አንድ ሰው የከተማን ቦታ በሉዝ ስለመያዝ የወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 ከመውጣቱ በፉት የይዞታ ማረጋገጫ እንዱሰጠው ጠይቆ የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ የቦላ ክ/ከተማ አስ/የመሬት ልማት እና www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XL እንዱሰጠው ውሳኔ ያገኘው አዋጁ በስራ ላይ በነበረበት ጊዜ ከሆነ የውሳኔው አፈፃፀም ሉቀጥል የሚገባው በአዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 37/1 መሰረት ሳይሆን በአዋጁ አንቀጽ 6/3/ በሉዝ ስሪት መሰረት ስለመሆኑ ማናጅመንት ጽ/ቤት
No summary available.
መስከረም 28 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች:- የቦላ ክፍለ ከተማ አስተዲደር የመሬት ልማት እና ማኔጅመንት ጽ/ቤት ተጠሪ፡- አቶ ደገፈ ምሰኔ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ የአፈጻጸም ክርክርን የሚመለከት ነው።
ለአፈጻጸሙ መነሻ የሆነው ፍርድ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.
አመልካች ለተጠሪው የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ አዘጋጅቶ እንዱሰጣቸው በማለት የሰጠው ውሳኔ ነው። የአሁን ተጠሪ ይህን ውሳኔ መነሻ በማድረግ ለከፈቱት የአፈጻጸም ክስ አመልካች በሰጠው መልስ ካርታው ሉሰጣቸው የሚገባው በአዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት ወደ ሉዝ ስሪት በማስገባት በመሆኑ ተጠሪ ሉከፍለት የሚገባ ክፍያ አለ በማለት ገልጿል። ተጠሪ በበኩላቸው ጉዲዩ ሳይፈጸም የቆየው በአመልካች ችግር መሆኑን እና ከአዋጁ በፉት የተጀመሩ ጉዲዮች በቀድሞ ሕግ መሰረት ሉስተናገደ የሚገባ መሆኑን በመግለጽ ተከራክረዋል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
አፈጻጸሙን የመራው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በግራቀኙ መካከል ያለውን የአፈጻጸም ክርክር መርምሮ ተጠሪ በተለያየ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 721/2004 ከመውጣቱ በፉት አመልካች የይዞታ ማረጋገጫ እንዱሰጣቸው የጠየቁ መሆኑን እና ሉፈጸምላቸው እንዲልቻለ በመ. ከተሰጠው ውሳኔ መገንዘብ የሚቻል በመሆኑ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታው ሉሰጣቸው የሚገባው በአዋጁ አንቀጽ 6 መሰረት ሳይሆን በአንቀጽ 37/1/ መሰረት ነው ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም ይግባኙ የቀረበለት ፍ/ቤት ግራቀኙን አከራክሮ የስር ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ አጽንቷል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም ሲሆን ይዘቱም፡- ተጠሪ ካርታ የወሰደበት ጊዜ እንጂ የጠየቁበት ጊዜ ወደ ሉዝ ስሪት ገብተው የሚስተናገደበትን ጊዜ የማይወስን መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የካርታ መስተንግድ ጠየቅኩ ያለበት ጊዜ በአዋጅ ቁጥር 2001 ጊዜ ሲሆን በዚህ ወቅት አዋጅ ቁጥር 272/94 እና የከተማ አስተዲደር መመሪያ ቁጥር 1/94 በሰነድ አልባ የሚስተናገደ አካላት ወደ ሉዝ ስሪት ስለሚገቡበት ሁኔታ እና የካርታ መስተንግድ ስለሚያገኙበት አግባብ የተደነገገ ሆኖ ሳለ የስር ፍ/ቤቶች ይህን አልፈው ተጠሪ ያለ ሉዝ ክፍያ እና ስሪት ካርታ እንዱሰጣቸው የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ ከአዋጅ ቁጥር 721/2004 አተገባበር አኳያ ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዚህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል። ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የተጠሪ መልስ ይዘት በአጭሩ፡- አመልካች የገዛሁት እና ውለ ተመዝግቦ ማስረጃ እንዱሰጠኝ የጠየቅኩት ንብረት ሰነድ አልባ አይደለም፤ቤቱ በፍቃድ እና በፕላን የተሰራ እና በሻጭ ስም የተመዘገበ ነው፤አመልካች መስሪያ ቤት ጉዲዩ እንዲይፈጸም በማድረግ ሉዝ እስኪታወጅ አቆይቶታል፤ጊዜው የተራዘመው በአመልካች ጥፊት እንጂ በተጠሪ ጥፊት አይደለም፤አመልካች ውለን ያስገባሁት እና እንዱመዘገብልኝ የጠየቅኩት ከአዋጁ በፉት ስለሆነ ሉፈጸምልኝ የሚገባው ውለን ባስገባሁበት ወቅት በነበረው ሕግ መሰረትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ነው በማለት መልስ ሰጥተዋል። አመልካችም የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። እኛም እንዱጣራ የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረነዋል።
ተጠሪ ንብረቱ በስማቸው ተመዝግቦ የባለቤትነት ማስረጃ እንዱሰጣቸው በማለት በአመልካች ላይ ክስ ያቀረቡት በመስከረም ወር 2008 ዓ.ም መሆኑን፤ጉዲዩ የቀረበለት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ. በሰጠው ውሳኔ ተጠሪ ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ ይፈጸምልኝ በማለት ሲመላለሱ የቆዩ በመሆኑ አመልካች ለተጠሪው የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ አዘጋጅቶ እንዱሰጣቸው በማለት ውሳኔ የሰጠ ቢሆንም ተጠሪ በየትኛው ሕግ መሰረት ሉስተናገደ እንደሚገባ በውሳኔው ላይ ለይቶ ያላስቀመጠ መሆኑን፤ተጠሪ ይህንኑ ውሳኔ መሰረት በማድረግ የአፈጻጸም ክስ የከፈቱ መሆኑን እና የስር ፍ/ቤቶችም ተጠሪ ሉስተናገደ የሚገባው በአዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 37/1/ መሰረት ነው በማለት የአፈጻጸም ትዕዛዝ የሰጡ መሆኑን ከክርክሩ ሑደት መገንዘብ ችለናል።
የከተማን ቦታ በሉዝ ስለመያዝ የወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 6/3 በነባር ይዞታ ላይ የሰፈረ ንብረት ባለቤትነት ከውርስ በስተቀር በማናቸውም መንገድ ለላላ ሰው ከተላለፈ ንብረቱ የተላለፈለት ሰው የቦታው ባለይዞታ መሆን የሚችለው በሉዝ ስሪት መሰረት ነው በማለት ይደነግጋል። የዚሁ አዋጅ አንቀጽ 37/1 ክልልች እና የከተማ አስተዲደሮች ቀደም ሲል ቀርበው በእንጥልጥል ላይ ያለ የከተማ ቦታ ጥያቄዎችን በሚመለከት አዋጅ ከጸናበት ቀን ጀምሮ ባለት ሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ በቀድሞ ሕግ መሰረት ውሳኔ መስጠት አለባቸው በማለት ይደነግጋል።
የስር ፍ/ቤቶች ተጠሪ አዋጅ ቁጥር 721/2004 ከመውጣቱ በፉት አመልካች የይዞታ ማረጋገጫ እንዱሰጣቸው የጠየቁ በመሆኑ እና ሉፈጸምላቸው ያልቻለ በመሆኑ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታው ሉሰጣቸው የሚገባው በአዋጁ አንቀጽ 6 መሰረት ሳይሆን በአንቀጽ 37/1 መሰረት ነው ከሚል መደምደሚያ ላይ የደረሱ ቢሆንም ተጠሪ አስተዲደሩwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ጥያቄዬን አልተፈጸመልኝም በማለት በመደበኛው ፍ/ቤት ክስ ያቀረቡ በመሆኑ የተጠሪ ጉዲይ ከአስተዲደሩ እጅ መውጣቱን የሚያሳይ እንጂ በአዋጁ አንቀጽ 37/1 በተገለጸው አግባብ ቀደም ሲል ቀርቦ በእንጥልጥል ላይ እንደነበረ ሉወሰድ የሚገባ ሆኖ አላገኘነውም።
በልላ በኩል ተጠሪ ክስ ያቀረቡት አዋጅ ቁጥር 721/2004 ከወጣ በኋላ በ2008 ዓ.ም ሲሆን ጉዲዩ የቀረበለት ፍ/ቤት ውሳኔ የሰጠውም ተጠቃሹ አዋጅ በስራ ላይ እያለ በመሆኑ የተጠሪ ጉዲይ ሉስተናገድ የሚገባው በአዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 37/1 መሰረት ሳይሆን በአዋጁ አንቀጽ 6/3 በሉዝ ስሪት መሰረት ነው። የስር ፍ/ቤቶችም ጉዲዩን በዚህ አግባብ በማየት መወሰን ሲገባቸው ተጠሪ ሉስተናገደ የሚገባው በአዋጁ አንቀጽ 37/1 መሰረት ነው በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ. መጋቢት 11 ቀን 2009 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. ጥቅምት 16 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥሕ/ቁ 348/1 መሰረት ተሽሯል።
ከላይ በፍርድ ሐተታው ላይ በተገለጸው ምክንያት አፈጻጸሙ ሉቀጥል የሚገባው በአዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 37/1 መሰረት ሳይሆን በአዋጁ አንቀጽ 6/3 በሉዝ ስሪት መሰረት ነው ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ግራቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
ጥር 17 ቀን 2010 ዓ.ም በመዝገቡ የተሰጠው የዔግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ይጻፍ