ዉልን መነሻ ያደረገ ያልተከፈለ ገንዘብ ለማስከፈል የቀረበ ክስ በአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች የስረ ነገር ስልጣን ስር የማይወድቅ እነ ወ/ሮ ስኳሬ ለገሰ እና የአዱስ አበባ ዉሃና www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XXXVI አዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 41 ፍሳሽ ባለስልጣን
No summary available.
ቀን፡- 24/9/2010ዓ.ም ዳኞች፡- ተኽሉት ይመስል ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራዉ አብዬ ካሳሁን አመልካቾች፡- 1ኛ ወ/ሮ ስኳሬ ለገሰ 2ኛ ወ/ሮ ፊንቱ ተዘራ 3ኛ አቶ ፀጋዬ ወ/ተንሳይ ቀረቡ።
4ኛ ወ/ሮ ጥሩወርቅ አሰፊ ተጠሪ፡- የአዱስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን- የቀረበ የለም።
መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ ዉዝፍ የዉሀ ፍጆታ ሂሳብ ለማስከፈል የቀረበ ክስ የሚመለከት ሲሆን የተጀመረዉ በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሁኑ ተጠሪ በአሁኑ አመልካቾች እና በዚህ መዝገብ የክርክሩ ተካፊይ ያልሆኑትን 1ኛ የአ/ከ/ክ/ከተማ ወረዲ 7 አስተዲደር ጽ/ቤት 2ኛ ወ/ሮ ሽቶ መሀመድ 3ኛ አቶ ጳዉልስ አለማየሁ ተከሳሾች ነበሩ።
የአሁኑ ተጠሪ ከቀረበዉ ክስ መረዲት የተቻለዉ የአሁኑ አመልካቾች እና በስር 6ኛ እና 7ኛ ተከሳሾች የነበሩትን ጨምሮ ከጥቅምት 2006 እስከ ጥርwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
2008ዓ/ም ድረስ የተጠቀሙበት ዉሀ ፍጆታ ብር 5895.55 ያልከፈለ በመሆኑ እንዱከፍለ ይወሰን ዘንድ ዲኝነት ጠይቋል።
አመልካቾች መጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እንዱሁም በፍሬ ጉዲይ የበኩላቸዉን የመከላከያ መልስ አቅርበዋል። አመልካቾች ባቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ፍ/ቤቱ የሥረ ነገር ስልጣን የለዉም ያለ ሲሆን በፍሬ ገዲዩም በተጠሪ ክስ የተጠቀሰዉ ሂሳብ የቤት ቁጥር 1180 ሳይሆን የቤት ቁጥር 797 ነዉ የሚል ክርክር አቅርበዋል።
በዚህ አግባብ ክርክሩ የቀረበለት የሥር ፍ/ቤትም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዉ በብይን ካለፈ በኃላ አመልካቾች አገልግልት ያገኙ መሆኑ በማረጋገጡ ተጠሪ በክሱ የጠቀሰዉ ብር 5895.55 ይክፈለ ሲል ፍርድ ሰጥቷል። አመልካቾች ይህ ዉሳኔ በመቃወም ለከተማዉ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ይግባኝ አቤቱታ አቅርበዉ ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኃላ የክርክሩ መሰረታዊ ይዘት ዉል መነሻ ያደረገ በመሆኑ የከተማዉ ፍርድ ቤቶች የስረ ነገር ስልጣን የላቸዉም በማለት የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ በአብላጫ ድምጽ ሽሯል።
በመቀጠል በሰበር ስልጣኑ የተመለከተዉ ፍርድ ቤት ጉዲዩ በአዱስ አበባ ፍ/ቤቶች ስረ ነገር ስልጣን የሚወድቅ መሆኑን በመግለጽ የይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት ዉሳኔ በድምጽ ብልጫ በመሻር የመ/ደ/ፍ/ቤት ዉሳኔ አጽንቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበዉም የስር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ በመቃወም ለማሳረም ነዉ።
የመልስ መልስም ቀርቧል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የጉዲዩ አመጣጥም ባጭሩ ከላይ የተገለጸዉ ይዘት ያለዉ ሲሆን እኛም በስር የከተማዉ ሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት መሆን አለመሆኑን እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነዉም በስር ፍ/ቤት የአሁኑ ተጠሪ ከቀረበዉ ክስ መገንዘብ የተቻለዉ የአሁኑ አመልካቾች የተጠቀሙበትን የዉሃ ፍጆታ እንዱከፍለ የሚጠይቅ ነዉ። የክሱ መሰረታዊ ይዘት ዉል መነሻ ያደረገ ክርክር ነዉ።
የከተማ ሰበር ሰሚ ችልት የከተማ ይግባኝ ሰሚ ችልት ዉሳኔ ለመሻር መነሻ ያደረገዉ ክርክሩ በሁለት የከተማዉ አስተዲደራዊ ተቋማት የተነሳ ከሚል እሳቤ ስለመሆኑ የዉሳኔዉ ግልባጭ ያመለክታል። ከመዝገቡ እንደተረዲነዉ የአሁኑ አመልካቾች በስር 1ኛ ተከሳሽ ከነበረዉ ቤት የተከራዩ መሆኑ እንዱሁም ከአሁኑ ተጠሪ የዉሃ አገልግልት የሚያገኙ ስለመሆኑ ያከራከረ ጉዲይ አይደለም። ከዚህ የምንረዲዉ ተጠሪ ክስ ያቀረበዉ በዉለ መሰረት የዉሃ ፍጆታ ሂሳብ እንዱከፈለዉ ነዉ። የአሁኑ ተጠሪ የዉሃ አገልግልት መስጠቱ አመልካቾች ደግሞ ተጠቃሚዎች ከመሆናቸዉ አንፃር የተገለገለበት ሂሳብ የመክፈል ግዳታ ያላቸዉ መሆኑን ተጠቅሶ የቀረበዉ ክርክር መነሻዉ ዉል እንጂ የሁለት ተቋማት ክርክር ስለመሆኑ መዝገቡ አያሳይም። ይህ ከሆነ ደግሞ የሥር ይግባኝ ሰሚ ችልት በዉሳኔዉ እንደገለፀዉ ክርክሩ ዉል መነሻ ያደረገ ያልተከፈለ ገንዘብ ለማስከፈል የቀረበ ክስ ከመሆኑ አንፃር የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች የስረ ነገር ስልጣን ያላቸዉ ስለመሆኑ የሚሳይ አንዲችም የህግ መሰረት ያለዉ ክርክር አልቀረበም። በልላ በኩል የከተማዉ ሰበር ሰሚ ችልት አዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 41(1)(ሰ) የተረጎመበት አግባብ የድንጋጌዉ መሰረታዊ ይዘትና መንፈስ ያልተከተለ ነዉ። የስረ ነገር ስልጣን ክርክር ጉዲይ ፍ/ቤቱ በራሱ ጊዜ የሚያነሳ ስለመሆኑም የፍ/ሕ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 9(2) እና 231 ድንጋጌዎች መሰረታዊ ይዘት ያስገነዝቡናል። በመሆኑም የከተማዉ ሰበር ሰሚ ችልት ክርክሩ ዉል መነሻ ያደረገ መሆኑን መገንዘብ እየተገባዉ ጉዲዩ በከተማዉ ፍ/ቤቶች የሚታይ ነዉ በማለት የደረሰበት መደምደሚያ አዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 41 ያላገናዘበ ነዉ ብለናል። በዚህም ተከታዩን ወስነናል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
No topics extracted.