የፍርድ አፈጻጸምን የሚመራ ፍ/ቤት በፍትሐብሕር ሥነሥርዓት ሕግ በተዘረጋው ሥርዓት መሰረት እንደፍርደ ይዘት እና መንፈስ ውጤት ባለው መልኩ ፍርደን ከማስፈፀም በቀር የፍርደን ይዘት በመመልከት የፍርደን ይዘት አድማስ በማጥበብም ሆነ በማስፊት ፍርድን የመተርጎም ስልጣን የላለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 372፤378
No summary available.
የሰ.መ.
ሕዲር 28 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች:- ኢትዮ ቴላኮም ሰራተኞች የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር የሕብረት ሥራ ማሕበር ተጠሪዎች፡- እነ ሰለሞን እሸቴ (191 ሰዎች) መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የአፈጻጸም ክርክርን የሚመለከት ነው። ለአፈጻጸሙ መነሻ የሆነው ውሳኔ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዲደር በሕብረት ሥራ ማሕበራት ማደራጃ በሽምግልና ዲኝነት ታይቶ ታሕሣስ 28 ቀን 2009 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ ነው። ይህንኑ ውሳኔ መነሻ በማድረግ አፈጻጸሙን የመራው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አመልካች ፍርደን ላለመፈጸም የተጠሪዎች ድርሻ ተለይቶ አልቀረበም በማለት የሰጠው ምክንያት ተጠሪዎች ለግልግል ዳኞች አቤቱታ ሲያቀርቡ 191 ሰዎች አንድ ላይ ሆነው ሲሆን ውሳኔም ያገኙት በጠቅላላው ለ191 ሰዎች በመሆኑ ድርሻቸውን ስለሚያውቁት እና ሉከፊፈለት ስለሚችለ የተሰጠው ምክንያት ተቀባይነት የለውም በማለት የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በግልግል ዳኞች ውሳኔ መሰረት ለተጠሪዎች ብር 5,361,749.61 ወጪ አድርጎ ይክፈላቸው፤አመልካች ከአዱስ ኢንተርናሽናል ባንክ ለተገባው አክሲዮን ባለድርሻwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በመሆናቸው ባለመብቶቹ የደረሰበት የገንዘብ መጠን የሚገባቸውን ሰርተፍኬት በየስማቸው አዘጋጅቶ ይስጣቸው በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል።
አመልካች በዚህ ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኘ አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም ይግባኙ የቀረበለት ፍ/ቤት ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ የስር ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ አጽንቷል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- ማሕበሩ 7200 አባላት ያለት ሲሆን የትርፍ ክፍፍል ለአባላቱ የሚከፊፈለው በሕብረት ስራ ማሕበራት አዋጅ ቁጥር 985/2009 አንቀጽ 45 እና በማሕበሩ ደንብ አንቀጽ 46 መሰረት አባለ በማሕበሩ ካፒታል ውስጥ ያለውን የእጣ እና ቁጠባ መጠን መሰረት በማድረገ በመሆኑ የሽምግልና ዳኞችም ይህንኑ መሰረት አድርገው በውሳኔአቸው ተ.ቁ 2 እና 7 ላይ ተጠሪዎች ከማሕበሩ በወጡበት 2003 ዓ.ም ያልተከፊፈለ ትርፍ ብር 2,179,133.05 ድርሻቸው ተሰልቶ እንዱከፈላቸው የሚለው ውሳኔ በመለወጥ የአፈጻጻም ትዕዛዝ መሰጠቱ ተገቢ አይደለም፤እንዱሁም የማሕበሩ አባል ሲሞት ቤተሰቦቹ በዔዲ እንዲይጠየቁ ያዋጡትን ብር 3,155,216.56 የአጠቃላይ የማሕበሩ አባላት ገንዘብ ታስቦ ይከፈል በማለት የተሰጠው ትዕዛዝ እና ከሳሾች የማህበር አባል በነበሩበት ጊዜ ለተገዛው የአክሲዮን ድርሻ በደረሰበት ካፒታል መጠን ሰርተፍኬት አዘጋጅቶ ይስጣቸው ተብል የተሰጠው የአፈጻጸም ትዕዛዝ ከዋናው ውሳኔ ውጪ የተሰጠ በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የሽምግልና ዳኞች በቀን 28/04/09 በሰጡት ውሳኔ ተጠሪዎች ከብር 5,361,749.61 ውስጥ ድርሻቸው ተለይቶ ሉከፈላቸው እንደሚገባ ተወስኖ እያለ የአፈጻጸም ችልቱ ይኸው ገንዘብ ሙለ በሙለ የተጠሪዎች ድርሻ እንደሆነ ተቆጥሮ ወጪ ሆኖ እንዱከፈል ማዘዙ ፍርደን የተከተለ መሆን አለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዚህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል። ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የተጠሪዎች መልስ ይዘት በአጭሩ፡- ተጠሪዎች በሽምግልና ዲኞቹ ውሳኔ መሰረት የሚገባን ድርሻ ተለይቶ ከነወለደ እንዱከፈለን እና በአዱስ ኢንተርናሽናል ባንክ ከተገዛው የብር 7,500,000 አሁን የተደረሰበትን ካፒታል ጨምሮ የአክሲዮን ድርሻችንን የሚገልጽ የጽሐፍ ማስረጃ እንዱሰጠን እንጂ የማይገባንን እና ውሳኔ ያልተሰጠበትን ክፍያ እንዱሰጠን ስላልጠየቅን በሽምግልና ዲኞቹ ውሳኔ መሰረት እንዱፈጸምልን የሚል ነው።
አመልካች በሰጠው የመልስ መልስ ተጠሪዎቹ ከአዱስ አንተርናሽናል ባንክ ከተገዛው ሼር በስተቀር የ 2003 ዓ.ም የትርፍ ክፍፍል ብር 2,179,133.05 እና የማሕበሩ አባል ብድሩን ሳይከፍል ቢሞት ለዔዲ መሸፈኛ የተዋጣው ብር 3,155,216.56 የጠቅላላ የማሕበሩ ገንዘብ መሆኑን አምነው በሽምግልና ዳኞች ውሳኔ መሰረት እንዱከፈላቸው መልስ መስጠታቸው የስር ፍ/ቤቶች ተጠሪዎች ያልጠየቁትን ከሽምግልና ዳኞች ውሳኔ ውጪ ክፍያ እንዱከፈላቸው ትዕዛዝ መስጠታቸውን የሚያሳይ ነው፤ተጠሪዎች ከአዱስ ኢንተርናሽናል ባንክ ማሕበሩ የገዛውን አክሲዮን በተመለከተ አሁን በደረሰበትን ካፒታል ተዘጋጅቶ ሰርተፍኬት እንዱሰጠን በማለት የሰጡት ምላሽ ግን ከሽምግልና ዲኞኞች ውሳኔ ውጪ ስለሆነ በዚህ አግባብ ያቀረቡት መከራከሪያ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት የመልስ መልስ ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። ይህ ችልትም በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባዋል በማለት የተያዘውን የብር 5,361,749.61 የአፈጻጸም ትዕዛዝ ከግራቀኙ ክርክር፤ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው የአፈጻጸም ትዕዛዝ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
ለአፈጻጸሙ መነሻ የሆነው ውሳኔ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዲደር በሕብረት ሥራ ማሕበራት ማደራጃ በሽምግልና ዲኝነት ታይቶ ታሕሣስ 28 ቀን 2009 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሆኑን፤ተጠሪዎች የአፈጻጸም ክስ ያቀረቡት በውሳኔው መሰረት ይፈጸምልን በሚል መሆኑን፤አፈጻጸሙን የመራው የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አመልካች የተጠሪዎች ድርሻ ተለይቶ ባለመቅረቡ ፍርደን ለመፈጸም አለመቻለን በመግለጽ ያቀረበውን ምክንያት ለግልግል ዳኞች አቤቱታ ያቀረቡት አንድ መቶ ዘጠና አንደ ተጠሪዎች በመሆናቸው እና ድርሻቸውን የሚያውቁት በመሆኑ ፍርደን ላለመፈጸም የተሰጠው ምክንያት ተቀባይነት የለውም በማለት የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በግልግልwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ዳኞች ውሳኔ መሰረት ለተጠሪዎች ብር 5,361,749.61 ወጪ አድርጎ እንዱከፍላቸው በማለት የአፈጻጸም ትዕዛዝ የሰጠ መሆኑን ከክርክሩ ሑደት መገንዘብ ችለናል።
አመልካች ገንዘቡን በሚመለከት በስር ፍ/ቤቶች የተሰጠው የአፈጻጸም ትዕዛዝ ተገቢ አይደለም በማለት የሚከራከረው ማሕበሩ 7200 አባላት ያለት ሲሆን የትርፍ ክፍፍል ለአባላቱ የሚከፊፈለው አባለ በማሕበሩ ካፒታል ውስጥ ያለውን የእጣ እና ቁጠባ መጠን መሰረት በማድረግ ሲሆን የሽምግልና ዳኞችም ውሳኔ የሰጡት ተጠሪዎች ከማሕበሩ በወጡበት 2003 ዓ.ም ያልተከፊፈለ ትርፍ ብር 2,179,133.05 ድርሻቸው ተሰልቶ እንዱከፈላቸው፤የማሕበሩ አባል ሲሞት ቤተሰቦቹ በዔዲ እንዲይጠየቁ ያዋጡትን ብር 3,155,216.56 የአጠቃላይ የማሕበሩ አባላት ገንዘብ ታስቦ ይከፈላቸው የሚል ሆኖ ሳለ ከኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በግልግል ዳኞች ውሳኔ መሰረት ለተጠሪዎች ብር 5,361,749.61 ወጪ ተደርጎ እንዱከፈላቸው በማለት የተሰጠው የአፈጻጸም ትዕዛዝ ከውሳኔው ይዘት ውጪ ነው በሚል ነው። ተጠሪዎች ለዚህ ችልት በሰጡት መልስም የአፈጻጸም ክስ ያቀረብነው በሽምግልና ዲኞቹ ውሳኔ መሰረት የሚገባን ድርሻ ተለይቶ ከነወለደ እንዱከፈለን አልጠየቅንም በማለት የአመልካችን አቤቱታ በመደገፍ መልስ ሰጥተዋል።
በመሰረቱ በሕግ አግባብ ታይቶ የተሰጠ ፍርድ እንደ ፍርደ መፈጸም ያለበት ስለመሆኑ፤አፈጻጸሙን የሚመራው ፍ/ቤትም በሥነ-ሥርዓት ሕጉ በተዘረጋው ሥርዓት መሰረት እንደፍርደ ይዘት እና መንፈስ ውጤት ባለው መልኩ ፍርደን የሚያስፈጽም በቀር የፍርደን ይዘት በመመልከት የፍርደን ይዘት አድማስ በማጥበብም ሆኖ በማስፊት ፍርድን የመተርጎም ስልጣን እንደላለው ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 372፤378 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ ይቻላል። አመልካች ለዚህ ችልት ባቀረበው የሰበር አቤቱታ የስር ፍ/ቤት የሰጠው የአፈጻጸም ትዕዛዝ ከዋናው ውሳኔ ይዘት ውጪ ነው በማለት የሚከራከር ከመሆኑ አኳያ የስር ፍ/ቤት የአፈጻጸም ትዕዛዝ በዋናው ፍርድ መሰረት የተሰጠ መሆን አለመሆኑን እንደሚከተው መርምረናል።
ለአፈጻጸሙ መነሻ የሆነው ውሳኔ በቂርቆስ ክፍለከተማ አስተዲደር በሕብረት ሥራ ማሕበራት ማደራጃ በሽምግልና ዲኝነት ታይቶ ታሕሣስ 28 ቀን 2009 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ሲሆን በውሳኔው ገጽ 9 ተ.ቁ 2 ላይ ተጠሪዎች ከማሕበሩ በወጡበት የ2003www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ዓ.ም በጀት ዓመት ያልተከፊፈለ ትርፍ ብር 2,179,133.05 መሆኑ የሚያሳይ የኦዱት ሪፖርት የቀረበ በመሆኑ በቀረበው የኦዱት ሪፖርት ውጤት መሰረት ተጠሪዎች ድርሻቸው ተሰልቶ የትርፍ ክፍፍለ በየድርሻቸው መሰረት ከነወለደ እንዱሰጣቸው የሚል ሲሆን፤በዚሁ ገጽ ተ.ቁ 3 ላይ በኢንሹራንስ ስም የመድን ዋስትና በማለት ከአባላት የተሰበሰበው ገንዘብ በመንግስት ኦዱተሮች ተመርምሮ የተገኘው ገንዘብ ብር 3,155,216.56 የተሰበሰበው ተጠሪዎች ለማሕበሩ እያንዲንዲቸው እየከፈለ ያጠራቀሙት ብር 5 እና በመተዲደሪያ ደንቡ መሰረት ከማሕበሩ ከቆጠቡት ገንዘብ ሲበደሩ ከጠቅላላው ብድር ላይ 1% እና 5 ብር ከነወለደ ታስቦ ተጠሪዎች ከማሕበሩ እስከወጡበት 2003 ዓ.ም ድረስ ያላቸው ሂሳብ በነፍስወከፍ እንዱከፈላቸው የሚል ነው። ከውሳኔው ይዘት መገንዘብ የሚቻለው ካልተከፊፈለው የማሕበሩ የ2003 ዓ.ም በጀት ዓመት ትርፍ ብር 2,179,133.05 እና በኢንሹራንስ ስም የመድን ዋስትና በማለት ከአባላት የተሰበሰበው ብር 3,155,216.56 ውስጥ የተጠሪዎች ድርሻ ተሰልቶ እንዱከፈላቸው በማለት ውሳኔ መሰጠቱን እንጂ በኦዱት ሪፖርተ መሰረት የተገለጸው የ2003 ዓ.ም በጀት ዓመት ትርፍ ብር 2,179,133.05 እና በኢንሹራንስ ስም የመድን ዋስትና በማለት ከአባላት የተሰበሰበው ብር 3,155,216.56 የተጠሪዎች ድርሻ ስለሆነ ይከፈላቸው በማለት የተሰጠ ውሳኔ አለመሆኑን ነው።
በመሆኑም የማሕበሩ የ2003 ዓ.ም በጀት ዓመት ትርፍ ብር 2,179,133.05 እና በኢንሹራንስ ስም የመድን ዋስትና በማለት ከአባላት የተሰበሰበው ብር 3,155,216.56 በተመለከተ አፈጻጸሙ ሉቀጥል የሚገባው ተጠሪዎች ከዚህ ገንዘብ ውስጥ ያላቸው ድርሻ በቅድሚያ በሂሳብ ባለሙያ ተሰልቶ እና ተለይቶ እንዱቀርብ ከተደረገ በኋላ ተገቢ የሆነ የአፈጻጸም ትዕዛዝ ላሰጥበት የሚገባ ሆኖ አግኝተናዋል። የስር ፍ/ቤት ጉዲዩን በዚህ አግባብ በማየት ፍርደን በውሳኔ መሰረት ማስፈጸም ሲገባው ውሳኔ ያረፈበት ጠቅላላ ገንዘብ የተጠሪዎች ድርሻ እንደሆነ በመቁጠር የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በግልግል ዳኞች ውሳኔ መሰረት ለተጠሪዎች ብር 5,361,749.61 ወጪ አድርጎ እንዱከፍላቸው በማለት ትዕዛዝ መስጠቱ፤ይግባኙ የቀረበለት ፍ/ቤትም ይህንኑ ሳያርም መቅረቱ ስለፍርድ አፈጻጸም የተደነገጉትን የሥነ-ሥርዓት ሕጉ ድንጋጌዎችን ያላገናዘበ እና መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ. ጥር 25 ቀን 2009 ዓ.ም የሰጠው የአፈጻጸም ትዕዛዝ፤ይህንኑ ትዕዛዝ በማጽናት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. ጥቅምት 09 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥሕ/ቁ 348/1 መሰረት ተሻሽሎል።
የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በግልግል ዳኞች ውሳኔ መሰረት ለተጠሪዎች ብር 5,361,749.61 ወጪ አድርጎ እንዱከፍላቸው በማለት የተሰጠው የአፈጻጸም ትዕዛዝ ተሽሯል። ከዚህ ውጪ የተሰጠው የአፈጻጸም ትዕዛዝ አልተነካም።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በቂርቆስ ክፍለከተማ አስተዲደር በሕብረት ሥራ ማሕበራት ማደራጃ በሽምግልና ዲኝነት ታይቶ ታሕሣስ 28 ቀን 2009 ዓ.ም የማሕበሩ የ2003 ዓ.ም በጀት ዓመት ትርፍ ብር 2,179,133.05 እና በኢንሹራንስ ስም የመድን ዋስትና በማለት ከአባላት የተሰበሰበው ብር 3,155,216.56 አስመልክቶ በሰጠው ውሳኔ መሰረት ከላይ በፍርድ ሐተታው ላይ በተገለጸው መንገድ ተጠሪዎች ሉከፈላቸው የሚገባ ድርሻ ተለይቶ እንዱቀርብለት በማድረግ ፍርደን እንዱያስፈጽም በማለት በፍ/ብ/ሥ/ስ/ሕ/ቁ 343/1 መሰረት ጉዲዩ ተመልሶለታል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ግራቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።
No topics extracted.