የዲኝነት ስራ አካሄድ ላይ በሚፈጸሙ ወንጀልች በተለይም አንድ ችልት በያዘዉ መዝገብ ላይ ችልት መድፈርን በተመለከተ ወዱያዉኑ ቅጣት ሉወስን ስለሚችልበት አግባብ የወንጀል ህጉ አንቀጽ 449 ፣ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁ/480 እና
No summary available.
መ/ቁ/158613 ሐምል 18 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡ ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች፡- ወ/ሮ ማስተዋል ሰፈረ ተጠሪ፡- የለም መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ አማራ ብ/ክ/መ/ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር አጣሪ ችልት ተጠሪ ለችልት ስራ እንቅፊት ሆናለች በማለት ጥፊተኛ ናት በሚል የመጨረሻ የጽሐፍ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ይህም ከማህደሯ ጋር እንዱያያዝ ትእዛዝ በመስጠቱ እና አመልካች ይህንን ትእዛዝ ለማስለወጥ አቤቱታ በማቅረቧ የስር ፍርድ ቤት ትእዛዝ አግባብነት ከወንጀል ህግ አንቀጽ 449 አንጻር ለመመርመር እንዱቻል ለዚህ ሰበር ችልት የቀረበ ነዉ።
እኛም የቀረበዉን አቤቱታ ከስር ፍርድ ቤት ትእዛዝ ይዘት እና አግባብነት ካለዉ ህግ ጋር በማገናዘብ መርምረናል።መዝገቡን መርምረን እንደተገነዘብነዉ ፍርድ ቤቱ ለትእዛዙ መሰረት ያደረገዉ መነሻ ምክንያት አመልካች የፍርድ ቤቱ ንብረት ክፍል ሰራተኛ ሆና ለዳኞች የሚሰጥ የሞባይል ካርድ ለዳኞች ቢሮ ድረስ ለማቅረብ ፈቃደኛ አልሆነችም በሚል ምክንያት ጉዲዩን ችልት ቀርባ እንድታስረዲ ስትጠራም ችልት ለመቅረብ እምብተኛ ከመሆኗም በተጨማሪ በፖሉስ ተጠርታ ስትቀርብም ተገቢዉን ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኗ ለችልት ስራ እንቅፊት ሆናለች በሚል ምክንያትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንዱሰጣትና ከማህደሯ እንዱያያዝ ትእዛዝ ስለመስጠቱ ገልጧል።ችልቱ ይህንን የቅጣት ዉሳኔ ሲሰጥ የህግ መሰረቱ ግልጽ ባለመሆኑ አከራካሪ ሆኖ ቀርቧል።ለዚህም ነዉ በዚህ መዝገብ የቀረበዉ ጉዲይ ከወንጀል ህግ አንቀጽ 449 አንጻር አግባብነቱን መመርመር ያስፈለገዉ።
በመሰረቱ የዲኝነት ስራ አካሄድ ላይ የሚፈጸሙ ወንጀልች ዓይነትና ቅጣታቸዉ የሚደነግገዉ የወንጀል ህጉ አንቀጽ 443 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ላይ እንደተመለከተዉ እንደጉዲዩ ባሕርይና ጥፊት ዓይነት ቅጣት የሚጣልበት ሲሆን በተለይ ችልት መድፈርን አስመልክቶ ችልቱ በያዘዉ መዝገብ ላይ ወዱያዉኑ ቅጣት ሉወስን የሚችልበት አግባብ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 449 እንዱሁም በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁ/480 እና 481 በግልጽ ተደንግጎ ይገኛል።የእነዚህ ድንጋጌዎች ይዘትም ሲታይ የዲኝነት ስራ በማከናወን ያለዉን ዲኛ በማናቸዉም መንገድ ማወክ፣መስደብ ፣ማፋዝ፣ መዛትና በመሰል ሁኔታ እንቅፊት መፍጠር እንዱሁም የዲኝነት ስራ አካሄድ ስነስርዓት አለማክበር፣ለችልቱ ክብርና ለዲኝነት ስራ መልካም አመራር ተቃራኒ የሆነ ጠባይ የሚያሳይ ማንኛዉም ሰዉ ፣ የችልት ተግባርና ስራ የሚያደናቅፈና ተገቢዉን ክብር ለማይሰጡ ለማይታዘዙና ተገቢዉን ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆን የችልቱን ስራ የሚያደናቅፍን ማንኛዉም ሰዉ በዚያዉ መዝገብ ወዱያዉኑ ተገቢ ቅጣት መጣል የሚያስችል ነዉ።የነዚህ ድንጋጌዎች ዋነኛ ዓላማ የችልቱን ስራ አካሄድ በማስከበር ያለእንቅፊት የዲኝነት ስራዉን ማሳለጥ መሆኑን እንገነዘባለን።
በዚህ መዝገብ ወደ ተያዘዉ ጉዲይ ስንመለስ አመልካች የሞባይል ካርድ ለችልቱ ዳኞች የማቅረብ አስተዲደራዊ ግዳታ ወይም የስራ ሃላፉነት አልተወጣችም በሚል ምክንያት ወደ ችልቱ እንድትጠራ መደረጉ የተገለጸ ሲሆን ከጅምሩ አስተዲደራዊ የስራ ሃላፉነት አለመወጣት አለ ከተባለ በአስተዲደራዊ ስነ ስርዓት ጉዲዩ ተጣርቶ ተገቢዉ እንዱወሰን ማድረግ እንደሚገባ ይታወቃል።ከዚህ አልፍ ግን ችልቱ ምክንያቱን ለመገንዘብ ፈልጎ ወደ ችልት እንድትቀርብና ተገቢዉን ምላሽ እንድትሰጥ ትእዛዝ ከሰጠ በኋላ አመልካች ችልት ቀርባ የችልቱን ትእዛዝ አልቀበልም ማለቷ እንዱሁም ለችልቱ ተገቢዉን ክብር አለመስጠቷ ከተረጋገጠ እና ችልቱ ይህ ተግባሯ ጥፊት ነዉ ብል ካመነበት ቅጣት ሉወስን የሚችለዉ ለድርጊቱ ማቋቋሚያ ድንጋጌ በመለየት በወ/ህጉwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
አንቀጽ 443 ወይም በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ አንቀጽ 480 ወይም 481 በተደነገገዉ አግባብ ላሆን ይገባል።ከዚህ ዉጪ በህግ በግልጽ ባልተደነገገ አግባብ የሚጣል ቅጣት የህግ መሰረት የለዉም ።በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት አመልካች ላይ የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እንዱሰጥና ይህም ከማህደሯ ጋር እንዱያያዝ በማለት የሰጠዉ የቅጣት ዉሳኔ የህግ መሰረት የላለዉ ስለሆነ ሉታረም የሚገባ ሆኖ አግኝተናል።ነገርግን አመልካች የፈጸመችዉ ድርጊት በአስተዲደራዊ መንገድ ተጣርቶ አስተዲደራዊ እርምጃ የሚወሰድበት ነዉ ወይስ የችልቱን ስራ መድፈር ነዉ? በሚለዉ ላይ በመለየት ተገቢና አስተማሪ ዉሳኔ መስጠትን ይህ ዉሳኔ ቀሪ አያደርገዉም ብለናል። በዚሁ አግባብ ተከታዩን ትእዛዝ ሰጥተናል።
ትእዛዝ።
1ኛ/የአማራ ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መ/ቁ/03-75294 በ11/08/2010 ዓ.ም አመልካች ላይ የሰጠዉ የቅጣት ትእዛዝ ተሽሯል።
2ኛ/ አመልካች የፈጸመችዉ ድርጊት በአስተዲደራዊ ስነስርዓት ወይም በችልት መድፈር የሚሸፈን ነዉ የሚለዉን በመለየት ተገቢዉን የመወሰን ጉዲይ ይህ ዉሳኔ ቀሪ አያደርገዉም ብለናል።
3ኛ/ይኸዉ እንዱታወቅ ለክልለ ጠ/ፍ/ቤት የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ይተላለፍ ብለናል።ይጻፍ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።