በአንድ የወንጀል ክስ ማመልከቻ ላይ ተጠቅሶ የቀረበ ድንጋጌና የክሱ ፍሬነገር ዝርዝር ላይ በስህተት የተጠቀሰ ወይም ሳይጠቀስ የታለፈ መሰረታዊ ነገር መኖሩ ሳይረጋገጥ ከወዱሁ አንቀጽ ካልተለወጠ በሚል ምክንያት ክስ እንዱሻሻል ትእዛዝ መስጠትና ይህ ካልተፈጸመ በሚል የክሱን መዝገብ መዝጋቱ ክስ እንዱሻሻል የሚደረግብትን ህጋዊ የፋዳራል ጠ/አቃቤ ህግ እና **ተጠሪ፡-** ነቢላ አህመድ www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XLIX ያላገናዘበ ስለመሆኑ አንድ ተከሳሽ ላይ የቀረበ ክስ ሁለት ሆኖ 1ኛዉ ክስ ቀደም ሲል ፍርድ ቤት በሰጠው ትእዛዝ መሰረት ተሻሽል ባለመቅረቡ የሚዘጋ ቢሆን ሁለተኛዉ ክስ ላይ ያለምንም ህጋዊ ምክንያት ዉሳኔ ሳይሰጥ ማለፍ ሥነ-ሥርዓታዊ ስላለመሆኑ በወ/መ/ስ/ስ/ህግ ቁ/112፣113/2/፣119
No summary available.
የሰ/መ/ቁ/155789 ጥቅምት 21 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡ ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንደሻዉ አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች፡- የፋዳራል ጠ/አቃቤ ህግ ተጠሪ፡- ነቢላ አህመድ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበዉ ጉዲይ የወንጀል ክስ የሚሻሻልበት አግባብ የሚመለከት ነዉ።አመልካች ተጠሪ ላይ ያቀረበዉ ክስ 1ኛ/የኢ.ፋ.ዱ.ሪ.የወንጀል ህግ አንቀጽ 556/2/ሀ በመተላለፍ ድንጋይ ወርዉራ የግል ተበዲይ አመለወርቅ ታደሰ ደረቷንና የቀኝ እግሯን በመምታት ቀላል የአካል ጉዲት በማደረስ ፣2ኛ/ የወንጀል ህጉን አንቀጽ 615 በመተላለፍ በአንደኛዉ ክስ የተጠቀሰችዉን የግል ተበዲይ አስነዋሪ ስድብ ሰደበቻት በማለት ተደራራቢ ክስ ያቀረባበት ሲሆን ተጠሪ የእምነት ክደት ቃል ከመስጠቷ በፉት መቃወሚያ በሚል ምክንያት በአንደኛዉ ክስ ላይ ድንጋጌዉና የተፈጸመዉ ድርጊት አይጣጣምም በማለቷ የፋዳራል የመ/ደረጃ ፍርድ ቤት ይህንኑ መቃወሚያ በመመርኮዝ አቃቤ ህግ 1ኛዉን ክስ አንቀጽ 556/2/ሀ ወደ አንቀጽ 560/1/ አሻሽል እንዱያቀርብ ትእዛዝ ሰጥቶ አቃቤ ህግ የተሻሻለ ክስ ባለማቅረቡ በወ/መ/ስ/ስ/ህግ ቁ/122/3/ መሰረት መዝገቡን ዘግቷል። አቃቤ ህግ ይህንኑ በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ይግባኝ ቅሬታ ያቀረበ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ የስር ፍርድ ቤት ትእዛዝ በማጽናት ዉሳኔ ሰጥቷል።
ለዚህ ሰበር ችልት አቤቱታ ቀርቦ በዚህ ላይ ሲሆን የአቃቤ ህግ አቤቱታ ይዘት ባጭሩ የስር ፍርድ ቤት የወንጀል ህግ አንቀጽ 556/2/ሀ እና 560/1/ ማቋቋሚያ ፍሬነገሮችን በአግባቡ ሳያገናዝብ የሰጠዉ ትእዛዝ ተገቢ ባለመሆኑ እንዱታረም የሚል ሲሆን የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ክሱ ካልተሸሻለ አላይም በማለት የስር ፍርድ ቤት መዝገቡን መዝጋቱ ተገቢነት ለመመርመር እንዱቻል ጭብጥ ተይዞ ተጠሪ መልስ እንዱትሰጥ ተደርጓል።ተጠሪም የተፈጸመዉ ድርጊት የእጅ እልፉት ነዉ በሚል የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ ተገቢ ነዉ በማለት ተከራክራለች።አቃቤ ህግ ክርክሩን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቷል።
የጉዲዪ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ ባጭሩ የተገለጸ ሲሆን እኛም ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል ሲባል የተያዘዉን ጭብጥ መሰረት በማድረግ አግባብነት ካለዉ ህግ ጋር በማገናዘብ መርምረናል።መዝገቡን መርምረን እንደተገነዘብነዉ ፍርድ ቤት ክስ እንዱሻሻል ትእዛዝ የሚሰጠዉ በምን አግባብ ነዉ? ህጋዊ ዉጤቱስ ምንድነዉ? የሚለዉ መታየት ያለበት ነጥብ ሆኖ አግኝተናል። የወንጀል ክስ ማመልከቻ አዘጋጃጀት አስመልክቶ ይዘቱና ዓይነቱ በምን አኳኋን እና ዝርዝር ሉኖረዉ እንደሚገባ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት አንቀጽ 111 እና 112 ላይ ተመልክቷል።ከነዚህ ድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ የሚቻለዉ ክሱ በዝርዝር እንዱገልጽ ከሚጠበቅባቸዉ መሰረታዊ ፍሬነገሮች ዉስጥ በክሱ የተጠቀሰዉ የወንጀል ህግ ድንጋጌ እና ተከሳሹ የፈጸመዉ የወንጀል ተግባር የክሱ ፍሬነገር ከህጉ አነጋገር ጋር በጣም የተቀራረበ መሆን እንዲለበት ነዉ። የክሱ አዘገጃጀትና ዝርዝር ይዘት ላይ መገለጽ የሚገባዉ መሰረታዊ ነገር ባለመገለጹ ተከሳሹን ያሳሳተዉ እንደሆነ ወይም ትክክለኛ ፍርድ ለመስጠት የማይቻል ከሆነ ደግሞ ፍርድ ቤቱ በራሱ አስተያየት ወይም ማመልከቻ በቀረበለት ጊዜ እንደነገሩ ሁኔታ ክሱ እንዱለወጥ፣ እንዱጨመር ወይም አዱስ ክስ እንዱዘጋጅ ትእዛዝ መስጠት እንደሚችል በወ/መ/ስ/ስ/ህግ አንቀጽ 118 እና 119/1/ ድንጋጌዎች ይዘት ያስገነዝባለ። ስለሆነም ክስ እንዱሻሻል ትእዛዝ የሚሰጠዉ በክስ ማመልከቻ ፍርም ወይም በክሱ ማመልከቻ ላይ ስለወንጀለ አስፈላጊ ዝርዝር ዉስጥ ስህተት ሲገኝ ወይም ሳይጠቀስ ሲቀርና ይህምwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
መሰረታዊ ነገር ሆኖ ሲገኝ እንደሆነ ስለመሆኑ እንገነዘባለን። በዚህ ምክንያት ፍርድ ቤቱ ክስ እንዱሻሻል ትእዛዝ ሰጥቶ ኣቃቤ ህግ የተሻሻለ ክስ አዘጋጅቶ ያላቀረበ እንደሆነ ተከሳሹ ለጊዜዉ እንደሚለቀቅ የወ/መ/ስ/ስ/ህግ ቁ/122/3/ ድንጋጌ ይገልጻል። ስለሆነም በፍ/ቤቱ ትእዛዝ መሰረት ክሱ ተሻሽል ያልቀረበ እንደሆነ ዉጤቱ መዝገቡን ለጊዜዉ በመዝጋት ተከሳሹን መልቀቅ እንደሆነ ህጉ በግልጽ ደንግጓል።
በዚህ መዝገብ በተያዘዉ ጉዲይ በ1ኛዉ ክስ የወንጀል ህግ አንቀጽ 556/2/ሀ ተጠቅሶ በክሱ ዝርዝር ላይ ደግሞ ተጠሪ በሰዉ አካልና ጤና ላይ ጉዲት ለማድረስ አስባ የግል ተበዲይ አመለቀወርቅ ታደሰ ላይ ድንጋይ ወርዉራ ደረቷንና የቀኝ እግሯን በመምታት የህመም ስሜት አንዱሰማት በማድረግ ቀላል የአካል ጉዲት ማድረስ ወንጀል ፈጽማለች የሚል ሲሆን የስር ፍርድ ቤት ይህ ድንጋጌ ወደ 560/1/ ተለዉጦ ክሱ ተሻሽል መቅረብ አለበት በማለት ትእዛዝ የሰጠዉ በኣቃቤ ህግ በኩል የቀረበዉ ክስ ዝርዝር ስህተት ስላለበት ወይም መጠቀስ ያለበት መሰረታዊ የክሱ ፍሬነገር ባለመጠቀሱ ሳይሆን ተፈጸመ የተባለዉ ድርጊት ክስ የቀረበበትን ድንጋጌ አያቋቁምም ከሚል መነሻ እንደሆነ መገንዘብ ተችሎል። በመሰረቱ ክስ እንዱሻሻል የሚደረግበት ምክንያት እና አቃቤ ህግ ያቀረበዉን ክስ በማስረጃ አረጋግጧል ወይስ አላረጋገጠም? በአቃቤ ህግ ማስረጃ የተረጋገጠዉ የድርጊቱ አፈጻጻምና ዉጤቱ በየትኛዉ የህግ ድንጋጌ የሚሸፈን ነዉ?
የሚለዉ ጉዲይ በየራሱ ተለያይቶ የሚታይ ስለመሆኑ ከወ/መ/ስ/ስ/ህግ ቁ/119 እና 113/2/ ይዘት መገንዘብ ይቻላል። የክስ ማመልከቻ እንዱሻሻል የሚደረገዉ ከላይ በተገለጸዉ አግባብ በክሱ ዝርዝር ላይ መገለጽ የሚገባዉ መሰረታዊ ጉዲይ ሳይገለጽ የቀረ እንደሆነ ወይም ደግሞ ያለአግባብ የተገለጸዉ ነገር ተከሳሹን የሚያሳስት ነዉ ተብል ሲታሰብ ነዉ። በልላ በኩል አቃቤ ህግ በክሱ መሰረት የድርጊቱን ፍሬነገር በማስረጃ ማስረዲት ወይም አለማስረዲት እና ዉጤቱን በተመለከተ ፍርድ ቤቱ ድምዲሜ ላይ ሉደርስ የሚገባዉ የአቃቤ ህግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ እንደሆነ ከወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ.141 መገንዘብ አዲጋች አይደለም። የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 112 ላይ እንደተገለጸዉ ደግሞ የክስ ማመልከቻ ስለወንጀለና ስለሁኔታዉ የሚሰጠዉ ዝርዝር መግለጫ ወንጀለኛዉ የፈጸመዉ ተግባር ወንጀል ከሚያደርገዉ ህግ አነጋገር ጋራ በጣም የተቀራረበ መሆን አለበት ሲል ህግ አዉጪዉ በጥንቃቄ የተመለከተዉ የተፈጸመዉ ድርጊት የተጠቀሰዉን ድንጋጌ ማቋቋሚያ ፍሬነገር ማሟላት አለማሟላት ፍርድ ቤቱwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በማስረጃ የሚያረጋግጠዉ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ እንደሆነ ያስገነዝባል።ለዚህም ነዉ አቃቤ ህግ በክሱ በገለጸዉ ልክ ሳይሆን ከዚያ ባነሰ ሁኔታ ወይም ክስ ባይቀርብበትም በአማራጭ ክስ ላቀርብበት የሚችል ድንጋጌ የሚሸፈን የወንጀል ፍሬነገር መፈጸሙ በማስረጃ በተረጋገጠ ጊዜ ፍርድ ቤቱ ተገቢ ነዉ ወደሚለዉ ድንጋጌ ለመለወጥ እንዱችል በወ/መ/ስ/ስ/ህግ ቁ/113/2/ ስልጣን የተሰጠዉ። ከዚህም በሻገር አቃቤ ህግ እንደክሱ አቀራረብ በማስረጃ ማስረዲት ካልቻለ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹን በነጻ የማሰናበት ስልጣን በህጉ የተሰጠዉ ነዉ።
በተያዘው ጉዲይ ላይ 1ኛዉ ክስ የተጠቀሰዉ ድንጋጌ እና በክሱ ዝርዝር የተገለጸዉ ፍሬነገር ላይ ጉድለት ወይም ስህተት ስለመኖሩ አልተገለጸም ።ይልቁንም በግል ተበዲይ ላይ የደረሰዉ ጉዲት መጠነኛ ነዉ የሚል ምክንያት ብቻ ነዉ ።በድርጊቱ ምክንያት የግል ተበዲይ ላይ የደረሰዉ ጉዲት መጠን የሚረጋገጠዉ በማስረጃ ስለሚሆን ከወዱሁ ማስረጃ ሳይሰማ ድምዲሜ ላይ መድረሱ ተገቢ ሆኖ አልተገኘም። ስለሆነም አመልካች በክሱ ማመልከቻ ላይ ጠቅሶ ያቀረበዉ የወንጀል ህጉ ድንጋጌና የክሱ ፍሬነገር ዝርዝር ላይ በስህተት የተጠቀሰ ወይም ሳይጠቀስ የታለፈ መሰረታዊ ነገር መኖሩ እስካልተረጋገጠ ድረስ የተፈጸመዉ ድርጊትና አግባብነት ያለዉ ድንጋጌ የትኛዉ ነዉ የሚለዉ የክሱ ማቋቋሚያ ፍሬነገር መሟላት አለመሟላት ማስረጃ ተሰምቶ የሚለይና ፍርድ ቤቱ በህጉ አግባብ ዉሳኔ የሚሰጥበት ሆኖ እያለ ከወዱሁ አንቀጽ ካልተለወጠ በሚል ምክንያት ክስ እንዱሻሻል ትእዛዝ መስጠትና ይህ ካልተፈጸመ በሚል የክሱን መዝገብ መዝጋቱ ክስ እንዱሻሻል የሚደረግብትን ህጋዊ ምክንያት እና አላማ ያገናዘበ ሆኖ አላገኘንም።ከዚህም ባሻገር ተጠሪ ላይ የቀረበዉ ክስ ሁለት ሆኖ እያለ 1ኛዉ ክስ በፍርድ ቤቱ ትእዛዝ መሰረት ተሻሽል ባለመቅረቡ የሚዘጋ ቢሆን እንኳን ሁለተኛዉ ክስ ላይ ዉሳኔ ላለመስጠት ፍርድ ቤቱ ምንም ዓይነት ህጋዊ ምክንያት ሳይኖረዉ ማለፈም የክርክር አመራር ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት ሆኖ አግኝተናል።በዚሁ አግባብ ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
1ኛ/የፋዳራል የመ/ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/112647 ላይ በ24/06/09 ዓ.ም እና በ08/07/09 ዓ.ም የሰጠዉ ብይን እና ይህንኑ በማጽናት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/194971 በ02/04/2010 ዓ.ም የሰጠዉ ፍርድ በወ/መ/ስ/ስ/ህግ ቁ/195/2/ሀ መሰረት ተሰርዟል።
2ኛ/የፋዳራል የመ/ደረጃ ፍርድ ቤት የዘጋዉን መዝገብ በማንቀሳቀስ ክርክሩን ሰምቶ ተገቢዉን ዉሳኔ እንዱሰጥበት በማለት በወ/መ/ስ/ስ ህግ ቁ/ 195/2/ሀ መሰረት ጉዲዩን መልሰንለታል።ይጻፍ።
No topics extracted.