ሥራ ላይ ባለ ህጎች መሰረት በየትኛውም ደረጃ በሚገኝ የክልል ፍርድ ቤት ታይተው የመጨረሻ ውሳኔ የተሰጠባቸው ጉዲዮች መሰረታዊ የህግ ስህተት አለባቸው በሚል ለክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት አቤቱታ በክልል ሰበር ሰሚ ችልት አልተቋቋመም፤ እንዱሁም በክልል የሰበር ስርዓት በዝርዝር ህጎች አልተቀመጠም በሚል ምክንያት ጉዲዮች በቀጥታ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ሉቀርቡ የማይገባ ስለመሆኑና ሥራ ላይ ባለት ህጎች አግባብ በክልል ሰበር ችልት መታየት ያለባቸው ስለመሆኑ የኢፋዳሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3)(ለ)፣የሐረሪ ክልል ህገ መንግስት አንቀጽ70(2)(ሀ)፣የሐረሪ ሕ/ብ/ክ/መ/ ፍርድ ቤቶችና የዳኞች አስተዲደር ጉባኤ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 3/1988፤የሐረሪ ክልል የዳኞች አስተዲደር ጉባኤ እነ ወ/ሮ አለምሸዋ አባተ አበበ እና እነ አቶ ሚሉዮን አባተ አበበ www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XXXVIII አዋጅ ቁጥር 3/1988 እና ማሻሻያ አዋጆች ቁጥር 8/1991 እና 17/1991 እንደገና ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ቁጥር 68/1999 /የፋ/ፍ/ቤቶችን አዋጅ እንደገና ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀጽ 2(1) በፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቀደም ሲል በሰ/መ/ እና ላልችም በርካታ መዛግብት ተሰጥቶ የነበረው የህግ ትርጉም በዚህ መዝገብ ውሳኔ ተለውጧል።/
No summary available.
መጋቢት 23 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡- መዓዛ አሸናፉ ሰለሞን አረዲ ተኽሉት ይመስል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነአ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራው ፀሃይ መንክር አመልካቾች፡
ጉዲዩ የቀረበው የሐረሪ ክልል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ህዲር 15 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠውን ውሳኔ የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በይ/መ/ መጋቢት 11 ቀን 2010 ዓ.ም በዋለው ችልት በመሻር ባሳለፈው ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመ በመሆኑ ጉዲዩ በዚህ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ታይቶ በክልለ ይግባኝ ሰሚ ችልት ውሳኔ የተፈፀመው ስህተት ይታረምልን በማለት አመልካቾች የሰበር አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
ከመዝገቡ መረዲት እንደሚቻለው የአሁን አመልካቾች በተጠሪዎች ላይ በክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ በሐረር ከተማ ቀበላ 09 ውስጥ የሚገኘውንና በይዞታችንwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ባቆየነው ቦታ ላይ የሰራነውን ግምቱ .00 (ስድሳ ሽህ) የሆነ ሶስት ክፍል ሰርቪስ ቤቶች ተጠሪዎችን አስጠግተናቸው እንደ ኪራይ የሚታሰብ ብር 500.00 (አምስት መቶ) እየከፈለ ይኖሩበት ነበር፤ ይሁን እንጂ በይዞታችን ላይ በገንዘባችን የሰራነውን ይህን ሶስት ክፍል ቤት ስመ ሃብት ወደራሳቸው ለማዞር እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑን ስለደረስንባቸው ቤቱን ለቀው እንዱያስረክቡን ይወሰንልን በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል። ተጠሪዎች ለክሱ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና የበኩላቸውን መከራከሪያ አቅርበዋል።
ጉዲዩን በቅድሚያ የተመለከተው የከፍተኛው ፍርድ ቤት መቃወሚያውን ውድቅ በማድረግ የግራቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ አከራካሪውን ቤት አመልካቾች በራሳቸው ይዞታ በህጋዊ የግንባታ ፈቃድ መሰረት የሰሩት ስለመሆኑ በሰውና በሰነድ ማስረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ ተጠሪዎች በቤቱና ቤቱ በተሰራበት ይዞታ ላይ ምንም ዓይነት መብት የላቸውም በማለት ተጠሪዎች ቤቱን ለቀው ለአመልካቾች እንዱያስረክቡ ወስኗል።
ተጠሪዎች ይህን ውሳኔ በመቃወም የይግባኝ ቅሬታቸውን ለሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ጉዲዩ በክልለ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለስልጣን ተጣርቶ እንዱቀርብ ካደረገና የግራቀኙን የይግባኝ ክርክር ከሰማ በኋላ ውሳኔ ሰጥቷል። በሰጠው ውሳኔ ክርክር ያስነሳው ቤትና ቦታ ከአሁን አመልካቾች ህጋዊ ይዞታ ውጪ በመሆኑና ይኸው ቦታም በመንግስት ይዞታነት ሥር ያለ በመሆኑ አመልካቾች በህጋዊ መንገድ ካርታ ተሰጥተውበት ካለው ይዞታ ውጪ በሆነ የመንግስት ይዞታ ላይ በጨረቃ ቤትነት ተገንብቶ ባለው ሰነድ አልባ ቤት ላይ ክስ የማቅረብ መብት የላቸውም በማለት የስር ፍርድ ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ ሽሯል።
የሰበር አቤቱታው በቀጥታ ለዚህ ፍርድ ቤት የቀረበው ይህን በመቃወም ነው።
አመልካቾች ሚያዚያ 26 ቀን 2010 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር ማመልከቻ የሐረሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ ተሸሮ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዱፀና ጠይቀዋል።
ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብና ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት የተደረገ ሲሆን ተጠሪዎች ሰኔ 21/2010 ዓ.ም በተጻፈ መልስ ውሳኔው በህጉ አግባብ የተሰጠ ነውwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ተብል እንዱፀና ተከራክረዋል።አመልካቾችም ክርክራቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርበዋል። መዝገቡም ለምርመራ የተቀጠረው በዚህ ሁኔታ ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን ይህ ችልትም ጉዲዩን መርምሯል። እንደመረመርነው ጉዲዩ የፋዳራል ጉዲይ ነው የሚባልበት ምክንያት የላለ ሲሆን የክልል ጉዲይ መሆኑ ግራቀኙን አላከራከረም። የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበትን በክልል ጉዲዮች የተሰጠ የመጨረሻ ውሳኔ ለማረም በሰበር ችልት የማየት ስልጣን ያለው መሆኑም ይታወቃል። ነገር ግን የተያዘው ጉዲይ በክልለ ሰበር ችልት ሳይታይ በቀጥታ ለዚህ ፍርድ ቤት የቀረበው ይህ ሰበር ሰሚ ችልት አስቀድሞ በተመሳሳይ ጉዲዩች በሰጠው ትርጉም ምክንያት መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። ስለሆነም የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት አስቀድሞ ያሳለፊቸው ገዥ ትርጉሞች በአዋጅ ቁጥር 454/1997 መሰረት በድጋሚ ሉታዩ የሚገባ ሆኖ ተገኝቷል።
ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ሚያዚያ 25/2008 ዓ.ም በዋለው ችልት በሰጠው ውሳኔ የሰበር ችልት በህግ አግባብ ሳይቋቋም የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን በሰበር አቤቱታ ስርዓት ሉያስተናግደ የሚችለበት አግባብ ሉኖር እንደማይችል፤
በሐረሪ ክልል የሰበር ስርዓት በዝርዝር ህጎች በግልጽ ያልተቀመጠና ያለው አሰራርም በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ያለመኖሩን የሚያስገነዝብ በመሆኑ፤ በውስን ጉዲዮች ላይ ብቻ በክልለ ሰበር ችልት ተቋቁሟል እየተባለ የሰበር ስርዓት ተግባራዊ የሚሆንበት አግባብ ተገቢ ሆኖ አልተገኘም በማለት የክልለ ሰበር ችልት ሰጥቶት የነበረውን ውሳኔ በመሻር የክልለ ይግባኝ ሰሚ ችልት በሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው የሚል ወገን አቤቱታውን ሉያቀርብ የሚገባው በቀጥታ ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ነው በማለት ወስኗል። በተመሳሳይም በሰ/መ/ ህዲር 8/2009 ዓ.ም በተሰጠ ውሳኔ በሐረሪ ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ያልተቋቋመ መሆኑን፤ በሐረሪ ክልል የሰበር ስርዓት በዝርዝር ህጎች ያልተቀመጠና ያለው አሰራርም በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ያለመኖሩን የሚያስገነዝብ መሆኑን በመግለጽ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ጉዲዩን ተቀብል መወሰኑ ተቀባይነት የለውም በማለት ጉዲዩ ላቀርብ የሚገባው በቀጥታ ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ስለመሆኑ ተወስኗል። በነዚህና በመሰል መዛግብት በተሰጠውwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
አስገዲጅ ትርጉም ምክንያት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዲዮችን በሰበር ማየቱን እንዲቆመ ተገንዝበናል። በተያዘው ጉዲይም የሰበር አቤቱታው ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ሳይቀርብ በቀጥታ ለዚህ ፍርድ ቤት የቀረበው በዚህ ምክንያት ነው።
ስለ ፍርድ ቤቶች ጣምራነት እና ስልጣን በሚደነግገው የኢፋዳሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80 ንዐስ አንቀጽ 3(ለ) ሥር እንደተመለከተው የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበትን በክልል ጉዲዮች የተሰጠ የመጨረሻ ውሳኔ ለማረም በሰበር ችልት የማየት ስልጣን እንደሚኖረውና ዝርዝሩ በህግ እንደሚወሰን ይደነግጋል።
በተመሳሳይ የሐረሪ ክልል ህገ መንግስት አንቀጽ 70(2)(ሀ) በማንኛውም የክልለ ፍርድ ቤት የተሰጠ የመጨረሻ ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሲሆን የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰበር የማየት ሥልጣን እንዲለውና ዝርዝሩ በህግ እንደሚወሰን ይደነግጋል።
በዚህ መልኩ በህገመንግስታቱ የተቋቋመው እና ሥልጣኑ የተለየውን የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የተመለከቱ ዝርዝር ህጎች መውጣታቸውን ከክልለ ፍርድ ቤቶች የማቋቋሚያ አዋጆችና ማሻሻያቸው መገንዘብ ይቻላል። የሐረሪ ሕዝብ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ፍርድ ቤቶችና የዳኞች አስተዲደር ጉባኤ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 3/1988 ምዔራፍ ሁለት ስለመደበኛ ፍርድ ቤቶች መቋቋምና ስለዲኝነት ስልጣናቸው የሚደነግግ ሲሆን በአንቀጽ 3(1) ሥር የሐረሪ ህዝብ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት መቋቋሙ ተመልክቷል። የችልቶቹን አሰራር በሚደነግገው አንቀጽ 7(1) ሥር ደግሞ በማንኛውም ደረጃ የሚገኙ የክልለ ፍርድ ቤቶች ለሥራቸው አስፈላጊ የሆኑ ችልቶች እንደሚኖራቸው ተመልክቷል። የክልለን ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዲኝነት ሥልጣን የሚዘረዝረው የአዋጁ አንቀጽ 15 በንዐስ ቁጥር 3 ስር ደግሞ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበትን በየትኛውም ደረጃ በሚገኝ የክልለ ፍርድ ቤት የተሰጠን የመጨረሻ ፍርድ ወይም ውሳኔ በሰበር ችልት የማየት ሥልጣን እንዲለው ይደነግጋል።
ከዚህም በቀር የሐረሪ ህዝብ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ፍርድ ቤቶችና የዳኞች አስተዲደር ጉባኤ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 3/1988 እና ማሻሻያ አዋጆች ቁጥር 8/1991 እና 17/1991 እንደገና ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ቁጥር 68/1999 ማሻሻያ ካደረገባቸው ጉዲዮች አንደ የክልለን ሰበር ችልት የተመለከተ ነው። በዚህ መሰረት በቀዲሚው አዋጅ ቁጥር 3/1988 አንቀጽ 15(3) የተመለከተው ተሰርዞ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
“መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበትን በየትኛውም ደረጃ በሚገኝ የክልለ ፍርድ ቤት የተሰጠን የመጨረሻ ፍርድ ወይም ውሳኔ በሰበር ችልት የማየት ስልጣን ይኖረዋል።
የሰበር አቤቱታ አቀራረብ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት እና በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ሥነስርዓት ስለ ይግባኝ አቀራረብ በተደነገጉት መሰረት ነው” በሚል ተተክቷል።
ከፍሲል የተጠቀሱት የፋዳራለም ሆነ የክልለ ህገመንግስቶች እንዱሁም የሐረሪ ህዝብ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ፍርድ ቤቶችና የዳኞች አስተዲደር ጉባኤ ማቋቋሚያ አዋጅ እና ማሻሻዎች ሁለ የክልለ ሰበር ችልት መቋቋሙን፤ የሰበር ችልቱን ሥልጣን እና ለሰበር ችልቱ አቤቱታ የሚቀርብበትን ስርዓት ሁለ በህግ መደንገጉን የሚያሳዩ ናቸው።
የሰበር ችልቱን ዝርዝር አደረጃጀትና አሰራር ሥርዓት መደንገጉ ለክልለ ህግ አውጭ አካል የተተወ በመሆኑ በዚህ መልኩ ዝርዝር ህጎች እንዱወጡ ማድረግ ተገቢ ሲሆን እስካሁን በክልለ ህግ አውጭ አካል በወጡት አዋጆ መሰረት የክልለ ሰበር ችልት በአግባቡ ተደራጅቶ አገልግልት የማይሰጥበት የህግ ምክንያት የለም። ሥራ ላይ ባለት ህጎች አግባብ ችልቱ እንዱደራጅና አገልግልት እንዱሰጥ ማድረግም ከፍርድ ቤቱ ኃላፉዎች የሚጠበቅ ነው።
ይህ ከሆነ ደግሞ ሥራ ላይ ባለት ህጎች መሰረት በክልለ ሰበር ችልት ታይተው ውሳኔ የተሰጠባቸው ጉዲዮች ላይ ለዚህ ሰበር ችልት አቤቱታ ሲቀርብ በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አልተቋቋመም፤ እንዱሁም በክልለ የሰበር ስርዓት በዝርዝር ህጎች አልተቀመጠም በማለት ውድቅ መደረጉና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ጉዲዩን ተቀብል እንዲይወሰን መደረጉ፤ እንዱሁም ጉዲዩች ሉቀርቡ የሚገባው በቀጥታ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ስለመሆኑ የተሰጠው ትርጉም ከፍሲል የተጠቀሰውን የህገመንግስቱንና የፍርድ ቤቱን ማቋቋሚያ አዋጆች የተከተለ ባለመሆኑ አስቀድሞ የተሰጠው ትርጉም ሉለወጥ ይገባል ብለናል።
ስለሆነም የፋዳራል ፍርድ ቤቶችን አዋጅ እንደገና ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀጽ 2(1) መሰረት ቀደም ሲል በዚህ ፍርድ ቤት በሰ/መ/ ሚያዚያ 25/2008 ዓ.ም፤ በሰ/መ/ ህዲር 8/2009 ዓ.ም እንዱሁም በላልች ተመሳሳይ መዛግብት ሰጥቶት የነበረውን ትርጉም ለውጠናል። በዚህ መዝገብ የተሰጠው ውሳኔ ለጉዲዩ ገዥ ይሆናል ብለናል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በዚህ ምክንያት አመልካቾች የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔን በመሻር ባሳለፈው ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመ በመሆኑ በሰበር ችልት ታይቶ ይታረምልን በማለት ያቀረቡትን የዲኝነት ጥያቄ በቅድሚያ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ሉያቀርቡ ይገባል በማለት ተከታዩን ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት በሰ/መ/ ሚያዚያ 25/2008 ዓ.ም፤ በሰ/መ/ ህዲር 8/2009 ዓ.ም እንዱሁም በላልች ተመሳሳይ መዛግብት ሰጥቶት የነበረው ትርጉም የፋዳራል ፍርድ ቤቶችን አዋጅ እንደገና ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀጽ 2(1) መሰረት ከላይ በፍርደ በተመለከተው መሰረት ለውጠናል።
አመልካቾች የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔን በመሻር ባሳለፈው ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመ በመሆኑ በሰበር ችልት ታይቶ ይታረምልን በማለት ያቀረቡት አቤቱታ በሐረሪ ህዝብ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ሉስተናገድና ውሳኔ ላሰጥበት የሚገባ ነው ብለናል።
መስከረም 7/2011 ዓ.ም የተሰጠው የዔግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ይጻፍ።
በዚህ ፍርድ ቤት ስለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ።
No topics extracted.