ለአንድ ጉዲይ ለምስክርነት የተቆጠረ ሰው በፍርድ ቤት ጥሪ መሰረት ቀርቦ የመመስከር ግዳታ ያለበት ሲሆን ምስክሩ ላቀርብ ካልቻለም ፍርድ ቤቱ ተገቢ መስል በታየው መንገድ ትዕዛዝ በመስጠት ምስክሩ በሕግ አግባብ ተገድ ወይም ታስሮ እንዱቀርብ በማዘዝ ምስክርነቱን በመስማትና ተገቢ ነው ካለም በልላ ማስረጃም ጭምር በማጣራት የቀረበለት ጉዲይ ላይ ተገቢውን ዲኝነት ላሰጥ የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 116፣118(2)(ለ)
No summary available.
መስከረም 25 ቀን 2011 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ አርሺሶ አመልካች፡- ወ/ሮ ፈይዛ ከሚል ጠበቃ ልሣነወርቅ ተኪ- ቀረቡ።
ተጠሪ፡- አቶ አብዱ አህመድ -ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን ቀጥል ያለውን ፍርድ ሰጠተናል።
የክርክሩ ምክንያት የፍቺ ውጤት የሆነው የንብረት ክርክር ነው። የአሁኗ አመልካች የካቲት 10 ቀን 2007 ዓ/ም ጽፈው ባቀረቡት ክስ ከተጠሪ ጋር የነበራቸው ጋብቻ በ23/04/2007 ዓ/ም በተሰጠ የፍቺ ውሳኔ መፍረሱ፣ በትዲር ውስጥ ከሚያዚያ 1995 ዓ/ም ጀምሮ ከቤት እስከወጡበት የካቲት 2006 ዓ/ም ድረስ በአዱስ አበባ ከተማ ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዲ 12 ክልል ውስጥ ባለአንድ ፍቅ ዘመናዊ ቪላ ቤት፣ የቤት ቁጥር አዱስ የሆነ፣ የሰላዲ ቁጥር ኮድ A-13872 የሆነና ግምቱ ብር 550,000 የሚያወጣ ያሪስ መኪና፣ በሀሰን ላውንደሪ ንግድ ቤት ውስጥ በአቶ ሰኢድ ሙዘይን ዲኝነትና በአቶ ኤልያ ሰይድ ጸሒፉነት ብር 480,000.00 የእቁብ ገንዘብና የቤት ቁሳቁሶችን ያፈሩ መሆኑን ዘርዝረው ክፍፍለ እንዱደረግ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀዋል።
የአሁኑ ተጠሪ መጋቢት 25 ቀን 2007 ዓ/ም በተፃፈ መልስ ዲኝነት የተጠየቀበት ቤት የተሰራው በ12/01/1994 ዓ/ም ሆኖ አመልካችና ተጠሪ ደግሞ በሸሪዓ ህግ መሰረት የተጋቡት ጥር 20 ቀን 1997 ዓ/ም በመሆኑ ንብረቱ የተፈራው ከጋብቻ በፉትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
መሆኑን፣ ቤቱን ለመስራት የሚያሥችላቸው ገቢ ስላልነበራቸውም አባታቸውን በላውንደሪ ስራ ስለሚረደ ቤቱን ከጋብቻ በፉት ወላጅ አባታቸው አቶ አህመድ መሃመድ ሰርተው የሰጧቸው መሆኑን የእቁብ ገንዘብ በጋብቻ እያለ ታህሳስ 29 ቀን 2004 ዓ/ም ደርሶአቸው ለትዲራቸው ለጋራ ጥቅም ያዋለት መሆኑን በአዱስ ከተማ ክፍለ ከተማ ቀበላ 13 ክልል ውስጥ በቤት ቁጥር 069 በአቶ መሃመድ ይማም ዲኝነት፣ በአቶ እንድሪስ አለሙ ጸሐፉነት፣ በአቶ ወንድሜነህ አለሙ ሰብሳቢነት የነበረው እቁብም ለመክፈል ባለመቻላቸውም በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ክስ ቀርቦባቸው ገንዘቡን እንዱከፍለ ታህሳስ 30 ቀን 2005 ዓ/ም ተወስኖባቸው ከወጪ ኪሳራ ጋር ብር 149,365.95 እንዱከፍለ በመገደድ መኪናውን ሽጠው እዲውን ከከፈለ በኋላ ቀሪውን ገንዘብ ለትዲር ጥቅም ያዋለ መሆኑን፣ አመልካች ከቤት የወጡት የካቲት 26 ቀን 2006 ዓ/ም ሳይሆን ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ/ም መሆኑን፣ በአቶ ሀሰን ላውንደሪ በአቶ ሰይድ ሙዘይን ዲኝነት በአቶ ኤልያስ ሰይድ ጸሐፉነት በሚሰበሰብ እቁብ ውስጥ የላለበት መሆኑን እና የቤት ቁሳቁሶችን ቢካፈለ ተቃውሞ የላላቸው መሆኑን ዘርዝረው ተከራክረዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ለጉዲዩ አግባብነት አላቸው ያላቸውን ሰባት ጭብጦችን በመመስረት የግራ ቀኙን ምስክሮች ቃል ሰምቶና ጉዲዩን መርምሮ በአመልካችና በተጠሪ መካከል የነበረው ጋብቻ በፍቺ ውሳኔ ሲፈርስ በሚያዚያ ወር 1995 ዓ/ም የተደረገ ጋብቻ ፈርሷል የተባለ ቢሆንም ተጠሪው የጋብቻ ሰርተፉኬት ጋብቻው በሐይማኖት ስርዓት ጥር 20 ቀን 1997 ዓ/ም ተፈፅሞ በውልና ክብር መዝገብ ሹም አገልግልት በ09/09/2003 ዓ/ም ተመዝግቦ ህጋዊ መረጃ እንደተሰጣቸው የሚያሣይ ማስረጃ ያቀረቡና አመልካችም ይህንን ማስረጃ አልካደም ወደሚለው ድምዲሜ ደርሶ እና ቀድሞ በፍቺ ጊዜ ጋብቻው የተፈጸመበት ጊዜ ሚያዚያ ወር 1995 ዓ/ም ነው ተብል የተሰጠውን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 208 ስር የሚወድቅ ስህተት ነው በማለት ይህንኑ ስህተት ነው ያለውን ጊዜ አርሞ በአመልካችና በተጠሪ መካከል ጋብቻው የተፈጸመው ጥር 20 ቀን 1997 ዓ/ም ነው፣ ቤቱ የተሰራውም ከዚህ በፉት መሆኑ ስለተረጋገጠ የተጠሪ የግል ሃብቱ ነው፣ አመልካች ከቤት የወጣችው ከየካቲት 2006 ዓ/ም በፉት ነው፣ በጋብቻ ጊዜ የጋራ እዲ የነበራቸው መሆኑ ተረጋግጧል። ኮድ ቁጥር 2 A-13872 መኪና ለጋራwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
እዲ የተሸጠ መሆኑ ስላልተረጋገጠ መኪናው የጋራቸው ነው፣ እቁቡን በተመለከተም የወጣላቸው መሆን ያለመሆኑንና የገንዘብ መጠን ምን ያህል እንደሆነ አመልካች ያላስረደና ተጠሪ ለግል ጥቅማቸው ያዋለ መሆኑም ያልተረጋገጠ በመሆኑ አመልካች ያቀረቡት ጥያቄ ተገቢነት የላለው መሆኑን፣ የቤት ዔቃዎችን በተመለከተ በተጠሪ በታመነው መሰረት እንዱካፈለ ሲል ወስኗል። ከዚህ ውሰኔ ውስጥ በጋብቻ ጊዜ፣ በቤቱና በእቁቡ ላይ በተሰጠው የውሳኔ ክፍል የአሁኗ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳደራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ የሥር ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 208 መሰረት የጋብቻውን ጊዜ ማረሙ ፍፁም የሥነ ስርዓት ህጉንና መሰረታዊ የዲኘነት አሰራር መርህን ያልተከተለ መሆኑን ከገለጸ በኋላ በውጤት ደረጃ ግን ለጋብቻ መኖር መቅረብ ያለበት የጋብቻ ምስክ ወረቀት በመሆኑ ይኼው ሰነድ መቅረቡ ተገቢ እንደሆነ ዘርዝሮ ጋብቻው የተፈፀመው ጥር 20 ቀን 1997 ዓ/ም ተብል የተሰጠውን የውሳኔ ክፍልና ከዚሁ ጋር ተያይዞ በቤቱ ላይ ተሰጠውን ውሳኔ ሙለ በሙለ አጽንቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- የሥር ፍርድ ቤት በአመልካችና በተጠሪ መካከል የነበረውን ጋብቻ እንዱፈርስ ውሳኔ በሰጠበት ጊዜ ጋብቻው በሚያዚያ ወር 1995 ዓ/ም መሆኑን በግልጽ አስፍሮ ውሳኔ በሰጠበት እና በዚህ ረገድ የተሰጠው ውሳኔም በይግባኝ ባልተለወጠበት ሁኔታ በንብረት ክርክር ጊዜ ተጠሪ ያቀረቡትን ክርክርና ማስረጃ ተቀብል ጋብቻው ጥር 20 ቀን 1997 ዓ/ም የተፈጸመ ነው በማለት መወሰኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 208 ጋር አብሮ በማይሄድ ምክንያት ከመሆኑም በላይ አመልካችና ተጠሪ ከ1994 ዓ/ም ጀምሮ ግንኙነት ፈጥረው በ1996 ዓ/ም አመልካች አርግዘው በ1997 ዓ/ም ልጅ የወለደ መሆኑና ቤቱም ተጠሪ በ1994 ዓ/ም በጨረታ ባገኙት ቦታ ላይ በትዲር ውስጥ መሰራት ተጀምሮ ቤቱ ተሰርቶ የተጠናቀቀው በ2000 ዓ/ም መሆኑ ከሚመለከተው አካል ለስር ፍርድ ቤት በተላከው ማስረጃ የተረጋገጠ ሆኖ እያለ ይኼው ማስረጃና በጉዲዩ ላይ የተሰሙት ምስክሮች ቃል በአግባቡ ሳይታይ መታለፈን፣ የእቁብ ገንዘብን በተመለከተ አመልካች የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ፈጽመው ምስክሮችን አላቀረቡም የተባለው አመልካችም መጥሪያውን ለእቁቡ ዲኛና ሰብሳቢ ለማድረስ ጥረት አድርገው ምስክሮቹ አውቀው እየተደበቁ ስላስቸገሩኝ በሚኖሩበት ወረዲwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
አስተዲደር በኩል እንዱደርሳቸው በማለት በቃለ መሃላ አቤቱታ አመልካች አቅርበው እያለ ፍርድ ቤቱ ይህንኑ በማየት ተገቢውን ትዕዛዝ መስጠት ሲገባው ምስክሮቹ በአመልካች ጉድለት እንዲልቀረቡ በመቁጠር ውሳኔ መስጠቱ ያላግባብ ነው የሚለ ናቸው። አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ችልት እንዱታይ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ ቀርበውም ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጎአል። እንዱሁም የሥር ፍርድ ቤትና የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት መዛግብትም እንዱመጡ ተደርጎ የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት መዝገብ መጥቶ የሥር ፍ/ቤት የመዝገብ ግልባጭ የያዘ መሆኑ ተረጋግጧል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረናል። እንደመረመርነውም የዚህን ችልት ምላሽ የሚያሥፈልጋቸው አበይት ጭብጦች የሥር ፍርድ ቤት በፍቺ ውሳኔ የለየውን የጋብቻ ጊዜ በንብረት ክርክር ጊዜ በመመልከት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 208 መሰረት ማረሙ፣ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት የተጠሪ የግለ ነው በማለት የወሰነበት አግባብና እቁቡን በተመለከተ የተሰጠው ዲኝነት ተገቢ መሆን ያለመሆኑን የሚመለከቱ ናቸው። በዚህም መሰረት እያንዲንዲቸውን ነጥቦች በሚከተለው መልኩ ተመልክተናል።
የመጀመሪያውን የጋብቻ ጊዜውን በተለመከተ ሲሆን የሥር ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ ሁለት ጊዜ ውሳኔ የሰጠ መሆኑን የክርክ ሂደት ያስገነዝባል። ይኼውም አንደ በፍቺ ውሳኔ ጊዜ ሲሆን በዚህ ጊዜ ጋብቻው በሚያዚያ ወር 1995 ዓ/ም የተፈጸመ መሆኑን ማረጋገጡን አምኖ ጋብቻው እንዱፈርስ መወሰኑን በ23/04/2007 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ ያስገነዝባል። ሁለተኛው ውሳኔ በንብረት ክርክር ጊዜ የተሰጠ ሲሆን በዚህ ጊዜ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ላሰጥ የቻለው ተጠሪው ጋብቻው የተፈፀመው ጥር 20 ቀን 1997 ዓ/ም ነው በማለት ተከራክረው በዚህ ረገድም የጋብቻ ምስክር ወረቀት ለማስረጃነት አቅርበው ይኼው የሰነድ ማስረጃ ጥር 20 ቀን 1997 ዓ/ም የተፈፀመው ጋብቻ ግንቦት 09 ቀን 2003 ዓ/ም በውልና ክብር መዝገብ ስም አገልግልት መመዝገቡን የሚያሳይ መሆኑን ጠቅሶና ቀድሞ በፍቺ ውሳኔ ጊዜ ጋብቻው ሚያዚያ ወር 1995 ዓ/ም የተፈፀመ ነው የተባለው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 208 ድንጋጌ መሰረት ሉታረም ይገባዋል በማለትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የሰጠው ውሳኔ ነው ። ከዚህም መረዲት የሚቻለው የሥር ፍርድ ቤት በፍቺ ውሳኔ ላይ ጋብቻው የተፈጸመው ሚያዚያ ወር 1995 ዓ/ም መሆኑን በግልጽ ዲኝነት ሰጥቶ ከቆዩ በኃላ በስርዓቱ መሰረት በበላይ ፍ/ቤት ባልተለወጠበት ሁኔታ በንብረት ክርክር ጊዜ ጋብቻዉ የፈፀመዉ ጥር 20 ቀን 1997ዓ.ም ወደሚለዉ ድምዲሜ የደረሰና ለዚህ ዉሳኔ አሰጣጥ ተገቢ ነዉ ብል በዋቢነት የጠቀሰው ድንጋጌም የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 208 መሆኑን ነዉ።
የክርክሩ መነሻ ጋብቻን መሰረት ያደረገ ሲሆን የሚመራዉም በተሻሻለዉ የፋዳራለ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 ድንጋጌዎችና በፍታብሓር ስነ ሥርዓት ሕግ እንዱሁም አግባብ ባላቸው የአዋጅ ቁጥር 25/1988 ድንጋጌዎች መሰረት ነው።
በአዋጅ ቁጥር 25/1988 እንደተመለከተዉ በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተጀመረ ክርክር ተገቢዉን ዉሳኔ ካገኘ በኃላ በይግባኝ የሚታየዉ በፋ/ከ/ፍ/ቤት ሲሆን ይህ ፍ/ቤት የስር ፍ/ቤትን ዉሳኔ በማጽናት የሚሰጠዉ ዉሳኔ የመጨረሻ ነዉ። በዉሳኔዉ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት የሚለዉ ወገን አቤቱታን ማቅረብ ያለበት ለፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ነዉ። የፋ/ከ/ፍ/ቤት በፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት ታይቶ የተሰጠዉን ዉሳኔ ከሻረዉ ግን በዉሳኔዉ ላይ ቅሬታ ያለበት ወገን ይግባኙን ለፋ/ጠ/ፍ/ቤት መደበኛ ችልት ማቅረብ እንደሚችልም በአዋጁ ተመልክቷል። ይህ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት መደበኛ ችልት በሰጠዉ ዉሳኔ ቅሬታ ያለዉ ተከራካሪ ወገን ከዚህ በኃላ አቤቱታዉን ሉያቀርብ የሚችለዉ ለሰበር ችልት ነዉ። ከዚህ ዉጪ በሆነ ሁኔታ ዉሳኔዉ ሉለወጥ ወይም ሉሻሻል አይችልም። ይህ እንግዱህ አጠቃላይ ሂደቱ (ስርአቱ) ሲሆን ዉሳኔዉን በመቃወም ወደ በላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ለማለት ወይም አቤቱታ ለማቅረብ የሚፈልግ ተከራካሪ ወገን ውሳኔውን በሰጠዉ ፍ/ቤት ሉታረም የሚገባ ወይም የሚችል ስህተት አለ ብል ካመነ ወደ በላይ ፍ/ቤት አቤት ከማለቱ በፉት ዉሳኔዉን ለሰጠዉ ፍ/ቤት አቤቱታ የሚያቀርብበት ስርአት እንዲለም ይታወቃል። የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 208 ጥያቄ የሚነሳዉም እዚህ ላይ ነዉ።
የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 208 ርእሱ እንደሚያመለክተዉ “ስህተት ስለማረም” በሚል የተደነገገ ነዉ። በዚህ ድንጋጌ መሰረት አቤቱታ የቀረበለት ፍ/ቤት (ዉሳኔዉን የሰጠዉ) ሉያርም ወይም ሉያስተካክል የሚችለዉ በሰጠዉ ዉሳኔና ትእዛዝ ላይ የአፃፃፍ ስህተትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የቁጥር አፃፃፍ ጉድለት ወይም ያልታሰበና ባለማስተዋል የተዘለለ ድንገተኛ የቃል ስህተት መኖሩን ካረጋገጠ ብቻ ነዉ። ይህ ደግሞ ግልጽ ነዉ። በክርክሩ ዋነኛ ጭብጥ እና ተያያዥነት ባለዉ ጉዲይ ላይ አከራክሮ የሰጠዉን ዉሳኔ ስህተትን ማረም በሚል ሉያሻሽል ወይም ሉለዉጥ አይችልም።
በያዝነዉ ጉዲይ እንደምናየዉ የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ የሰጠበት ክርክሩ ዋነኛ ጭብጥ በአመልካችና በተጠሪ መካከል የነበረዉ ጋብቻ የተፈፀመበት ጊዜን የሚመለከት ይህንንም ፍ/ቤቱ ከመረመረዉ በኃላ በ 23/4/2007ዓ.ም በሰጠዉ የፍቺ ዉሳኔ ጊዜዉ ሚያዝያ 1995ዓ/ም የሚል ግልጽ ዉሳኔ ሰጥቶበታል። ይህ ዉሳኔ በበላይ ፍ/ቤት በይግባኝ ወይም በሰበር ስርዓት ቀርቦ ስለመለወጡ የሚያሳይ ክርክርም ሆነ ማስረጃ ተጠሪ አላቀረቡም። በ 23/4/2007ዓ.ም የፍቺ ዉሳኔ ከተሰጠ በኃላም ተጠሪ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.
208 የተመለከተዉን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ የጋብቻ ጊዜዉ እዱሻሻል አቤቱታ አላቀረቡም። ጉዲዩ በቤተሰብ ሕጉ የሚገዛ እንደመሆኑ መጠን የጋብቻዉን ጊዜ በፍቺ ዉሳኔ ለይቶ መወሰን ጋብቻዉ በንብረት ላይ ስለሚኖረዉ ህጋዊ ዉጤት ለመወሰን እጅግ አስፈላጊ ጉዲይ ነዉ። ተጠሪ በፍቺ ጊዜ ጋብቻው የተፈፀመዉ ሚያዝያ ወር 1995ዓ/ም ነዉ ተብል በግልጽ የተወሰነዉን የዉሳኔ ክፍል በበላይ ፍ/ቤት ሳያስቀይሩ በንብረት ክፍፍል ላይ ክርክር ሲደረግ የጋብቻዉ ጊዜ 1995ዓ/ም ሳይሆን ጥር 20 ቀን 1997ዓ/ም በማለት ያቀረቡት ክርክር በይዘቱ ሲታይ በፍቺ ዉሳኔ ላይ የተሰጠዉን መሰረታዊ የፍርድ ይዘት የሚቀይር እንጂ በተሰጠዉ ዉሳኔና ትእዛዝ ላይ የአፃፃፍ ስህተት የቁጥር አፃፃፍ ጉድለት ወይም ያልታሰበና ባለማስተዋል የተዘለለ ድንገተኛ የቃል ስህተት እንዱታረም የቀረበ ነዉ ተብል ሉወሰድ የሚችል አይደለም። ይግባኝ ሰሚዉ ፍ/ቤትም በዚህ ረገድ የሥር ፍ/ቤት የተከተለዉ የክርክር አመራርና የዲኝነት አሰጣጥ የስነ ስርዓት ሕጉንና መሰረታ የዲኝነት አሰራር መርህን ያልተከተለ መሆኑን እያረጋገጠ ለጋብቻ መኖር መቅረብ ያለበት የጋብቻ ምስክር ወረቀት ነዉ በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ በተጠሪ በኩል በይግባኝ ስርዓት ወይም በመስቀለኛ ይግባኝ አግባብ ጊዜዉን ጠብቆ የቀረበለት አቤቱታ በላለበት በመሆኑ በህግ አግባብ ያልቀረበለትን ክርክርና ማስጃ በመቀበል የሥር ፍ/ቤትን ዉሳኔ በዉጤት ደረጃ መቀበል የሚቻልበት የሕግ አግባብ የላለ መሆኑን ያላገናዘበ በተለይም በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.342 አግባብ ይግባኝ ሰሚዉ ፍ/ቤት የስር ፍ/ቤትን ዉሳኔ ምክንያቱን ለዉጦ የሚያጸናዉ በሕግ አግባብwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የቀረበ ክርክርና ማስረጃ መኖሩን በማረጋገጥ ስለመሆኑ የተመለከተዉን ድንጋጌም ያላገናዘበ ሆኖ አግኝተናል። ስለሆነም የተጠሪ ጥያቄ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 208 መሰረት የሚስተናገድ ባልሆነበት ሁኔታና የጋብቻውን ጊዜ በፍቺ ውሳኔ ጊዜ ለይቶ መወሰን በንብረት ክፍፍለ ክርክር ላይ የቤተሰብ ሕጉ ድንጋጌዎችን በትክክል ለመተግበር የሚያስችል በሆነበት ሁኔታ ይህንኑ በጣሰ መልኩ ጋብቻው የተፈፀመው ጥር 20 ቀን 1997 ዓ.ም ነው ተብል በስር ፍርድ ቤት መወሰኑም ሆነ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ይኼው የስር ፍርድ ቤት የፍርድ አሰጣጥ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 208 ድንጋጌ የወጣ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ የጋብቻ መኖር በቅድሚያ ለማስረዲት የሚቻለው የጋብቻ ምስክር ወቀት በማቅረብ ነው በሚል ምክንየት ብቻ በስነ ስርዓት ሕጉ ያልቀረበውን ክርክርና ማስረጃ በመቀበል በውጤት ደረጃ የሥር ፍርድ ቤትን ውሳኔ የተቀበለበት አግባብ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተናል። በዚህም መሰረት በአመልካችና በተጠሪ መካከል ጋብቻው የተመሰረተው በሚያዚያ ወር 1995 ዓ/ም ነው ወደሚል ድምዲሜ ደርሰናል።
ቀጥለን የተመለከትነው በጋብቻ ውጤቶች ላይ የተሰጠውን ውሳኔ ተገቢነት ሲሆን በአመልካች እስከዚህ ችልት ከሚከራከሩባቸው ንብረቶች መካከል አንደ በኢዱስ አበባ ከተማ ን/ስ/ላ/ክፍለ ከተማ ወረዲ 12 ክልል ውስጥ የሚገኘውና ባለአንድ ፍቅ ዘመናዊ ቪላ ቤት ነው። ተጠሪ ይህን ቤት የግል ንብረት ነው በማለት የሚከራከሩት ቤቱ የተሰራው በ12/01/1994 ዓ/ም ነው፣ ጋብቻው ደግሞ ጥር 20 ቀን 1997 ዓ/ም ነው የተፈፀመው በሚል ነው። ሆኖም ጋብቻው ጥር 20 ቀን 1997 ዓ.ም ነው የተፈፀመው የሚለው የተጠሪ ክርክር ከላይ በዝርዝር በተመለከተው ሰነ ስርዓታዊ በሆነ ምክንያት ተቀባይነት ያላገኘ ሲሆን ቤቱ የተሰራው በ12/01/1994 ዓ/ም የሚለው ክርክር ግን በስር ፍርድ ቤት በግራ ቀኙ የተሰሙት ምስክሮች ከሰጡት የምስክርነት ቃልና የክፍለ የመንግስት አስተዲደር አካል ለስር ፍርድ ቤት ከሰጠው ማስረጃ አንፃር ምላሽ ሉያገኝ የሚገባው ጉዲይ ነው። በዚህ ረገድ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ሶስት ምስክሮችን ያሰሙ ሲሆን የሰጡት የምስክርነት ቃልም ሲታይ 1ኛው ምስክር አመልካች ጸንሰው እያለ በ1996 ዓ/ም በን/ስ/ላ/ክፍለ ከተማ አካባቢ ቤት መስራት ጀምረዋል፣ በ1997 ዓ/ም ቤቱ ተሰርቶ ሳይጠናቀቅ ገብተዋል በማለት ሲመሰክሩ 2ኛው ምስክራቸው ደግሞ በ1997 ዓ/ም የአመልካችና የተጠሪ ቤተሰብ ቅልቅል ተደርጎ በዚያ ዝግጅት ቤትwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
መገኘታቸውን፣ ቤቱ በተወሰነ መልኩ ያለማለቁን፣ ሆኖም መቼ እንደተጀመረ እና እንደአለቀ የማያውቁ መሆኑን ገልፀው ሲመሰክሩ 3ኛ ምስክር ሁነው አመልካች የሰጡት የምስክርነት ቃል ደግሞ ጋብቻቸውን ናዝሬት ከተማ በ1995 ዓ/ም አድርገው ጥር ወር 1996 ዓ/ም ማርገዛቸውን፣ የካቲት ወር 1997 መውለዲቸውን ከጋብቻ በፉት ተጠሪ በ1994 ዓ/ም የቤቱን መሰሪያ ቦታ በጨረታ እንዲገኘ እንደነገሯቸው፣ ከተጋቡ በኃላ በ1995 ዓ/ም ቁፊሮ እንዲዩና በ1997 ዓ/ም ቤቱ ተሰርቶ ጥቂት ነገር ሲቀር የቤተሰብ ቅልቅል ተደርጎ ቤቱ እንደገቡ፣ ቤት ከተገባ በኋላ እንደተሰራ መመስከራቸውን የሚያሳይ መሆኑን ከስር ፍርድ ቤት የውሳኔ ግለባጭ ተመልክተናል። ተጠሪ በበኩላቸው ሁለት ምስክሮች ያሰሙ ሲሆን 1ኛው ምስክራቸው ወላጅ አባታቸው መሆኑን ገልፀው በሰጡት የምስክርነት ቃል ጋብቻው በ1997 ዓ/ም እንደተፈጸመ፣ አመልካችና ተጠሪ በሚኖሩበት ቤት አቶ ጫላ በተባለው መሃንዱስ በ1994 ዓ/ም ቤቱን ለማሰራት ውል ተዋውለው መሃንዱሱም በ1996 ዓ/ም መግቢያ ላይ አጠናቅቆ ቤቱን ያስረከባቸው መሆኑን፣ ቤቱንም ልጃቸው የሆኑት ተጠሪ በላውንደሪ ስራ ስለሚያገለግሎቸው በራሱ ገንዘብ ያሰሩለት መሆኑን የመሰከሩ ሲሆን የተጠሪ ሁለተኛው ምስክር ደግሞ ቤቱን የሰሩ መሆናቸውን ገልጸው በሰጡት የምስክርነት ቃል ቤቱን ሰኔ 10 ቀን 1994 ዓ/ም በተደረገ በግንባታ ውል ከተጠሪ አባት ጋር እንዲደረጉ፣ ግንባታውን አንድ አመት ከሁለት ወር ፈጅቶባቸው በ1995 ዓ/ም መጨረሻ አካባቢ ለተጠሪ አባት ማስረከባቸውንና ቤቱንም ያሰሩት የተጠሪ አባት መሆናቸውን፣ ቤቱ ሉጠናቀቅ አከባቢ አመልካች መጥተው ማየታቸውን፣ ቤቱ ሙለ በሙለ አልቆ ያስረከቡ መሆኑን ዘርዝረው መስክረዋል። በ2ኛው የተጠሪ ምስክርና በተጠሪ ወላጅ አባት መካከል ሰኔ 10 ቀን 1994 ዓ/ም የተረገው የግንባታ ውልም ለማስረጃነት እንዱቀርብ ተደርጎአል። በልላ በኩል በአዱስ አበባ የሥራና ከተማ ልማት ቢሮ በሉዝ ደንብ ቁጥር3/87 መሰረት የቦታ ቁጥር 4073/93 የግንባታ ስራ ፈቃድ ውል ከተጠሪ ጋር የተደረገ የቦታ ካርታ እና የቦታ አቀማመጥን የሚገልፅ በ01/13/93 ዓ/ም የተዘጋጀ፣ የመኖሪያ ቤት ስራ ለመስራት በቀን 23/01/1994 ዓ/ም የተሰጠ ፈቃድ ለስር ፍርድ ቤት የላከ ሲሆን የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ን/ስ/ላ/ክፍለ ከተማ የማይንቀሳቀስ ንብረት ምዝገባና መረጃ ኤጂንሲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በቁጥር የማ/ን/ም/መ/ኤ 590/2008 በቀን 09/05/2008 ዓ/ም በተፃፈ ደብዲቤ የይዞታ ካርታው በቀን 12/01/94 ዓ/ም እንደተሰጠ፣ የግንባታ ፈቃድ ደግሞwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
በ23/01/94 ዓ/ም መሰጠቱንና ስለግንባታው መኖር በ12/10/2000 ዓ/ም የተረጋገጠ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ መግለፁን ከስር ፍርድ ቤት የውሳኔ ግልባጭ ተመልክተናል።
በስር ፍርድ ቤት የተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች ካላይ የተመለከቱትን ሲሆኑ ቀጥል መነሳት ያለበት የህግ ጥያቄ የስር ፍርድ ቤት እነዚህን ፍሬ ነገሮችን ከተሻሻለው የፋዳራለ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ዲኝነት ሰጥቶቷል ለማለት ይቻላል? ወይስ አይቻልም? የሚለውን ነው።
በመሰረቱ የተጋቢዎችን ንብረትን ሃብት አስመልክቶ የተሻሻለው የፋዳራለ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 የጋራ ንብረት እና የግል ንብረት የሚመራበትን ስርዓት ይደነግጋል። በአዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 62 /1/ ባልና ሚስት ከግል ጥረታቸውና ከግል ወይም ከጋራ ንብረታቸው የሚያገኙዋቸው ገቢዎች ሁለ የጋራ ሀብታቸው ይሆናለ በማለት የደነገገ ሲሆን በንዐስ አንቀጽ 2 ላይ የአንደኛው ተጋቢ የግል ሀብታቸው ነው ካልተባለ በስተቀር ባልና ሚስት ከተጋቤ በኋላ በግብይት የሚያገኙት ንብረት ሁለ የጋራ ሀብታቸው ይሆናል ተብል ተደንግጓል። በተያዘው ጉዲይ ክርክር የተነሳበት ቤት የተሰራበት ቦታ በሉዝ ውል የተገኘው ከሚያዚያ ወር 1995 ዓ/ም በፉት መሆኑ ግልጽ ቢሆንም ግንባታው የተጀመረውና የተጠናቀቀው የግራ ቀኙ በትዲር ውስጥ አብረው ባለበት ወቅት ስለመሆኑ የአመልካች የሰው ምስክሮች የሰጡትን የምስክርነት ቃል እና የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ን/ስ/ላ/ክፍለ ከተማ የማይንቀሳቀስ ንብረት ምዝገባና መረጃ ኤጂንሲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቁጥር የማ/ን/ም/መ/ኤ 590/2008 በቀን 09/05/2008 ዓ/ም በተፃፈ ደብዲበቤ ከሰጠው መግለጫ የምንረዲው ጉዲይ ነው።
የተጠሪ ምስክሮች ቃል ሲታይ ግን የሚመለከተው አካል ከሰጠው መግለጫ ጋር አብሮ የማይሄድ በመሆኑ የማስረጃነት ዋጋ ሉሰጠው የሚችል አይደለም። ተጠሪና አመልካች ከሚያዚያ ወር 1995 ዓ/ም በፉት በፍቅር ግንኙነት ውስጥ የነበሩ መሆኑና አመልካች በግልጽ ጠቅሰው ያቀረቡትን ክርክርም ተጠሪ ማስተባበያ ክርክር ያላቀረቡበት መሆኑን የተገነዘብን በመሆኑ ተጠሪ የመንግስትና የህዝብ ንብረት የሆነውን ይዞታ በሉዝ ውል በስማቸው ወስደው ቆይተው በቦታው ላይ ንብረቱን ያሰፈሩት ከአመልካች ጋር ሕጉ ጥበቃ በሚያደርገው ግንኙት ውስጥ መሆኑ ተረጋግጧል፡፤ ስለሆነም ለክርክሩ ምክንያት የሆነው በተሻሻለው የፋዳራለ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 57፣62 እናwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
63 ድንጋጌዎች አግባብ የአመልካችና የተጠሪ የጋራ ንብረት ልባል የሚገባ ሆኖ አግኝተናል።
በመጨረሻ የተመለከትነው በእቁቡ ላይ የተሰጠውን ውሳኔን ነው። በስር ፍርድ ቤት አመልካች የንብረት ክፍፍል ጥያቄ ሲያቀርቡ ክፍፍል እንዱደረግ ዲኝነት የጠየቁት በሀሰን ላውንደሪ የንግድ ቤት ውስጥ በአቶ ሰይድ ሙዘይን ዲኝነት በአቶ ኤልያስ ሰይድ ፀሒፉነት የሚጣለውን የእቁብ ገንዘብ ብር 480,000.00 ነው። ተጠሪ በዚህ ረገድ በቀረበው የአመልካች የዲኝነት ጥያቄ ላይ መልስ ሲሰጡ እቁቡ ታህሳስ 29 ቀን 2004 ዓ/ም ደርሶአቸው ለጋራ ትዲር ጥቅም ያዋለ መሆኑን ከዚህ ውጪ በእቁቡ የላለበትና ክሱ ሐሰት መሆኑን ገልፀዋል፡፤ የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን የዲኝነት ጥያቄ ውድቅ ያደረገው አመልካች ራሳቸው በሰጡት የምስክርነት ቃል የእቁቡ ገንዘብ ስንት እንደሆነና መቼ እንደወጣላቸው በእርግጠኝነት ያልገለጹ መሆኑንና የእቁቡ ዲኛ እና ፀሐፉዎች ቀርበው እንዱያስረደ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቶላቸውም ትዔዛዙም አድርሰው ምስክሮቹ ቀርበው እንዱያስረደ ያላደረጉ መሆኑን በምክንያትነት ይዞ መሆኑን የስር ፍርድ ቤት የውሳኔ ግልባጭ ያሳያል። አመልካች በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት በዚህ ረገድ አጥብቀው የሚከረከሩት የእቁቡ ዲኛ እና ፀሒፉ ለምስክርነት እንዱቀርቡ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ትዕዛዝ ለማድረስ ጥረት ቢያደርጉም ምስክሮቹ አውቀው እየተደበቁ ስለአስቸገሯቸው ይህንኑ ለስር ፍርድ ቤት በቃለ መሃላ አሳውቀው ምስክሮቹ በሚኖሩበት ወረዲ አስተዲደር በኩል መጥሪያው እዱደርሳቸው ተደርጎ እንዱቀርቡ እንዱደረግላቸው ጠይቀው እያለ የስር ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ የሰጠው ትዕዛዝ ሳይኖር ምስክሮቹን አመልካች አላስቀረቡም ማለቱ ስህተት ነው በሚል መሆኑን ተገንዝበናል። የስር ፍርድ ቤት ዋና መዝገብ ቀርቦም በዚህ ረገድ አመልካች ያቀረቡት ማመልከቻ መኖር ያለመኖሩንና የስር ፍርድ ቤት ተገቢው ብይን የሰጠበት ጉዲይ መሆን ያለመሆኑን ስንመለከትም አመልካች ለምስክሮቹ መጥሪያው በክፍለ የወረዲው አስረዲደር በኩል እንዱደርሳቸው እንዱታዘዝላቸው መጠየቃቸውንና የሥር ፍ/ቤት በዚህ ጥያቄ ላይ ተገቢውን ትዕዛዝ ሳይሰጥ አልፍ በጉዲዩ ላይ ውሳኔ የሰጠ መሆኑን ተገንዘበናል።
በመሰረቱ ምስክር ማስረጃ እንደመሆኑ መጠን የሚቀርበው በፍርድ ቤት መጥሪያ ተደርጎለትና ይኼው መጥሪያም ምስክሩን ማስረጃዬ ነው ብል የቆጠረው ሰው በስነwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
ስርዓት ህጉ ከቁጥር 96 እስከ 102 ድረስ ስለመጥሪያ አደራረስ የተመለከቱትን ድንጋጌዎችን በመከተል መጥሪያውን ለምስክሩ እንዱያደርሰው በማድረግ ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁጥር 116 ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ የምንረዲው ጉዲይ ነው። ለአንድ ጉዲይ ለምስክርነት የተቆጠረ ሰው ደግሞ በፍርድ ቤቱ ጥሪ መሰረት ቀርቦ የመመስከር ግዳታ ያለበት ሲሆን ምስክ ላቀርብ ካልቻለም በሕግ አግባብ ተገድ የሚቀርብ መሆኑን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ ከቁጥር 116 እና ተከታይ ድንጋጌዎች የምንረዲው ጉዲይ ነው።
ምስክሩ በጥሪው መሰረት ላለመቅረብ ሆነ ብል እየተሰወረ ያስቸገረ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ተገቢ መስል በታየው መንገድ ትዕዛዝ በመስጠት ተጠሪው ምስክር ተገድ ወይም ታስሮ እንዱቀርብ ማዘዝ እንደሚገባው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 118(2)(ለ) ድንጋጌ ያሳያል። ከዚህ አንፃር ስናይ የሥር ፍርድ ቤት ምስክሮችን ያላስቀረበው በሕጉ የተዘረጋውን ስርዓት ተከትል ያለመሆኑን ተገንዝበናል። አመልካች እንዱቀርቡ የጠየቋቸው የዔቁብ ዲኛ እና ፀሐፉ ቀርበው መሰማታቸው ክርክሩ ከሚመራበት የፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 111፣ 249 እና 257 አኳያ እንደዚሁም ከማስረጃ አቀራረብና አቀባበል አኳያ ተገቢነት ያለው ሆኖ ሳለ የሥር ፍር ቤት እነዚህን ምስክሮች ሳይሰማ ለዚህ የሰበር አቤቱታ ምክንያት በሆነው የእቁብ ጉዲይ ውሳኔ መስጠቱም ሆነ የፋፋራለ ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይህንኑ የፍርድ አመራር ጉድለት በይግባኝ ሳያርም መቅረቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም በግልጽ የቀረበን ክርክር በተቆጠረው ማስረጃ ወይም አግባብነት ባለው መንገድ ሣያጣሩ /ሣያነጥሩ/ መወሰን ደግሞ የፍርድ አካሄደን ያልተሟላ የሚያደርግና የተከራካሪ ወገንን የመከራከር መብት የሚያጣብብ፣ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መፈፀም በመሆኑ በዚህ ረገድ የተሰጠው ውሳኔ ሉታረም የሚገባ ሆኖ አግንተናል።
ሲጠቃለልም ከላይ ከተመለከቱት መረታዊና ህጋዊ ምክንያቶች አንፃር ሲታይ የሥር ፍርድ ቤቶች ክርክር የተነሳበት ቤት የተጠሪ የግል ንብረት ነው፣ እቁቡም በማስረጃ አልተረጋገጠም በማለት መወሰናቸው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።www.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.fsc.gov.etwww.
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ ሚያዚያ 17 ቀን 2008 ዓ/ም ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ መስከረም 13 ቀን 2010 ዓ/ም የፀናው ውሳኔ በፍትሒብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሻሽሎል።
በአመልካችና በተጠሪ መካከል ጋብቻው የተመሰረተው ጥር 20 ቀን 1997 ዓ/ም ነው ተብል የተሰጠውን የውሳኔ ክፍል በመሻር በፍቺው ወሳኔ መሰረት ጋብቻው ሚያዚያ ወር 1995 ዓ/ም ጀምሮ ያለ ነው ብለናል።
በን/ስ/ላ/ክፍለ ከተማ ወረዲ 12 ክልል ውስጥ የሚገኘውና የቤት ቁጥር አዱስ የሆነው ክርክር የተነሳበት ቤት የግራ ቀኙ የጋራ ንብረት ነው ተብል ተወስኗል። ክፍፍለም በቤተሰብ ሕጉ በተመለከተው አግባብ ሉከናወን ይገባል ብለናል።
የእቁብ ገንዘቡን በተመለከተ የተሰጠውን የውሰኔ ክፍል በመሻር የሥር ፍርድ ቤት በዚህ ነጥብ ላይ ብቻ ክርክሩን በመ/ እንዱቀጥል አድርጎ የእቁቡን ዲኛ እና ጸሃፉ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 118(2)(ለ) አግባብ እንዱቀርቡ አድርጎ ምስክርነታቸውን በመስማትና ተገቢ ነው ካለም በልላ ማስረጃም ጭምር ከአጣራ በኋላ አግባብነት ካለው የቤተሰብ ህግ ድንጋዎች አንፃር በመመልከት በጉዲዩ ላይ ተገቢውን ዲኝነት ላሰጥበት ይገባል በማለት ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 343(1) መሰረት መልሰን ልከንለታል። ይፃፍ።
በላልች የንብረት ክርክሮች የተሰጠው የውሳኔ ክፍል አልተነካም።
በዚህ ችልተ ለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሳራ የግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
ትእዛዝ በዚህ ችልት መጋቢት 12 ቀን 2010ዓ/ም የተሰጠው የእግድ ትዕዛዝ ተነስቶአል።
ይፃፍ