ ሳይሆን ይቅርታዉን የሰጠዉ አካል የፈጸመዉ ስህተት ነዉ።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
እንዱሁም የተዘጋዉ መዝገብ ከምን ያህል ጊዜ በኃላ ሉከፈት እንደሚችልና እንደማይችል በግልጽ በሕጉ ያልተደነገገ መሆኑ አመልካች ፈጥኖ አቤቱታዉን እንዲያቀርብ የሚያደርገዉ ከመሆኑ አንጻር በሕጉ ክፍተት ምክንያት አመልካች መብቱን ሉያጣ አይገባም። ከዚህ በተጨማሪ አመልካች የኢ.ፋ.ዳ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 22(2)፣ የወ/ሕ/አንቀጽ 6 እና 9(1)ን መሰረት በማድረግ አቤቱታ ያቀረበበት ጉዲይ በባህሪዉ እንደመደበኛ የክርክር ጉዲይ የሚታይ ሳይሆን አቤቱታ በቀረበ ጊዜ ሉስተናገድ የሚችል ከመሆኑም በላይ አቤቱታዉን በቀጥታ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በማቅረብ ማስወሰን እንዱችል ከፍተኛዉ ፍ/ቤት በዉሳኔዉ የገለጸበት ከመሆኑ አንጻር መዝገቡ እንደገና አይንቀሳቀስም መባለ ምክንያታዊ አይደለም።
ሲጠቃለል የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካች የተዘጋዉ መዝገብ እንዱንቀሳቀስለት የጠየቀበትን አቤቱታ በሥነ-ሥርዓት ሕጉ በግልጽ የጊዜ ገደብ ባልተቀመጠበትና ለመዝገቡ መዘጋትም ዋናዉ ምክንያት የይቅርታ ሰጪዉ አካል ስህተት እንጂ የአመልካች ቸልተኝነት ወይም ይግባኙን አለመፈለጉ ባልሆነበት ሁኔታ የተዘጋዉን መዝገብ ለማንቀሳቀስ አመልካች በቂ ምክንያት አላቀረበም በማለት የሰጠዉ ትዕዛዝ የአመልካችን መብት የሚያጣብብና መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉሻር የሚገባዉ ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም የሚከተለዉ ተወስኗል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ሚያዚያ 04 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 195(2/ለ/2) መሰረት ተሽሯል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የተዘገዉን መዝገብ እንደገና በማንቀሳቀስ በይግባኙ ላይ ግራ ቀኙን በማከራከር ተገቢዉን እንዱወስን ጉዲዩን መልሰንለታል። ይጻፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ ተመላሽ ይደረግ።
No topics extracted.