የዔርቅ ስምምነት ውል እንደዉሳኔ ተቆጥሮ በፍርድ ቤት ለአፈፃፀም አቅርቦ ለማስፈፀም ስምምነቱ ግልጽና የፈፃሚዉን አካል ግዳታ በማያሻማ ሁኔታ የሚገልጽ መሆን ያለበት ሲሆን ግልጽ ያልሆነ የእርቅ ስምምነት ሲቀርብ፣ ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት የላላ ተከራካሪ ወገን ክርክር እንኳ መስማት ሳያስፈልገዉ ክሱን ዉድቅ ማድረግ የሚችል ስለመሆኑ ፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 3312(1)
No summary available.
ቀን - 30/09/2010 ዳኞች፡ ተኽሉት ይመሰል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራዉ አብዬ ካሳሁን አመልካቾች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የእርቅ ስምምነት ይፈጸምልኝ በሚል በቀረበዉ ክስ መነሻነት የተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ በሚል የቀረበዉን የሰበር አቤቱታ የሚመለከት ነዉ። ክርክሩ የተጀመረዉ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካቾች ከሳሽ፣ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
አመልካቾች ለፍርድ ቤቱ ያቀረቡት ክስ ይዘትም በአጭሩ በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ወረዲ 09 ቀበላ ዉስጥ የሚገኝ እና ቁጥሩ 7251 የሆነዉ ቤት ግራ ቀኝ በዉርስ አግኝተን የጋራችን የሆነዉን ቤት በተመለከተ በ19/10/07 ዓ.ም በመካከላችን የተደረገ የእርቅwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ስምምነት ዉል ይፈጸምልን የሚል ነዉ። ተጠሪ በበኩለ የእርቅ ስምምነቱ እንዱፀድቅ ቀደም ሲል ለፍርድ ቤት ቀርቦ ተቀባይነት ያላገኘ መሆኑን፣ ከሳሾች የእርቅ ስምምነት ነዉ በማለት ያቀረቡትም የቤቱን ካርታ የማይገልጽ በመሆኑ የቀረበዉ ክስ ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩ በመጀመሪያ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ከግራ ቀኝ በዚህ መልኩ የቀረበዉን ክርክር እና ማስረጃ ከሰማ በኋላ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት ካርታ የላለዉ እና ብረትነቱም የመንግስት ሆኖ ቀበላ የሚያስተዲድረዉ መሆኑ መረጋገጡን ገልፆ አመልካቾች ክስ የማቅረብ መብት የላቸዉም በማለት ወስኗል። አመልካቾች ይህን ዉሳኔ ባለመቀበል ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ቢሆንም፣ ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት አመልካቾች ለክሳቸዉ መሰረት ያደረጉት የእርቅ ስምምነት በየትኛዉ ላይ እንደሚፈጸም የማያመለክት መሆኑን ጠቅሶ የቀረበዉን ይግባኝ ሰርዞታል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ ይህኑን ዉሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ሲሆን፣ አመልካቾች በቀን 23/12/09 ዓ.ም ተዘጋጅቶ በጠበቃቸዉ አማካይነት በቀረበዉ ሦስት ገጽ የሰበር አቤቱታ የስር ፍርድ ቤቶች ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ የሚለባቸዉን ምክንያቶች በመዘርዘር ታርሞ ይወሰንላቸዉ ዘንድ ዲኝነት ጠይቀዋል። አቤቱታዉ ተመርምሮ ያስቀርባል በመባለም ተጠሪ በተደረገለት ጥሪ መሰረት ቀርቦ ግራ ቀኝ ክርክራቸዉን በጽሐፍ ተለዋዉጠዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከፍ ሲል የተመለከተዉን ሲመስል፣ ይህ ችልትም ለሰበር አቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉን ዉሳኔ ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። አመልካቾች በስር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ ለጠየቁት ዲኝነት መሰረት ያደረጉት በግራ ቀኝ መካከል በ19/10/2007 ዓ.ም ተደረገ የተባለዉን የእርቅ ስምምነት ነዉ። ተጠሪ በበኩለ ስምምነቱ ለአፈፃፀም ቀርቦ ተቀባይነት ማጣቱን ጠቅሶ ተከራክሯል። ግራ ቀኙ በዚህ መልኩ ካቀረቡት ክርክር አኳያ በፍ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 246(1) መሰረት ተይዞ እልባት ማግኘት የሚገባዉ ትክክለኛ ጭብጥ በፍርድ ቤት ሉፈጸም የሚችል በግራ ቀኝ መካከል የተደረገ የእርቅ ስምምነት መኖር አለመኖሩ ነዉ። የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአመልካቾችን ክስ ዉድቅ ያደረገዉwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ለክርክሩ ምክንያት ለሆነዉ የእርቅ ስምምነት መነሻ የሆነዉ ቤት ካርታ የላለዉ እና የመንግሰት መሆኑን በመጥቀስ ነዉ። ይህም የሚያሳየዉ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከቤቱ ባለቤትነት ጋር በተያያዘ በግራ ቀኝ የተነሳ ክርክር ሳይኖር ከፍ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 182 በሚፃረር መልኩ ከክርክሩ ጭብጥ ዉጪ በመዉጣት ዉሳኔ መስጠቱን በመሆኑ ሉታረም የሚገባዉ ነዉ ብለናል።
በልላ በኩል አመልካቾች ለክሳቸዉ መሰረት ያደረጉት የእርቅ ስምምነት ተገቢዉን የፍሬ ነገር መግለጫ ያልያዘ እና ስምምነቱ በየትኛዉ ቤት ላይ እንደሚፈጸም የማያመለክት ስለመሆኑ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አረጋግጦ ለዚህ ሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነዉን ትዕዛዝ መስጠቱን ተመልክተናል። አመልካቾች ለዚህ ሰበር ችልት ባቀረቡት አቤቱታም ተጠሪ ስምምነቱ ሉፈጸም የሚችል ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ሳይከራከር ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ይህን ዉሳኔ መስጠቱ አግባብ አለመሆኑን የተከራከረ ቢሆንም፣ ስምምነቱ ግልጽና ሉፈጸም የሚችል ስለመሆኑ ገልጸዉ አልተከራከሩም።
እኛም ለክርክሩ ምክንያት የሆነዉን የእርቅ ስምምነት አስቀርበን እንዲየነዉ እርቅ ስምምነቱ ስለየትኛዉ ቤት፣ እንዱሁም ተጠሪ በእርቅ ስምምነቱ መሰረት እንዱፈጽም የሚጠበቅበት ግዳታ ምን እንደሆነ በተብራራ መልኩ አያስቀምጥም። በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 3312(1) መሰረት እንደዉሳኔ ተቆጥሮ በፍርድ ቤት ለአፈፃፀም አቅርቦ ማስፈጸም ይቻል ዘንድ ስምምነቱ ግልጽና የፈፃሚዉን አካል ግዳታ በማያሻማ ሁኔታ የሚገልጽ መሆን አለበት። በዚህ ዓይነት ግልጽ ያልሆነ የእርቅ ስምምነት ሲቀርብ፣ ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት የላላ ተከራካሪ ወገን ክርክር እንኳን መስማት ሳያስፈልገዉ ይህኑን ጠቅሶ ክሱን ዉድቅ ማድረግ ይችላል። ከዚህ አንፃር ሲታይ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ቤቱ የመንግስት ነዉ በሚል የስር ፍርድ ቤት የደረሰበትን ድምዲሜ ማረም ሲገባዉ ይህን አለማረሙ ስህተት ቢሆንም፣ አመልካቾች ለክሳቸዉ መሰረት ያደረጉት ስምምነት ግልጽ እና የተብራራ አይደለም በሚል ምክንያት የቀረበለትን አቤቱታ ዉድቅ በማድረግ የሰጠዉ ትዕዛዝ በአግባቡ ነዉ ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ስላልተገኘ ተከታዩ ተወስኗል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/101014 በቀን 03/02/09 ዓ.ም በዋለዉ ችልት ቤቱ የመንግስት ነዉ በማለት የሰጠዉ የዉሳኔ ክፍል ተሽሯል።
ይህ ችልት በቀን 13/03/2010 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ የዔግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ ብለናል።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።
No topics extracted.