በአዋጅ ቁጥር 147/91 መሰረት አንድ ማሕበር አቶ ደሱ ታምሩ መስከረም 21 335www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XXXIV ካበቃ በኃላ ወይም መብትና ግዳታዉ የሕብረት ሥራ ማሕበር ወደ አልሆነ የንግድ ማሕበር ተላልፍ በሚገኝበት ወቅት ጉዲዩ በሽምግልና ዲኝነት የሚታይበት የህግ አግባብ የላለ ስለመሆኑ እና መደበኛ ፍ/ቤቶች ጉዲዩን ለማየት የስረነገር ስልጣን ያላቸው ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 147/91 አንቀጽ 47 እና 49 እና ፈያ ጠቅላላ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግል ማህበር ቀን 2011 ዓ.ም 56. የይዞታ ማረጋገጫ ማስረጃ አላግባብ ተሰርዞብኛል በሚል የሚቀርብ አቤቱታ ጉዲዩ በቀጥታ ከመሬት ይዞታ ባለመብትነት ጋር ተያያዥነት ያለው በመሆኑ የተከራካሪ ወገኖች መደበኛ ነዋሪነት ወይም የተከራካሪው ወገን የፋዳራል መንግሥቱ ተመዝጋቢ መሆን ግምት ውስጥ ሳይገባ የክርክሩን ልዩ ባህርይ በማየትና የጉዲዩን ዓይነት መሰረት በማድረግ ንብረቱ የሚገኝበት የከተማ አሥተዲደር ፍ/ቤት የቀረበውን ክስ ተቀብል የመወሰን የሥረ- የደሴ ከተማ ዓይነሥውራን ማሕበር እና የኢትዮጲያ ዓይነሥውራን ብሓራዊ ማሕበር www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XXXV ሥልጣን ያለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 25 ፤አዋጅ ቁጥር 226/07 አንቀጽ 57/1
No summary available.
የሰ.መ.
ሐምል 30 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች:- የደሴ ከተማ ዓይነ ሥውራን ማሕበር ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ዓይነ ሥውራን ብሓራዊ ማሕበር መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው። በዚሁ መሰረት የመ.
የሆኑ መዝገቦች ተጣምረው ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የተሰረዘን የይዞታ ማረጋገጫ ካርታን በሚመለከት የቀረበ ክርክርን የሚመለከት ነው። በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን ተጠሪ አመልካች፤በዚህ የሰበር ክርክር የላለ የደሴ ከተማ አሥተዲደር ኢን/ከ/ል/አገ/መምሪያ ተጠሪ የአሁን አመልካች ደግሞ ጣልቃገብ በመሆን ተከራክረዋል። የአሁን ተጠሪ በሥር ፍ/ቤት ያቀረበው ክስ ይዘት በአጭሩ፡- ተጠሪው በ1952 ዓ.ም የተቋቋመ እና በበጎ አድራጎት ድርጅት እና ማሕበራት ኤጀንሲ የተመዘገበ ማሕበር መሆኑ፤ማሕበሩ በኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ ቅርንጫፍ ማሕበራት ያለት እና በደሴ ከተማ ውስጥም የኢትዮጵያ ዓይነሥውራን ብሓራዊ ማሕበር የደቡብ ወል ዞን ዓይነሥውራን ቅርንጫፍ ማሕበር ያቋቋመ መሆኑን፤ማሕበሩ በደሴ ከተማ ቧንቧ ውሃ ክፍለ ከተማ ከ1971 ዓ.ም ጀምሮ የያዘውን ይዞታ ካርታ አውጥቶ እና ግንባታ ገንብቶ አትክልት በመትከል ከሰላሣ ሥድሥት ዓመታት በላይ የሚጠቀምበት መሆኑን፤የሥር ተጠሪው ምንም ዓይነትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ሕጋዊ ምክንያት ሳይኖረው የተጠሪን ካርታ በመሰረዝ በአሁን ወቅት በልላ ባልተቋቋመ እና ሕጋዊ ሰውነት በላለው በደሴ ከተማ አሥተዲደር በደቡብ ወል ዞን ዓይነሥውራን ማሕበር ሥም ካርታ እንዱሰራ ያደረገ መሆኑን በመግለጽ የተጠሪ ካርታ ሉሰረዝ አይገባም ተብል ይወሰንለት ዘንድ ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው።
የሥር ተጠሪ በሰጠው መልስ ተጠሪው ማሕበር ቅርንጫፍ ለመክፈት የተፈቀደለት ስለመሆኑ ማሥረጀ ያላቀረበ መሆኑን፤ቦታው በቅድሚያ ለደሴ ዓይነሥውራን ማሕበር ት/ቤት መሥሪያ መሆኑን እና ለደሴ ከተማ እና አካባቢዋ ዓይነሥውራን ማሕበር በ1972 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረ ቢሆንም የተወሰኑ ግለሰቦች በቂ ባልሆነ ምክንያት ሥያሜውን በተጠሪ ሥም በመቀየር ከታለመለት ዓላማ ውጪ ቤቱን በማከራየት ተጠሪው ሲጠቀምበት የነበረ መሆኑን፤የከተማው ከንቲባ ጽ/ቤት ባቋቋመው አጣሪ ቡድን አማካኝነት ተጣርቶ በቀረበው አሥተያየት ጉዲዩ ተመርምሮ ተጠሪ ከተመለከተው ዓላማ ውጪ በማከራየት የሚጠቀምበት በመረጋገጡ ካርታው መሰረዙ የአካባቢውን ዓይነሥውራን ተጠቃሚ የሚያደርግ እና ሕጋዊ ተግባር መሆኑን በመግለጽ የተጠሪ ክስ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
የአሁን አመልካችም ጣልቃ ገብቶ እንዱከራከር አመልክቶ ተፈቅድለት ባቀረበው ክርክር ተጠሪ ክስ ያቀረበበት ጉዲይ አሥተዲደራዊ ጉዲይ በመሆኑ ፍ/ቤቱ ጉዲዩን የማየት ሥልጣን የላለው መሆኑን፤ሥረዛ የተደረገበት ካርታ የኢትዮጵያ ዓይነሥውራን ብሓራዊ ማሕበር የደቡብ ወል ዞን ዓይነሥውራን ቅርንጫፍ የሚል እና በአዋጁ መሰረት ቅርንጫፍ ስለመሆኑ ማሥረጃ ያልቀረበበት በመሆኑ ተጠሪው ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብት እና ጥቅም የላለው መሆኑን፤አከራካሪው ይዞታ የተሰጠው ለወል ክፍለ ሐገር ዓይነሥውራን ት/ቤት መሆኑን፤ የተጠሪ ማሕበር ሥያሜውን ወደ ደሴ ከተማ ዓይነሥውራን ማሕበር በሚል በ1999 ዓ.ም ካርታ ተሰርቶ እየተጠቀመ የተወሰኑ ግለሰቦች በቂ ባልሆነ ምክንያት ካርታ ሰጪውን በማሣሣት የተቀየረ መሆኑ በመረጋገጡ ወደ ቀድሞው እንዱመለስ ውሳኔ ማሳለፈ ሕጋዊ ተግባር መሆኑን፤ተጠሪ ይዞታውን ለላላ 3ኛ ወገን በማከራየት ገንዘቡን ለተወሰኑ ግለሰቦች መጠቀሚያ ማድረጉ ስለተረጋገጠ ካርታው እንዱሰረዝ የተሰጠው ውሳኔ ሕጋዊ መሆኑን እና አመልካች በክልለ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማሕበራት አዋጅ መሰረት ተመዝግቦ ሕጋዊwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ሰውነት የተሰጠው መሆኑን በመግለጽ የተጠሪው ክስ ውድቅ እንዱደረግ በማለት ተከራክሯል። ተጠሪም አመልካች ላቀረበው የጣልቃገብነት መከራከሪያ መልስ ሰጥቷል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የዲኝነት ሥልጣኑ የተመለከተው በደሴ ከተማ ነክ ጉዲዮች መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ምሥክሮችን ከሰማ እና ጉዲዩን የሚመለከት የተለያየ የሰነድ ማሥረጃ በትዕዛዝ እንዱቀርብለት ካደረገ በኋላ የግራቀኙን ክርክር እና ማሥረጃ መርምሮ የቀረቡት ማሥረጃዎች የሚያሳዩት ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቦታ ለዓይነስውራን ት/ቤት በሚል ከ1971 ዓ.ም ጀምሮ በጊዜው እውራን ተራድኦ ድርጅት በአሁኑ ወቅት ደግሞ የኢትዮጵያ አይነስውራን ብሓራዊ ማሕበር ለተባለው ለአሁን ተጠሪ ማሕበር የተሰጠው መሆኑን፤ተጠሪ በቀድሞው የኢትዮጵያ አይነስውራን ብሓራዊ ማሕበር የወል ክ/ሐገር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በአሁኑ ወቅት ደግሞ የኢትዮጵያ ዓይነስውራን ብሓራዊ ማህበር የደቡበ ወል ዞን አይነስውራን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ያለው መሆኑን እና ይኸው ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከብሓራዊ ማሕበሩ ጋር በመሆን ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቦታ እንዱሰጠው፤ካርታ እንዱሰራለት እና የግንባታ ፈቃድ እንዱሰጠው የጠየቀ መሆኑን፤ቦታው ከተሰጠው በኋላም በብሓራዊ ማሕበሩ ስም የሉዝ ውል በመግባት እና የግንባታ ፈቃድ በማውጣት በቦታው ላይ ግንባታ ያከናወነ እና ቦታው ለአመልካቸ የተሰጠ ስለመሆኑም የሥር ተከሳሹም ሆነ የከንቲባው ጽ/ቤት የሚያውቁ እና የፈቀደ መሆኑን በመሆኑ ቦታው ለተጠሪ የተሰጠ ነው፤የሥር ተከሳሽ ካርታው የተሰረዘው ቦታው የአመልካቸ ነው በሚል ቢሆንም ቦታው ሲሰጥም ሆነ ካርታው ሲሰራ አመልካች ቦታው እንዱሰጠው ያመለከተ እንዱሁም ቦታውን የተረከበ ስለመሆኑ ያላስረዲ በመሆኑ የሥር ተከሳሹ ካርታውን ያመከነው ከሕግ ውጪ ነው፤አመልካች ሕጋዊ ሰውነት ያገኘው እና ቦታው ይገባኛል በማለት አቤቱታ ያቀረበው ከጥር ወር 2006 ዓ.ም ወዱህ በመሆኑ አመልካች ባልነበረበት ወቅት ለተገኘ መብት ባለመብት አያደርገውም፤የተጠሪ ካርታ መክኖ በደሴ ከተማ አሥተዲደር እና የደቡብ ወል ዞን ዓይነስውራን ማሕበር በሚል የተሰራ ቢሆንም በዚህ ስም የሚጠራ እና የተመዘገበ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ማሕበር የላለ ስለመሆኑ በሚመለከታቸው አካላት የተረጋገጠ በመሆኑ አመልካች ክስ በቀረበበት ቦታ ላይ መብት እና ጥቅም የለውም ሲል ወስኗል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለደሴ ከተማ ነክ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የይግባኝ አቤቱታ አቅርቧል። ይግባኙ የቀረበለት ፍ/ቤት ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ ተጠሪው በፋዳራል መንግሥት የተመዘገበ ማሕበር በመሆኑ እና ዋና መሥሪያ ቤቱም አዱስአበባ በመሆኑ ተጠሪ የመሰረተው ክስ በፋዳራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 5/6 መሰረት በፋዳራል ፍ/ቤቶች የዲኝነት ሥልጣን ሥር የሚታይ ነው፤በሕገመንግሥቱ በተሰጠው ውክልና መሰረት የተጠሪ ክስ በክልለ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የሚታይ በመሆኑ የሥር ፍ/ቤት ጉዲዩን የማየት የሥረ ነገር ሥልጣን የለውም ተጠሪ ሥልጣን የለውም በማለት ወስኗል።
ተጠሪ በበኩለ በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርቧል፤ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ ክልልች በሥራቸው ያለትን ከተሞች ለማቋቋም፤ለማደራጀት፤ሥልጣን እና ተግባራቸውን ለመወሰን እንዱችለ የወጣው አዋጅ ቁጥር 91/96 እና ይህንኑ አዋጅ ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ቁጥር 226/07 አንቀጽ 57/1 የከተማውን መዋቅራዊ ፕላን አጠባበቅ፤የመሬት ይዞታ ባለመብትነት፤የሕንጻ ግንባታ ፈቃድ አሰጣጥ፤የቦታ አሰራር እና አጠቃቀም ሕግጋት ደንቦች እና መመሪያዎች አፈጻጸምን የሚመለከቱ ጉዲዮች የመዲኘት ፍትሐብሓራዊ ሥልጣን ያለው የከተማ ነክ ጉዲዮች ፍ/ቤት መሆኑን ይደነግጋል፤ አከራካሪው ጉዲይ በደሴ ከተማ ቧንቧ ውሃ ክፍለከተማ የሚገኘውን ይዞታ ካርታ እና ፕላን ሉሰረዝብን አይገባም የሚል በመሆኑ በከተማ ነክ ጉዲዮች ፍ/ቤት የሚታይ ነው በማለት ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር በፍሬነገሩ ላይ አከራክሮ እንዱወስን በማለት ጉዲዩን ለይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት መልሶለታል።
አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም የመ. በሆነው መዝገብ የሰበር አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን ይዘቱም በፋዳራል መንግሥት የተቋቋሙ እና የተመዘገቡ የንግድ ማሕበሮችን በሚመለከት የሚነሱ ክርክሮችን አይቶ ውሳኔ ለመስጠት የሥረ ነገር ሥልጣን ያላቸው የፋዳራል ፍ/ቤቶች ናቸው፤ክርክሩ ከማንኛውም የክስ ምክንያት የመነጨ ቢሆንም የክርክሩ ተሳታፉ በፋዳራል መንግሥት የተመዘገበ ከሆነ ወይም መደበኛ ነዋሪነታቸው በተለያየ ክልል በሆነ ተከራከሪዎች መካከል የተነሳ ክርክር የማየት ሥልጣን ያላቸው የፋዳራል ፍ/ቤቶች ናቸው፤ተጠሪ የፋዳራል መንግሥት የተመዘገበwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ማሕበር በሆኑ እና መደበኛ መቀመጫውም አዱስ አበባ በመሆኑ፤አመልካች ደግሞ በአማራ ክልል የተመዘገበ ማሕበር በመሆኑ ክርክሩን የማየት ሥልጣን ያላቸው የፋዳራል ፍ/ቤቶች ሆነው ሳለ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የከተማው ፍ/ቤቶች ጉዲዩን የማየት ሥልጣን አላቸው በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ተጠሪ በፋዳራል መንግሥት የተመዘገበ ማሕበር ሆኖ ሳለ የደሴ ከተማ ነክ ጉዲዮች ፍ/ቤት ጉዲዩን የማየት ሥልጣን አለው የመባለን አግባብነት ለማጣራት ሲባል ጉዲዩ በዚህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል። ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
በልላ በኩል የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የከተማው ፍ/ቤቶች ጉዲዩን የማየት ሥልጣን አላቸው በማለት የሥር ይግባኝ ሰሚው የከተማው ፍ/ቤት በፍሬነገሩ ላይ አከራክሮ እንዱወስን በማለት ጉዲዩን ለይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በመለሰው መሰረት ጉዲዩ የተመለሰለት የሥር ይግባኝ ሰሚው የከተማው ፍ/ቤት ዋናውን ጉዲይ አይቶ የወረዲው ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ አጽንቶታል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት በየደረጃው ላለ የክልለ ፍ/ቤቶች አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም አቤቱታው ተቀባይነት አላገኘም። አመልካች በዋናው ጉዲይ ላይ በተሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት የመ. በሆነው መዝገብ የሰበር አቤቱታ አቅርቧል።
አመልካች በመ. ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ይዘት ተጠሪ በፋዳራል መንግሥቱ የተመዘገበ ማሕበር ስለመሆኑ እና መደበኛ መቀመጫውም አዱስ አበባ ከተማ ስለመሆኑ በሥር ፍ/ቤቶች በቀረበው የምዝገባ የምሥክር ወረቀት ተረጋግጧል፤አመልካች ደግሞ በአማራ ክልል በደሴ ከተማ አሥተዲደር የተመዘገበ በመሆኑ ክርክሩን የማየት የሥረ-ነገር ሥልጣን ያለው የፋዳራል ፍርድ ቤት ነው፤የከተማው ፍ/ቤቶች የይዞታ መብት አጠባበቅን የሚመለከት ክርክር የማየት ሥልጣን ያላቸው ቢሆንም አዋጅ ቁጥር 25/88 ን እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጣቸውን አስገዲጅ የሕግ ትርጉሞች በማይቃረን ሁኔታ እንጂ ተቃራኒ በሆነ ሁኔታ ላሆን አይገባውም፤በመሆኑም አመልካች በመ. ለዚህ ችልት ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ምላሽ ሳያገኝ በፍሬጉዲዩ ላይ በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠውwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ሲሆን አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ችልት መታየት ያለበት ሆኖ ስለተገኘ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎ ግራቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም ሉጣራ ይገባል ተብል የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ፤ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ፡-
የደሴ ከተማ አሥተዲደር ፍ/ቤቶች አመልካች ያቀረበውን ክስ ተቀብል ለመወሰን የሚያስችል የሥረ-ነገር ሥልጣን አላቸው? ወይስ የላቸውም?
የሥር ፍ/ቤቶች በዋናው ጉዲይ ላይ የሰጡት ውሳኔ ተገቢ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለትን ጭብጦች በመያዝ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረነዋል።
የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ፡የፋዳራል ፍ/ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 5 (2)እና(6) መደበኛ ነዋሪነታቸው በተለያዩ ክልልች ውስጥ በሆኑ ሰዎች መካከል የሚነሱ ክርክሮችን፤በፋዳራል መንግሥቱ አካላት የተመዘገቡ ወይም የተቋቋሙ የንግድ ድርጅቶች እና ማሕበሮችን በሚመለከት የሚነሱ ክርክሮችን ተቀብለው የማስተናገድ ሥልጣን እንዲላቸው ይደነግጋል።
በልላ በኩል አዋጅ ቁጥር 91/96 እና ይህንኑ አዋጅ ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ቁጥር 226/07 አንቀጽ 57/1 የከተማውን መዋቅራዊ ፕላን አጠባበቅ፤የመሬት ይዞታ ባለመብትነት፤የሕንጻ ግንባታ ፈቃድ አሰጣጥ፤የቦታ አሰራር እና አጠቃቀም ሕግጋት ደንቦች እና መመሪያዎች አፈጻጸምን የሚመለከቱ ጉዲዮች የመዲኘት ፍትሐብሓራዊ ሥልጣን ያለው የከተማ ነክ ጉዲዮች ፍ/ቤት መሆኑን ይደነግጋል።
ሁለቱም አዋጆች የየራሣቸውን ዓላማ ይዘው የወጡ ከመሆናቸው አኳያ በመዝገቡ የተያዘው ጉዲይ በየትኛው ፍ/ቤት የሥረ ነገር ሥልጣን ሥር ላታይ እንደሚገባ መለየት አስፈላጊ ነው። በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 5 (2)እና(6) መደበኛ ነዋሪነታቸው በተለያዩ ክልልች ውስጥ በሆኑ ሰዎች መካከል የሚነሱ ክርክሮችን፤በፋዳራል መንግሥቱ አካላት የተመዘገቡ ወይም የተቋቋሙ የንግድwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ድርጅቶች እና ማሕበሮችን በሚመለከት የሚነሱ ክርክሮች በማለት የተገለጸው ሀሳብ የጉዲዮች ዓይነት ምንም ይሁን ምን ነዋሪነታቸው በተለያዩ ክልልች ውስጥ በሆኑ ሰዎች መካከል የሚነሳ ክርክርን፤በፋዳራል መንግሥት የተመዘገበን ማሕበር የሚመለከት ክርክርን የመዲኘት ሥልጣን የፋዳራል ፍ/ቤቶች መሆኑን የሚያሳይ ነው።
በአዋጅ ቁጥር 91/96 እና ይህንኑ አዋጅ ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ቁጥር 226/07 አንቀጽ 57/1 የከተማውን መዋቅራዊ ፕላን አጠባበቅ፤የመሬት ይዞታ ባለመብትነት፤የሕንጻ ግንባታ ፈቃድ አሰጣጥ፤የቦታ አሰራር እና አጠቃቀም ሕግጋት ደንቦች እና መመሪያዎች አፈጻጸምን የሚመለከቱ ጉዲዮች የመዲኘት ፍትሐብሓራዊ ሥልጣን ያለው የከተማ ነክ ጉዲዮች ፍ/ቤት መሆኑን በመግለጽ የሚደነግግ ሲሆን ለጉዲዩ ዓይነት ትኩረት በመስጠት በድንጋጌው ተለይተው የተቀመጡ ጉዲዮች በከተማው አሥተዲደር ፍ/ቤቶች የሥረ-ነገር ሥልጣን ሥር እንዱታዩ ታሳቢ በማድረግ የተደነገገ ነው።
በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 5 (2)እና(6) መሰረት በፋዳራል ፍ/ቤቶች የስረ ነገር ስልጣን ስር የሚወድቀው መደበኛ ነዋሪነታቸው በተለያዩ ክልልች ውስጥ በሆኑ ሰዎች መካከል የሚነሳ ወይም በፋዳራል መንግሥቱ አካላት የተመዘገቡ ወይም የተቋቋሙ የንግድ ድርጅቶች እና ማሕበሮችን በሚመለከት የሚነሱ ማናቸውም ዓይነት ክርክሮችን ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነጥብ ምላሽ የሚያሻው መሰረታዊ ነጥብ በመሆኑ አዋጆቹ ከወጡለት ዓላማ አንጻር በጥንቃቄ ላታይ የሚገባው ነው።
መደበኛ ነዋሪነታቸው በተለያዩ ክልልች ውስጥ በሆኑ ሰዎች መካከል እንዱሁም በፋዳራል መንግሥቱ ተመዝጋቢ የሆነ ማሕበር ተከራካሪ የሆነበት ነው ተብል አካላት ክስ የቀረበበት ጉዲይ በደሴ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ይዞታን በሚመለከት የተሰጠን የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ አላግባብ ተሰርዞብናል በማለት የተነሳ ክርክርን የሚመለከት ነው።
የይዞታ ማረጋገጫ ማስረጃ ከመሬት ይዞታ ባለመብትነት ጋር በቀጥታ ተያያዥነት ያለው በመሆኑ ይህንኑ በሚመለከት የሚቀርክ ክስ በከተማው ፍ/ቤቶች የዲኝነት ሥልጣን ሥር የሚታይ እንደሆነ ከአዋጅ ቁጥር 91/96 እና ይህንኑ አዋጅ ለማሻሻል ከወጣው አዋጅ ቁጥር 226/07 አንቀጽ 57/1 ድንጋጌ ይዘት መገንዘብ ይቻላል።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጣው አዋጅ ቁጥር 25/88 መደበኛ ነዋሪነታቸው በተለያዩ ክልልች ውስጥ በሆኑ ሰዎች መካከል የሚነሳ ወይም በፋዳራል መንግሥቱwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
አካላት የተመዘገቡ ወይም የተቋቋሙ የንግድ ድርጅቶች እና ማሕበሮችን በሚመለከት የሚነሱ ክርክሮች በፋዳራል ፍ/ቤቶች የሥረነገር የዲኝነት ሥልጣን የሚታዩ መሆናቸው የሚደነግግ ቢሆንም በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገመንግሥት አንቀጽ 52/2/ለ ለክልልች በተሰጠው ሕግ የማውጣት ሥልጣን መሰረት በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት የወጣው አዋጅ ቁጥር 91/96 እና ይህንኑ አዋጅ ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ቁጥር 226/07 ደግሞ የከተማውን መዋቅራዊ ፕላን አጠባበቅ፤የመሬት ይዞታ ባለመብትነት፤የሕንጻ ግንባታ ፈቃድ አሰጣጥ፤ የቦታ አሰራር እና አጠቃቀም ሕግጋት ደንቦች እና መመሪያዎች አፈጻጸምን የሚመለከቱ ጉዲዮች በከተማው ፍ/ቤቶች የዲኝነት ሥልጣን ሥር የሚታዩ መሆናቸውን የሚደነግግ በመሆኑ በመዝገቡ የተያዘው ጉዲይ በየትኛው ፍ/ቤት የሥረ ነገር የዲኝነት ሥልጣን ላታይ ይገባል የሚለውን ለመለየት የክርክሩን ልዩ ባህርይ ማየት አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
አከራካሪ የሆነው ጉዲይ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የተሰጠን የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ስረዛን የሚመለከት ሲሆን አከራካሪ የሆነው ይዞታ የሚገኘውም በደሴ ከተማ ውስጥ ነው። የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 25 የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሚመለከት የሚቀርበው ክስ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ላስቻለው ፍ/ቤት መቅረብ እንዲለበት ይደነግጋል።
ክልልች በሕገመንግሥቱ በተሰጣቸው ሕግ የማውጣት ሥልጣን መሰረት የወጣው አዋጅ ቁጥር 91/96 እና ይህንኑ አዋጅ ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ቁጥር 226/07 ደግሞ የከተማውን መዋቅራዊ ፕላን አጠባበቅ፤የመሬት ይዞታ ባለመብትነት፤የሕንጻ ግንባታ ፈቃድ አሰጣጥ፤የቦታ አሰራር እና አጠቃቀም ሕግጋት ደንቦች እና መመሪያዎች አፈጻጸምን የሚመለከቱ ጉዲዮች በከተማው ፍ/ቤቶች የዲኝነት ሥልጣን ሥር የሚታዩ መሆናቸውን የሚደነግግ በመሆኑ፤ አከራካሪ የሆነው ጉዲይ የማይንቀሳቀስ ንብረትን የሚመለከት በመሆኑ እና የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 25 የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሚመለከት የሚቀርበው ክስ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ላስቻለው ፍ/ቤት መቅረብ እንዲለበት የሚደነግግ በመሆኑ አከራካሪ ከሆነው ጉዲይ አንጻር የተከራካሪ ወገኖች መደበኛ ነዋሪነት ወይም የተከራካሪው ወገን የፋዳራል መንግሥቱ ተመዝጋቢ መሆን ግምት ውስጥ ሳይገባ የጉዲዩን ዓይነት መሰረት በማድረግ አዋጅ ቁጥር 91/96 እና ይህንኑ አዋጅ ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ቁጥር 226/07 አንቀጽ 57/1 መሰረት የከተማው አሥተዲደርwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ፍ/ቤቶች ተጠሪ ያቀረበውን ክስ ተቀብለው የመወሰን የሥረነገር ሥልጣን አላቸው ብለናል።
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ፡ዋናውን ጉዲይ በተመለከተ ፍሬነገርን የማጣራት እና ማሥረጃን የመመዘን ሥልጣን ያላቸው ፍ/ቤቶች አከራካሪው ቦታ ከ1971 ዓ.ም ጀምሮ በጊዜው እውራን ተራድኦ ድርጅት በአሁኑ ወቅት ደግሞ ለአሁን ተጠሪ የተሰጠው መሆኑን፤ተጠሪ በቀድሞው የኢትዮጵያ አይነስውራን ብሓራዊ ማሕበር የወል ክ/ሐገር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በአሁኑ ወቅት ደግሞ የኢትዮጵያ ዓይነስውራን ብሓራዊ ማህበር የደቡበ ወል ዞን አይነስውራን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ያለው መሆኑን እና ይኸው ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከብሓራዊ ማሕበሩ ጋር በመሆን ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቦታ እንዱሰጠው፤ካርታ እንዱሰራለት እና የግንባታ ፈቃድ እንዱሰጠው የጠየቀ መሆኑን፤ቦታው ከተሰጠው በኋላም በብሓራዊ ማሕበሩ ስም የሉዝ ውል በመግባት እና የግንባታ ፈቃድ በማውጣት በቦታው ላይ ግንባታ ያከናወነ እና ቦታው ለተጠሪ የተሰጠ መሆኑን፤ቦታው ለተጠሪ ሲሰጥም ሆነ ካርታው ሲሰራ አመልካች ቦታው እንዱሰጠው ያመለከተ እንዱሁም ቦታውን የተረከበ ስለመሆኑ ያላስረዲ መሆኑን፤የሥር ተከሳሽ ካርታውን ያመከነው ከሕግ ውጪ መሆኑን፤አመልካች ሕጋዊ ሰውነት ያገኘው እና ቦታው ይገባኛል በማለት አቤቱታ ያቀረበው ከጥር ወር 2006 ዓ.ም ወዱህ መሆኑን በማረጋገጥ አመልካች ክስ በቀረበበት ቦታ ላይ መብት እና ጥቅም የለውም ሲለ ወስነዋል።
በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 80/3/ሀ እና በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 10 መሰረት ለዚህ ችልት የተሰጠው ሥልጣን መሰረታዊ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበትን የመጨረሻ ውሳኔ ማረም እንጂ ፍሬነገርን የማጣራት እና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን አልተሰጠውም። አከራካሪ የሆነው ይዞታ የተጠሪ መሆኑ እና ለተጠሪ ተሰጥቶ የነበረው የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ አላግባብ የተሰረዘ መሆኑን፤አመልካች ክስ በቀረበበት ቦታ ላይ መብት እና ጥቅም የላለው መሆኑን ፍሬነገርን የማጣራት እና ማስረጃን የመመዘን ሥልጣን ባላቸው የሥር ፍ/ቤቶች የተረጋገጠ በመሆኑ እና ይህ ችልትም ፍሬነገርን የማጣራት እና ማሥረጃን የመመዘን ሥልጣን የላለው በመሆኑ በየደረጃው ያለ የክልለwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ፍ/ቤቶች ዋናውን ጉዲይ በተመለከተ በሰጡት ውሳኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥሕተት አላገኘንበትም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ.1 መጋቢት 14 ቀን 2009 ዓ.ም የከተማው ፍ/ቤቶች ጉዲዩን የማየት ሥልጣን አላቸው በማለት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥሕ/ቁ 348/1 መሰረት ጸንቷል።
የደሴ ከተማ ነክ ጉዲዮች የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ./07 ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤የደሴ ከተማ ነክ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በመ.ቁ 1150/09 ሚያዝያ 24 ቀን 2009 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ.ቁ 03- 18027 መጋቢት 21 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥሕ/ቁ 348/1 መሰረት ጸንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ግራቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
ሚያዝያ 08 ቀን 2010 ዓ.ም በመዝገቡ የተሰጠው የዔግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ይጻፍ -መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል። ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.