አንድ ተከሳሽ የቀረበበትን ክስና ማስረጃ በመመርመር ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ መልሱን አቶ ተኽላይ ፍሰሃ እና www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww. XXX እንዱያቀርብ የታዘዘው እና ቀጠሮ የተሰጠው ከ10 ቀን ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከሆነ የተከሳሹን የመከላከልና የመከራከር የመሰማት መብቱን የሚነፍግ በመሆኑ በቂ ጊዜ ተሰጥቶት የመከላከያ መልሱን እና ክርክሩን እንዱያቀርብ መደረግ ያለበት ስለመሆኑ ኢ.ፋ.ዳ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 37፣ የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.240[2] ወ/ሮ ለታይ ለገሰ
No summary available.
ህዲር 26 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡ …..1. ተኽሉት ይመሰል 2. ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) 3. ቀነዓ ቂጣታ 4. ተሾመ ሽፈራዉ 5. ፀሐይ መንክር አመልካች፡ ……አቶ ተኽላይ ፍሰሃ - የቀረበ የለም።
ተጠሪ፡ ………….ወ/ሮ ለታይ ለገሰ - የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የጀመረዉ በትግራይ ክልል ሰሜን ምዔራብ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የሽሬ እ/ስላሴ ምድብ ችልት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች ተከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ ከሳሽ ሁኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዲዩ ለዚህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ.ቁ.98593 በ14/6/2010 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ መርምሮ ለመወሰን ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ ከሳሽ (የአሁን ተጠሪ) ባቀረቡት ክስ ተከሳሽ በሽሬ እ/ስላሴ ከተማ 04 ቀበላ ክልል ዉስጥ የሚገኘዉን በ140 ካ.ሜ ቦታ ላይ ያለዉን ቤት በብር 250 ሺህ ሸጠዉልኝ ገንዘቡን ተቀብለዉ ስመ ሀብቱን ሉያዛዉሩልኝ ፈቃደኛ ስላልሆኑ ቤትና ቦታዉን ስመ ሀብት እንዱያዛዉሩልኝ እንዱወሰንልኝ በማለት ከሷል።
በዚህ ክስ ላይ ተከሳሽ መልስ እንዱሰጡ ትዕዛዝ ቢሰጥም ተከሳሽ መጥሪያ ተቀብለዉ ያለ በቂ ምክንያት መልስ ይዘዉ ሳይቀርቡ በመቅረታቸዉ መልስ የመስጠት መብታቸዉ ታልፎል። ነገር ግን ተከሳሽ ክስ በሚሰማበት ቀነ ቀጠሮ በቃል ተከራክሯል።
ከዚህ በኋላ የከፍተኛዉ ፍ/ቤት የከሳሽ የሰዉ ምስክሮችን በመስማት እና በመሐንዱሶች ተጣርቶ እንዱቀርብ በማድረግ በሰጠዉ ዉሳኔ ተከሳሽ ሁለት ክፍል ማሻሻያ እና ሽንት ቤት ያለበትን ቦታ ለከሳሽ ሸጠዉ ከሳሽ ደግሞ በቦታዉ ላይ ሕንጻ ገንብተዉ ስለሚገኙ የሕንጻዉ ባለቤት ከሳሽ በመሆኑ፣ ቤትና ቦታዉ የከሳሽ በመሆኑ ተከሳሽ ስመ ሀብቱንwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ወደ ከሳሽ እንዱያዛዉር በማለት ወስኗል። ይህ ጉዲይ በይግባኝ ለትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የቀረበ ሲሆን ፍ/ቤቱ ግራ ቀኛቸዉን በማከራከር በሰጠዉ ዉሳኔ የሥር ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ ይህን ዉሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች በ26/6/2010 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ የሥር የከፍተኛ ፍ/ቤት በቀረበብኝ ክስ ላይ በ15/9/2010 ዓ.ም መልስ እንዱቀርብ ያዘዘ ሲሆን አመልካች በዚህ ቀን በችልት ፉት ቀርቤ መልሴን በጽሐፍ አዘጋጅቼ ለማቅረብ ጊዜ ስላጠረብኝና ከጠበቃ ጋር ተማክሬ በቀጣይ ቀጠሮ መልስ እንዲቀርብ እንዱታዘዝልኝ የጠየቀኩኝ ሲሆን ፍ/ቤቱ መልሴን እንዲቀርብ ማዘዝ ሲገባዉ ይህን ሳያደርግ የሰጠዉ ዉሳኔ እና የሥር የጠቅላይ ፍ/ቤት ይህን ዉሳኔ ማረም ሲገባዉ በማጽናት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ። ስለሆነም የሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ ተሽሮ የጠየቅኩት ዲኝነት እንዱወሰንልኝ በማለት በዋናዉ ክርክርም በዝርዝር ቅሬታቸዉን አቅርቧል።
ይህ ችልት ጉዲዩን በማየት የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዱሰጡ ባዘዘዉ መሰረት በ23/9/2010 ዓ.ም የተጻፈ መልስ አቅርቧል። የመልሱም ይዘት በአጭሩ፡ የአሁን ተጠሪ በዋናዉ ጉዲይ ላይ የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት ነዉ የሚለበትን ምክንያቶች በመዘርዘር የሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ እንዱጸናልኝ በማለት ተከራክሯል። አመልካች የመልስ መልስ ስላላቀረበ ታልፎል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኛቸዉን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል።
እንደመረመርነዉ በዚህ ጉዲይ ምላሽ ማግኘት ያለበት የአሁን አመልካች በጽሐፍ መልስ የመስጠት መብቱ መታለፈ በአግባቡ ነዉ ወይስ አይደለም? የሚለዉ ነጥብ መሆኑን ተገንዝበናል። በዚህ መሰረት የስር የዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ዉሳኔ ግልባጭ ሲታይ የአሁን አመልካች የፍ/ቤቱ መጥሪያ ደርሶት ያለ በቂ ምክንያት መልሱን ይዞ እንዲልቀረበ በመግለጽ መልስ የመስጠት መብቱን ማለፈን ያሳያል። በልላ በኩል ከስር የጠቅላይ ፍ/ቤት ዉሳኔ መገንዘብ እንደሚቻለዉ የአሁን ተጠሪ ባቀረበዉ ክርክር በፖሉስ በኩል የፍ/ቤትን መጥሪያ ለአመልካች በ8/9/2009 ዓ.ም የሰጠሁት ስለሆነ ለ15/9/2009 ዓ’ምwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
መልሱን ይዞ ለመቅረብ በቂ ጊዜ እንደነበረዉ ገለጾ ተከራክሯል። አመልካች በበኩለ ባቀረበዉ ክርክር በ10/9/2009 ዓ’ም መጥሪያ ቢመጣለትም አንብቡልኝ ብላቸዉ ሉያነቡልኝ ፈቃደኛ አልሆኑም፤ አመልካች በ13/9/2009 ዓ’ም ፍ/ቤት ቀርቦ በመታመሜ ምክንያት መልስ ለማዘጋጀት አልቻልኩም ስለዚህ ከባለሙያ ተማክሬ መልሴን እንዲቀርብ ብል እንዲመለከቱ፤ አመልካች መጥሪያዉን ቢቀበል ኖሮ ለ15/9/2009 ዓ’ም መልስ አዘጋጅቶ ለመቅረብ እንደሚችል በመግለጽ መታለፈ ተገቢ መሆኑን በመግለጽ የስር ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል። ስለዚህ የአሁን ተጠሪ ባቀረበዉ ክርክር እንኳን ቢሆን አመልካች መልሱን ይዞ እንዱቀርብ እየተደረገ ያለዉ በስምንት ቀናት ዉስጥ እንደሆነ እና አመልካች ከባለሙያ ተማክሮ መልሱን ለማቅረብ ጊዜ እንዲልበቃዉ በመግለጽ ፍ/ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዱሰጠዉ እንዲመለከተ ማየት ይቻላል። አመልካች የቀረበበትን ክስና ማስረጃ በመመርመር ተገቢ ነዉ ያለዉን መልስ ለማቅረብ ከተሰጠዉ ቀጠሮ ከ10 ቀን በፉት ሉደርሰዉ እንደሚገባዉ የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.240 [2] ያስገነዝባል።
ከዚህ አንጻር የአሁን አመልካች መልሱን እንዱያቀርብ የታዘዘዉ እና ቀጠሮ የተሰጠዉ ከ10 ቀን ባነሰ ጊዜ ዉስጥ መሆኑን ያሳያል። ይህ ደግሞ አመልካች በሕግ በተመለከተ ጊዜ ዉስጥ ተገቢዉን ዝግጅት በማድረግ መልሱን አዘጋጅቶ እንዱቀርብ የሚያስችለዉ ጊዜ ሆኖ አይገኝም። ይህ ደግሞ በኢ.ፋ.ዳ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 37 መሰረት የተጠበቀዉን መብት የሚነፍግ ነዉ። ስለሆነም የስር ፍ/ቤቶች የአሁን አመልካች በሕጉ አግባብ ተገቢዉን የመከላከያ መልሱን እንዱያቀርብና ሙለ ክርክሩን እንዱያቀርብ ማድረግ ሲገባቸዉ የመከላከልና የመከራከር መብቱን በመንፈግ ዉሳኔ መስጠታቸዉን መገንዘብ ተችሎል።
ሲጠቃለል የስር ፍ/ቤቶች የአሁን አመልካች የመከላከያ መልሱን ሳያቀርብ እና ክርክሩን አቅርቦ ሳይሰማ የሰጡት ዉሳኔ የመከላከልና የመከራከር የመሰማት መብቱን የነፈገ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህ ምክንያት የሚከተለዉ ተወስኗል።
ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት መደበኛ ችልት በመ.ቁ.98593 በ14/6/2010 ዓ’ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.348 [1] መሰረት ተሽሯል።
በትግራይ ክልል የሰሜን ምዔራብ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የተዘጋዉን መዝገብ በማንቀሳቀስ በፍርድ ሐተታዉ በተመለከተዉ መሰረት የአሁን አመልካች የመከላከያ መልሱን እና ክርክሩን እንዱያቀርብ በማድረግ፤ ግራ ቀኛቸዉን በማከራከር፤ ጉዲዩን በማጣራት ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ እንዱሰጥበት በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ’ 343 [1] መሰረት ተመልሶለታል።
የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለስር ፍ/ቤት ይድረስ።
ግራ ቀኛቸዉ በዚህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
ይህ ዉሳኔ ታህሳስ 1 ቀን 2011 ዓ’ም ተነብቧል።
No topics extracted.