አንድ ቼክ በሚወጣበት ጊዜ በቼክ አውጭው ሂሣብ የፍደራል ጠቅላይ መስከረም 24 421www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XLIV በቂ ስንቅ አለመኖሩ እየታወቀ ቼክ የተሰጠ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ ከግል ተበዲዩ ጋር የቤተሰባዊ ግንኙነት ያላቸው ስለሆነና ቼኩን የሰጠው በመተማመኛ መልኩ ነው በማለት ድርጊቱ በቸልተኝነት የተፈፀመ ነው በሚል በወንጀል ህግ ዓንቀፅ 693(1) መሰረት የቀረበ ክስ ወደ ወንጀል ህግ አንቀፅ 693(2) በመቀየር ተከሳሹን ጥፊተኛ ማለት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 23፤59 ድንጋጌ ያላገናዘበ ስለመሆኑ ዓቃቤ ህግ እና አቶ አሰግድ አባ ቦሬ ቀን 2011 ዓ.ም. 71. “በአዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 27 መሰረት አግባብ ያለው አካል በሕገወጥ መንገድ የተያዘን የከተማ ቦታን የማስለቀቂያ ትዕዛዝ መስጠት እና ካሣ መክፈል ሳያስፈልግ የሰባት የሥራ ቀናት የጽሐፍ ማሥጠንቀቂያ ብቻ ለባለይዞታው በአካል በመስጠት ወይም በቦታው በሰፈረው ንብረት ላይ በመለጠፍ የማስለቀቅ ሥልጣን ይኖረዋል” በማለት የተቀመጠው ሀሳብ በሕጋዊ መንገድ በትግራይ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ፍትሕ ቢሮ ዓቃቤሕግ እና አቶ ንጉስ ሀይለ www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XLV የከተማ ቦታዎችን ለማስለቀቅ የተቀመጠውን የማስለቀቂያ ትዕዛዝ የመስጠት እና ካሣ የመክፈል ሥርዓት ማሟላት ሳያስፈልግ በሕገወጥ መንገድ የተያዘን የከተማ ቦታን ማስለቀቅ የሚቻልበትን ሥርዓት የሚደነግግ እንጂ የከተማ ቦታን ወሮ ለያዘ ሰው የወንጀል ሀላፉነትን የሚያስቀር ስላለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 26(4)፣27
No summary available.
የሰ.መ.
ሐምል 25 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች:- በትግራይ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ፍትሕ ቢሮ ዓቃቤሕግ-አልቀረቡም ተጠሪ፡- አቶ ንጉስ ሀይለ-አልቀረበም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ወንጀል ነው። የአሁን አመልካች ተጠሪው የአዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 35/1/ለ ድንጋጌን በመተላለፍ ማንም ሳይፈቅድለት በቀን 06/07/08 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት በሐወልቲ ክፍለከተማ ቀጠና 10 ስፊቱ 11.28 ሜ2 የሆነ የመንግሥት መሬት ጨምሮ ቤት ስለሰራበት በፈጸመው የከተማ ቦታ ያለአግባብ መያዝ ወንጀል ተከሷል በማለት ያቀረበውን ክስ የተመለከተው በትግራይ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት የሐወልቲ ፍ/ቤት ተጠሪን በተከሰሰበት የሕግ አንቀጽ ጥፊተኛ ሆኖ ስላገኘው ቅጣቱን በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 02/2006 በማስላት በሰባት ዓመት ጽኑ እሥራት እና በብር 40,000 / አርባ ሺህ ብር / የገንዘብ መቀጮ እንዱቀጣ ሲል ወስኗል።
ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለመቐለ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ አቅርቧል። ይግባኙ የቀረበለት ፍ/ቤት ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ ተጠሪ የሰሩትን የድንጋይ አጥር እንዱያፈርሱ በቃል የተነገራቸው ከመሆኑ በቀር የተሰጣቸውwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የ7 ቀን የጽሐፍ ማሥጠንቀቂያ የለም፤አዋጁ የሰባት ቀን የጽሐፍ ማስጠንቀቂያ መሰጠት እንዲለበት የሚደነግግ ሆኖ ሳለ እና ተጠሪ በቃል በተሰጣቸው ማስጠንቀቂያ መሰረት የሰሩትን የድንጋይ አጥር አፍርሰው ሳለ የሥር ፍ/ቤት በአዋጁ የተቀመጠው ማሥጠንቀቂያ የመስጠት ቅድመሁኔታ ባልተሟላበት ሁኔታ የሰጠው የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ ተገቢ አይደለም በማለት የሥር ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር ተጠሪን በነጻ አሰናብቷል። አመልካች በበኩለ በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት በየደረጃው ላለ የክልለ ፍ/ቤቶቸ አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም አቤቱታው የቀረበላቸው ፍ/ቤቶች የሥር ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ አጽንተዋል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- አስቀድሞ የመሬት ወረራ ወንጀል ለመስራት አስቦ መሬትን የወረረ ሰው ማሥጠንቀቂያ ካልተሰጠው በቀር በወንጀል ጥፊተኛ ልባል አይገባም የሚል ድንጋጌ በአዋጁ ባልተቀመጠበት ሁኔታ ይግባኝ ሰሚው የሥር ፍ/ቤቶች ለተጠሪ ማሥጠንቀቂያ አልተሰጠም በሚል ምክንያት ተጠሪን በነጻ በማሰናበት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የአሁን ተጠሪ የከተማ ይዞታውን የያዘው ከሕግ ውጪ መሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ በአዋጅ ቁጥር 721/04 አንቀጽ 27 መሰረት ማሥጠንቀቂያ ባልተሰጠበት ሁኔታ ጥፊተኛ ልባል አይገባም በማለት የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዚህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል። ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የተጠሪ መልስ ይዘት በአጭሩ፡- በአዋጁ አንቀጽ 26/4 እና 27/2 የተቀመጠው ማስጠንቀቂያ የመስጠት ግዳታ በአዋጁ አንቀጽ 35/1/ለ የተቀመጠው ቅጣት ክብደት አኳያ ተጠሪን የመሰለ ሰዎች ማስጠንቀቂያ በመስጠት አሥተዲደራዊ መፍትሓ ለማምጣት እና በማስጠንቀቂያ ከተግባሩ እንዱቆጠብ በመሆኑ የሥር ፍ/ቤቶች ይህንኑ በመገንዘ ተጠሪን በነጻ ማሰናበታቸው ተገቢ ነው፤ይህ የሚታለፍ ከሆነም ተጠሪ ለጊዜው የሰራሁትን አጥር ያፈረስኩ እና የፈጸምኩት ተግባርም ቀላል ስለሆነ ጥፊተኛ ልባል የሚገባው በወንጀል ሕግ አንቀጽ 686/1 ከመግሥት ፈቃድ ውጪ የመንግሥትን ቦታ መያዝ ወንጀል በሚል ላሆን ይገባል፤ይህ የሚታለፍ ከሆነም ይዞታው ከባለቤቴ ይዞታwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
አጠገብ የሚገኘውን ቦታ ክረምቱ እስኪያልፍ በሚል ለማገድ የተሰራ እንጂ ቦታውን ለማካተት ስላልሆነ የአመልካች አቤቱታ ውድቅ ላደረግ ይገባል፤ቅጣቱም ቀል ሉወሰን ይገባል የሚል ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። ይህ ችልትም ጉዲዩ ለሰበር ይቅረብ ሲባል እንዱጣራ የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረነዋል።
ተጠሪ የአዋጁን አንቀጽ ከአዋሳኛቸው ጎን ያለውን የመንግሥት ቦታ ወደ ራሣቸው ይዞታ በመቀላቀል የድንጋይ አጥር የሰሩበት መሆኑ በወረዲው ፍ/ቤት የተረጋገጠ ፍሬነገር ነው። የከተማን ቦታ በሉዝ ስለመያዝ የወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 35/1/ለ ማንም ሰው አዋጁን ወይም በአዋጁ መሰረት የወጡ ደንቦችን ወይም መመሪያዎችን በመተላለፍ የከተማ ቦታን አጥሮ ከያዘ ግንባታ ካካሄደበት ወይም ከአዋሳኝ ይዞታው ጋር ከቀላቀለ ከሰባት እሥከ አሥራ አምሥት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት እና ከብር 40,000 እሥከ 200,000 በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል በማለት ይደነግጋል። የአዋጁ አንቀጽ 26/1 አግባብ ያለው አካል ከቦታው ለሚነሳው ንብረት ተመጣጣኝ ካሣ በቅድሚያ እንዱከፈል በማድረግ የከተማ ቦታ ይዞታን ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የማስለቀቅ እና የመረከብ ሥልጣን ይኖረዋል በማለት ይነግጋል። የዚሁ አንቀጽ ንዐስ ቁጥር 4 አግባብ ያለው አካል በሕገወጥ መንገድ የተያዘን የከተማ ቦታን በአዋጁ አንቀጽ 27 መሰረት የማስለቀቂያ ትዕዛዝ መስጠት እና ካሣ መክፈል ሳያስፈልግ የሰባት የሥራ ቀናት የጽሐፍ ማሥጠንቀቂያ ብቻ ለባለይዞታው በአካል በመስጠት ወይም በቦታው በሰፈረው ንብረት ላይ በመለጠፍ የማስለቀቅ ሥልጣን ይኖረዋል በማለት ይደነግጋል።
የሥር ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤቶች ተጠሪ የሰሩትን የድንጋይ አጥር እንዱያፈርሱ በቃል የተነገራቸው ከመሆኑ በቀር የተሰጣቸው የ7 ቀን የጽሐፍ ማሥጠንቀቂያ የለም፤በአዋጁ አንቀጽ 26/4 ላይ የተቀመጠው የሰባት ቀናት የጽሐፍ ማስጠንቀቂያ የመስጠት ግዳታ ባልተሟላበት ሁኔታ እና ተጠሪ በቃል በተሰጣቸው ማስጠንቀቂያ መሰረት የሰሩትን የድንጋይ አጥር ባፈረሱበት ሁኔታ ጥፊተኛ መባላቸው ተገቢ አይደለም ከሚልwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
መደምደሚያ ላይ የደረሱ ቢሆንም በአዋጁ አንቀጽ 26/4 ላይ አግባብ ያለው አካል በሕገወጥ መንገድ የተያዘን የከተማ ቦታን በአዋጁ አንቀጽ 27 መሰረት የማስለቀቂያ ትዕዛዝ መስጠት እና ካሣ መክፈል ሳያስፈልግ የሰባት የሥራ ቀናት የጽሐፍ ማሥጠንቀቂያ ብቻ ለባለይዞታው በአካል በመስጠት ወይም በቦታው በሰፈረው ንብረት ላይ በመለጠፍ የማስለቀቅ ሥልጣን ይኖረዋል በማለት የተቀመጠው ሀሳብ በአዋጁ አንቀጽ 27 መሰረት በሕጋዊ መንገድ ለተያዙ የከተማ ቦታዎችን ለማስለቀቅ የተቀመጠውን የማስለቀቂያ ትዕዛዝ የመስጠት እና ካሣ የመክፈል ሥርዓት ማሟላት ሳያስፈልግ በሕገወጥ መንገድ የተያዘን የከተማ ቦታን ማስለቀቅ የሚቻልበትን ሥርዓት የሚደነግግ እንጂ የከተማ ቦታን ወሮ ለያዘ ሰው የወንጀል ሀላፉነትን የሚያስቀር አይደለም። በመሆኑም የሥር ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቶች የአዋጁን አንቀጽ 26/4 ድንጋጌን ያለአግባብ በመተርጎም ለተጠሪ የተሰጠው የሰባት ቀናት የጽሐፍ ማስጠንቀቂያ በላለበት ሁኔታ ተጠሪ ጥፊተኛ ልባል አይገባም በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
ሐምል 26 ቀን 2008 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. ግንቦት 02 ቀን 2009 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በመ. ጥቅምት 10 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 195/2/ለ/2 መሰረት ተሽሯል።
ከላይ በፍርድ ሐተታው ላይ በተገለጸው ምክንያት የሐወልቲ ወረዲ ፍ/ቤት በመ. ሰኔ 01 ቀን 2008 ዓ.ም የሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 195/2/ለ/2 መሰረት ጸንቷል።
የመቐለ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካችን በነጻ በማሰናበት የሰጠው ውሳኔ የተሻረ መሆኑን አውቆ የቅጣት ውሳኔውን በተመለከተ መርምሮ ተገቢውን እንዱወስን ጉዲዩ ተመልሶለታል።
-መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል። ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.