በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት በመጀመሪያ ጨረታ ሽያጭ ላይ ተወዲድሮ አሸናፉ የተባለ ገዥ ዋጋ ከፍል ግዥዉን ባለመፈጸሙ ድጋሚ ጨረታ ሲደረግ የሽያጭ ዋጋ ቢቀንስ በሁለተኛዉ እና በአንደኛዉ ጨረታ መካከል ለተፈጠረዉ የዋጋ ልዩነትና ኪሳራ የመክፈል ግዳታ ሁለተኛውን ጨረታ ተወዲድሮ አሸናፉ የሆነው ሰው ላይ የማይወድቅ አቶ ረሽድ አደም እና አቶ ታሪኩ አማረ www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XLIII የፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁ./429
No summary available.
መስከረም 24 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡ ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንደሻዉ አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች፤የአማራ ብ/ክ/መ/ፍትህ ቢሮ ተጠሪዎች፡ 1ኛ/ፈንቴ ንጉስ 2ኛ/ታድል ጥላሁን 3ኛ/ምናለ ዲኛዉ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበዉ ጉዲይ ተጠሪዎች የኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 453/2/ ተላልፈዉ ሀሰተኛ ምስክርነት ቃል ሰጥተዋል ተብል ከቀረበባቸዉ ክስ በነጻ እንዱሰናበቱ በስር ፍርድ ቤት የተሰጠዉ ፍርድ አግባብነት ለመመርመር የቀረበ ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ እነ ቄስ ወርቁ ገላዬ /9 ሰዎች/በተጠረጠሩበት የደን እንጨት መቁረጥ ወንጀል የአሁኖቹ ተጠሪዎች በፍገራ ወረዲ ፖሉስ ጣቢያ ላይ በምስክርነት ቀርበዉ ተጠርጣሪዎቹ ጥር 24 ቀን 2008 ዓ.ም ከቀኑ 6፡30 ላይ ፍገራ ወረዲ ምንጡራ ቀበላ ሸንበቆ ጎጥ ከተባለዉ ቦታ የማህበራት የተፈጥሮ ደን የሆነዉን ሁለም ተከሳሾች መጥረቢያ በመያዝ ደኑን ሲጨፈጭፊ አይተናል በማለት ቃል ከሰጡ በኋላ የአቃቤ ህግ ምስከር ሆነዉ በፍገራ ወረዲ ፍርድ ቤት የምስክርነት ቃላቸዉን በ07/10/08 ዓ.ምwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ሲሰጡ ሁለም ተከሳሾች መጥረቢያ ይዘዉ ሲቆርጡ አላየንም በማለታቸዉ ደን ቆርጠዋል ተብለዉ ክስ የቀረበባቸዉ ተከሳሾቹ በ21/10/08 ዓ.ም በተሰጠ ፍርድ በነጻ እንዱሰናበቱ ስለተወሰነ ተጠሪዎች የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ እና 453/2/ ተላልፈዉ ሀሰተኛ ምስክርነት ሰጥተዋል በሚል ክስ የቀረበባቸዉ ሲሆን ተጠሪዎች ክሱን ክደዉ ስለተከራከሩ ክሱን በመጀመሪያ የዲኝነት ስልጣን የተመለከተዉ የደቡብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራቀኙን ማስረጃ ሰምቶና መርምሮ ተጠሪዎች የተመሰከረባቸዉን በመከላከያ ማስረጃ አላስተባበለም በማለት በተከሰሱበት አንቀጽ ስር ጥፊተኛ ናቸዉ በማለት እያንዲንዲቸዉ በ6ወር ቀላል እስራት እንዱቀጡ ዉሳኔ ሰጥቷል።ተጠሪዎች በዚህ ዉሳኔ ቅር ተሰኝተዉ ለአማራ ብ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ በማቅረባቸዉ ፍርድ ቤቱ ግራቀኙን አከራክሮ የተጠሪዎች ድርጊት ጥፊት መሆኑን ለማስረዲት በአቃቤ ህግ በኩል የቀረበዉ ማስረጃ ተጠሪዎች በፖሉስ የምርመራ መዝገብ የሰጡት የምስክርነት ቃል እና ከዚህ ጋር ማነጻጸሪያ ሆኖ የቀረበዉ ተጠሪዎች ፍርድ ቤት ቀርበዉ ቃለ መሃላ ፈጽመዉ የሰጡት ምስከርነት ቃል ብቻ ስለመሆኑ ገልጾ በፖሉስ የምርመራ ወቅት የሚሰጠዉ ምስክርነት ቃል ፍርድ ቤት ከተሰጠ ምስክርነት ቃል ጋር ተነጻጽሮ የትኛዉ ትክክለኛ ነዉ የሚለዉን ለመለየት ተጨማሪ ማስረጃ እንደሚያስፈልግ ከዚህም ባሻገር ከጅምሩም ቢሆን የወንጀል ህጉ አንቀጽ 453 የሚሸፍነዉ ዲኝነት ወይም ዲኝነት ነክነት ባለዉ ሂደት ላይ የሚሰጥ ምስክርነትን ቃል የሚመለከት ስለመሆኑና ፖሉስ ስልጣንና ተግባር እንዱሁም የወንጀል ምርመራ ሂደት ዲኝነት ነክነት ያለዉ ተግባር ነዉ ተብል በዚህ አንቀጽ ስር ሉሸፈን እንደማይገባ በማተት የስር ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ ያስተላለፈዉን የጥፊተኝነትና የቅጣት ዉሳኔ በመሻር ተጠሪዎች በነጻ እንዱሰናበቱ ዉሳኔ ሰጥቷል።አመልካች በዚህ ዉሳኔ ቅር ተሰኝቶ ለክልለ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም ተቀባይነት አላገኘም።
ለዚህ ሰበር ችልት አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ላይ ሲሆን የአመልካች ሰበር አቤቱታ ይዘት ባጭሩ የፖሉስ ተቋም የዲኝነት ነክነት ያለዉ ተቋም አይደለም ተብል በስር ፍርድ ቤት የተሰጠዉ ትርጉም የፖሉስ ተቋም በወንጀል ጉዲይ የመጀመሪያ የምስክርነት ቃል የሚሰጥበትና አቃቤ ህግም ይህንኑ መሰረት አድረጎ ክስ የማቅረብ ወይም ያለማቅረብ ጉዲይ ዉሳኔ የሚሰጥበት ስለሆነ በስር ፍርድ ቤት የፖሉስ ተቋም የዲኝነት ነክነት ተግባር የሚፈጸሚበት አይደለም ተብል የተሰጠዉ ትርጉም መሰረታዊ የህግ ስህተትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የተፈጸመበት ነዉ በማለት እንዱታረም ጠይቋል።የአመልካች ሰበር አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ ተጠሪዎች እነ ቄስ ወርቁ ገላየ 9 ሰዎች በተከሰሱበት የደን መቁረጥ ወንጀል ምርመራ በፍገራ ወረዲ ፖሉስ ጽ/ቤት ቀርበዉ ወንጀለ ሲፈጸም የተመለከቱ መሆኑን መስክረዉ በፍ/ቤት ደግሞ የአቃቤ ህግ ምስክር ሆነዉ ቀርበዉ በፖሉስ የሰጡትን ቃል በመለወጣቸዉ ከቀረበባቸዉ ክስ በነጻ እንዱሰናበቱ የተሰጠዉ ዉሳኔ የወንጀል ህጉን አንቀጽ 453/2/ አያሟላም ተብል ዉድቅ መደረጉ አግባብነት ከመሰረታዊ ማስረጃ ምዘና መርህ አንጻር ለመመርመር በሚል ጭብጥ ተይዞ ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ ተደርጓል።በተጠሪዎች በኩል የቀረበዉ መልስ ባጭሩ በቀበላዉ ዉስጥ በህዝብ ተመራጭነት በተሰጣቸዉ ሃላፉነት ድርጊቱ በፖሉስ እንዱጣራ ከመጠየቅ ዉጪ የድርጊቱን ፈጻሚ ማነንነት እንደማያዉቁ ለፖሉስ ገልጸዉ እያለ ፖሉስ በማስፈራራትና በማንገራገር እነሱ ያላለትን ቃል በመመዝገብ ሳያነብላቸዉ እንዲስፈረማቸዉ ጠቅሰዉ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ትክክለኛዉን እዉነታ የምስክርነት ቃል የሰጡ ስለሆመኑና የስር ፍርድ ቤትም ይህንኑ መሰረት አድርጎ በነጻ ማሰናበቱ ተገቢ ነዉ በማለት ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ ባጭሩ የተገለጸ ሲሆን እኛም በስር ፍርድ ቤት የተሰጠዉ ዉሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ትርጉም ስህተት ተፈጽሟል ወይ? የሚለዉን አግባብነት ካለዉ ህግ ጋር በማገናዘብ መርምረናል። ከመዝገቡ መረዲት እንደሚቻለዉ ተጠሪዎች ላይ የቀረበዉ ክስ የወንጃል ህግ አንቀጽ 453/2/ ተላልፈዉ በፖሉስ የምርመራ መዝገብ የሰጡትን የምስከርነት ቃል ፍርድ ቤት ቀርበዉ በመለወጣቸዉ ሀሰተኛ የምስከርነት ቃል በመስጠት ወንጀል ፈጽመዋል ተብል ነዉ።የከፍተኛዉ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች በፖሉስ የምርመራ መዝገብ ላይ ተከሳሾች ደን ሲቆርጡ አይተናል ብለዉ መስክረዉ ፍርድ ቤት ቀርበዉ አላየንም በማለታቸዉ ሁለቱን የምስክርነት ቃል በማነጻጸር ልዩነት መኖሩን አረጋግጦ ፍርድ ቤት ቀርበዉ ሀሰተኛ ምስክርነት ቃል ሰጥተዋል በሚል በተከሰሱበት አንቀጽ ስር የጥፊተኛነት ዉሳኔ የሰጠ ሲሆን የአማራ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይህንን ዉሳኔ የሻረዉ በዋናነት የማስረጃ ምዘና መሰረት አድርጎ ሳይሆን የፖሉስ ተቋም የወንጀል ምርመራ ስራ በወንጀል ህግ አንቀጽ 453 ድንጋጌ መሰረት የዲኝነት ነክነት በሚለዉ ትርጉም የሚሸፈን መሆን አለመሆኑን በመመርመር ስለመሆኑ ከዉሳኔዉ ይዘት መገንዘብ ተችሎል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ስለሆነም በዚህ ችልት ሉመረመር የሚገባዉ ነገር የክልለ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የፖሉስ የወንጀል ምርመራ ስራ የዲኝነት ነክነት ያለዉ ስርዓት የሚካሄድበት በሚለዉ ሐረግ የሚሸፈን አይደለም በማለት የሰጠዉ ትርጉም አግባብነት ላይ ነዉ።እንደሚታወቀዉ በወንጀል ፍትህ አስተዲደር ስራ ዉስጥ የፖሉስ ተቋም በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ እንደሆነ እሙን ነዉ።ከፖሉስ ተቋም ዋነኛ ተግባር ዉስጥ ወንጀልን መከላከል እንዱሁም ወንጀል ተፈጽሞ ሲገኝ ተገቢዉን ምርመራ ማድረግና ወንጀለኛዉን አድኖ ለህግ በማቅረብ ብልም ፍርድ ማሰጠት እንዱሁም ፍርደን ማስፈጸም ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ተግባርና ሃላፉነት ስለመሆኑ የፖሉስ ተቋም ማቋቋሚያ አዋጆችና የወ/መ/ስ/ስ/ህግ ድንጋጌዎች ይዘት የሚያስገነዝቡን ጉዲይ ነዉ።ስለሆነም በወንጀል ፍትህ አስተዲደር ስርዓት ዉስጥ የፖሉስ ተቋም ሚና ከፍተኛ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ አሁን ከቀረበዉ ክርክር አንጻር ተጠሪዎች በፖሉስ የምርመራ መዝገብ ላይ የሰጡትን የምስከርነት ቃል በፍርድ ቤት ቀርበዉ ለዉጠዋል በሚል ሀሰተኛ የምስክርነት ቃል ሰጥተዋል የሚለዉ የአቃቤ ህግ ክስ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 453 ስር የሚሸፈን መሆን አለመሆኑን ለመመርመር እንዱረዲን የድንጋጌዉ የተቀረጸበትን ሃይለቃል ማየት ይገባል። የወንጀል ህግ አንቀጽ 453/1/ ላይ የተደነገገዉ ‹‹የዲኝነት ወይም የዲኝነት ነክነት ስርዓት በሚካሄድበት ጊዜ ምስክር ሆኖ የቀረበ ማንም ሰዉ ማንኛዉንም ተከራካሪ ወገን ለመጥቀም ወይም ለመጉዲት አስቦ ሀሰተኛ ምስከርነት ወይም ልዩ አዋቂነት አስተያት የሰጠ እንደሆነ ወይም እዉነቱን የደበቀ እንደሆነ ሀሳቡ ከግቡ ባይደርስም ...›› በዚህ ደንጋጌ ስር ጥፊተኛ ተብል እንደሚቀጣ እንዱሁም የተፈለገዉ ዉጤት የተገኘ እንደሆነ በንኡስ አንቀጽ ሁለት ስር በተደነገገዉ አግባብ የሚቀጣ ስለመሆኑ ተመልክቷል።የእንግሉዝኛዉ ቅጂም እንዱህ ይነበባል።‹‹453/1/ whoever being a witness in judicial or quasi-judicial proceeding knowingly makes or gives a false statement or expert opinion or hides the truth whether to the advantage or the prejudice of any party thereto…>>.በሚል ይገልጻል።
በዚህ ድንጋጌ ዉስጥ ከተመለከቱት የወንጀለ ማቋቋሚያ መሰረታዊ ፍሬነገሮች ዉስጥ አከራካሪ ሆኖ የቀረበዉ ድርጊቱ የተፈጸመዉ ዲኝነት ወይም የዲኝነት ነክነት ያለዉ ስርዓት የሚካሄድበት የሚለዉ ሃይለቃል የፖሉስ የወንጀል ምርመራ ስራን ያካትታልwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ወይ የሚለዉ ነዉ።ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት ‹‹ዲኝነት›› እና ‹‹ዲኝነት ነክነት›› ለሚለዉ ቃል ትርጉም መፈለግ ግድ ይላል።የእነዚህ ቃላት ትርጉም በሀገራችን የህግ ኮድች ወይም መዝገበ ቃላት ላይ በቀጥታ ማግኘት አስቸጋሪ በመሆኑ ተመሳሳዩን የእንግሉዘኛ ትርጉም መመልከት ተመራጭ ሆኖ አግኝተናል።በዚህ ረገድ ታዋቂዉ የህግ መዝገብ ቃል BLAKS LAW DECTIONARY ላይ እንደተተረጎመዉ፡- ‹‹JUDICIARY-the branch of government invested with judicial power›› በማለት ትርጉም የሰጠ ሲሆን ‹‹QUASI-JUDICIAL ..hold hearings, weigh evidence; and draw conclusions from them, as basis for their official action, and to exercise discretion of judicial nature>>.በሚል ትርጉም ሰጥቷል።
ከዚህ መገንዘብ የሚቻለዉ የመጀመሪያዉ የዲኝነት ስራ የሚያከናዉን የዲኝነት ስልጣን የተሰጠዉ አንደኛዉ የመንግስት አካል ወይም መደበኛዉን ፍርድ ቤት የሚያመለክት ሲሆን የዲኝነት ነክነት ስራ የሚካሄድበት ደግሞ በዲኝነት መልክ ወይም መሰል ሁኔታ ክርክር የሚሰማበት፣የቀረበለት ማስረጃ ተመዝኖ ከድምዲሜ የሚደረስበትና የበኩለን ዉሳኔ የሚሰጥበት ሂደት የሚከናወንበት ተቋም የሚመለከት ነዉ።በዚህ ረገድ ተጠቃሽ የሆኑት ተቋማት እንደግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ፣የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ቦርድ፣ የግለግል ተቋማትና ላልችም መሰል ከፉል የዲኝነት ስልጣን የተሰጣቸዉ አስተዲደራዊ ተቋማት ስለመሆናቸዉ ሀገራችንን ጨምሮ የተለያዩ ሀገሮች ልምድ ያመላክታል። ይህ በዘርፈ በተደረጉ ጥናቶችና በርካታ ጽሁፍች ላይም የሚጠቀስ ነዉ። ከዚህም ባሻገር የተሻሻለዉ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ሀተታ ዘምክንያት ላይ እንደተመለከተዉ ቀደም ሲል ስራ ላይ የነበረዉ የ1949 ዓ.ም የወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀጽ 447 ስር ሀሰተኛ ምስክርነትን አስመልክቶ የተደነገገዉ ያስተዲደር ፍትሐ ብሓር፣የወንጀል ወይም የሽምግልና ዲኝነት፣ የዲኝነት ወይም የዲኝነት ነክነት ያለዉ ስነስርዓት የሚፈጸምበት በሚል የተዘረዘረዉ የተንዛዛ በመሆኑ የዲኝነት ወይም የዲኝነት ነክነት ያለዉ ስርዓት የሚካሄድበት በሚል በአዱሱ የወንጀል ህግ አንቀጽ 453 ስር ተሻሽል የቀረበ ስለመሆኑ ተገልጿል።ከዚህም አንጻር ሲታይ የወንጀል ምርመራ ሂደት በዚህ አንቀጽ ስር እንዱሸፈን ያልተደረገ ስለመሆኑ ነዉ።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ሲጠቃለል የዲኝነት ነክነት ያለዉ ስርዓት የሚካሄድበት የሚለዉ ሀረግ ጥቅል ትርጉም ዲኝነት መሰል ተግባር የሚከናወንበት ሂደት የሚያመላክት ሲሆን በህጉ የተለየ ሁኔታ ካልደነገገ በስተቀር በስነስርዓት ህጉ በተደነገገዉ አግባብ ክርክር የሚመራበትና ምስክርም ሲሰማ እዉነትን ለመመስከር ቃለመሃላ ፈጽሞ ቃለን የሚሰጥበት አካሄድ የሚከተል መሆኑን መገንዘብ አዲጋች አይደለም ።ከዚህ ጋር በተያያዘ በፖሉስ በወንጀል ምርመራ ወቅት ምስክሩ የሚሰጠዉ ቃል ልክ እንደመደበኛዉ የዲኝነት አካል ወይም የዲኝነት ነክነት ወይም መሰል ተቋም ቃለ መሃላ ፈጽሞ የሚሰጥ የምስክርነት ቃል ካለመሆኑም በተጨማሪ ምስክሩ በፖሉስ የምርመራ መዝገብ ላይ የሰጠዉ የምስክርነት ቃል እና በፍርድ ቤት የሰጠዉ የምስክርነት ቃል መካከል ልዩነት በተፈጠረ ጊዜ በፖሉስ የሰጠዉ የምስክርነት ቃል እዉነት ነዉ ነገር ግን በፍርድ ቤት የሰጠዉ የምስክርነት ቃል ሀሰት ነዉ ለማለት የምስክሩ ቃል መለያየት ብቻዉን በቂ ማስረጃ ነዉ ብል ለመዉሰድ የሚያስችል የህግ መሰረት የለም።በእርግጥ አንድ ምስክር ለፖሉስ የሰጠዉን ቃል ፍ/ቤት ሲቀርብ ከቀየረ ከሁለቱ አንደ የሀሰት ቃል መሆኑ እሙን ነዉ።ሆኖም አመልካች ክስ ከመመስረቱ በፉት ከሁለቱ ቃልች መካከል የሀሰት ቃል የትኛዉ እንደሆነ በትክክል በልላ ማስረጃ ማስረዲት ይጠበቅበታል።
በዚህ መዝገብ በተያዘዉም ጉዲይ ተጠሪዎች በፖሉስ የምርመራ መዝገብ የሰጡት የምስክርነት ቃል እዉነተኛ የሆነዉን ለዉጠዉ በፍርድ ቤት ቀርበዉ የሀሰት የምስክርነት ቃል ሰጥተዋል በማለት አቃቤ ህግ የወንጀል ህግ አንቀጽ 453/2/ መሰረት በማደረግ ያቀረበዉን ክስ ለማስረዲት ያቀረበዉ ማስረጃ ተጠሪዎች በፖሉስ ምርመራ ላይ የሰጡት ቃል እና በፍርድ ቤት የሰጡትን ቃል በማነጻጸር እንደመሆኑ ጉዲዩን በይግባኝ የመረመረዉ አማራ/ብ/ክ/መ/ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድንጋጌዉ በፖሉስ የወንጀል ምርመራ ሂደት የተሰጠን የምስክርነት ቃል በቀጥታ ከፍርድ ቤት የምስክርነት ቃል በማነጻጸር የኋለኛዉ የሀሰት ቃል ነዉ ለማለት በፖሉስ የተሰጠ ቃል የዲኝነት ነክነት ከሚለዉ የሚያጠቃለል አይደለም በማለት የደረሰበት ድምዲሜ ላይ መሰረታዊ የህግ አተረጓጎም ስህተት የተፈጸመበት ነዉ የሚባልበት ምክንያት አላገኘንም።በዚሁ አግባብ ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የአማራ ብ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ/17096 በ05/10/09 ዓ.ም የሰተጠዉ ፍርድ እና ይህንኑ በማጽናት ክልለ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/70512 ላይ በ26/03/2010 ዓ.ም የሰጠዉ ትእዛዝ በወ/መ/ስ/ስ/ህግ ቁ/195/2/ለ/2 መሰረት ጸንቷል። ይጻፍ።
No topics extracted.