አንድ ለክርክር ምክንያት የሆነ ንብረት በአፈፃፀም ምክንያት በሐራጅ እንዱሸጥ የአፈፃፀም መዝገቡን የያዘዉ ፍርድ ቤት ወስኖ የሐራጅ ማስታወቂያ ወጥቶ ገዥ ካልተገኘ ንብረቱን ባለ ገንዘቡ የመረከብ መብት ያለው ሲሆን ይህን የሻለቃ አሰፊ መንገሻ ህጋዊ ወራሾች እና አቶ ዮናስ ዲኜ www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XLI ማስተባበል የሚቻለዉ ደግሞ ባለገንዘቡ ቤቱን እንዱረከብ በሚል ተሰጥቶ የነበረዉ ትዕዛዝ ስነ-ስርዓት ህጉ በሚፈቅደዉ አግባብ በልላ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሻሩ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 428(2)
No summary available.
የሰ/መ/ቁ/ - 144272 ቀን - 24/11/2010 ዳኞች፡ ተኽሉት ይመሰል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራዉ አብዬ ካሳሁን አመልካች፡- የሻለቃ አሰፊ መንገሻ ህጋዊ ወራሾች - ወኪል ወ/ሮ ክብሬ አሰፊ -ቀርበዋል ተጠሪ፡- አቶ ዮናስ ዲኜ -በላለበት **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል
**
ክርክሩ የተጀመረዉ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት በጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን ተጠሪ ከሳሽ፣ አመልካች 1ኛ ተከሳሽ፣ በዚህ ችልት የክርክሩ ተካፊይ ያልሆኑት አርባ ምንጭ ከተማ ማዘጋጃ ቤት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አቶ በላይ አስራቴ በቅደም ተከተል ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተከሳሾች ነበሩ።
ተጠሪ በቀን 06/08/2008 ዓ.ም አዘጋጅቶ ለፍርድ ቤቱ ያቀረበዉ ክስ ይዘት በአጭሩ በአርባ ምንጭ ከተማ ስፊቱ 3,200.00 ካ/ሜትር የሆነዉ ቦታ በህጋዊ መንገድ በ1976 ዓ.ም ተሰጥቶት በቦታዉ ላይ የተሻለ ድርጅት ለመገንባት በዝግጅት ላይ እያለ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ምክንያት ንብረቱን የሚመለከቱ የተለያዩ ሰነድችን በቤት ዉስጥ ትቶ ወደ ኤርትራ መሄደን፤ አባቱ አቶ ዲኜ መክበብ በተሻረ ዉክልና ድርጅቱን እና ቤቱን በባንክ በማስያዝ ከ3ኛ ተከሳሽ ባንክ ገንዘብ ከተበደረ በኋላ ገንዘቡ ሙለwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በሙለ ተከፍሎል በሚል የስር 3ኛ ተከሳሽ ለ1ኛ ተከሳሽ ማስረከቡን፣ 2ኛ ተከሳሽ ያላግባብ ካርታ በመስጠት እንዱሁም 1ኛ ተከሳሽ ቤቱን በሽያጭ ለ4ኛ ተከሳሽ ያስተላለፈ መሆኑን በመጥቀስ ዉለ ፈርሶ የቤቱ ካርታ ወደነበረበት ሁኔታ እንዱመለስ እና ይዞታዉን ከእነ ጋራዥ ድርጅቱ እንዱያስረክቡት ይወሰንለት ዘንድ ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነዉ።
የአሁን አመልካች ለቀረበባቸዉ ክስ በሰጡት መልስ የከሳሽ አባት፣ አቶ ዲኜ መክበብ፣ ከከሳሽ በተሰጣቸዉ ዉክልና መሰረት ቤቱን አስይዞ ከ3ኛ ተከሳሽ ገንዘብ ሲበደሩ አባታቸዉ የዋስትና ግዳታ ገብተዉ የነበረ መሆኑን፤ አቶ ዲኜ መክበብ የብድር ገንዘቡን ባለመክፈላቸዉ ገንዘቡን እንዱከፍለ የተሰጠዉን ዉሳኔ ተከትል ቤቱ በአፈፃፀም በጨረታ እንዱሸጥ የሐራጅ ማስታወቂያ ወጥቶ የነበረ ቢሆንም ቤቱ ሉሸጥ ባለመቻለ አበዲሪዉ 3ኛ ተከሳሽ ባንክ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ በጨረታዉ መነሻ ዋጋ ቤቱን ተረክቦ ለብዙ ዓመታት ሲያስተዲድረዉ ከቆዬ በኋላ አመልካቾች በዋስትና ግዳታዉ ምክንያት ሉሸጥ ይችል የነበረዉን የአባታቸዉን ንብረት ለማስቀረት ሲባል የባንኩን ገንዘብ ሙለ በሙለ በመሸፈናቸዉ 3ኛ ተከሳሽ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት እንዲስረከባቸዉ እና ቤቱም በስማቸዉ እንዱሆን መደረጉን፤ አመልካቾች በዚህ መልኩ የተረከቡትን ቤት በህግ አግባብ ለስር 4ኛ ተከሳሽ በሽያጭ ያስተላለፈ መሆኑን ጠቅሰዉ ተከራክረዋል።
ላልች ተከሳሾችም በክሱ ኃላፉነት የለብንም የሚለባቸዉን ምክንያቶች በመዘርዘር መልስ ሰጥተዋል።
ጉዲዩ በመጀመሪያ የቀረበለት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ከግራ ቀኝ በዚህ መልኩ የቀረበዉን ክርክር እና ማስረጃ ከሰማ በኋላ የተጠሪ አባት፣ አቶ ዲኜ መክበብ፣ ቤቱ ከ3ኛ ተከሳሽ ባንክ ለተበደሩት የገንዘብ ዔዲ መክፈያ እንዱሆን የጠየቁት ቤቱ የእራሴ ነዉ በሚል እንጂ ከተጠሪ ባገኙት ዉክልና መሰረት ባለመሆኑ አባቴ የእኔን ቤት በመያዣ አስይዞታል በሚል ተጠሪ ያቀረበዉን ክርክር አለመቀበለን፤ አመልካቾች ለቤቱ መያዝ ምክንያት የሆነዉን እዲ በመክፈላቸዉ 3ኛ ተከሳሽን ተክተዉ የቤቱ ባለቤት ሉሆኑ የሚችለበት ህጋዊ ምክንያት አለመኖሩን፤ ይሁንና የስር 4ኛ ተከሳሽ ቤቱን የገዛዉ በቅን ልቦና በመሆኑ የሽያጭ ዉል ይፍረስ በሚል ከሳሽ ያቀረበዉ ዲኝነት ተቀባይነት እንደላለዉ፤ አመልካቾች ዔዲዉን ሙለ በሙለ በመክፈላቸዉ ቤቱwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ከተሸጠበት ብር 600,000.00 ዉስጥ ብር 412,309.42 ተመላሽ ተደርጎላቸዉ ቀሪዉ ብር 187,690.58 አመልካቾች ለተጠሪ እንዱከፍለ በማለት ወስኗል። አመልካቾች ይህን ዉሳኔ ባለመቀበል ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበዉ ይግባኝም ተቀባይነት አላገኘም።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበዉም ይህኑን ዉሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ሲሆን፣ አመልካቾች በቀን 27/10/2009 ዓ.ም አዘጋጅተዉ በጠበቃቸዉ አማካይነት ባቀረቡት 5 ገጽ የሰበር አቤቱታ በስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በትዕዛዝ የፀናዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ የሚለባቸዉን ምክንያቶች በመዘርዘር ታርሞ ይወሰንላቸዉ ዘንድ ዲኝነት ጠይቀዋል። አቤቱታዉ ተመርምሮ ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ እንዱቀርብ ጥሪ የተደረገለት ቢሆንም ባለመቅረቡ ጉዲዩ በላለበት ታይቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸዉ ሲሆን፣ ይህ ችልትም ለሰበር አቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉን ዉሳኔ ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመረዉም ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ባቀረበዉ ክስ ለጠየቀዉ ዲኝነት መሰረት ያደረገዉ ንብረትነቱ የራሱ የሆነዉን ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት አባቱ፣ አቶ ዲኜ መክበብ፣ ህጋዊ የሆነ የዉክልና ስልጣን ሳይኖራቸዉ ለባንክ መያዣ አድርገዉ ገንዘብ መበደራቸዉን የስር 3ኛ ተከሳሽ ባንክም በዚህ አግባብ በእጁ የገባዉን ቤት ያላግባብ ለአመልካቾች ማስተላለፈ እና አመልካቾችም መብት ሳይኖራቸዉ ቤቱን ለስር 4ኛ ተከሳሽ በመሸጥ ያደረጉት ዉል መብቱን የሚነካ መሆኑን ሲሆን፤ አመልካቾች በበኩላቸዉ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት የአባቱ፣ የአቶ ዲኜ መክበብ፣ እንጂ የተጠሪ አለመሆኑን እና ቤቱ ለአመልካቾች እንዱተላለፍ የተደረገዉም የብድር ዔዲዉ ባለመከፈለ ምክንያት ቤቱ በሐራጅ እንዱሸጥ በፍርድ ቤት በተሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረት ገዥ ባለመገኘቱ አበዲሪዉ ባንክ (የስር 3ኛ ተከሳሽ) በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ቤቱን ሲያስተዲድረዉ ከቆዬ በኋላ አመልካቾች የባንክ ዔዲዉን በመሸፈናቸዉ በስማቸዉ እንዱሆን አድርጎ በዚህም መሰረት የቤቱ ባለ ሀብት በመሆን ለስር 4ኛ ተከሳሽ በሽያጭ ያስተላለፈ መሆኑን ገልጸዉ የተከራከሩ መሆኑን ተገንዝቧል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በስር 3ኛ ተከሳሽ የነበረዉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አርባ ምንጭ ቅርንጫፍ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት በመያዣነት ይዞ ለተጠሪ አባት ገንዘብ አበድሮ የብድር ገንዘቡ ባለመመለሱ ክስ ቀርቦበት በመ/ቁ/614/82 መጋቢት 8 ቀን 1984 ዓ.ም በተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረት እንዱፈጸምለት አበዲሪዉ ባንክ ባቀረበዉ የአፈፃፀም ክስ መነሻነት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/176/85 ላይ ጥቅምት 1 ቀን 1988 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቤቱን በሐራጅ ሸጦ ለፍርድ ባለ መብት ዔዲዉን በማስከፈል እንዱያስፈጽም ዉክልና መስጠቱ፤ በዚህም መሰረት ቤቱ እንዱሸጥ የሐራጅ ማስታወቂያ ቢወጣም ገዥ ባለመገኘቱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቤቱን እንዱረከብ እና የስም ዝዉዉርም እንዱደረግ ፍርደን እንዱያስፈጽም ዉክልና የተሰጠዉ የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መስጠቱ፤ በዚህም ንግድ ባንክ ቤቱን ተረክቦ ከ1992 ዓ.ም ጀምሮ ሲያስተዲድረዉ የነበረ መሆኑ፤ ይህ ከሆነ በኋላ የተጠሪ አባት ለተበደረዉ ገንዘብ የአመልካቾች አባት ሻለቃ አሰፊ መንገሻ ዋስ በመሆን በአዱስ አበባ የሚገኘዉን ቤታቸዉን ለባንክ መያዣ ሰጥተዉ የነበረ በመሆኑ እና ለዚህ ክርክር መነሻ የሆነዉ ቤት የብድር ዔዲዉን መክፈል ባለመቻለ የአመልካቾች አባት ቤት በዔዲ ምክንያት መሸጥ የለበትም በሚል ምክንያት አመልካቾች የባንኩን ዔዲ ሙለ በሙለ በመክፈላቸዉ ባንኩ ለዚህ ክርክር ምክንያት የሆነዉን ቤት እንዱረከቡ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/176/85 መስከረም 25 ቀን 1998 ዓ.ም በሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረት አመልካቾች ቤቱን ሰኔ 23 ቀን 1998 ዓ.ም የተረከቡ ስለመሆኑ የተረጋገጠ ከመሆኑም በላይ ተጠሪም ይህ ስለመሆኑ ክድ አልተከራከረም።
በመሰረቱ በአፈፃፀም ምክንያት በሐራጅ እንዱሸጥ የሐራጅ ማስታወቂያ ወጥቶ ገዥ ካልተገኘ ባለ ገንዘቡ ንብረቱን የመረከብ መብት እንዲለዉ እና የአፈፃፀም መዝገቡን የያዘዉ ፍርድ ቤትም ይህ እንዱሆን የማዘዝ ስልጣን እንዲለዉ በፍ/ሥ/ህጉ አንቀጽ 428(2) ስር የተመለከተዉ ድንጋጌ ያስገነዝባል። በዚህም መሰረት ለክርክሩ ምክንያት የሆነዉ ባንክ እንዱሸጥ የሐራጅ ማስታወቂያ ወጥቶ ገዥ ባለመገኘቱ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ የስር 3ኛ ተከሳሽ (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) መረከቡ ከተረጋገጠ የቤቱ ባለ መብት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነዉ ተብል ይገመታል። ይህን ግምት ማስተባበል የሚቻለዉ ባንኩ ቤቱን እንዱረከብ በሚል ተሰጥቶ የነበረዉ ትዕዛዝ ስነ-ስርዓት ህጉ በሚፈቅደዉ አግባብ በልላ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሻሩ ሲረጋገጥ እንደሆነ ይታመናል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ከዚህ ጋር በተያያዘ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ባቀረበዉ ክርክር የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በቀን 25/01/98 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሻለቃ አሰፊ መንገሻ ወራሾች ዔዲዉን አጠቃለዉ መክፈላቸዉን ባንኩ ማረጋገጡን ጠቅሶ ቤቱ ለተጠሪ እንዱመለስለት ሲል ትዕዛዝ መስጠቱን ሲሆን፤ አመልካቾች በበኩላቸዉ ተሰጠ የተባለዉ ትዕዛዝ በሦስት ዲኛ መሆን ሲገባዉ በአንድ ዲኛ የተሰጠ ከመሆኑም በላይ ከ 6 ዓመት በፉት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቤቱን ተረክቦ እንዱያስተዲድረዉ ተሰጥቶ የነበረዉን ትዕዛዝ በመሻር በመሆኑ ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከራክረዋል። የስር ፍርድ ቤት በበኩለ በዚህ መልኩ የተሰጠዉን ትዕዛዝ የተቀበለ መሆኑን በዉሳኔዉ የገለጸ ቢሆንም፣ የዚህን ትዕዛዝ ህጋዊነት ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ የፍትሐብሕር ሥ/ሥርዓት ህጉ ድንጋጌዎች እንዱሁም አመልካቾች በዚህ ረገድ ካቀረቡት ክርክር አንፃር በማገናዘብ ተገቢዉን ማጣሪያ በማድረግ አለመሆኑን የዉሳኔዉ ይዘት ያስገነዝባል። ይህ በአጠቃላይ የሚያሳየዉ የስር 3ኛ ተከሳሽ፣ ማለትም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ለክርክሩ ምክንያት የሆነዉ ቤት በዔዲ ምክንያት መረከቡ በተረጋገጠበት እና ይህ መሆኑ ባንኩን በቤቱ ላይ የባለቤትነት መብት የሚሰጠዉ ሆኖ፣ ባንኩ የቤቱ ባለቤት እንዱሆን የተደረገበት ትዕዛዝ በልላ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በህግ አግባብ የተሻረ መሆኑ ሳይረጋገጥ፣ የስር ፍርድ ቤት ባንኩ በቤቱ ላይ መብት አለኝ በሚል ምክንያት ለአመልካቾች ያስተላለፈበት አግባብ ህገ ወጥ ነዉ በሚል ድምዲሜ ላይ መድረሱን ነዉ።
በልላ በኩል፣ ከፍ ሲል እንደተገለጸዉ፣ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ክሱን ሲያቀርብ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት የእኔ ነዉ በሚል ነዉ። ይሁንና አመልካቾች ቤቱ ለእርሱ ሳይሆን የአባቱ የአቶ ዲኜ መክበብ መሆኑን ገልፀው ተከራክረዋል። በመሆኑም ከሳሽ በጠየቀዉ ዲኝነት መሰረት ሉወሰንለት የሚችለዉ የቤቱ ባለቤት እርሱ መሆኑ ሲረጋገጥ ነዉ። ምንም እንኳ ቤቱ በስሙ (በተጠሪ) ተመዝግቦ የሚታወቅ ቢሆንም፣ የተጠሪ አባት፣ አቶ ዲኜ መክበብ ቀደም ሲል በአፈፃፀም መዝገብ ላይ ባቀረቡት አቤቱታ፣ ቤቱ ሉመዘገብ የቻለዉ በወቅቱ ከአንድ ቤት በላይ ስለማይፈቀድ በተጠሪ ስም እንዱሆን ተደረገ እንጂ ቤቱ የተጠሪ ሳይሆን የእራሳቸዉ መሆኑን ገልጸዉ ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት አግኝቶ ቤቱ በሐራጅ እንዱሸጥ ትዕዛዝ መሰጠቱን መዝገቡ ያሳያል። የስር ፍርድ ቤትም የቤቱ ባለ ሀብት የተጠሪ አባት እንጂ ተጠሪ አለመሆኑን የተቀበለ ስለመሆኑ ከዉሳኔዉ ይዘት ተገንዝበናል። ፍርድ ቤቱ በአንድ በኩል ቤቱ የአባቱ እንጂwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የተጠሪ አይደለም እያለ፣ በልላ በኩል ግን ቤቱ ከተሸጠበት ገንዘብ በዉሳኔዉ የተመለከተዉ የገንዘብ መጠን ለተጠሪ እንዱከፈል ያለበት ምክንያትም ግልጽ አይደለም።
የቤቱ ስመ ሀብት በተጠሪ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ከመሆኑ አንፃር ሲታይ፣ የስር ፍርድ ቤት ቤቱ የተጠሪ ሳይሆን የተጠሪ አባት ነዉ በሚል ድምዲሜ ላይ የደረሰዉም በግራ ቀኝ ከቀረበዉ ክርክር እና ማስረጃ አንፃር በአግባቡ በማጣራት ነዉ ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም።
በአጠቃላይ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት የስር 3ኛ ተከሳሽ ባንክ በዔዲ ምክንያት በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተረክቦ በስሙ አድርጎ የነበረዉ እና ይህ በልላ ትዕዛዝ መሻሩ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ባንኩ ቤቱን ለአመልካቾች ለማስተላለፍ መብት የለዉም በሚል የደረሰበት ድምዲሜ፤ እንዱሁም ተጠሪ የቤቱ ባለ ሀብት መሆኑ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ በዉሳኔዉ የተመለከተዉ ገንዘብ እንዱከፈለዉ በሚል በስር ፍርድ ቤት የተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ተከታዩ ተወስኗል።
የደቡብ ብ/ብ/ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 12/08/09 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ፤ እንዱሁም የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 04/05/09 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ ተሽሯል።
የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተዘጋዉን መዝገብ በማንቀሳቀስ፣ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት የተጠሪ ነዉ? ወይስ የአባቱ የአቶ ዲኜ መክበብ? የአቶ ዲኜ መክበብ ነዉ የሚባል ከሆነ ተጠሪ ከጠየቀዉ ዲኝነት አንፃር የሚያስከትለዉ ህጋዊ ዉጤት ምንድን ነዉ? ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት የስር 3ኛ ተከሳሽ ባንክ እንዱረከብ በሚል ቀደም ሲል ፍርደን በሚያስፈጽም ፍርድ ቤት ተሰጥቶ የነበረዉን ትዕዛዝ ተከትል ባንኩ ቤቱን ተረክቦ ሲያስተዲድር ከቆዬ በኋላ ቤቱ ለተጠሪ ይመለስ በሚል የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/ 33/88 በቀን 27/10/98 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ትዕዛዝ አንድ ትዕዛዝ ሉሻር ወይም ሉሻሻል የሚችልበትን ስርዓት የተከተለ ነዉ ወይስ አይደለም? የሚለትን ጭብጦች ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች አንፃርwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በማገናዘብ አጣርቶ ተገቢዉን ዉሳኔ ይሰጥበት ዘንድ መዝገቡ በፍ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 343(1) መሰረት ተመልሶለታል።
No topics extracted.