የአንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት አከራይ የሆነ ሰዉ ላልተከፈለዉ የዉዝፍ ኪራይ ክፍያ አከፊፈል ሲባል አዲማ ሳይንስና ቴክኖልጂ www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XLII ለቤቱ ማገጫነት ወይም ለስፍራ ማልሚያነት ከሚጠቀምባቸዉ ዔቃዎች ላይ ዔቃዎቹ የራሱ ባይሆኑም ይህንኑ አከራዩ እስካላወቀ ወይም ማወቅ ነበረበት እስካልተባለ ድረስ በሕግ የተቋቋመ የመያዣ መብት ያለዉ መሆኑና በልዩ ሁኔታ ንብረቱ ለአፈጻጸም መዋል መቻል አለመቻለ በግራ ቀኙ ክርክርና ማስረጃ ተጣርቶና ተረጋግጦ መወሰን ያለበት ስለመሆኑ ፍ/ብ/ሕ/ቁ 2924፣2925፣2926(2) ዩኒቨርሲቲ እና ወ/ሮ ሺወርቅ ሲባኒ
No summary available.
ጥቅምት 28 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ኃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች:- አዲማ ሳይንስና ቴክኖልጂ ዩኒቨርሲቲ ነ/ፈጅ ፈየራ ኦልጅራ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ ሺወርቅ ሲባኒ ጠበቃ ሲሳይ ወ/ዮሐንስ ቀረቡ።
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዚህ ሰበር ክርክር መነሻ የሆነው የአፈጻጸም ጉዲይ ሲሆን የተጀመረው በኦሮሚያ ክልል የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው። በዚህ ፍ/ቤት አመልካች ፍርድ ባለመብት፣ አቶ ደርቤ መኮንን የፍርድ ባለዔዲ ሲሆኑ የአሁን ተጠሪ ደግሞ የመቃወም አመልካች ነበሩ። አመልካች የፍርድ ባለዔዲዉ ንብረት ነዉ ባለዉ የቡና ማሽን ላይ አፈጻጸሙ እንዱቀጥልለት የጠየቀ ሲሆን የአሁን ተጠሪ የቡና ማሽኑ የፍርድ ባለዔዲዉ ንብረት ሳይሆን የራሳቸዉ ንብረት እንደሆነና እንዱለቀቅላቸዉ በመጠየቅ አቤቱታ አቅርበዋል። አመልካች በበኩላቸዉ ለአቤቱታዉ በሰጡት መልስ የፍርድ ባለዔዲዉ ይህንን ንብረት ከአመልካች በተከራየዉ ቤት ዉስጥ የሚጠቀምበት ስለሆነና የፍርድ ባለዔዲ የቤት ኪራይ ስላልከፈለና አመልካች ንብረቱ የላላ ሰዉ መሆኑን አስቀድሞ ስለማያዉቅ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2924 መሰረት ዉሳኔዉ ሉፈጸምበት ስለሚገባ አቤቱታዉ ተገቢነት የለዉም በማለት ተከራክሯል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የስር ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ምስክሮች ሰምቶ ክርክር ያስነሳዉ የቡና ማሽን የፍርድ ባለዔዲዉ ሳይሆን የተጠሪ መሆኑ ስለተረጋገጠ ንብረቱ ላይ ተሰጥቶ የነበረዉ የእግድ ትዕዛዝ ተነስቶ ለተጠሪ ይልቀቅ በማለት ወስኗል። በዚህ ዉሳኔ ቅር ተሰኝቶ አመልካች ባቀረበዉ ይግባኝ መነሻነት ጉዲዩን የተመለከተዉ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ግራ ቀኙን ካከራከረ በኃላ ዉሳኔዉን በማጽናት ወስኗል። አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረበዉ ይህን ዉሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነዉ።
የአመልካች ሰበር አቤቱታ ይዘት፡- የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2925 መሰረት አመልካች የቡና ማሽኑን ለኪራይ ዔዲ አከፊፈል ዋስትና እንዲይዝ የሚከለክለ ነገሮች ስለመኖራቸዉ በጭብጥነት ይዞ ማጣራት ሲገባዉ ንብረቱ የተጠሪ መሆኑ ተረጋግጧል በሚል እና አመልካች ማሽኑ የተጠሪ አለመሆኑን አላስተባበለም በሚል ብቻ መወሰኑ ተገቢ አይደለም። ይግባኝ ሰሚዉ ፍ/ቤት በበኩለ አመልካች የቡና ማሽኑ የተጠሪ ስለመሆኑ የሚያዉቅ መሆኑ በማስረጃ ያልተረጋገጠ መሆኑን ከደመደመ በኃላ ተጠሪ ማሽኑን በፍርድ ባለዔዲ ማከራየቷን ለአመልካች የማሳወቅ ግዳታ የለባትም፤ የግል ንብረቷ መሆኑን አስረድታለች በሚል የስር ፍ/ቤት ዉሳኔ ማጽናቱ ስህተት ነዉ።
እንዱሁም ይግባኝ ሰሚዉ ፍ/ቤት ለጉዲዩ ተፈጻሚነት የላለዉን የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1193(2)ን በመጥቀስ አመልካች የቡና ማሽኑን ለፍ/ባለዔድዉ ዔዲ መክፈያነት መያዝ አይቻልም ብል የስር ፍ/ቤትን ዉሳኔ ማጽናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይሻርልን የሚል ነዉ።
የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች ከስር የፍርድ ባለዔዲ ጋር ተከራክሮ ለማስፈጸሚያነት ያስያዙት የቡና ማሽን የአሁኑ ተጠሪ ንብረቱ የግላ ነዉ በማለት የኪራይ ዉል በማቅረባቸዉ ብቻ ለአፈጻጸም ሉዉል አይገባም መባለን ከፍ/ሕ/ቁ 1193(1) እና 2924 አንጻር ለመመርመር ሲባል መዝገቡ ለሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል የተባለ ሲሆን ግራቀኙ መልስና የመልስ መልስ በጽሁፍ በማቅረብ ተከራክረዋል።
ተጠሪ ለአቤቱታዉ የሰጡት መልስ ይዘት፡- አንድ ንብረት ላይ ፍርድ ሉፈጸም የሚችለዉ የባለዔዲዉ ንብረት መሆኑ ሲረጋገጥ ሲሆን ክርክር ያስነሳዉ የቡና ማሽን የፍርድ ባለዔዲዉ ሳይሆን የግላ መሆኑ ተረጋግጦ እንዱለቀቅልኝ በስር ፍ/ቤት መወሰኑwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ተገቢ ነዉ። አመልካች በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1193(1) መሰረት ክርክር ያስነሳዉ ንብረት የፍርድ ባለዔዲዉ መሆኑን ግምት በመዉሰድ ለአፈጻጸም እንዱዉል የጠየቀ ቢሆንም ተጠሪ ደግሞ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1193(2) መሰረት አመልካች የያዘዉ ግምት ልክ አለመሆኑን በበቂ ማስረጃ በማስረዲት ያስተባበልን በመሆኑ ንብረቱ እንዱለቀቅ በስር ፍ/ቤት የተሰጠዉ ዉሳኔ የሚነቀፍ አይደለም በማለት ተከራክረዋል። አመልካች ባቀረበዉ የመልስ መልስ የሰበር አቤቱታዉን በሚያጠናክር መልኩ ተከራክሯል።
የግራ ቀኙ ክርክር በአጭሩ ከላይ የተገለጸዉን የሚመስል ሲሆን እኛም አቤቱታ ከቀረበበት ዉሳኔ እና አግባብነት ካላቸዉ የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን መርምረናል። የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዘዉ ጭብጥ አንጻር መርምረን እንደተረዲነዉ አመልካች የንግድ ቤቱን ለፍርድ ባለዔዲ አከራይቶ የነበረ ሲሆን የፍርድ ባለዔዲ ያልከፈለዉ ዉዝፍ ኪራይ በመኖሩ ክስ አቅርቦበት አስወስኗል። አመልካች የተወሰነለት ገንዘብ አፈጻጸም የፍርድ ባለዔዲዉ በተከራየዉ ቤት ዉስጥ ይሰራበት በነበረዉ የቡና ማሽን ተሽጦ እንዱፈጸምለት የጠየቀ ሲሆን ተጠሪ በበኩላቸዉ የቡና ማሽኑ የፍርድ ባለዔዲዉ ንብረት ሳይሆን የራሳቸዉ ንብረት በመሆኑ ለአፈጻጸም ሉዉል እንደማይገባና ሉለቀቅላቸዉ እንደሚገባ በመጠየቅ ተከራክረዋል። የስር ፍ/ቤት ማስረጃ ከሰማ በኃላ የቡና ማሽኑ የፍርድ ባለዔዲዉ ሳይሆን የተጠሪ መሆኑን ካረጋገጠ በኃላ ለአፈጻጸም ሉዉል ስለማይገባ ለተጠሪ ይለቅላቸዉ በማለት ወስኗል። አመልካች አጥብቆ የሚከራከረዉ ንብረቱ የፍርድ ባለዔዲዉ ባይሆንም አመልካች ይኸዉ ንብረት የላላ ሰዉ መሆኑን አውቆ የነበረ መሆኑ እስካልተረጋገጠ ድረስና በተከራየዉ ቤት ዉስጥ የሚጠቀምበት እስከሆነ ድረስ ላልተከፈለ የቤት ኪራይ አከፊፈል ሉውል ይገባል በማለት ነዉ።
በመሰረቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 378 ተከታዮች ድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ እንደሚቻለዉ በመርህ ደረጃ አንድ ፍርድ በአንድ ንብረት ላይ ሉፈጸም የሚችለዉ ንብረቱ የፍርድ ባለዔዲዉ ንብረት መሆኑ ሲረጋገጥ ነዉ። በልላ በኩል የፍ/ብ/ሕ/ቁ 2924 ያንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት አከራይ የሆነ ሰዉ ባለፈዉ ዓመት ላልተከፈለዉ ኪራይና ላለበትም ዓመት ስድስት ወር ሉከፈለዉ ለሚገባዉ ኪራይ ዋስትና ለቤቱ ማጌጫ ከሚያገለግለት ዔቃዎችም ሆነ ለስፍራዉ ማልሚያ ከሚጠቅሙት መሳሪያዎች ላይ የመያዣ መብት ያለዉ መሆኑን ሲደነግግ፤ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 2926(2) ደግሞ በስዉርwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ወይም በኃይል የተወሰደትን ዔቃዎች ሳይቀሩ አከራይ በአስር ቀን ዉስጥ በፍርድ በማስያዝ የአከራዩን መብቶች በቀደምትነት መክፍያ እንዱሆኑ ማድረግ የሚችል መሆኑን፤ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 2925 አከራዩ የዔቃዎቹ ባለሀብትነት የተከራዩ አለመሆኑን አዉቆ እንደሆነ ወይም ማወቅ ይገባዉ ኑሮ እንደሆነ በዔቃዎቹ ላይ የመያዣ መብቱ ሉፈጸም እንደማይችልና የራሱ አለመሆናቸዉን ያወቀዉ ዉለ ጸንቶ በሚቆይበት ጊዜ የሆነ እንደ ሆነ ዉለ በቅርብ ጊዜ ዉስጥ እንዱፈርስ ካላመለከተ በቀር በእነዚህ ዔቃዎች ላይ ይዞ የማቆየት መብቱ ይቀርበታል ተብል በግልጽ ተመልክቷል። ከነዚህ ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ መገንዘብ የሚቻለዉ የአንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት አከራይ የሆነ ሰዉ ከላይ ለተገለጸዉ ጊዜ ላልተከፈለዉ የዉዝፍ ኪራይ ክፍያ አከፊፈል ሲባል ተከራዩ ለቤቱ ማጌጫነት ወይም ለስፍራ ማልሚያነት ከሚጠቀምባቸዉ ዔቃዎች ላይ ዔቃዎቹ የራሱ ባይሆኑም ይህንኑ አከራዩ እስካላወቀ ወይም ማወቅ ነበረበት እስካልተባለ ድረስ በሕግ የተቋቋመ የመያዣ መብት ያለዉ መሆኑና በልዩ ሁኔታ ለአፈጻጸም ሉያዉላቸዉ የሚችል መሆኑን ነዉ።
በተያዘዉ ጉዲይ ክርክር ያስነሳዉ የቡና ማሽን የፍርድ ባለዔዲዉ ንብረት ሳይሆን የተጠሪ መሆኑ የተረጋገጠ ቢሆንም የፍርድ ባለዔዲዉ ለተከራየዉ ቤት ማልሚያነት ይጠቀምበት የነበረ መሆኑ እስካልተካደና እስከተረጋገጠ ድረስ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ 2924 ተከታዮቹ ድንጋጌዎች አንጻር ለአፈጻጸም ሉዉል የሚገባዉ ነዉ ወይስ አይደለም የሚለዉ ሳይጣራና ሳይረጋገጥ ንብረቱ የባለዔዲዉ ሳይሆን የተጠሪ ነዉ ስለተባለ ብቻ ለአፈጻጸም ሉዉል አይገባም ተብል መወሰኑ ስህተት ነዉ። ስለሆነም የቡና ማሽኑ የተጠሪ መሆኑ ቢረጋገጥም የፍርድ ባለዔዲዉ ለተከራየዉ ቤት ማልሚያ የሚጠቀምበት መሣሪያ በመሆኑ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ 2924 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት፡-
አመልካች በቡና ማሽኑ ላይ የመያዣ መብት ያለዉ መሆን ያለመሆኑ?
አመልካች የተወሰነለት የኪራይ ገንዘብ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2924 መሰረት የመያዣ መብት የሚያሰጠዉ መሆን አለመሆኑ?
እንዱሁም ከፍ/ብ/ሕ/ቁ 2925 ድንጋጌ አንጻር አመልካች ቤቱን ሲያከራይ የቡና ማሽኑ የፍርድ ባለዔዲዉ ወይም የተከራዩ አለመሆኑን ያዉቅ የነበረ መሆኑ ወይም ማወቅ ይገባዉ የነበረ ወይም ዉለ ጸንቶ በቆየበት ወቅትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ይህንኑ አዉቆ የነበረ መሆን ያለመሆኑ? በቅድሚያ በማስረጃ ሉጣራና ሉረጋገጥ ይገባል።
ሲጠቃለል የስር ፍ/ቤት ክርክር ያስነሳዉ የቡና ማሽን የፍርድ ባለዔዲዉ ሳይሆን የተጠሪ መሆኑን ቢያርጋግጥም ከአመልካች ክርክርና ከፍ/ብ/ሕ/ቁ 2924 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች አንጻር ንብረቱ ለአፈጻጸም መዋል መቻል አለመቻለ በግራ ቀኙ ክርክርና ማስረጃ ሳይጣራና ሳይረጋገጥ ንብረቱ ለአፈጻጸም ሉዉል አይገባም ተብል መወሰኑ የተጠቀሱትን የሕግ ድንጋጌዎች ይዘት ያላገናዘበ እና መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በለመሆኑ ዉሳኔዉ ተሽሮ አጣርቶ እንዱወስን ለስር ፍ/ቤት መመለሱ ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም የሚከተለዉ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
2 ከላይ በፍርድ ሀተታዉ በተገለጸዉ አግባብ ግራ ቀኙን አከራክሮና በማስረጃ አጣርቶ ተገቢዉን ዉሳኔ እንዱሰጥበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343(1) መሰረት ጉዲዩ ለአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይመለስለት ተብሎል። ይጻፍ።
3 ሚያዚያ 02 ቀን 2010 ዓ.ም አፈጻጸሙ ለጊዜዉ ታግድ እንዱቆይ የተሰጠዉ የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ይጻፍ።
4 የሰበር ክርክሩ ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸዉን ይቻለ።
No topics extracted.