የቀበላ የንግድ ሱቅ አላግባብ ተይዞብኛል ይመለስልኝ አቶ ገዛህኝ አየለ ግንቦት 30 ቀን 327www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XXXIII ለክስ ምክንያት የሆነው ጉዲይ በግለሰቦች መካከል የተደረገ ውል ሲሆን ጉዲዩን ተቀብል የማየት የዲኝነት ስልጣን የከተማ አስተዲደር ፍ/ቤቶች ሳይሆን የፋዳራል ፍርድ ቤቶች ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 4፤የድሬዲዋ አስተዲደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 416/1996 አንቀጽ 33(1)(ረ) እና እነ አቶ ኑረዱን ዓሉ 2009 ዓ.ም. 54. በንግድ ምዝገባ ፍቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 መሰረት አግባብ ባለው አካል አስተዲደራዊ እርምጃዎች የተወሰደበት ማናቸውም ሰው በህግ ጉዲይ ላይ ይግባኝ ቅሬታ ካለው ጉዲዩን ማቅረብ የሚገባው ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በይግባኝ እንጂ በቀጥታ ክስ ለአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ላቀርብ የማይገባ ስለመሆኑ የንግድ ምዝገባ ፍቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 ዓንቀፅ 46፣47(2)፣47(3) አቶ ኤበሳ አመንቴ ጃለታ እና እነ የአዱስ ከተማ ክ/ከተማ አካባቢ ጥበቃ ፅ/ቤት
No summary available.
ቀን-መስከረም 21 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ኃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች:- አቶ ደሱ ታምሩ ተጠሪ፡- ፈያ ጠቅላላ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግል ማህበር መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዚህ ሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዲይ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በዚሁ ፍ/ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረቡት ክስ ይዘት፡የተጠሪ አባላት እናብብ ጠቅላላ የኮንስትራክሽን ስራ ኃ/የተ/የህብረት ስራ ማህበር በሚል ተደራጅተን ስንሰራ ቆይተን ወደ ፉያ ጠቅላላ ስራ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር በሚል ወደ ንግድ ማህበር ቀይረናል። አመልካች የዚህ ማህበር ስራ አስኪያጅ በመሆን ከሰኔ ወር 2003 ዓ.ም እስከ መጋቢት 26 ቀን 2006 ዓ.ም ሲሰራ በቆየበት ወቅት በተለያየ ምክንያት የወሰደዉና ማህበሩ ላይ ጉዲት ያደረሰዉን በጠቅላላዉ ብር 83,517.18 ይክፈለን የሚል ነዉ።
አመልካች በሰጠዉ መልስ በስራ አስኪያጅነት የሰራሁት ማሕበሩ የሕብረት ሥራ ማህበር በነበረበት ወቅት እንጂ የንግድ ማህበር ከሆነ በኃላ ሥራ አስኪያጅ አቶ አለማየሁ አደኛ ነበር። ዲኝነት የተጠየቀባቸዉን ገንዘቦች ለመክፈል በወቅቱ የሂሳብ ሰራተኛ ወይም ገንዘብ ያዥ ስላልነበርኩ ለመክፈል ኃላፉነት የለብኝም በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩን በቅድሚያ የተመለከተዉ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በኃላ መርምሮ አመልካች ተጠሪ ዲኝነት የጠየቀዉንwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ገንዘብ ለመክፈል ኃላፉነት አለበት በማለት ብር 83,517.18 ለተጠሪ እንዱከፍል ወስኗል። በዚህ ዉሳኔ ቅር ተሰኝተዉ አመልካቾች ባቀረቡት ይግባኝ መነሻነት ጉዲዩን የተመለከተዉ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ግራቀኙን ካከራከረ በኃላ መርምሮ አመልካች ኃላፉነት አስከትሎል የተባለዉን ድርጊት የፈጸመዉ የተጠሪ ማህበር ወደ ንግድ ማህበር ከመቀየሩ በፉት እናብብ ጠቅላላ የኮንስትራክሽን ስራ ኃ/የተ/የህብረት ስራ ማህበር በነበረበት ወቅት በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 147/91 አንቀጽ 47 እና 49 መሰረት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን ያለዉ የሽምግልና ዲኝነት አካል እንጂ ለመደበኛ ፍ/ቤት ቀርቦ አይደለም በማለት የስር ፍ/ቤት የስረ-ነገር ስልጣን ሳይኖረዉ የሰጠዉ ዉሳኔ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ በመሻር ወስኗል። በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ተጠሪ ያቀረበዉን ይግባኝ የተመለከተዉ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ግራ ቀኙን ካከራከረ በኃላ መርምሮ ክስ በተመሰረተበት ወቅት ተጠሪ ኃላፉነቱ የተወሰነ የሕብረት ሥራ ማሕበር መሆኑ ቀርቶ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በመሆኑና በአዋጅ ቁጥር 147/91 የሚተዲደር ሳይሆን በንግድ ሕጉ የሚገዛ በመሆኑ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዲዩ የሚታየዉ በሽምግልና ዲኝነት ነዉ በማለት መደበኛ ፍ/ቤት የስረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን የለዉም ሲል የስር ፍ/ቤትን ዉሳኔ መሻሩ ተገቢ አለመሆኑን በመግለጽ ዉሳኔዉን ሽሮ የፍሬ ጉዲይ ይግባኙን ተመልክቶ ተገቢዉን ይወስን ዘንድ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዲዩን በመመለስ ወስኗል። ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ውሳኔ ላይ አመልካች ቅር በመሰኘታቸዉ ዉሳኔዉን ለማስለወጥ ነው።
አመልካች ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ይዘት፡- በእናብብ ጠቅላላ የኮንስትራክሽን ስራ ኃ/የተ/የህብረት ስራ ማህበር እና በፈያ ጠቅላላ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር መካከል በዉልም ሆነ በሕግ ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ሳይኖር እንዱሁም ግንኙነት እንዲላቸዉም ክርክርም ሆነ ማስረጃ ቀርቦ ባልተረጋገጠበት የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ተጠሪ ከመጀመሪያዉ ክሱን ለማቅረብ የቻለዉ የቀድሞ የሕብረት ሥራ ማህበሩ መብትና ግዳታዎች በሙለ ወደ አሁኑ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በመለወጡ ምክንያት መሆኑን በግራ ቀኙ ከቀረበዉ ክርክር እና ማስረጃ መገንዘብ ይቻላል ሲል የደረሰበት ድምዲሜ የተሳሳተ ነዉ። የሕብረት ሥራ ማህበሩ ከፈረሰ ከዓመታት በኋላ ክስ የቀረበዉ በልላ ማህበር ስም ነዉ። በልላ በኩል ተጠሪ ኃ/የተ/የግል ማህበሩን የሚመለከቱትን ብቻ በመለየት ክስ አልመሰረተም። ስለሆነም የፋዳራልwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም ሆነ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ጉዲዩን ለማየት በሕብረት ሥራ ማህበራት አዋጅ ቁጥር 147/91 አንቀጽ 49(3) እና የፋዳራል ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ የሰጠዉን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም በሚቃረን መልኩ የሰጡት ዉሳኔ ተሽሮ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ ይጽናልኝ የሚል ነዉ።
የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ በዚህ ጉዲይ የተጠሪ ድርጅት ቀደም ብል እናብብ ጠቅላላ የኮንስትራክሽን ሥራ ኃላፉነቱ የተወሰነ የሕብረት ሥራ ማህበር ነበር በማለት በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ሲወሰን ምንም ዓይነት ማስረጃ ሳይቀርብና በሕብረት ሥራ ማህበርና ኃ/የተ/የግ ማህበር መካከል ያለዉ ልዩነት ከግንዛቤ ዉስጥ ሳይገባ ነዉ በማለት አመልካች ያቀረበዉን ቅሬታ ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል የተባለ ሲሆን ግራ ቀኙ መልስ እና የመልስ መልስ በጽሁፍ በማቅረብ ተከራክረዋል።
ተጠሪ የሰጠዉ መልስ ይዘት፡- እናብብ ጠቅላላ የኮንስትራክሽን ስራ ኃ/የተ/የህብረት ስራ ማህበር በጥቃቅንና አነስተኛ ሲደራጅ የነበረዉ ስያሜ ሲሆን በ2004 ዓ.ም ወደ ፈያ ጠቅላላ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግል ማህበር በሚል የስያሜ ለዉጥ አድርጓል። በሁለቱ መካከል የስም ለዉጥ እጂ የአባላትም ሆነ የንብረት ልዩነት በላለበት ሁኔታ ምንም የሕግ ግንኙነት የላቸዉም የሚለዉ ቅሬታ ተገቢነት የለዉም።
የቀድሞ ማህበር አባላቱንና ንብረቱን በመያዝ የተጠሪን ንግድ ማህበር መስከረም ወር 2006 ዓ.ም ሲቀየር አመልካች እስከ መጋቢት 2006 ዓ.ም በሥራ አስኪያጅነት አገልግለዉ ከማህበር አባልነት ተሰናብተዋል። አመልካች ሥራ አስኪያጅ በነበሩበት ጊዜ ሁለ ላደረሱት ጉድለት በአንድ ላይ ከሚጠየቁ በቀር ተጠሪ ክስ ማቅረብ ያለበት ለይቶ ነዉ የሚለዉ ክርክር ተገቢነት የለዉም። ስለሆነም አመልካች ያቀረበዉ ቅሬታ ተገቢነት የላለዉ በመሆኑ ዉድቅ ይደረግልኝ የሚል ነዉ። አመልካች በሰጡት የመልስ መልስ አቤቱታቸዉን በሚያጠናክር መልኩ ተከራክረዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር በአጭሩ ከላይ የተመለከተዉን የሚመስል ሲሆን ከስር ፍ/ቤት ዉሳኔ እና ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል ተብል ከተያዘዉ ጭብጥ ጋር በማገናዘብ መርምረናል። መርምረን እንደተገነዝብነዉ ተጠሪ በአመልካች ላይ ክስ ሲያቀርብ የጠየቀዉ ዲኝነት ፉያ ጠቅላላ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ተብል ከመመዝገቡ በፉት እናብብ ጠቅላላ የኮንስትራክሽን ሥራ ኃ/የተ/የህብረት ሥራ ማህበር በሚልwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በሚታወቅበት ወቅት አመልካች የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ሲሰራ ለግል ጥቅሙ ያዋለዉንና በልላ መንገድ በድርጅቱ ላይ ያደረሰዉን ጉዲት በድምሩ ብር 83,517.18 እንዱከፍለዉ ሲሆን የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ግራ ቀኙን አከራክሮና ማስረጃ መርምሮ አመልካች ሙለን ገንዘብ እንዱከፍል ወስኖበታል። የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በበኩለ ወደ ፍሬ ጉዲይ ክርክሩ ሳይገባ ለክሱ መነሻ የሆነዉ ነገር ማሕበሩ የሕብረት ሥራ ማሕበር በነበረበት ወቅት የተፈጸመ ተግባርን መነሻ ያደረገ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 149/91 አንቀጽ 49 እና 47 መሰረት ስልጣን የተሰጠዉ ለሽምግልና ዲኝነት አካል በመሆኑ መደበኛ ፍ/ቤት ጉዲዩን ዓይቶ ለመወሰን ስልጣን የለዉም በማለት ዉሳኔዉን ሽሮታል። የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በበኩለ ክርክሩ እየተደረገ ያለዉ ከሕብረት ሥራ ማሕበር ጋር ሳይሆን ኃላፉነቱ ከተወሰነ የግል ማሕበር ጋር በመሆኑ መደበኛ ፍ/ቤት ጉዲዩን ዓይቶ የመወሰን ስልጣን አለዉ በማለት የከፍተኛዉን ፍ/ቤት ዉሳኔ በመሻር የፍሬ ጉዲይ ክርክሩ ተመልክቶ እንዱወስን መልሶለታል።
በመሰረቱ በአዋጅ ቁጥር 147/91 አንቀጽ 47 እና 49 መሰረት ጉዲዩ በቅድሚያ በእርቅ ካላለቀ በሽምግልና ዲኝነት የሚታየዉ በአንድ ማሕበር እና በአባላቱ ወይም በቀድሞ አባለ ወይም በአመራሩ ወይም በቀድሞ አመራሩ ወይም ከላላ ማሕበር ጋር ክርክር ሲኖር ነዉ። አንድ ማሕበር ሕልዉናዉ ካበቃ በኃላ ወይም መብትና ግዳታዉ የሕብረት ሥራ ማሕበር ወደ አልሆነ የንግድ ማሕበር ተላልፍ በሚገኝበት ወቅት ክርክሩ በሽምግልና ዲኝነት ይታያል የሚል የሕግ ድንጋጌ ባለመኖሩ መደበኛ ፍ/ቤቶች ጉዲዩን ለማየት የስረ-ነገር ስልጣን ይኖራቸዋል።
በተያዘዉ ጉዲይ በስር ፍ/ቤት ከሳሽ የሆነዉ የአሁኑ ተጠሪ ከሕብረት ሥራ ማሕበር የተላለፈልኝ መብትና ግዳታ አለኝ አለ እንጂ ራሱ ኃ/የተወሰነ የግል ማሕበር በመሆኑ ጉዲዩን ለሽምግልና ዲኝነት ለመወሰድ የሚገደድበት አግባብ የለም። ስለሆነም አመልካች የሕብረት ሥራ ማሕበሩ የቀድሞ አባል በመሆኑ ብቻ ጉዲዩ በአዋጅ ቁጥር 147/91 አንቀጽ 47 እና 49 መሰረት በሽምግልኛ ዲኝነት ላታይ ይገባል በማለት ያቀረበዉ ክርክር ተገቢነት የለዉም።
ላላዉ ግራ ቀኙን ያከራከረዉና የአመልካች አቤቱታ ለሰበር ያስቀርባል ሲባል የተያዘዉ ጭብጥ ተጠሪ የቀድሞዉ እናብብ ጠቅላላ የኮንስትራክሽን ሥራ ኃላፉነቱ የተወሰነ የሕብረት ሥራ ማሕበር መብትና ግዳታ የተላለፈለት ድርጅት ስለመሆኑwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ማስረጃ ሳይቀርብና በሁለቱ ማሕበራት መካከል ያለዉ ልዩነት ከግንዛቤ ዉስጥ ሳይገባ ዉሳኔ መሰጠቱ በአግባቡ ነዉ ወይስ አይደለም የሚለዉን ጭብጥ በተመለከተ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት መደበኛ ፍ/ቤት ጉዲዩን ዓይቶ የመወሰን የዲኝነት ስልጣን አለዉ ሲል ወሰነ እንጂ በሁለቱ ማሕበራት መካከል የመብትና ግዳታዎች መተላለፍ መኖሩን አስመልክቶ በማስረጃ የተደገፈ ነዉ ወይስ አይደለም የሚለዉን የፍሬ ጉዲይ ክርክር ዓይቶ አልወሰነም። ይልቁንም ይግባኝ ሰሚዉ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የፍሬ ጉዲይ ክርክሩን ተመልክቶ እንዱወሰን መልሶለታል።
በመሰረቱ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 80/3/ሀ እና በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 10 መሰረት ለዚህ ችልት የተሰጠው ስልጣን መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበትን የመጨረሻ ውሳኔ ማረም እንጂ ፍሬ ነገርን የማጣራት እና ማስረጃ የመመዘን ስልጣን አይደለም። አመልካች ያነሳውን የፍሬ ጉዲይ ክርክርን በተመለከተ ገና የመጨረሻ ውሳኔ ያልተሰጠበትና በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ታይቶ እንዱወሰን የተመለሰ በመሆኑ በዚህ ረገድ የመጨረሻ ውሳኔ ባልተሰጠበት ጉዲይ አመልካች ያቀረበው ቅሬታ በሰበር የሚታይ አይሆንም።
ሲጠቃለል የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ተጠሪ የሕብረት ስራ ማህበር አለመሆኑን በማረጋገጥ መደበኛ ፍ/ቤት ጉዲዩን ለማየት የስረ-ነገር ስልጣን አለው በማለት የፍሬ ጉዲይ ክርክሩን ተመልክቶ እንዱወስን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት መመለሱ የሚነቀፍበት በቂ ምክንያት ባለመኖሩ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል ለማለት አልተቻለም። በመሆኑም የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
በፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ጥር 24 ቀን 2010 ዓ.ም የተሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ጸንቷል።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸዉን ይቻለ።