አንድ ክርክር ያስነሳ ንብረት በአፈፃፀም ሂደት በጨረታ ከተሸጠና ገንዘቡም ለፍርድ ባለገንዘብ ከተከፈለ በኃላ በጨረታዉ ሂደት ጨረታዉን ሉያስፈርስ የሚችል ጉድለት ካልተገኘ እንዱሁም ንብረቱ ለ3ኛ ወገን እንዲይተላለፍ የተሰጠ ዔግድ በሕግ አግባብ ያልተመዘገበ መሆኑ የአብክመ ገቢዎች ባለስልጣን ዐ/ሕግ እና አቶ መስፍን ጥላሁን www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XXXIX የቀዲሚነት መብትን ለመጠቀም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 418 መሰረት የሚቀርብ የመቃወም አቤቱታ ተቀባይነት የላለው ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 418፣426፣445
No summary available.
ቀን-ሕዲር 26 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ኃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች:- የአብክመ ገቢዎች ባለስልጣን ዐ/ሕግ ተጠሪ፡- አቶ መስፍን ጥላሁን ይህ መዝገብ አመልካችና ተጠሪ አቶ በላይ አካለ ከሚከራከሩበት የሰ/መ/ ጋር ከአንድ የስር ፍ/ቤት ዉሳኔ የተነሱ ጉዲዮች በመሆናቸዉ መዝገቦቹ ተጣምረዉ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዚህ ሰበር ክርክር መነሻ የሆነው የአፈጻጸም ጉዲይ ሆኖ የተጀመረዉ በአማራ ክልል በባህር ዲርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት ነዉ። በዚሁ ፍ/ቤት ተጠሪ የፍርድ ባለመብት፤ አቶ ነጋሹ ዉደ እና ሻ/ል ክ/ጎርጊስ ዘነበ የፍርድ ባለዔዲዎች፤ አቶ በላይ አካለ የጨረታ አሸናፉ ሲሆኑ የአሁኑ አመልካች ደግሞ የመቃወም አመልካች ነበር።
አመልካች ያቀረበዉ መቃወሚያ ይዘት፡- በፍርድ ባለዔዲዎች ስም የሚገኘዉ የድንጋይ ወፍጮ ወይም ክሬሸር የፍርድ ባለዔዲዎች ባልከፈለት የግብር ዔዲ ብር 2,324,972.07 ምክንያት በደብዲቤ ቁጥር ገቢ 1214/01/06 መጋቢት 22 ቀን 2006 ዓ.ም እና በቁጥር ዘል/ቀመ/2801/06 በቀን 23/07/06 ዓ.ም በተጻፈ ደብዲቤ በክልለ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 76/94 አንቀጽ 78(2) ለአመልካች በተሰጠዉ ስልጣን ዔግድ ተሰጥቶበት እያለ ወፍጮዉ የሚገኝበት ዘንዘልማ ቀበላ ሆኖ ሳለ ተጠሪ ፍ/ቤቱን በማሳሳት ንብረቱ ለማይገኝበት ለሕዲር 11 ቀበላ ንብረቱ በጨረታ እንዱሸጥ መደረጉ ሆን ተብል በመሆኑ ጨረታዉ ተሰርዞ ንብረቱን እንድንረከብ፤ ንብረቱ የድንጋይ ወፍጮwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
እንደመሆኑ የሽያጭ ጨረታዉም ሆነ የዔግድ ትዔዛዙ በግልጽ ማስታወቂያ ለሕዝብ ይፊ ያልተደረገና የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 414(2) እና 425(2) ድንጋጌዎችን መሰረት ያላደረገ በመሆኑ ጨረታዉ ተሰርዞ በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 76/94 አንቀጽ 81(1) መሰረት አመልካች የቀደምትነት መብት ያለዉ በመሆኑ ንብረቱን እንድንረከብ ይወሰንልን የሚል ነዉ።
ተጠሪ በሰጡት መልስ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 445 መሰረት ጨረታ እንዱፈርስ ጥያቄ መቅረብ የሚችለዉ በአሻሻጡ ስርዓት ላይ ግዙፍ የሆነ ጉድለት ወይም ትክክለኛ ያልሆነ የማጭበርበር ተግባር ተፈጽሞ ሲገኝ ሲሆን ይህ ባልሆነበት የቀረበዉ ጥያቄ ተቀባይነት የለዉም። አቤቱታዉ መቅረብ የነበረበት ንብረቱ በጨረታ ከመሸጡና ለሦስተኛ ወገን ከመተላለፈ በፉት ሆኖ ሳለ ከተሸጠ በኃላ የቀረበዉ አቤቱታ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 418 ድንጋጌ አንጻር ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከራክሯል።
የጨረታዉ አሸናፉ በበኩለ ጨረታዉን በሕጋዊ መንገድ ተወዲድሬ አሸንፋ የጨረታዉ ዉጤት ቀርቦ በችልት ጨረታዉ ጸድቆ ገንዘቡን በሙለ ለፍርድ ባለመብት ከፍዬ የድንጋይ ወፍጮዉን እንድረከብ ትዕዛዝ ተሰጥቶበታል። ይህ በሆነበት ጨረታዉ እንዱሰረዝ የቀረበዉ አቤቱታ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 418 እና 445 ድንጋጌዎችን ያላገናዘበ በመሆኑ ዉድቅ ይደረግልኝ የሚል ነዉ።
የስር ፍ/ቤት የግራቀኙን ክርክር መርምሮ የድንጋይ ወፍጮ ወይም ክረሸሩ ከአለበት ቦታ ተነቅል ገዥዉ አካል ወደ ፈለገበት ቦታ ሉወሰድ የሚችል በመሆኑ የሚንቀሳቀስ ንብረት ነዉ፤ አመልካች አቤቱታዉን ያቀረቡት ንብረቱ በጨረታ ከተሸጠ በኃላ በመሆኑና ንብረቱ የሚገኝበትን የዘንዘልማ ቀበላን በበላይነት የሚያስተዲድረዉ የሕዲር 11 ክፍለ ከተማ በመሆኑ የጨረታዉ አካሄድ ተገቢ በመሆኑ ጨረታዉ ሉፈርስ የሚችልበት የሕግ አግባብ የለም በማለት የአመልካችን መቃወሚያ ዉድቅ በማድረግ ዉሳኔ ሰጥቷል። አመልካች ይህን ዉሳኔ በመቃወም ባቀረበዉ ይግባኝ መነሻነት ጉዲዩን የተመለከተዉ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ግራ ቀኙን ካከራከረ በኃላ መርምሮ ክረሸሩ በመሬት ላይ የተተከለ በመሆኑ የማይንቀሳቀስ ንብረት መሆኑን፤ ይህ ከሆነ ደግሞ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 424(2) እና 454(2) መሰረት የጨረታዉ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከ30 ቀን ባላነሰ ጊዜ ሉነገር የሚገባዉ መሆኑን በመግለጽ ጨረታዉwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 445 መሰረት ጉድለት ያለበት በመሆኑ ጨረታዉ ፈራሽ ነዉ፤
ክሬሸሩ የድንጋይ ወፍጮ መቼና በማን እንደተከበረ፣ ማን ምን ያህል ባለገንዘብ ነዉ የሚለትን አጣርቶ እንዱወስን ጉዲዩን ለስር ፍ/ቤት በመመለስ ወስኗል። በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ተጠሪ ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ የተመለከተዉ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ግራቀኙን ካከራከረ በኃላ መርምሮ ክሬሸር የድንጋይ ወፍጮ የመኪና ዓይነት በመሆኑ ተንቀሳቃሽ ንብረት እንጂ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለመሆኑ ለ15 ቀናት የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ እንዱቆይ ተደርጎ የተሸጠና የፍ/ብ/ስ/ሥ/ሕ/ቁ 426 ድንጋጌን ያሟላ በመሆኑ ጨረታዉ ሉፈርስ አይገባም በማለት የክልለን ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ዉሳኔ በመሻር እና የከፍተኛዉን ፍ/ቤት ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ውሳኔ ላይ አመልካች ቅር በመሰኘታቸዉ ለማስለወጥ ነው።
አመልካች ያቀረበዉ የሰበር አቤቱታ ይዘት፡- የድንጋይ ወፍጮዉ ተተክል የሚሰራዉና የሚገኘዉ በዘንዘልማ ቀበላ ሆኖ እያለ እና ይህ ንብረትም አስቀድሞ በግብር ዔዲ ተከብሮ እያለ ተጠሪ ፍ/ቤቱን በማሳሳት ንብረት የማይገኝበትና ገቢ ተቋሙ ሉያዉቅ በማይችልበት ሕዲር 11 ቀበላ ጨረታ እንዱወጣ በማድረግ ጨረታዉን እንዱከናወን ያደረጉ መሆኑ እየታወቀ ሁለቱ ቀበላዎች ራሳቸዉን የቻለ ቀበላዎች ሆነዉ እያለ በአንድ ቀበላ ሥር እንዲለ ተደርጎ ጨረታዉ ሉፈርስ አይገባም ያለበት አግባብ የሥነ-ሥርዓት ሕጉን የተከተለ አይደለም። ክሬሸሩ ከመሬት ተተክል የሚሰራ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሆኖ እያለ እንደሚንቀሳቀስ ንብረት ይቆጠራል ተብል መወሰኑ ስህተት ነዉ። ስለሆነም ጨረታዉ ሕግን ያልተከተለ በመሆኑ ጨረታዉ እንዱፈርስ ይወሰንልኝ የሚል ነዉ።
የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች በስር ፍ/ቤት አከራካሪዉን ክሬሸር ወፍጮ አስመልክቶ የቅድሚያ መብት አለኝ ሲል ያቀረበዉ መቃወሚያ ጉዲዩ በጨረታ ተሽጦ የተፈጸመ ነዉ ተብል ዉድቅ የመደረጉን አግባብነት የአፈጻጸም ንብረት የመሸጥ ስነ ስርዓት መጠበቁንና የተሸጠዉ ንብረትስ የሚንቀሳቀስ ነዉ ወይስ የማይንቀሳቀስ ነዉ የሚለዉን ነጥብ በመለየት ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 424-426 እና 445 አንጻር ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል የተባለ ሲሆን ግራቀኙ መልስና የመልስ መልሰ በጽሁፍ በማቅረብ ተከራክረዋል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ተጠሪ የሰጡት መልስ ይዘት፡- ክሬሸር የድንጋይ ወፍጮ ድንጋይ በሚገኝበት ቦታ እየተዘዋወረ የሚሰራ ነዉ። ወፍጮዉም ለሥራዉ ሲባል ከመሬቱ ጋር የተያያዘ ቢሆንም ከቦታ ቦታ ለማዘዋወር ወፍጮዉ ሳይጠፊ እና አጉል ሳይሆን ምንም ብልሽት ሳይደርስበት ከመሬት ለመለያየት የሚችል ማሽን በመሆኑ ተንቀሳቃሽ ንብረት እንጂ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1132(2) መሰረት የማይንቀሳቀስ ንብረት ነዉ የሚባል አይሆንም። በልላ በኩል የድንጋይ ወፍጮዉ በሞተር የሚሰራ በመሆኑ እንደመኪና እና የኮንስትራክሽን ማሽኖች ልዩ ተንቀሳቃሽ ንብረቶች ምዝገባ የሚያስፈልገዉ ቢሆንም ጨረታዉ ሲሸጥ በተንቀሳቃሽ ንብረት ጨረታ ስርዓት የሚከናወን ነዉ። ወፍጮዉ የሚገኘዉ ባሕርዲር ከተማ ሕዲር 11 ክ/ከተማ በመሆኑ ለሕዲር 11 ቀበላ ትዕዛዝ ተሰጥቶ ታዛቢ ፖሉስ ባለበት ጨረታዉ የተካሄደ በመሆኑ ስህተት የለዉም። ቀበላዉ ትዔዛዙ ሲደርሰዉ ንብረቱ በክልል ስር አይገኝም በማለት አላስፈጽምም አለማለቱ ንብረቱ በክልለ ስር የሚገኝ መሆኑን ያረጋግጣል። እንዱሁም በጨረታዉ የተሸጠዉ ንብረት የሚገኝበትን ቦታ ስህተት ተፈጽሞበታል የሚለዉ ጉልህ የሆነ የማታለል ወይም የማታለል ተግባር መፈጸሙን የሚያረጋግጥ ባለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 445 መሰረት ጨረታዉን ሉፈርስ የሚያስችል ምክንያት አይደለም። በመሆኑም የአመልካች አቤቱታ ዉድቅ ተደርጎ የስር ፍ/ቤት ዉሳኔ ይጽናልኝ የሚል ነዉ። አመልካች በሰጠዉ የመልስ መልስ አቤቱታዉን በሚያጠናክር መልኩ ተከራክሯል።
በመዝገብ አመልካች ያቀረበዉ አቤቱታም ሆነ ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል ሲባል ለማጣራት የተያዘዉ ነጥብ ተመሳሳይ ሲሆን የጨረታዉ አሸናፉ ነዉ የተባለትና በዚህ መዝገብ ተጠሪ የሆኑት አቶ በላይ አካል የሰጡት መልስ የድንጋይ ወፍጮዉ ራሱን ችል ከመሬቱ ጋር ተለያይቶ አገልግልት መስጠት የሚችልና ከመሬቱ ጋርም ሲለያይ አጉል የማይሆንና የማይጠፊ መሆኑን አረጋግጦ የክልለ ሰበር ሰሚ የሰጠዉ ዉሳኔ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1132(2) ድንጋጌን ያገናዘበ ነዉ። አመልካች በቅድሚያ መብት ተጠቃሚ ላሆን የሚችለዉ ከሚሸጠዉ ንብረት ላይ ገንዘቡን በማግኘት ወይም ንብረቱን ቀድሞ በመሸጥ እንጂ ንብረቱ ተሸጦ ለላልች ባለመብቶች ከተሰጠ በኃላ የቅድሚያ መብቱን የጨረታ ማፍረሻ ምክንያት ሉያደርገዉ አይችልም። ዘንዘልማ ቀበላ በሕዲር 11 ክፍለ ከተማ ዉስጥ ያለ በመሆኑ አመልካች እንደሚለት በማጭበርበር የተሰራ ሳይሆን አመልካች ራሳቸዉ ዔግደን ለሚመለከተዉ አካል አለማድረሳቸዉንwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የሚያረጋግጥ ነዉ። ስለሆነም የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ዉሳኔ ይጽናልን የሚል ነዉ።
አመልካች በሰጠዉ የመልስ መልስ የሰበር አቤቱታዉን በሚያጠናክር መልኩ ተከራክሯል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተመለከተዉን የሚመስል ሲሆን ከስር ፍ/ቤት ዉሳኔ እና ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል ተብል ከተያዘዉ ጭብጥ ጋር በማገናዘብ መርምረናል። መርምረን እንደተረዲነዉ ክርክር ያስነሳዉ የፍርድ ባለዔዲ ንብረት የሆነዉ የድንጋይ ወፍጮ ወይም ክረሸር የፍርድ ባለመብትን ገንዘብ ለማስከፈል ተብል ጨረታ ወጥቶ አሸናፉዉ ከተለየና ገንዘቡን ከከፈለ በኃላ ገንዘቡ ለፍርድ ባለመብቶች ተከፍል ገዥዉ ንብረቱን እንዱረከብ ትዕዛዝ ተሰጥቶ ርክክቡ ከመፈጸሙ በፉት አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 418 መሰረት ያቀረበዉ አቤቱታ የቅድሚያ መብት ያለዉና ንብረቱን ከዚህ በፉት ያሳገደዉ መሆኑን እንዱሁም የጨረታ ሽያጩ አፈጻጸም ሥነሥርዓት ሕጉን ተከትል ማስታወቂያ ያልተነገረና ጉድለት ያለበት መሆኑን በመግለጽ ጨረታዉ ይፍረስ የሚል ነዉ። በተለይ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ጨረታዉ ጉድለት የለበትም ለማለት የሰጠዉ ምክንያት ክርክር ያስነሳዉ ንብረት ተንቀሳቃሽ ንብረት በመሆኑና የሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያዉ ተለጥፍ 15 ቀናት የቆየ በመሆኑ ጨረታዉ ጉድለት የላለበት በመሆኑ የሚፈርስበት ምክንያት የለም በማለት የአመልካችን አቤቱታ ዉድቅ በማድረግ ወስኗል። ከዚህ አንጻር የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ክርክር ያስነሳዉ ክሬሸር ወይም የድንጋይ ወፍጮ የሚንቀሳቀስ ንብረት ነዉ በሚል መደምደሚያ ላይ በመድረስ የጨረታ ሽያጩ ጉድለት የለዉም ማለቱ በአግባቡ ነዉ? ወይስ አይደለም?
እንዱሁም አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 418 መሰረት ንብረቱን አስቀድሞ ማሳገደንና በሕግ የቅድሚያ መብት ያለዉ መሆኑን በመግለጽ ያቀረበዉ አቤቱታ ዉድቅ ማድረጉ በአግባቡ ነዉ? ወይስ አይደለም? የሚለ ነጥቦች የዚህን ችልት ምላሽ የሚሹ አብይ ጭብጦች ናቸዉ።
ክርክር ያስነሳዉ የድንጋይ ወፍጮ ወይም ክሬሸር የተሸጠበት የጨረታ ሂደት ጉድለት አለበት ወይስ የለበትም የሚለዉን ለመመለስ በቅድሚያ ንብረቱ የሚንቀሳቀስ ንብረት ነዉ ወይስ የማይንቀሳቀስ ንብረት ነዉ የሚለዉ ምላሽ ሉያገኝ የሚገባዉ ነዉ።
በመሰረቱ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1130 እና 1132 መሰረት የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች የሚባለት መሬትና ቤት ወይም ከእነዚህ ነገሮች ጋር በግዙፍነት የተያያዘ ሆኖ የተባለዉ ነገርwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ሳይጠፊና አጉል ሳይሆን ለመለያየት የማይቻል ሲሆን መሆኑ ተደንግጓል። ከዚህና በላልች ድንጋጌዎች ከተቀመጡት ዉጭ ያለ ንብረቶች ተንቀሳቃሽ ንብረቶች መሆናቸዉ አሻሚ አይደለም።
በተያዘዉ ጉዲይ ክርክር ያስነሳዉ ክሬሸር ወይም የድንጋይ ወፍጮ ግብዓት ባለበት ቦታ እየተንቀሳቀሰና እየተተከለ ድንጋይ የሚፈጭ ሲሆን ከሚፈጨዉ የድንጋይ ቦታ ጋር ሳይነጣጠል ተተክል ካለበት ቦታ ወይም ጥሬ ዔቃ የመጠቀም መብት ጋር ካልተሸጠ በቀር ራሱን ችል እስከተሸጠ ድረስ የማይንቀሳቀስ ንብረት ነዉ ልባል የሚችል አይደለም። ስለሆነም ክሬሸሩ ከተተከለበት የድንጋይ ማዉጫ ቦታ የመጠቀም መብት ጋር የተሸጠ መሆኑን የሚገልጽ ነገር በላለበት ሁኔታ የማይንቀሳቀስ ንብረት ነዉ ልባል የሚችል ባለመሆኑ በስር ፍ/ቤት ተንቀሳቃሽ ንብረት ነዉ መባለ ስህተት አይደለም።
በልላ በኩል ስለኮንስትራክሽን መሣሪያዎች ምዝገባና ቁጥጥር በወጣ አዋጅ ቁጥር 177/91 እና በአዋጁ መሰረት በሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች ቁጥጥርና ምዝገባ እንዱሁም የባለቤትነት ደብተር አሰጣጥ አስመልክቶ በወጣዉ መመሪያ አንቀጽ 3(1/ለ) መሰረት ክሬሸር እንደአስፓልት ሚክሲንግ ፕላንትና ክሬን ሁለ ከቦታ ወደ ቦታ እየተወሰደና እየተተከለ የሚሰራ ምዝገባና የባለቤትነት ደብተር የሚሰጠዉ ልዩ ተንቀሳቃሽ ንብረት መሆኑ ተመላክቷል። በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 3(2) መሰረት ከምዘገባና ቁጥጥሩ ዓላማዎች ዉስጥ አንደ መሳሪያዎቹ ለዋስትና መያዣና ለተመሳሳይ አገልግልቶች የሚዉልበትን ሁኔታ ማመቻቸት መሆኑ ተመልክቷል። ከተጠቀሱት የአዋጁና የመመሪያዉ ድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ የሚቻለዉ ክሬሸር ወደ 3ኛ ወገን እንዲይተላለፍ ወይም እንዲይሸጥ የሚታገደዉ ክሬሸሩ ለሚገኝበት ቀበላ ወይም የአስተዲደር አካል ደብዲቤ በመጻፍ ሳይሆን ክሬሸሩን ለሚመዘግበዉና የስም ዝዉዉር በማድረግ የባለቤትነት ደብተር ከሚሰጠዉ አካል ዘንድ ዔገዲዉ እንዱመዘገብ በማድረግ ነዉ።
በተያዘዉ ጉዲይ አመልካች ክሬሸሩ ለሚገኝበት ቀበላ ደብዲቤ በመጻፈ ብቻ ንብረቱ በሕግ ፉት የጸናና ንብረቱ ወደ 3ኛ ወገን እንዲይተላለፍ የሚያግድ ዔግድ ነበረበት ለማለት አይቻልም።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ከላይ ከተገለጸዉ አንጻር የድንጋይ ወፍጮዉ ወይም ክሬሸሩ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሳይሆን ልዩ ተንቀሳቃሽ ንብረት ነዉ የተባለ በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 426 መሰረት የጨረታዉ ማስታወቂያዉ ተለጥፍ ለ15 ቀናት የቆየ መሆኑ በስር ፍ/ቤቶች የተረጋገጠ በመሆኑ የጨረታዉ ሂደት ጉድለት አለበት ልባል የሚችል አልሆነም።
በልላ በኩል አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 418 መሰረት የመቃወም አቤቱታ ያቀረበዉ ንብረቱ በሀራጅ ጨረታ ከተሸጠና ገንዘቡም ለፍርድ ባለገንዘቦች ከተከፈለ በኋላ የቀረበ በመሆኑ አመልካች በክልለ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 76/94 አንቀጽ 78(2) መሰረት ያለዉን የቀዲሚነት መብት ሉጠቀም አይችልም። ስለሆነም የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የአመልካችን አቤቱታ ዉድቅ በማድረግ መወሰኑ የሚነቀፍበት በቂ ምክንያት የለም።
ሲጠቃለል ከላይ በተገለጸዉ አግባብ አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 418 መሰረት የመቃወም አቤቱታዉን ያቀረበዉ ክርክር ያስነሳዉ ክሬሸር በጨረታ ከተሸጠና ገንዘቡም ለፍርድ ባለገንዘብ ከተከፈለ በኋላ በመሆኑ፤ በጨረታዉ ሂደትም ጨረታዉን ሉያስፈርስ የሚችል ጉድለት ባለመገኘቱ እንዱሁም ንብረቱ ለ3ኛ ወገን እንዲይተላለፍ የተሰጠ ዔግድ በሕግ አግባብ ያልተመዘገበ በመሆኑ የአመልካችን አቤቱታ ዉድቅ በማድረግ የተሰጠዉ ዉሳኔ የሚነቀፍበት በቂ ምክንያት ባለመኖሩ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ለማለት አልተቻለም። በመሆኑም የሚከተለዉ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ቁ 03-61518 ጥር 28 ቀን 2010 ዓ.ም እና 03-61481 የካቲት 02 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጣቸዉ ዉሳኔዎች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ጸንተዋል።
የዚህ ፍርድ ትክክለኛ ግልባጭ ከዚህ መዝገብ ጋር ተጣምሮ ከተወሰነዉ የሰ/መ/ ጋር ይያያዝ ተብሎል።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸዉን ይቻለ። መዝገቡ ዉሳኔ ያገኘ ስለሆነ ተዘግቷል። ይመለስ።