በወንጀል ጉዲይ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ አዱስ የወጣ ህግ ተከሳሹን የሚጠቅም በሆነ ጊዜ ተከሳሹ አዱሱ ህግ ተፈፃሚ እንዱሆን አቤቱታ ባቀረበ ጊዜ አዱስ የወጣው ህግ ተፈፃሚ እንዱሆን መደረግ ያለበት ስለመሆኑና በዚሁ ጉዲይ አቤቱታ የቀረበበት ጉዲይ በባህሪው እንደመደበኛ የክርክር ጉዲይ የሚታይ ሳይሆን በቀረበ ጊዜ ሉስተናገድ የሚችል በመሆኑ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የቀረበ አቤቱታ ነው በማለት ተቀባይነት የለውም የማይባል አማረ ረታ እና የፋዳራል ጠ/አቃቤ ህግ www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XLVI የኢ.ፋ.ዳ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 22(2)፣ የወ/ሕ/አንቀጽ 6 እና 9(1)፤ ዓለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት አንቀጽ15/1/
No summary available.
መ/ቁ/151034 ጥቅምት 28 ቀን 2011ዓ.ም ዳኞች፡ ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንደሻዉ አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች፡- አማረ ረታ ተጠሪ፡- የፍደራል ጠ/አቃቤ ህግ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበዉ ጉዲይ በወንጀል ጉዲይ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ አዱስ የወጣዉ ህግ ተከሳሹን የሚጠቅም በሆነ ጊዜ እንዳት ይፈጸማል የሚል ነዉ።ለዚህ ሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነዉ ጉዲይ አመልካች በጉሙሩክ አዋጅ ቁ/622/01 ስር ጥፊተኛ ተብል የቅጣት ዉሳኔ ተላልፍበት በማረሚያ ቤት ቅጣቱን እየፈጸመ እያለ አዱስ የወጣዉ የጉሙሩክ አዋጅ ቁ/859/06 ለተመሳሳይ ጥፊት የደነገገዉ ቅጣት አመልካችን የሚጠቅም ስለሆነ በአዱሱ አዋጅ መሰረት ቅጣቱ እንዱታይለት ለፋዳራል የመ/ደረጃ ፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርቦ ተቀባይነት ባለማግኘቱና ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይህንኑ በማጽናቱ ነዉ።
የአመልካች ሰበር አቤቱታ ይዘት ባጭሩ አመልካች አዋጅ ቁ/622/01 አንቀጽ 95/1/ሐ/እና 2 በመተላለፍ እሽጎችን መፍታትና ምልክቶችን ማንሳት እንዱሁም አንቀጽ 101/3 በመተላለፍ የማጓጓዝ ሃላፉነት ባለመወጣት ጥፊተኛ ተብል በፋዳራል የመ/ደረጃ ፍርድ ቤት በ16,000ብር እና 24 ዓመት ጽኑ እስራት እንዱቀጣ ስለመወሰኑና በዚህ ቅር ተሰኝቶ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርቦ ፍርድ ቤቱ ቅጣቱንwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ብቻ በማሻሻል18 ዓመት ጽኑ እስራት እንዱቀጣ መወሰኑን ፣ይህንኑ ቅጣት እየፈጸመ እያለ አዱስ የወጣዉ አዋጅ ቁ/859/06 በዚህ ጉዲይ ከቀድሞ አዋጅ ያነሰ ቅጣት የሚያስቀጣ በመሆኑ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕግ መንግስት አንቀጽ 22/2/ መሰረት አዱሱ አዋጅ ተፈጻሚ እንዱሆን አቤቱታ ማቅረቡንና የስር ፍርድ ቤቶች ይህንኑ ተቀብለዉ ቅጣቱን ማሻሻል ሲገባቸዉ አቤቱታዉን አናስተናግድም ማለታቸዉ የህግ ስህተት ስለሆነ እንዱታረም የሚል ነዉ።
የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ ጉዲዩን ከህገ መንግስቱ አንቀጽ 22/2/ እና ከወንጀል ህጉ አንቀጽ 6 እና 9 እንዱሁም ከአዋጅ ቁ/859/06 አንቀጽ 170 እና 171 አንጻር ለመመርመር እንዱቻል ጭብጥ ተይዞ አቃቤ ህግ መልስ እንዱሰጥ ተደርጓል።በአቃቤ ህግ በኩል የቀረበዉ መልስ ባጭሩ በአዱሱ አዋጅ መሰረት መነሻ ቅጣቱ ተከሳሽን የሚጠቅም መሆኑ ታይቶ ማሻሻያ ቢደረግለት ተቃዉሞ እንደላለዉ ገልጿል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ ባጭሩ የተገለጸ ሲሆን እኛም አቤቱታዉ ለሰበር ያስቀርባል ሲባል የተያዘዉን ጭብጥ መሰረት በማድረግ አግባብነት ካለዉ ህግ ጋር በማገናዘብ መርምረናል።መዝገቡን መርምረን እንደተገነዘብነዉ በወንጀል ጉዲይ የወንጀል ህግ ወደ ኋላ ተመልሶ እንዱሰራ የሚደረገዉ መቼ ነዉ እንዱህ ዓይነት አቤቱታስ እስከ መቼ መቅረብ ይችላል የሚለት ነጥቦች መታየት ያለባቸዉ ሆኖ አግኝተናል።
በመሰረቱ የወንጀል ህግ ወደኋላ ተመልሶ የማይሰራ መሆኑ በሀገራችን ህገ መንግስት እና በወንጀል ህግ በግልጽ የተደነገገ ከመሆኑም በተጨማሪ በዓለም አቀፍ ስምምነቶች ተደንግጎ የሚገኝ አለም አቀፍ ቅቡልነት ያለዉ መርሆ መሆኑ ይታወቃል።የኢ.ፋ.ዱ.ሪ.ህገ መንግስት አንቀጽ 22 /1/፣የኢ.ፋ.ዱ.ሪ.የወንጀል ህግ አንቀጽ 5 እንዱሁም ዓለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት አንቀጽ15/1/ይመለከታል።ከዚህ መርህ ልዩ ሁኔታ ተብል የተደነገገዉ ድርጊቱ ከተፈጸመ በኋላ የወጣዉ ህግ ለተከሳሹ ወይም ለተቀጣዉ ሰዉ ጠቃሚ ሆኖ ከተገኘ ከድርጊቱ በኋላ የወጣዉ ህግ ተፈጻሚ እንዱሆን የማድረግ ጉዲይ ነዉ። የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ22/2/፣የወንጀል ህጉ አንቀጽ 6 እንዱሁም የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች አለም አቀፍ ስምምነት አንቀጽ 15/1 ሁለተኛ ፓራግራፍ ይመለከታል። ይህም የሚያሳየዉ ህጉ ተከሳሽን መብትና ጥቅም በተሻለ ሁኔታ ማስከበርን መሰረት ያደረገwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ስለመሆኑና በወንጀል ጉዲይ ህግ መተርጎም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ተከሳሽን በሚጠቅም አኳኋን ሉተረጎም ይገባል የሚለዉን ቅቡልነት ያለዉ የወንጀል ህግ አተረጓጎም መርህ የተከተለ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል።
ስለዚህም ቅጣትን በሚመለከት አዱሱ የወንጀል ህግ ከመውጣቱ በፉት በተፈፀመ ወንጀል ከተፈረደበት እና ሆኖም ግን ወንጀለ በተፈፀመበት ጊዜ ስራ ላይ ከነበረው ወንጀል ህግ ይልቅ አዱሱ ህግ ለተከሳሹ ቅጣትን የሚያቀልለትና ተከሳሹን የሚጠቅም ሆኖ ከተገኘ ይሄው በአዱሱ ህግ ላይ ያለው ቅጣት የሚፈጽምበት ስለመሆኑ ከወንጀል ህጉ ቁ. 6 ድንጋጌ ይዘት የሚያስገነዝብ ስለመሆኑ ሰበር ችልቱ በመ/ቁ/ 95438 ዉሳኔ ሰጥቷል።በልላ በኩል አዱስ የወጣዉ ህግ የቀድሞዉን ህግ የሻረዉ እንደሆነና በቀድሞ ህግ ወንጀል የነበረዉ ድርጊት በአዱሱ ህግ ይኸዉ ድርጊት ወንጀልነቱ ቀሪ ከሆነ ወይም የማያሥቀጣ ከሆነ በቀድሞ ህግ ተፈርድበት ቅጣቱ እንደማይፈጸም ወይም እየተፈጸመ ከሆነም ቅጣቱ አፈጻጸም ወዱያዉኑ እንደሚቋረጥ የወንጀል ህግ አንቀጽ 9/1/ በግልጽ ደንግጓል።
ስለሆነም ከእነዚህ ድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ የሚቻለዉ ኋላ የወጣዉ የወንጀል ህግ ተከሳሹን ወይም የተቀጣዉን ሰዉ የሚጠቅም መሆን አለመሆኑ መመዘኛ ተደርጎ መታየት ያለበት ስለመሆኑ ነዉ።ኋላ የወጣዉ ህግ የቀድሞዉን ህግ በመሻር የድርጊቱን ወንጀልነት ቀሪ በማድረጉ በቀድሞ ህግ የተሰጠዉ ፍርድ ቀሪ ነዉ በሚል በግልጽ ህጉ ደንግጎ እያለ ኋላ የወጣዉ ህግ ቅጣት ማቅለለን መሰረት በማድረግ ተቀጪዉ ያቀረበዉ አቤቱታ ሉስተናገድ አይገባም የሚለዉ የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ የህገ መንግስቱን አንቀጽ 22/2/ እና የወንጀል ህጉን ልዩ ሁኔታ አንቀጽ 6 ያላገናዘበ ሆኖ አግኝተናል።
በሁለተኛ ደረጃ መታየት ያለበት ጉዲይ እንዱህ ዓይነት ሁኔታ ሲያጋጥም ተከሳሹ ወይም ተቀጪዉ አቤቱታ ማቅረብ የሚጠበቅበት የጊዜ ገደብ መኖር አለመኖሩ ላይ ነዉ።በመሰረቱ የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ ለይግባኝ ማቅረቢያና ተያያዥ ጉዲዮች የጊዜ ገደብ ቢያስቀምጥም ፍርድ አግኝቶ የተዘጋ መዝገብ በኃላ እንደገና መከፈቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በምን ያህል ጊዜ ዉስጥ አቤቱታ ላቀርብበት እንደሚገባ በሕግ የጊዜ ገደብ አልተቀመጠም። ይህ በሚሆንበት ወቅት የጊዜ ገደቡ የሚወሰነዉ የጉዲዩን ሁኔታዎችና የአቤቱታዉን ዓይነት በመመልከት እንጂ ከተወሰነ ጊዜ በኃላ የቀረበዉ አቤቱታwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ተቀባይነት የለዉም በሚል ድምዲሜ ላይ በመድረስ አይደለም።ከዚህ በተጨማሪ አመልካች የኢ.ፋ.ዳ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 22(2)፣ የወ/ሕ/አንቀጽ 6 እና 9(1)ን መሰረት በማድረግ አቤቱታ ያቀረበበት ጉዲይ በባህሪዉ እንደመደበኛ የክርክር ጉዲይ የሚታይ ሳይሆን አቤቱታ በቀረበ ጊዜ ሉስተናገድ የሚችል መሆኑን ህጉ ግልጽ የጊዜ ገደብ አለማስቀመጡ የሚያሳይ ነዉ።
በዚህ መዝገብ በተያዘዉ ጉዲይ አመልካች በቀድሞ የጉምሩክ አዋጅ ቁ/622/01 አንቀጽ 95/1/ሐ እና 2 እንዱሁም አንቀጽ 101/3/ በተደራራቢ ወንጀል ተከሶ ጥፊተኛነትና የቅጣት ዉሳኔ ተሰጥቶ ቅጣቱን በመፈጸም ላይ እያለ አዱስ የወጣዉ የጉምሩክ አዋጅ ቁ/859/06 አንቀጽ 170እና 171 የድርጊቱን አስቀጪነት እንዲለ ይዞ ነገር ግን ቅጣቱን በማሻሻለ አመልካች የኋለኛዉ ህግ ይጠቅመኛል በሚል ለስር ፍርድ ቤት አቤቱታ ሲያቀርብ ፍርድ ቤቱ እንዱህ ዓይነት አቤቱታ ሉስተናገድ የሚችልበት አግባብ የለም በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ ከላይ በዝርዝር የተመለከተዉን ህገ መንግስታዊ ድንጋጌ እና የወንጀል ህጉን ዓላማና ይዘት ያላገናዘበ ስለሆነ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል ብለናል።በዚሁ አግባብ ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል።
1ኛ/የፋዳራል የመ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ/81283 ላይ በ06/04/2008 ዓ/ም የሰጠዉ ትእዛዝ እና ይህንኑ በማጽናት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ/002346 ላይ በ20/03/2010 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ በመሰረዝ አመልካች ያቀረበዉ አቤቱታ ተመርምሮ ተገቢዉ ዉሳኔ እንዱሰጥ መዝገቡን በወ/መ/ስ/ስ/ህግ ቁ/195 /2/ሀ መሰረት ለፋዳራል የመ/ደረጃ ፍርድ ቤት መልሰናል ።ይጻፍ።
No topics extracted.