አንድ የአሽከርካሪነት ሙያ ያለዉ ሰዉ የትራፉክ ደህንነት ደንብን ተላልፍ በተሽከርካሪዉ የኋላ የዉጭ አካል ላይ ሰው አሳፍሮ ሲያሽከረክር ተሳፊሪው ለመዉረድ ሲል መዉደቁ ወይም ለመዉረድ ሲል ዘል በመዉደቁ ለደረሰበት ጉዲት አሽከርካሪውን በቸልተኝነት ተጠያቂ ከመሆን የማያስቀረው ስለመሆኑ የወ/ሕ/አንቀጽ 24፣ 59፣543(3)፣ በትራፉክ ደህንነት ደንብ ቁጥር 208/2003 አንቀጽ 36(1)
No summary available.
ቀን- ሕዲር 28 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ኃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች:- የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ፍትሕ ቢሮ ዐ/ሕግ ተጠሪ፡- አቶ ሙላቱ ያለዉ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ ወንጀል ሲሆን የተጀመረዉ አመልካች በካፊ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በተጠሪ ላይ በመሰረተዉ ክስ መነሻነት ነዉ። የክሱ ይዘት፡- የወንጀል ሕግ አንቀጽ 543(3) የተመለከተዉን በመተላለፍ በቦንጋ ከተማ 03 ቀበላ ታሕሳስ 02 ቀን 2009 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ በሚያሽከረክረዉ ኮድ 3-88132 በሆነዉ ሀይለክስ ቶዮታ መኪና ላይ የመንገድ ትራንስፖርት ትራፉክ ለመቆጣጠር የወጣዉን ደንብ ቁጥር 208/2003 አንቀጽ 36(1) የተመለከተዉን በመተላለፍ ሟች ተማሪ ወርቁ ኮንሰን በኋለኛዉ የመኪና ክፍል አሳፍሮ በማሽከርከር ላይ እያለ ሟች ወድቆ በጭንቅላቱና ጀርባዉ ላይ በደረሰዉ ከባድ ጉዲት ሕይወቱ ያለፈ በመሆኑ በፈጸመዉ በቸልተኝነት ሰዉ መግደል ወንጀል ተከሷል የሚል ነዉ።
በስር ፍ/ቤት ተጠሪ የእምነት ክህደት ቃለን ሲጠየቅ ክሱን ክድ በመከራከሩ የአመልካች ምስክሮች ተሰምተዉና የሰነድ ማስረጃ ቀርቦ ተጠሪ በተከሰሰበት አንቀጽ ስር እንዱከላከል ብይን የተሰጠ ሲሆን ተጠሪ የመከላከያ ምስክሮችን አሰምቷል። የስርwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ፍ/ቤት የግራቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ የተጠሪ ምስክሮች የተመሰከረበትን ያህል አላስተባበለም በማለት ተጠሪን የወ/ሕ/አንቀጽ 543(3) የተመለከተዉን በመተላለፍ የጥፊተኝነት ዉሳኔ በመስጠት ተጠሪ በ3 (ሦስት) ዓመት ከ3 (ከሦስት) ወር ጽኑ እስራት እና በብር 2000(ሁለት ሺህ) የገንዘብ መቀጮ እንዱቀጣ ወስኗል። ተጠሪ ይህን ዉሳኔ በመቃወም ያቀረበዉን ይግባኝ የተመለከተዉ የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ግራቀኙን ካከራከረ በኃላ መርምሮ ሟች መኪናዉ ሳይቆም ዘል እወረዲለሁ ሲል ወድቆ የሞተ በመሆኑና ተጠሪ ሟችን ከላይ በመጫኑ ደንብ መተላለፍ የፈጸመ ቢሆንን ተጠሪ ሟችን ከላይ በመጫኑ ብቻ ለሟች ሞት በቸልተኝነት ተጠያቂ የሚሆንበት ምክንያት የለም በማለት ተጠሪ በነጻ ሉሰናበት ይገባል በማለት በስር ፍ/ቤት የተሰጠዉን የጥፊተኝነት ዉሳኔ በመሻር በአብላጫ ድምጽ ወስኗል።
አመልካች በዚህ ዉሳኔ ቅር ተሰኝቶ ያቀረበዉን የሰበር አቤቱታ የተመለከተዉ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩን አቅርቦ ካከራከረ በኋላ መርምሮ ዉሳኔዉን በማጽናት ወስኗል። ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ ይህን ዉሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነዉ።
አመልካች ያቀረበዉ የሰበር አቤቱታ ይዘት፡- ተጠሪ መጫን በተከለከለ የመኪና የዉጭ ክፍል ላይ ሟችን እንደጫነዉ በጉዞ ላይ እንዲለ ሟች ወድቆ ጉዲት የደረሰበትና በዚያዉ ምክንያት መሞቱ ተረጋግጧል። የመንገድ ደህንነትን ለመጠበቅ የወጣዉን ደንብ ቁጥር 208/03 አንቀጽ 36(1) በመርህ ደረጃ በመኪናዉ የዉጭ ክፍል ላይ የሚያሳፍር ሰዉ በማናቸዉም ሁኔታዎች ጉዲት ሉደርስባቸዉ የሚችል መሆኑን በማያሻሚ ሁኔታ መግለጹን መገንዘብ ይቻላል። ተጠሪ ይህን ጥንቃቄ ማድረግ ግዳታ እያለበት ይህንን ክልከላ በመተላለፍ ጉዲት ሉደርስ እንደሚችል እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባዉ ይህን ተላልፍ ሰዉ በመጫኑ የሞት ጉዲት መድረሱ እስከተረጋገጠ ድረስ ተጠሪ ነጻ እንዱሰናበት መወሰኑ ስህተት ነዉ። የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ለዉሳኔዉ መሰረት ያደረገዉ የወ/ሕ/አንቀጽ 24 ሲሆን በተሳሳተ ሁኔታ በመገንዘብ ነዉ። ተጠሪ በመኪናዉ የላይኛዉ ክፍል ላይ ሰዉን በመጫን ዉድቆ ሕይወቱ ሉያልፍ እንደቻለ እየተረጋገጠ የስር ፍ/ቤት በምክንያትና ዉጤት መካከል ግንኙነት የለም ማለቱ ስህተት ነዉ።
የስር ፍ/ቤት ድርጊቱ አደጋ ነዉ በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ የወ/ሕ/አንቀጽ 58(3) እና 59 በሚገባ ያላገናዘበ ነዉ። ምክንያቱም የተጠሪ ድርጊት ጉዲት ይደርሳል ቢል የተከለከለን ድርጊት አይደርስም በሚል ባለማገናዘብ በቸልተኝነት የመኪና የዉጭ ክፍልwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ላይ ሟችን በመጫን ወድቆ የሞተ መሆኑ በሚገባ እስከተረጋገጠ ድረስ የሀሳብ ክፍለ ቸልተኝነት መሆኑ በቀላለ መረዲት እየተቻለ አደጋ ነዉ መባለ መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ ዉሳኔዉ ተሽሮ የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ዉሳኔ ይጽናልን የሚል ነዉ።
የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ ተጠሪ ሰዉ ለመጫን ባልተፈቀደ ቦታ ላይ ሕጻኑን ከኃላ ጭኖ ሲያሽከረክር ለመዉደቅ የተጋለጠና የሚከልለዉ ነገር በላለበት ወድቆ መሞቱ በተረጋገጠበት ሁኔታ በኋላ በኩል መጫን ቸልተኝነት አይደለም በማለት የስር ፍ/ቤት ከጥፊተኝነትም ሆነ ከቅጣት በነጻ ያሰናበተበትን አግባብነት ከወ/ሕ/አንቀጽ 59 እና ሰበር ሰሚዉ ችልት በሰ/መ/ አንጻር ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል የተባለ ሲሆን ተጠሪ በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ተጠርቶ ላቀርብ ባለመቻለ በላለበት ጉዲዩ ከመታየቱም በላይ በዚሁ ችልት እንዱቀርብ በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎለት ላቀርብ ባለመቻለ መልስ የመስጠት መብቱ ታልፎል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተገለጸዉን የሚመስል ሲሆን የአመልካችን አቤቱታ ያስቀርባል ሲባል ከተያዘዉ ጭብጥ አንጻር ከስር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ እና አግባብነት ካላቸዉ የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
ተጠሪ ሲያሽከረክረዉ በነበረዉ ፒካፕ ትዮታ መኪና ከኋለኛዉ ክፍል ላይ አሳፍሮ ሲያሽከረክር ሟች ወድቆ መሞቱ ተረጋግጧል። ተጠሪ ሟችን ከኋለኛዉ የመኪና አካል አሳፍሮ ያሽከረክር የነበረዉ የትራፉክ ደህንነት ደንብ ቁጥር 208/03 አንቀጽ 36(1) ስር በመኪና የኋለኛ አካል ላይ ሰዉ አሳፍሮ ማሽከርከር የሚከለክለዉን ደንብ በመተላለፍ ጭምር መሆኑ አሻሚ አይደለም። የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ሟች ላይ ለደረሰዉ የሞት ጉዲት ተጠሪን በቸልተኝነት ሰዉ መግደል ወንጀል ጥፊተኛ ያደረገ ሲሆን ይግባኝ ሰሚዉ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ተጠሪን በነጻ ሲያሰናብት የሰጠዉ ምክንያት ሟች ከመኪናዉ ዘል በሚወርድበት ጊዜ መዉሰድ ይገባዉ የነበረ ጥንቃቄ ርምጃ ባለመዉሰደ የደረሰ ሞት እንጂ ተጠሪ የሟችን መሞት ለማስቀረት ማድረግ እያለበት ያላደረገዉ ወይም ማወቅ እያለበት ወይም እየቻለ ባለመገመት ወይም ባለማሰብ የተገኘ ዉጤት መሆኑ ያልተረጋገጠ እንዱሁም የሟች ከመኪና ዘል መዉረደ ብቻ እንጂ በተጠሪ በኩል የተፈጸመ ቸልተኝነት የለም በማለት ነዉ። የዚህን ችልት ምላሽ የሚያሻዉ አብይ ጭብጥ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚዉ ፍ/ቤት ተጠሪ ሟችን በሚያሽከረክረዉ መኪና ከኋላ ዉጭ ላይ ጭኖ ሲያሽከረክር ወድቆ የሞተ መሆኑን በተረጋገጠበት ለሟችwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ሞት ምክንያቱ የተጠሪ ቸልተኝነት አይደለም ተብል በነጻ እንዱሰናበት መወሰኑ በአግባቡ ነዉ? ወይስ አይደለም? የሚለዉ ነዉ።
በመሰረቱ በወ/ሕ/አንቀጽ 59(1/ ሀ እና ለ) መሰረት አንድ ሰዉ በቸልተኝነት የወንጀል ተግባር ፈጽሟል የሚባለዉ ድርጊቱ በወንጀል የሚያስቀጣ ዉጤት ሉያስከትል እንደሚችል እያወቀ አይደርስም የሚል ግምት ወይም ባለማመዛዘን ወይም ድርጊቱ በወንጀል የሚያስቀጣ ዉጤት ሉያስከትል እንደሚችል ማወቅ እያለበት ወይም እየቻለ፣ ባለመገመት ወይም ባለማሰብ ድርጊቱን የፈጸመ እንደሆነ ነዉ። በተለይ ከአድራጊዉ የግል ሁኔታ አንጻር ሲታይ ሉደረጉ ይገባል ተብል በአግባቡ የሚጠበቁበትን ጥንቃቄዎች ያላደረገ እንደሆነ ቸልተኝነት አለዉ እንደሚባል ተመልክቷል።
በተያዘዉ ጉዲይ ተጠሪ ሟችን ከሚያሽከረክረዉ ተሽከርካሪ የኋለኛ የዉጭ ክፍል ላይ አሳፍሮ ሲያሽከረክር ሟች ከተሽከርካሪዉ ወድቆ ሕይወቱ ማለፈ ተረጋግጧል።
ተጠሪ ሟችን አሳፍሮበት ይጓዝ የነበረዉ ክፍል ላይ ሰዉ አሳፍሮ ማሽከርከር በትራፉክ ደህንነት ደንብ ቁጥር 208/2003 አንቀጽ 36(1) የተከለከለ ተግባር መሆኑ ተደንግጓል።
የትራፉክ ደህንነት ደንቡ ይህን ተግባር የከለከለበት ዋናዉ ምክንያት ለተሳፊሪ ደህንነት አደገኛ በመሆኑ በሰዉ ሕይወት ወይም አካል ላይ ጉዲት እንዲይደርስ ለመከላከል መሆኑ እሙን ነዉ። ተጠሪ የአሽከርካሪነት ሙያ ያለዉ ሰዉ እንደመሆኑ መጠን ይህን ደንብ ተላልፍ ሰዉን ከኋላ መጫን አደገኛና ተገቢዉ ጥንቃቄ ሉያደርግበት የሚገባዉ ሆኖ እያለ ሟችን በደንብ በተከለከለ የተሽከርካሪዉ አካል ላይ አሳፍሮ ጭኖ ሲሄድ ሟች ወድቆ ለደረሰበት ጉዲት ተጠሪ በቸልተኝነት ተጠያቂ ነዉ። ሟች ለመዉረድ ሲል መዉደቁ ወይም ለመዉረድ ሲል ዘል መዉደቁ የተጠሪን ቸልተኝነት አያስቀረዉም።
ምክንያቱም ሟች ለተሸከርካሪ ያለዉ ግንዛቤ አናሳ ላሆን ከመቻለ አንጻር ተሽከርካሪ በጉዞ ላይ እያለ መዉረድ የሚያስከትለዉን ጉዲት ላይገነዘብ ይችላል። ደንቡ በተጠሪ ላይ ወይም በአሽከርካሪዉ ላይ በዋናነት ግዳታ የጣለዉ ሰዎች መጓጓዛቸዉን እንጂ ከላይ መሳፈር ሉያስከትልባቸዉ የሚችለዉን ጉዲት በአግባቡ ላይገነዘቡ ስለሚችለ ነዉ። ሟች ተሽከርካሪዉ በጉዞ ላይ መዉረድ ወይም ዘል መዉረድ አደገኛ ዉጤት ያለዉ መሆኑን ቢያዉቅና የተሳሳተ ግንዛቤ ባይኖረዉ ኖሮ በጉዞ ላይ ካለ ተሽከርካሪ ዘል ባልወረደ ነበር። እንዱሁም ለሟች ጉዲት ዋናዉ ምክንያት የሟች ከተሽከርካሪዉ መዉረድ ብቻዉን ሳይሆን ተሽከርካሪዉ በጉዞ ላይ መሆኑ ነዉ። ስለሆነም የሟችን ሞትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ያስከተለዉ በዋናነት ተጠሪ በትራፉክ ደህንነት ደንብ ጭምር አደገኛ ዉጤት እንደሚያስከትል ግንዛቤ ዉስጥ ገብቶ በተከለከለ ስፍራ ወይም የመኪናዉ የኃላ የዉጭኛ አካል ላይ ሟችን አሳፍሮ በመሄድ በፈጸመዉ ቸልተኝነት ምክንያት ሟች ለመዉረድ ሲል ወድቆ በመሞቱ በመሆኑ የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ተጠሪ በወ/ሕ/አንቀጽ 543(3) የተመለከተዉን በመተላለፍ ጥፊተኛ ማለቱ ተገቢ ሆኖ እያለ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የጥፊተኝነት ዉሳኔዉን በመሻር ተጠሪን በነጻ ማሰናበቱ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉሻር የሚገባዉ ሆኖ ተገኝቷል።
ቅጣትን በተመለከተ ተጠሪ ጥፊተኛ የተባለበት የወ/ሕ/አንቀጽ 543(3) በተሻሻለዉ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 02/2006 መሰረት ወንጀለ ደረጃ የወጣለት በመሆኑ በዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ደረጃ 1 እርከን 21 ተወስድ የቀረበ የቅጣት ማክበጃ ምክንያት ባለመኖሩ በተጠሪ በኩል በቀረቡት የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ዉስጥ 4 ምክንያቶችን በመዉሰድና 4 እርከን በመቀነስ እርከን 17 ስር የ3 ዓመት ከ3 ወር የጽኑ አስራት ቅጣትና በገንዘብ የብር 2,000 መቀጮ እንዱቀጣ መወሰኑ የሚነቀፍበት በቂ ምክንያት ባለመገኘቱ እንዲለ ተወስዶል።
ሲጠቃለል ተጠሪ በትራፉክ ደህንነት ደንብ ቁጥር 208/2003 አንቀጽ 36(1) የተመለከተዉን ግልጽ ክልከላ በመተላለፍ በተሽከርካሪዉ የኋላ የዉጭ አካል ላይ ሟችን አሳፍሮ ሲያሽከረክር ሟች ለመዉረድ ሲል ወድቆ በደረሰበት ጉዲት የሞተ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ተጠሪን በነጻ ማሰናበቱ የወ/ሕ/አንቀጽ 24፣ 59 እና የወ/ሕ/አንቀጽ 543(3) ድንጋጌዎችን ያላገናዘበና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉሻርና የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠዉ የጥፊተኝነትና የቅጣት ዉሳኔ ሉጸና የሚገባዉ ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም የሚከተለዉ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በወ/ይ/መ/ ግንቦት 02 ቀን 2009 ዓ.ም ተሰጥቶ በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ጥር 30 ቀን 2010 ዓ.ም በተሰጠ ዉሳኔ የጸናዉ የሰጠዉ ዉሳኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 195(2/ለ/2) መሰረት ተሽሯል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የከፊ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ የካቲት 02 ቀን 2009 ዓ.ም የሰጠዉ የጥፊተኝነት ዉሳኔ እና ቅጣት ዉሳኔ ጸንቷል።
የዞኑ ፖሉስ መምሪያ ተጠሪን በማፈላለግ ይዞ ለሚመለከተዉ ማረሚያ ቤት እንዱያስረክብና ማረሚያ ቤቱም ተጠሪ ከዚህ በፉት የታሰረዉ መታሰቡ ሳይቀር የተወሰነበትን የ3(ሦስት) ዓመት ከ3(ሦስት) ወር የጽኑ እስራትና የብር 2000(ሁለት ሺህ) የገንዘብ መቀጮ ቅጣት እንዱያስፈጽም ታዟል። ይጻፍ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።
No topics extracted.