አንድ ተከሳሽ በአንድ ቸልተኝነትና በአንድ ድርጊት በደረሱ ጉዲቶች በተደራራቢ ወንጀልች ሲከሰስ ላላ የተለየ ሀሳብና ድርጊት መኖሩ እስካልተረጋገጠ ድረስ አንደን በቸልተኝነት ላላዉን ደግሞ ሆን ተብል ታስቦ በተፈጸመ ወንጀል ጥፊተኛ የሚደረግበት አግባብ አቶ ሀብታሙ ደስታ እና የፋዳራል ጠቅላይ ዐ/ሕግ www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XLVIII ቅጣትን በሚመለከት ተደራራቢ ወንጀልች ተፈጽመዉ ሲገኙ ቅጣት ሉወሰን የሚገባዉ ለእያንዲንደ ወንጀል መነሻ ቅጣት ከተያዘ በኃላ እነዚህን በመደመር ድምሩ የቅጣት መጠን የሚያርፍበትን ዝቅተኛ የቅጣት እርከን በመለየት ስለመሆኑ የተሻሻለዉ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 02/2006 አንቀጽ 22(1/ሀ)
No summary available.
ቀን-መስከረም 22 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ኃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች:- አቶ ሀብታሙ ደስታ - አልቀረበም።
ተጠሪ፡- የፋዳራል ጠቅላይ ዐ/ሕግ - ቀረቡ።
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ በተሽከርካሪ በቸልተኝነት ሰዉ የመግደል፣ በሰዉ አካል ላይ ጉዲት ማድረስና በመገናኛና በማጓጓዣ ላይ ጉዲት የማድረስ ወንጀልችን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረዉ በአፊር ክልል አዉሲረሱ ከፍተኛ ፍ/ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ በመሰረተዉ ክስ መነሻነት ነዉ። አመልካች ላይ ቀርበዉ የነበሩ ክሶች 3 ሲሆኑ 1ኛ ክስ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 543(2) የተመለከተዉን በመተላለፍ በቀን 14/04/2009 ዓ.ም ከቀኑ 9፡45 ሰዓት ላይ ኤሉዲር ከተማ ለመግባት 6 ኪ.ሜትር ሲቀረዉ ኮድ 3-78217 ኢት የሆነ የመከላከያ ደብል ጋቢና ኒሳን መኪና እያሽከረከረ በቸልተኝነት በተቃራኒ አቅጣጫ ሲጓዝ ከነበረ ኮድ 3-86206 ኢት የሆነ ገልባጭ መኪና ጋር በመጋጨቱ ጭኗቸዉ ከነበሩ ሰዎች መካከል ኢንጅነር ሀጎስ ገ/ጊዮርጊስ የተባለዉ ሕይወቱ በማለፈ በፈጸመዉ በቸልተኝነት ሰዉ መግደል ወንጀል ተከሷል የሚል ነዉ። 2ኛ ክስ የወ/ሕ/አንቀጽ 555(ሀ) የተመለከተዉን በመተላለፍ በ1ኛ ክስ በፈጸመዉ ግጭት በግል ተበዲይ ሂሩት ሰለሞን ላይ የላይኛዉና የታችኛዉ መንጋጋ አጥንት ስብራትና በታችኛዉwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
መንጋጋ በግራ በኩል ያለዉ አንድ ጥርሷ በመዉለቁ በፈጸመዉ ታስቦ በሚፈጸም ከባድ የአካል ጉዲት ወንጀል ተከሷል የሚል ነዉ። 3ኛ ክስ ደግሞ የወ/ሕ/አንቀጽ 506(1/መ) የተመለከተዉን በመተላለፍ በተመሳሳይ ጊዜና ቦታ ባደረሰዉ ግጭት የሚያሽከረክረዉ ተሽከርካሪ ጋቢና ሙለ በሙለ በመጨራመቱ፣ ቻንሲዉ በመታጠፈና የሞተር ሳፖርቶ በመቆረጡ እንዱሁም በሰ.ቁ 3-86206 ኢት መኪና ላይም አቫንታሪ ቦሉስትራ፣ ስፕረይ ጋቢናና ራዱያተር መሰበርና በር መታጠፍ በድምሩ ብር 1,100,000 ግምት ያለዉ የንብረት ጉዲት ያደረሰ በመሆኑ መገናኛዎችና መጓጓዣዎች ላይ ጉዲት የማድረስ ወንጀል ተከሷል የሚል ነዉ።
በስር ፍ/ቤት አመልካች የእምነት ክህደት ቃል ሲጠየቅ የወንጀል ድርጊቶቹን አለመፈጸሙን ገልጾ ጥፊተኝነቱን ክድ የተከራከረ ሲሆን የዐ/ሕግ ማስረጃዎች ተሰምተዉ አመልካች እንዱከላከል ብይን የተሰጠ ሲሆን አመልካች የመከላከያ ማስረጃ ያላቀረበ በመሆኑ ፍ/ቤቱ አመልካችን በተከሰሱበት ሦስቱም ክሶች ጥፊተኛ በማድረግ በ7(ሰባት) ዓመት ጽኑ እስራትና በብር 500 የገንዘብ መቀጮ እንዱቀጣ ወስኗል። በዚህ ዉሳኔ አመልካች ቅር ተሰኝቶ ባቀረበዉ ይግባኝ መነሻነት ጉዲዩን የተመለከተዉ የአፊር ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ግራ ቀኙን ካከራከረ በኃላ መርምሮ በ3ኛ ክስ ጉዲቱ ሆን ተብል የደረሰ ሳይሆን በቸልተኝነት መሆኑን በመግለጽ አመልካች ጥፊተኛ የተባለበትን የሕግ ድንጋጌ ከወ/ሕ/አንቀጽ 506 ወደ አንቀጽ 505(3) በመለወጥ ቅጣቱን በማሻሻል አመልካች በ5 ዓመት ከ1 ወር እስራት እና በብር 1,000 እንዱቀጣ ወስኗል።
የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ ይህንኑ ዉሳኔ በመቃወም ለማስቀየር ነዉ።
አመልካች ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ይዘት፡- ከወንጀል ሕግ አንቀጽ 61(3) አንጻር በአንድ ቸልተኝነት በተፈጸመ ድርጊት በሦስት ተደራራቢ ክስ ጥፊተኛ መደረጌ ተገቢ አይደለም። በ1ኛ ክስ በቸልተኝነት ሰዉ መግደል በሚል በወ/ሕ/አንቀጽ 543(2) ስር ጥፊተኛ ተብዬ በተመሳሳይ ድርጊት ለደረሰ የአካል ጉዲት የወ/ሕ/አንቀጽ 555(ሀ) ስር ሆን ብል የአካል ጉዲት በማድረስ ወንጀል ጥፊተኛ መባላ ተገቢ አይደለም።
እንዱሁም በወ/ሕ/አንቀጽ 23(2) እና 57 መሰረት ወንጀልችን የሚያቋቁሙ ፍሬ ነገሮች ጋር ተገናዝቦ ተገቢዉ ትርጉም ተሰጥቶት ዉሳኔዉ ይሻርልኝ። ቅጣቱም ቢሆን የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 02/2006 መሰረት ተደርጎ ያልተወሰነ በመሆኑ ቅጣቱ ቀልልwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
እንዱወሰንና የሚወሰነዉ ቅጣትም እስከአሁን የፈጸምኩት ግምት ዉስጥ ገብቶ በገደብ እንዱሆንልኝ የሚል ነዉ።
የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ በስር ፍ/ቤት በአመልካች ላይ የቀረበዉ ክስ መኪና በቸልተኝነት በማሽከርከር ጉዲት ማድረስ ሆኖ ሳለ በ2ኛ ክስ በወ/ሕ/አንቀጽ 555(ሀ) ስር ጥፊተኛ ተብል የተወሰነበት አግባብ ለማጣራት ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል የተባለ ሲሆን ግራ ቀኙ መልስና የመልስ መልስ በጽሁፍ በማቅረብ ተከራክረዋል።
ተጠሪ ያቀረበዉ መልስ፡- አመልካች በቀረበበት ሦስት ክሶች የተጠቀሰዉን ጉዲት ያደረሰዉ በአንድ የቸልተኝነት ድርጊት ቢሆንም በሕግ ጥበቃ በሚደረግላቸዉ ሦስት የተለያዩ መብቶች ላይ የተፈጸመ በመሆኑ በተደራራቢ ክስ ጥፊተኛ መደረጉ ተገቢ ነዉ። ይግባኝ ሰሚዉ ፍ/ቤት በ3ኛ ክስ አንቀጹን ለዉጦ ጥፊተኛ ማለቱም ሆነ ቅጣት መወሰኑ ተገቢ ነዉ። በቅጣት አሰላል ላይ የተፈጸመ ስህተት የላለ ከመሆኑም በላይ ቅጣት የሚገደብ ከሆነ ለማህበረሰቡ አስተማሪ ላሆን ስለማይችል የአመልካች አቤቱታ ዉድቅ ይደረግልን የሚል ነዉ። አመልካች በሰጠዉ የመልስ መልስ የሰበር አቤቱታዉን በሚያጠናክር መልኩ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተገለጸዉን የሚመስል ሲሆን የአመልካችን አቤቱታ ያስቀርባል ሲባል ከተያዘዉ ጭብጥ አንጻር ከስር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ እና አግባብነት ካላቸዉ የሕግ ድንጋጌዎች አኳያ መርምረናል። በዚህም መሰረት ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል ሲባል ከተያዘዉ ጭብጥ አንጻር መርምረን እንደተረዲነዉ አመልካች የሚያሽከረክረዉን ተሽከርካሪ በቸልተኝነት በማሽከርከር በፈጸመዉ ግጭት አንድ ሰዉ የሞተ ሲሆን አንድ ሰዉ ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዲት ከመድረሱም በላይ በተጋጩት ሁለት መኪኖች ላይ ጉዲት መድረሱ አከራከሪ አይደለም። አመልካች አጥብቆ የሚከራከረዉም ሆነ አቤቱታዉ ለሰበር ያስቀርባል ሲባል የተያዘዉ ጭብጥ አመልካች የአንድ ሰዉ ሕይወት እንዱያልፍ ያደረገዉም ሆነ ከባድ የአካል ጉዲት በሰዉ ላይ ያደረሰዉ በቸልተኝነት በማሽከርከር በፈጸመዉ ግጭት መሆኑ አሻሚ ባልሆነበት አመልካች በ2ኛ ክስ የወ/ሕ/አንቀጽ 555(ሀ) የተመለከተዉን በመተላለፍ ሆን ተብል በተፈጸመ ከባድ የአካል ጉዲት ማድረስ ወንጀል ጥፊተኛ መባለ ተገቢ ነዉ ወይስ አይደለም የሚለዉ ነዉ።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በመሰረቱ አንድ ተከሳሽ በአንድ ቸልተኝነትና በአንድ ድርጊት በደረሱ ጉዲቶች በተደራራቢ ወንጀልች ሲከሰስ ላላ የተለየ ሀሳብና ድርጊት መኖሩ እስካልተረጋገጠ ድረስ አንደን በቸልተኝነት ላላዉን ደግሞ ሆን ተብል ታስቦ በተፈጸመ ወንጀል ጥፊተኛ የሚደረግበት አግባብ የለም።
በተያዘዉ ጉዲይ አመልካች ተሽከርካሪዉን በቸልተኝነት በማሽከርከር በፈጸመዉ ግጭት በ1ኛ ክስ የተመለከተዉ የሰዉ ሕይወት በማለፈ የወ/ሕ/አንቀጽ 543(2) የተመለከተዉን በመተላለፍ በቸልተኝነት በፈጸመዉ ግድያ ከተከሰሰና ጥፊተኛ ከተባለ በተመሳሳይ ቸልተኝነትና ድርጊት በ2ኛ ክስ የተገለጸዉ ከባድ የአካል ጉዲት ሲደርስ ደግሞ የወ/ሕ/አንቀጽ 555(ሀ) የተመለከተዉን በመተላለፍ ሆን ተብል በተፈጸመ የአካል ጉዲት ማድረስ ወንጀል ጥፊተኛ ልባል የሚችልበት አግባብ የለም። በመሆኑም አመልካች በ2ኛ ክስ ጥፊተኛ ልባል የሚገባዉ የወ/ሕ/አንቀጽ 555(ሀ) የተመለከተዉን በመተላለፍ ሆን ተብል በተፈጸመ ከባድ የአካል ጉዲት ሳይሆን የወ/ሕ/አንቀጽ 559(2) የተመለከተዉን በመተላለፍ በቸልተኝነት በተፈጸመ የአካል ጉዲት ነዉ። ስለሆነም አመልካች በ2ኛ ክስ በስር ፍ/ቤት ጥፊተኛ የተባለበት የሕግ አንቀጽ በወ/መ/ሕ/ስ/ስ/ቁ 113(2) መሰረት ተለዉጦና ተሻሽል በወ/ሕ/አንቀጽ 559(2) የተመለከተዉን በመተላለፍ ጥፊተኛ ልባል የሚገባዉ ሆኖ ተገኝቷል።
ላላዉ ቅጣትን የተመለከተዉ ሲሆን ተደራራቢ ወንጀልች ተፈጽመዉ ሲገኙ ቅጣት ሉወሰን የሚገባዉ በተሻሻለዉ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 02/2006 አንቀጽ 22(1/ሀ) መሰረት ለእያንዲንደ ወንጀል መነሻ ቅጣት ከተያዘ በኋላ እነዚህን በመደመር ድምሩ የቅጣት መጠን የሚያርፍበትን ዝቅተኛ የቅጣት እርከን በመለየት መሆኑ ተመልክቷል። ሆኖም የስር ፍ/ቤቶች ለእያንዲንደ ወንጀል ቅጣቱን ጨርሰዉ ካሰለ በኃላ በመደመር የወሰኑ መሆኑ ስህተት ነዉ። በመሆኑም ቅጣቱን እንደገና ማስላቱ ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል። በዚሁም መሰረት በ1ኛ ክስ የወ/ሕ/አንቀጽ 543(2) ተላልፎል ተብል ጥፊተኛ ለተባለበት በስር ፍ/ቤት የተያዘዉ ደረጃ 4 እርከን 16 ሆኖ የ3 ዓመት ከ2 ወር እስራት መነሻ ቅጣት እንዲለ ይዘናል። እንዱሁም በ3ኛ ክስ ይግባኝ ሰሚዉ ፍ/ቤት የ1 ወር እስራት መነሻ ቅጣት የያዘዉን እንዲለ ወስደናል። 2ኛ ክስን በተመለከተ የወ/ሕ/አንቀጽ 559(2) ደረጃ 2 እርከን 8 ስር መነሻዉን 1 ዓመት ከ2 ወር እስራት ተይዟል። ለሦስቱም ክሶች የተያዘዉ መነሻ ቅጣት ሲደመር ዉጤቱ 4 ዓመትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ከ5 ወር ይመጣል። ይህም እርከን 19 ላይ ያርፊል። በአመልካች ላይ የተያዘ የቅጣት ማክበጃ ምክንያት የለም። አራት የቅጣት ማቅለያዎች በስር ፍ/ቤት የተያዙለት በመሆኑ እንዲለ ወስደን 4 እርከን ሲቀነስ እርከን 15 ላይ ያርፊል። ፍቅድ ስልጣኑ ከ2 ዓመት ከ9 ወር እስከ 3 ዓመት ከ3 ወር በመሆኑ አመልካች ቅጣቱ ተሻሽልለት በመነሻዉ በ2 ዓመት ከ9 ወር እስራት ሉቀጣ የሚገባዉ ሆኖ ተገኝቷል።
ሲጠቃለል የስር ፍ/ቤት አመልካች ከባድ የአካል ጉዲት ያደረሰዉ በቸልተኝነት መሆኑ ተረጋግጦ ባለበት በ2ኛ ክስ የወ/ሕ/አንቀጽ 555(ሀ) ተላልፎል ተብል ሆን ተብል በተፈጸመ ከባድ ጉዲት የማድረስ ወንጀል ጥፊተኛ መባለም ሆነ ቅጣት ተሰልቶ የተወሰነዉ የተሻሻለዉን የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 02/2006 አንቀጽ 22(1/ሀ) የተመለከተዉን ያገናዘበ ባለመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉሻሻል የሚገባዉ ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ተከታዩ ተወስኗል።
በአዉሲረሱ ከፍተኛ ፍ/ቤት ነሐሴ 03 ቀን 2009 ዓ.ም ተሰጥቶ በክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ 4390 ታሕሳስ 11 ቀን 2010 ዓ.ም ተሻሽል የተሰጠዉ ዉሳኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 195(2/ለ) መሰረት ተሻሽሎል።
አመልካች በ2ኛ ክስ ጥፊተኛ ልባል የሚገባዉ የወ/ሕ/አንቀጽ 559(2) የተመለከተዉን በመተላለፍ በቸልተኝነት ከባድ አካል ጉዲት በማድረስ ወንጀል ነዉ ተብል ተሻሽሎል።
በክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በአመልካች ላይ ተወስኖ የነበረዉ የ5 ዓመት ከ1 ወር እስራት እና የብር 1000 የገንዘብ መቀጮ ተሻሽል አመልካች በ2(ሁለት) ዓመት ከ9(ዘጠኝ) ወር እስራትና በብር 1000(አንድ ሺህ) እንዱቀጣ ተሻሽል ተወስኗል።
በዚሁ ቅጣት መሰረት እንዱያስፈጽም አመልካች ለሚገኝበት ማረሚያ ቤት ይጻፍ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።
No topics extracted.