የአንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት አከራይ የሆነ ሰዉ ላልተከፈለዉ የዉዝፍ ኪራይ ክፍያ አከፊፈል ሲባል አዲማ ሳይንስና ቴክኖልጂ www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XLII ለቤቱ ማገጫነት ወይም ለስፍራ ማልሚያነት ከሚጠቀምባቸዉ ዔቃዎች ላይ ዔቃዎቹ የራሱ ባይሆኑም ይህንኑ አከራዩ እስካላወቀ ወይም ማወቅ ነበረበት እስካልተባለ ድረስ በሕግ የተቋቋመ የመያዣ መብት ያለዉ መሆኑና በልዩ ሁኔታ ንብረቱ ለአፈጻጸም መዋል መቻል አለመቻለ በግራ ቀኙ ክርክርና ማስረጃ ተጣርቶና ተረጋግጦ መወሰን ያለበት ስለመሆኑ ፍ/ብ/ሕ/ቁ 2924፣2925፣2926(2) ዩኒቨርሲቲ እና ወ/ሮ ሺወርቅ ሲባኒ
No summary available.
መ/ቁ154222 ህዲር 28 ቀን 2011ዓ.ም ዳኞች፡ ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንደሻዉ አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች፡- አቶ ረሽድ አደም ተጠሪ፡- አቶ ታሪኩ አማረ መዝገቡ ለምርምራ የተቀጠረ በመሆኑ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ፍርድ።
በዚህ መዝገብ የቀረበዉ ጉዲይ በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት በመጀመሪያ ጨረታ ሽያጭ ላይ ተወዲድሮ አሸናፉ የተባለዉ ገዥ ዋጋ ከፍል ግዥዉን ባለመፈጸሙ ድጋሚ ጨረታ ሲደረግ የሽያጭ ዋጋ ቢቀንስ ልዩነት የመክፈል ሃላፉነት የሚመለከት ክርክር መነሻ ያደረገ ነዉ።የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ የፍርድ ባለእዲ የአሁኑ ተጠሪ ሲሆን የፍርድ ባለመብት ወ/ሮ ብሻሺ አዱሱ መካከል በነበረዉ የአፈጻጸም ክርክር የፍርድ ባለእዲ ንብረት የሆነ ቤት በጨረታ እንዱሸጥ በተሰጠ ትእዛዝ መሰረት በመጀመሪያ ጨረታ ላይ የአሁኑ አመልካች ወንድም የሆነዉ አቶ ከሉል አደም በጨረታዉ ተወዲድሮ ቤቱን በብር 200,000 አሸናፉ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ ገንዘቡን ገቢ ማድረግ ባለመቻለ ሁለተኛ ጨረታ እንዱወጣ ሲደረግ የአሁኑ አመልካች ተወዲድሮ በብር 137,000 አሸናፉ ሆኖ ሽያጩ እንዱከናወን በመደረጉ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁ/ 429/2/ መሰረት ተጫራቹ በመጀመሪያ ጨረታ እና በሁለተኛ ጨረታ መካከል ያለዉን የዋጋ ልዩነት ብር 63,200 አመልካች እንዱከፍል ተጠሪ አቤቱታ አቀረበ። የአፈጻጸም መዝገቡን የያዘዉ የመቱwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ወረዲ ፍርድ ቤት የግራቀኙን አስተያየት ከተቀበለ በኋላ የአመልካች ወንድም በመጀመሪያዉ ጨረታ የተወዲደረዉ ለአመልካች ስለመሆኑ በመግለጹና አመልካችም ይህንኑ አምኗል በሚል በሁለቱም ጨረታ የተወዲደረዉ አመልካች ነዉ በሚል የዋጋ ልዩነቱን ብር 63,200 የአሁኑ አመልካች እንዱከፍል በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁ/429/2/ መሰረት ትእዛዝ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ዉሳኔ ቅር ተሰኝቶ ለኢለባቦር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን ከፍተኛዉ ፍርድ ቤት ግራቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የአመልካች ወንድም በአመልካች ስም ጨረታ እንዱወዲደር ግልጽ ዉክልና መስጠቱ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ አመልካች ልዩነቱን የመክፈል ግዳታ የለበትም በማለት የፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 2205 ዋቢ በማድረግ የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ ሽሯል።በልላ በኩል በስር ፍርድ ቤት ቀርቦ ከደመወዙ ተቆርጦ ይከፈል በማለት ቃለን የሰጠዉን በመጀመሪያ ጨረታ አሸናፉ ተብል ግደታዉን ያልተወጣዉ ሰዉ ላይ የመጠየቅ መብት ጠብቆለታል።የአሁኑ ተጠሪ በዚህ ዉሳኔ ቅር ተሰኝቶ ለኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኝ ቅሬታ በማቅረቡ ፍርድ ቤቱ ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ አመልካች በህግ አግባብ ለወንድሙ የሰጠዉ ዉክልና ባይኖርም ወንድሙ የሆነዉ ከሉል አደም በሰጠዉ ሀሳብና አመልካች በሰጠዉ ሀሳብ መሰረት የዋጋ ልዩነቱን የመክፈል ሃላፉነት የአመልካች ነዉ በማለት የወረዲዉን ፍርድ ቤት ዉሳኔ አጽንቷል።አመልካች በዚህ ቅር ተሰኝቶ ለኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን ሰበር ችልቱ ግራቀኙን አከራክሮ የይግባኝ ሰሚ ችልት ዉሳኔ አጽንቷል።
ለዚህ ሰበር ችልት አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ላይ ሲሆን የአመልካች አቤቱታ ይዘት ባጭሩ አመልካች በህግ አግባብ ለወንድሙ አቶ ከሉል አደም የሰጠዉ ዉክልና ሳይኖር አቶ ከሉል አደም በመጀመሪያዉ ጨረታ በራሱ ስም ተወዲድሮ አሸናፉ ነዉ ለተባለበት አመልካች ሃላፉነት ሉወስድ እንደማይገባ ፣አቶ ከሉል አደም በመጀመሪያ ጨረታ አሸናፉ ተብል ግዳታዉን ባለመወጣቱ ካስያዘዉ ገንዘብ ላይ ተቀንሶ ገቢ መደረጉን በሁለተኛ ጨረታ እንዲይወዲደር መደረጉ እና አቶ ከሉል አደም የዋጋ ልዩነት ከደመወዙ ተቀንሶ ገቢ ይደረግ እያለ ባለበት ሁኔታ አመልካች እንዱከፍል መደረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነዉ በሚል የስር ፍርድ ቤቶች ዉሳኔ እንዱታረም ጠይቋል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በመጀመሪያ ጨረታ ተወዲድሮ ካሸነፈ በኋላ ክፍያዉን ሳይፈጽም የቀረዉ የአመልካች ወንድም ሆኖ ሳለ በዚሁ ምክንያት ድጋሚ ጨረታ ወጥቶ አመልካች ተወዲድሮ ባነሰ ዋጋ በማሸነፈ አመልካች ልዩነት እንዱከፍል የመወሰኑን አግባብነት ከፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁ/429 አንጻር ለመመርመር እንዱቻል ጭብጥ ተይዞ ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ ተደርጓል።በተጠሪ በኩል የቀረበዉ መልስ ባጭሩ በመጀመሪያዉ ጨረታ ላይ አመልካችና ቤተሰቦቹ እንደተወዲደሩ፣ አቶ ከሉል አደም ለአመልካች በሚል እንደተወዲደረ በስር ፍርድ ቤት ላይ መግለጹና አመልካችም ይህንኑ በፍርድ ቤት ስለማረጋገጡ በመግለጽ የስር ፍርድ ቤቶች ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለዉም በማለት ተከራክሯል።የአመልካች ጠበቃ ክርክሩን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥና የግራቀኙ ክርክር ይዘት ከላይ ባጭሩ የተገለጸ ሲሆን እኛም ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል ሲባል የተያዘዉን ጭብጥ መሰረት በማድረግ አግባብነት ካለዉ ህግ ጋር በማገናዘብ መርምረናል።ከመዝገቡ እንደተገነዘብነዉ አከራካሪዉ ጉዲይ በመጀመሪያ ጨረታ እና በሁለተኛ ጨረታ መካከል የንብረቱ ዋጋ ልዩነት ሲፈጠር ሃላፉነት የሚከተለዉን ወገን የመለየት ጉዲይ ነዉ።በፍ/ብ/ስ/ህግ አንቀጽ 429 ላይ በጨረታ ለገዛዉ ንብረት ዋጋዉን ሳይከፍል ወይም ግዳታዉን ሳይፈጽም የቀረ ገዢ ንብረቱ በሁለተኛ ጨረታ ሲሸጥ ለጎደለዉ ገንዘብ በሃላፉነት የሚጠየቅበት ሁኔታ ተደንግጓል።በዚሁ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ ሁለት ላይ እንደተደነገገዉ ንብረቱ እንደገና በሚሸጥበት ጊዜ ዋጋ የቀነሰ እንደሆነ በመጀመሪያ ጨረታ ንብረቱን የገዛዉና ዋጋዉን ያልከፈለዉ ተጫራች የፍርድ አፈጻጸም እዲ በሚከፈልበት ዓይነትና ሁኔታ ልዩነቱንና ኪሳራዉን እንዱከፍል እንደሚገደድ ተመልክቷል።ስለዚህም የዋጋ ልዩነቱንና ኪሳራዉን የመክፈል ግደታ የተጣለዉ በመጀመሪያ ጨረታ ተወዲድሮ የጨረታዉ አሸናፉ ነዉ የተባለዉ ሰዉ ላይ ስለመሆኑ ያስገነዝባል።
በዚህ መዝገብ በተያዘዉ ክርክር በመጀመሪያ ጨረታ ተወዲድሮ የጨረታዉ አሸናፉ ነዉ የተባለዉ እና በዚሁ አግባብ ግዳታዉን ያልተወጣዉ የአመልካች ወንድም የሆነዉ አቶ ከሉል አደም ስለመሆኑ በስር ፍርድ ቤት ክርክር ሂደት የተገለጸ ጉዲይ ነዉ።አከራካሪ የሆነዉ ጉዲይ የአመልካች ወንድም በመጀመሪያ ጨረታ የተወዲደረዉ ለአመልካች ወይስ ለራሱ ጥቅም ነዉ የሚለዉ ነዉ።በዚህ ረገድ የአመልካች ወንድም በስር ፍርድ ቤትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ቀርቦ የተጫረተዉ በራሱ ስም ቢሆንም ለአሁኑ አመልካች ጥቅም ስለመሆኑ ገልጾ ገንዘቡን በወቅቱ ገቢ ማድረግ ባለመቻለ ለሚፈጠረዉ የዋጋ ልዩነት ከራሱ ደመወዝ ተቀንሶ ገቢ እንዱደረግ የጠየቀ ሲሆን የስር ፍርድ ቤት የዚህ ሰዉ ጥያቄ ያለፈበት ምክንያት ግልጽ አይደለም። በአመልካች በኩል የቀረበዉ ክርክር የመጀመሪያ ጨረታ ላይ እንዲልተወዲደረ፣ ወንድሙ አቶ ከሉል አደም በጨረታዉ በአመልካች ስም እንዱወዲደር ዉክልና ያልሰጠ ስለመሆኑ ሲሆን የስር ፍርድ ቤት ላይ ቀርቦ ወንድሙ ለእሱ እንደተወዲደረ አምኗል በማለት በመዝገብ ላይ ያሰፈረዉ ትክክል እንዲልሆነ አጥብቆ ተከራክሯል።ስለሆነም የአመልካች ወንድም በመጀመሪያዉ ጨረታ የተወዲደረዉና አሸናፉ የተባለዉ ለራሱ ጥቅም ወይስ ለአሁኑ አመልካች ጥቅም ነዉ የሚለዉን ጥያቄ ለይቶ በመወሰን ረገድ በየደረጃዉ ክርክሩን የተመለከቱት ፍርድ ቤቶች የተለያየ መነሻ በመያዝ የተለያየ ዉሳኔ ማስጠታቸዉን ከላይ ተመልክተናል።ይሕም አንደ ፍርድ ቤት ግራቀኙ በችልት በሰጡት ሀሳብ ለአመልካች ጥቅም ስለመሆኑ ታምኗል የሚል መነሻ የያዘ ሲሆን ላላኛዉ ደግሞ በመጀመሪያ ጨረታ አመልካች ግልጽ ዉክልና መስጠቱ አልተረጋገጠም በማለት ነዉ።
በመሰረቱ ባንድ ጉዲይ ላይ ሃላፉነት የሚመነጨዉ ከህግ ወይም ከዉል እንደሆነ ይታወቃል።ከዚህ መዝገብ ክርክር እንደተገነዘብነዉ የአመልካች ሃላፉነት ምንጩ በአመልካችና በወንድሙ መካከል በነበረዉ ግንኙነት ወንድሙ ለፈጸመዉ ተግባር እንደወኪል ታይቶ ሃላፉነት እንዱወስድ የሚል ክርክር ነዉ።በፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 2079 እንደተደነገገዉ የላላ ሰዉ እንደራሴ በመሆን ስራዎችን የመፈጸም ስልጣን የሚገኘዉ ከህግ ወይም ከዉል ነዉ።ዉክልናዉ በዉል የተሰጠ እንደሆነ ተወካዩ በወካዩ ስም ህጋዊ ስራዎችን እንዱሰራ የሚደረግበት ዉል መኖሩን መሰረት ያደረገ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 2099 ይገልጻል። በዉል የሚሰጥ ዉክልና ጠቅላላ ዉክልና ወይም ልዩ ዉክልና ተብል በሁለት ተከፍል የሚታይ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህጉ አንቀጽ 2002 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ይዘት ያስገነዝባለ።በተለይም የማይንቀሳቀስ ንብረት ጋር በተያያዘ ከማስተዲደር ስልጣን ያለፈ ተግባር ማከናወን የሚቻለዉ በልዩ ዉክልና ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 2005/2/ድንጋጌ ይዘት ያስገነዝባል።
በዚህ መዝገብ በተያዘዉ ክርክር አከራካሪዉ ጉዲይ የአመልካች ወንድም የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመግዛት በመጀመሪያ ጨረታ ላይ የተወዲደረዉ በራሱ ስም ቢሆንምwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ለአመልካች ጥቅም ነዉ በሚል የአመልካች ወኪል ሆኖ እንደተወዲደረ ተወስድ ሃላፉነቱ የአመልካች መሆን አለበት ወይስ አይደለም የሚል ነዉ።በዚህ ረገድ የአመልካች ወንድም አቶ ከሉል አደም በመጀመሪያ ጨረታ የተወዲደረዉ በራሱ ስም ከመሆኑም በተጨማሪ ከአመልካች የተሰጠዉ ግልጽ ዉክልና ስለመኖሩ የቀረበ ማረጋገጫ የለም።በስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ መሰረት ያደረገዉ አቶ ከሉል አደም በአንድ በኩል በራሱ ስም መጫረቱን እየገለጸ ፤ በልላ በኩል ለወንድሜ ነዉ የተጫረትኩት ገንዘቡን መክፈል አልችልም ከደመወዝ ይቆረጥ በማለቱና አመልካች ስር ፍርድ ቤት ቀርቦ ይህንኑ አምኗል በሚል ምክንያት ነዉ።እዚህ ላይ አመልካች አጥብቆ የሚከራከረዉ አመልካች በግልጽ ለወንድሙ አቶ ከሉል አደም በዚህ በግልጽ ዉክልና መስጠቱ ባልተረጋገጠበትና ስር ፍርድ ቤት ላይ የተመዘገበዉ ቃል አመልካች በግልጽ የመጀመሪያዉ ጨረታ ላይ ሃላፉነት የወሰደበት ሁኔታ በላለበት ፍርድ ቤቱ አመልካች አምኗል የሚል በመመዝገብ አመልካችን ሃላፉ ማድረግ ተገቢ አይደለም የሚል ነዉ።በዚሀም ላይ ጉዲዩን በተለያየ ደረጃ የተመለከቱት የስር ፍርድ ቤቶች አመልካች በፍርድ ቤት ቀርቦ በችልት ላይ የተመዘገበ ቃል እምነት የሚጣልበት ነዉ ወይስ አይደለም በሚለዉ ነጥብ ዙሪያ የተለያየ አቋም መዉሰዲቸዉ ከመዝገቡ ላይ ይታያል።ከላይ እንደተመለከትነዉ ይህ ጉዲይ የፍትሒብሓር ክርክርም ቢሆን ሃላፉነትን የሚያሥከትል ከመሆኑ አኳያ አመልካች በዚህ ጉዲዩ ላይ የሰጠዉ ቃል አሻሚና አከራካሪ ከሆነ እሱን ሃላፉነት ዉስጥ የሚያስገባ ላሆን አይገባም።በልላ በኩል የአመልካች ወንድም የሰጠዉ ቃል ቢሆን ራሱ ሃላፉነት የሚወስድበት ከሚሆን በስተቀር በራሱ ስም ጨረታዉን መወዲደሩን ግልጾ እርስ በርሱ የሚጣረስ ሃሳብ ማቅረቡ በግልጽ እየታየ ወንድሙ ለፈጸመዉ ተግባር አመልካች ሃላፉነት እንዱወስድ ለመወሰን የሚያስችል የህግ መሰረት የለዉም።ሲጠቃለል በዚህ ጉዲይ አመልካች በመጀመሪያ ጨረታ በራሱ ወይም በህጋዊ ወኪል አማካይነት ስለመወዲደሩና ስለማሸነፈ በበቂ ማስረጃ ባልተረጋገጠበት ወይም ሃላፉነት ስለመዉሰደ አጣራጣሪና አከራካሪ በሆነበት ሁኔታ ዉስጥ በሁለተኛዉ እና በአንደኛዉ ጨረታ መካከል ለተፈጠረዉ የዋጋ ልዩነት በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁ /429/2/ መሰረት ሉከፍል የሚገደድበት የህግም ሆነ የዉል ግንኙነት ምክንያት ባለመኖሩ የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት እና ሰበር ሰሚ ችልቶች አመልካች ሃላፉነት አለበት በማለት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረምwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ይገባል ብለናል።በልላ በኩል የኢለባቦር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዉሳኔዉ ላይ እንዲመላከተዉ ተጠሪ ከአቶ ከሉል አደም ላይ የሚጠይቀዉ መብት በዚህ ዉሳኔ የተገደበ አይሆንም ብለናል። በዚሁ አግባብ ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል።
1ኛ/የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ/210226 ላይ በ28/06/09ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና ይህንኑ በማጽናት የሰበር ችልቱ በመ/ቁ/268042 ላይ በ09/04/2010 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ አንቀጽ 348/1/መሰረት ተሸሯል።
2ኛ/የኢለባቦር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/29822 ላይ በ19/03/09 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ ጸንቷል።ይጻፍ።
3ኛ/በዚህ ፍርድ ቤት ለተደረገዉ ክርክር ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸዉን ይቻለ ብለናል።