ባልና ሚስት በጋብቻ ዉስጥ ያፈሩት ቤት ፍቺን ተከትል እንዱከፊፈለ ዉሳኔ ተሰጥቶ በአፈጻጸም ሂደት አንደኛው ወገን ድርሻ ከፍል ለማስቀረት የጠየቀና የተወሰነ ገንዘብ ብቻ ይዞ ቀርቦ ቀሪዉን ለመክፈል ጊዜ ከመጠየቅ በቀር ግዥዉን ለመፈጸምና የቅድሚያ ግዥ መብቱን በጊዜው ሳይጠቀም ከቀረ የቅድሚያ ግዥ መብቱ ሉጠበቅ የሚችልበት አግባብ የላለ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ስ/ሕ/ቁ 430(1)
No summary available.
መስከረም 22 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ኃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች:- ወ/ሮ እድገት ፍጊ - ጠበቃ መሐመድ ሲራጅ ቀረቡ ተጠሪ፡- ም/ኢ/ር አሻግሬ ወ/ማሪያም - አልቀረቡም።
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዚህ ሰበር ክርክር መነሻ የሆነው አፈጻጸምን የሚመለከት ጉዲይ ሲሆን የተጀመረው በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል በየም ልዩ ወረዲ ፍርድ ቤት ነው። በግራ ቀኙ መካከል የነበረዉ ጋብቻ በፍቺ መፍረሱን ተከትል የነበራቸዉ ቤት ግምቱ ብር 53,000 ሆኖ ከቀረበ በኃላ ተጠሪ ብር 2000 ጨምሮ በብር 55,000 ለማስቀረት የጠየቀ ሲሆን አመልካች በበኩላቸዉ በብር 60,000 ለማስቀረት ጠይቀዉ ሁለቱም ገንዘብ ለማምጣት በሚል ሄደዉ ተጠሪ ገንዘብ ይዞ ቢመለስም አመልካች ሳይቀርቡ ቀርተዋል። ሀራጅ ጨረታ ወጥቶ በሁለተኛዉ ጨረታ መ/ር አብነት ወልዳ በብር 54,184 ብር ያሸነፈ ሲሆን ተጠሪ አመልካች ከፍዬ አስቀራለሁ ባለት መሰረት ድርሻዉን ብር 30,000 በአንድ ጊዜ ከፍለዉ የሚያስቀሩ ቢሆን የማይቃወም መሆኑን የገለጸ ሲሆን አመልካችwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ብር 12,000 ይዘዉ መቅረባቸዉንና ልጆች ስላሎቸዉ ቀሪዉን ለመክፈል ጊዜ እንዱሰጣቸዉ በመጠየቅ ተከራክረዋል።
የስር ፍ/ቤት ጉዲዩን መርምሮ ግራ ቀኙ ያቀረቡት የቅድሚያ ግዥ መብት የሕግ ድጋፍ የለዉም በማለት የጨረታ አሸናፉ የሆነዉ መ/ር አብነት ወልዳ ብር 54,184 ከፍል ቤቱን እንዱረከብ የአፈጻጸም ትዕዛዝ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ የአፈጻጸም ትዕዛዝ ቅር ተሰኝተዉ ቅሬታ በየደረጃዉ ላለ ፍ/ቤቶች ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኘም። ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ዉሳኔ አመልካች ቅር በመሰኘታቸዉ ነው።
አመልካች ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ይዘት፡- በወረዲዉ ፍ/ቤት ትዕዛዝ ማዘጋጃ ቤት መጋቢት 04 ቀን 2006 ዓ.ም በባለሙያ ገምቶ ያቀረበዉ ግምት 38,000 ሲሆን በቀጠሮ ከተጠሪ ድርሻ ዉስጥ 12,000 ይዤ ብቀርብም ተጠሪ ሳይቀርብና እንደፍርደ እንዱፈጸምለት ሳይጠይቅ ከሰባት ዓመት በኃላ እንሰትና የጓሮ አትክልት አልምቼበት እያለሁ በ2010 ዓ.ም እኔ ባላወቅኩበት ሁኔታ ብር 53,000 ነዉ ተብል ተገምቶ በላዬ ላይ መሸጡ ተገቢ ባለመሆኑ የአፈጻጸም ትዔዛዙ ይሻርልኝ። አንድ መኖሪያ ቤት ያለአግባብ ሦስት ዙር መገመቱ ስህተት ነዉ። ከፍቺ በኃላ ያለማሁትን የጓሮ አትክልት በብር 816 የተገመተ ቢሆንም ሳይታሰብልኝ ቀርቷል። በአጠቃላይ በቤቴ የመኖር መብቴ እንዱከበርልኝ በቀደምትነት የመግዛት መብቴ ይጠበቅልኝ የሚል ነዉ።
የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ የጨረታ መነሻ ዋጋ ከታወቀ በኃላ ግራቀኙ ይሸጥ የተባለዉን ንብረት ይህንኑ ዋጋ በማጣቀስ ያስቀሩት እንደሆነ የቅድሚያ መብት መብታቸዉን በማረጋገጥ ረገድ ስርዓቱን ከተከተለ በኃላ የቅድሚያ መብት ላሰጥ አይገባም በሚል የደረሰበት መደምደሚያ አግባብነት ከሁለም በላይ ንብረቱ የባልና ሚስት የጋራ ሀብት ከመሆኑ እና አመልካች ከሐራጅ መሸጫ ዋጋ የተሻለ ዋጋ ላቅርብ እያለ ጥያቄያቸዉ የመታለፈን አግባብነት ከፍ/ብ/ሕ/ቁ 430 ድንጋጌ አፈጻጸም አንጻር ለማየት ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል የተባለ ሲሆን ግራ ቀኙ መልስና የመልስ መልስ በጽሁፍ በማቅረብ ተከራክረዋል።
የተጠሪ መልስ ይዘት፡- በሕጋዊ መንገድ በማዘጋጃ ባለሙያ ተገምቶ፤ የጓሮ አትክልት ግምት ብር 816 መሆኑንን የአመልካችም መብት በቅድሚያ ተጠብቆላት እኔን ድርሻ ሰጥታ እንድትጠቀም ቢፈቀድላትም በቀጠሮ ሳትቀርብ ቀርታለች። በስር ፍ/ቤት አመልካች የእኔን መብት በመጋፊቷና በተደጋጋሚ መሰናክል በመፍጠሯ በሀራጅwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ጨረታ ቤቱ ተሸጦ ድርሻዬ ብር 26,500.0 ተረክቤ የእሷን ድርሻ በሥር ፍ/ቤት ተቀምጦላት እያለ ባለቀ ጉዲይ ያቀረበችዉ ቅሬታ ተገቢነት የላለዉ በመሆኑ የሰበር አቤቱታዋ ዉድቅ ይደረግልኝ የሚል ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥና የግራ ቀኙ ክርክር ከላይ የተመለከተዉን የሚመስል ሲሆን ከስር ፍ/ቤት ዉሳኔ እና ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል ተብል ከተያዘዉ ጭብጥ ጋር በማገናዘብ መርምረናል። መርምረን እንደተረዲነዉ ግራ ቀኙ በጋራ በጋብቻ ዉስጥ ያፈሩትን ቤት ፍቺን ተከትል እንዱከፊፈለ ዉሳኔ የተሰጠ ሲሆን በአፈጻጸም ሂደት ቤቱ በማዘጋጃ ቤት ብር 51,8161 ተገምቶ ቀርቧል። ተጠሪ ብር 2,000 ጨምሮ ለመግዛትና የአመልካችን ድርሻ ከፍል ለማስቀረት የጠየቀና ገንዘብ ይዞ የቀረበ ሲሆን አመልካች በብር 60,000 ለማስቀረት ጠይቃ ተጠሪም ፈቃደኛ ቢሆንም አመልካች ብር 12,000 ይዛ በመቅረብ ቀሪዉን ለመክፈል ጊዜ ከመጠየቅ በቀር ግዥዉን ለመፈጸምና የቅድሚያ ግዥ መብት ልትጠቀም አልቻለችም። ከዚህም በኃላ የስር ፍ/ቤት ቤቱን ሁለት ጊዜ ጨረታ ወጥቶ ጨረታዉን በብር 53,000 ያሸነፈዉ መ/ር አብነት ወልዳ ገንዘቡን ከፍል ቤቱን በአፈጻጸም እንዱረከብ ትዕዛዝ ተሰጥቷል። ተጠሪ ከሽያጭ ገንዘቡ ድርሻዉን የወሰደ ሲሆን አመልካች ድርሻዋን ባለመዉሰዶ በአደራ በመስሪያ ቤቱ ግዥና ፊይናንስ ክፍል እንዱቀመጥ ተደርጓል። አመልካች አጥብቃ የምትከራከረዉ በ2003 ዓ.ም በማዘጋጃ ቤት ተገምቶ በቀረበዉ ግምት መሰረት ብር 12,000 ለመክፈል ይዤ ቀርቤና ላላዉን በሂደት ለመክፈል ጠይቄ ባለሁበት ከቤቱ ተፈናቅዬ ቤቱን ገዥዉ እንዱረከብ ትዕዛዝ መሰጠቱ ስህተት ነዉ በሚል ነዉ።
በመሰረቱ አመልካች ክርክር ያስነሳዉን ቤት የቅድሚያ ግዥ መብት ጠይቃ አልተከለከለችም። እንዱሁም በፍ/ብ/ሥ/ስ/ሕ/ቁ 430(1) መሰረት በሀራጅ ጨረታዉ ለመሳተፍ ጠይቃ አልተከለከለችም። አመልካች ለመግዛት በጠየቀችዉ ብር 60,000 እንድታስቀር ተጠሪ ስምምነቱን ገልጾ የነበረ ሲሆን አመልካች የተጠሪን ድርሻ ለመክፈል ይዛ የቀረበችዉ ገንዘብ ብር 12,000 ብቻ በመሆኑ ቤቱን ልታስቀር አልቻለችም። ጊዜ ተሰጥቶኝ በሂደት ልክፈል የሚለዉ ክርክርም ቢሆን ባለገንዘብ በሆነዉ በተጠሪ ፈቃድ ላይ የሚመሰረት በመሆኑ ጊዜ እንዱሰጥ ሉገደድ አይችልም። በልላ በኩል አመልካች ግምት መክፈል የነበረብኝ በ2003 ዓ.ም በነበረዉ ግምት ነዉ የሚለዉ ክርክሯም የሕግ መሰረት የለዉም። ምክንያቱም ፍርደ እስካልተፈጸመ ድረስ ቤቱ በአመልካች እጅwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ቢቆይም የጋራ ሀብት በመሆኑ በቆይታ የሚመጣዉ የግምት ጭማሪ ሁለቱንም የሚጠቅም በመሆኑ ነዉ።
ላላዉ አመልካች ከቤቱ ልፈናቀል አይገባም በማለት ብትከራከርም ቤቱን በሀራጅ ጨረታ ተሳትፍ ግዥ የፈጸመዉ ተጠሪ ሳይሆን መ/ር አብነት ወልዳ በመሆኑ ገዥዉ ተከራካሪ ባልሆነበትና በተጠሪነት ወደ ክርክሩ እንዱገባ ባልተደረገበት ሁኔታ የሀራጅ ሽያጩ ሉሰረዝ ወይም የአመልካች የቅድሚያ ግዥ መብት ሉጠበቅ የሚችልበት አግባብ የለም።
ስለሆነም አመልካች አቤቱታ ተገቢነት የለዉም።
ሲጠቃለል አመልካች ካቀረቡት የሰበር አቤቱታ አንጻር የስር ፍ/ቤት ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል ለማለት አልተቻለም። በመሆኑም የሚከተለው ውሳኔ ሰጥተናል።
1ኛ. በየም ልዩ ወረዲ ፍ/ቤት በመ/ መስከረም 24 ቀን 2010 ዓ.ም ተሰጥቶ፤ በከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ጥቅምት 08 ቀን 2010 ዓ.ም በተሰጠ ትዕዛዝ እና በደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ታሕሳስ 24 ቀን 2010 ዓ.ም በተሰጠ ትዕዛዝ የጸናዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ጸንቷል።
2ኛ. በስር ፍ/ቤት የተጀመረዉ አፈጻጸም ለጊዜዉ ታግድ እንዱቆይ ጥር 10 ቀን 2010 ዓ.ም የተሰጠዉ የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ይጻፍ።
3ኛ. በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል። መዝገቡ ተዘግቷል፣ ወደ መዝገብ ቤት ተመላሽ ብለናል።
No topics extracted.